×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲/፲፱፻፹፯

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፲ ኣዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲ / ፲፱፻፳፯ ዓም የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ማቋቋሚያ . . . . . . . . . . . ገጽ ፳፬ አዋጅቁጥር ፲ ፲፱፻ዥ፯ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ _ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ማቋቋሚያ ኣዋጅ ቁጥር ፲ ፲፱፻ዥ፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ አደጋ ” ማለት የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል ወይም የአንድአካባቢ ነዋሪ በተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽችግሮች ምክንያት የምግብና ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶቹን ለማሟላት ሳይችል ቀርቶ በዘወትር አኗኗሩ ላይ ቀውስ በመድረሱ ያለ ሌሎች እርዳታ ኑሮውን ሊቀጥል የማይች ልበት ሁኔታ መከሰት ነው ፤ “ ዕርዳታ ” ማለት የአደጋ ሰለባዎችን የምግብና ሌሎች መሠረታዊ የኑሮ ፍላጎቶቻቸውን ከማሟላት በተጨማሪ አደጋ የደረሰበት አካባቢ ለወደፊቱ ለተመሣሣይ አደጋ እንዳይጋለጥ የሚወሰዱ ሁለገብ እርምጃዎችን ያጠቃ ልላል ፤ ( ኅትየ2 - 60 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ የሺ ) | ገጽ ፭ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓም NegaritGazeta No . 10 - - - 24 August 1995 - Page75 ፫ “ የዕርዳታ ፕሮግራም ” ማለት የምግብና ሌሎች ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች አቅርቦትና ሥርጭት ፣ ንፁህ የመጠጥ ውኃ መኖርን ፣ የጤናና የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍን ፣ ለአረጋውያንና ለአካለ ስንኩላን የሚሰጡ ድጋፎችን ፣ እንደ እንስሳት የመሳሰሉ የገጠሩን ጥሪት ከእልቂት ማዳንን ፣ ከእርሻው ውጭ ተጻባይ የሆኑ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዲጐለብቱ መርዳትን ፣ አካባቢን መልሶ መገንባትን ፣ ድርቅን ለመቋቋም የሚያ ስችሉ ሌሎች የልማት ተግባሮችን እና ከዕርዳታ ጋር በተያያዘ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ዕቅዶችን የሚመለከቱ እርምጃዎችን ያጠቃልላል ። መቋቋም ፩ : የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ ኮሚሽን ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሆናል ። | ፫ ፩ ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ ኣበባ ይሆናል ። | ኛ ዓላማ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ ኅብረተሰቡን ለአደጋ የሚያጋልጡ መሠረታዊ መንስኤ ዎችን በማስወገድ አደጋን መከላከል ፤ ፪ አደጋ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ኣቅምን ኣስቀድሞ ማጎልበት ፣ ፫ ለአደጋ ሰለባዎች አስፈላጊው ዕርዳታ በወቅቱ መድረሱን ማረጋገጥ ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩• የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ብሔራዊፖሊሲያዘጋጃል ! ተግባራዊ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል ፤ ፪ ለአደጋ የተጋለጡ አካባቢዎችን በማጥናት ለወደፊቱ አደጋን ለመከላከል የሚረዱ ስልቶችን ይቀይሳል ፤ ፫ ብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድንና ብሔራዊ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችትን ያስተዳድራል ፤ ፩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የአደጋ መንስ ኤዎችን አስቀድሞ ያጠናል ፤ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትም ይዘረጋል ፤ ፩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አደጋ በሚደር ስበት ጊዜ የጉዳቱን መጠንና ስፋቱን መወሰድ ከሚገባው እርምጃ ጋር ያሳውቃል ' አደጋው የሚመለ ከተው ሥፍራም አደጋ የደረሰበት ሥፍራ መሆኑን በይፋ ይገልጻል ፤ ፮ ከመንግሥት በሚሰጠው መመሪያ መሠረት በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር ማናቸውንም ዓይነት ዕርዳታ ይጠይቃል ' ይቀበላል ፤ ፮ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚሰጠውን ማናቸ ውንም ዓይነት ዕርዳታ ይመዘግባል ' ለተረጂዎች እንዲ ደርስ ያደርጋል ። ፰ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ስለተገኘው ዕርዳታዓይነት ' | መጠንና አጠቃቀም በመገናኛ ብዙሀን ለሕዝብ ያሳውቃል ፤ ገጽ ፪ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓም NegaritGazeta No . 10 - 24 August 1995 - - Page 76 • አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የአደጋ ሰለባ | _ ዎችን መልሶ ያቋቁማል ፤ ፲መንግሥታዊያልሆኑ የዕርዳታ ሰጪድርጅቶችን የዕርዳታ ተግባር ያስተባብራል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ፲፩• የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ' በስሙ ይከሳል ' ይከሰሳል ፤ ኸቡ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን | 12 ) to carry out such other activities as would enhance the - ያከናውናል ። ፮ . የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ ፤ ፩ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ብሔራዊ ኮሚቴ ( ከዚህ | በኋላ “ ኮሚቴ ” እየተባለ የሚጠራ ) ' # በመንግሥት የሚሾሙ አንድ ኮሚሽነርና አንድ ምክትል ኮሚሽነር እና ጅ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። $ የኮሚቴው አባላት ኮሚቴው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፤ ፩• በመንግሥት የሚሰየም ኃላፊ ጅ የግብርና ሚኒስትር ፫ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ / ቤት የክልል ጐዳይ ዘርፍኃላፊ ፩ የገንዘብ ሚኒስትር ፭ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፮ . የመከላከያ ሚኒስትር ፮ : የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚነስትር * የሥራና የከተማ ልማት ሚኒስትር . . . ዙ የሎሚሽኑ ኮሚሽነር . . . . . • የኮሚቴው ስብሰባ ፩ ኮሚቴው በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። # ከኮሚቴው አባላት አብዛኞቹ በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይኖራል ። ፫ የሎሚቴው ውሣኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፤ ሆኖም ድምጽእኩል በእኩል የተከፈለእንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፩ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎችእንደተጠበቁ ሆነው ፡ ኮሚቴው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። 1• የኮሚቴው ሥልጣንና ተግባር ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ብሔራዊ ፖሊሲ ላይ ይመክራል ' ሲጸድቅም በሥራላይ መዋሉን ያረጋግጣል ፤ ጅ አደጋ የደረሰበት ሥፍራ በይፋ እንዲገለጽ ይወስናል ፤ ፫ የዕርዳታ ፕሮግራሞችን በመገምገም አስፈላጊውን የዕርዳታ ወጭእንዲመደብ ያደርጋል ። ፩ የዕርዳታ ፕሮግራሞች የአደጋ መሠረታዊ መንስኤዎችን በማስወገድና ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚ ዕድገት አስተ ዋጽኦ በማድረግ ላይ እንዲያተኩሩያደርጋል ። ጅ በልማት መስኮች የአደጋ መከላከል ፕሮግራሞች ተገቢው | ትኩረት እንዲሰጣቸው ያደርጋል ። ገጽ ሮ፯ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ዓም : Negarit Gazeta No . 10 24 August 1995 – Page77 ፲፩• የኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ - ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ዋና አስፈጻሚ በመሆን የኮሚሽኑን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከተውን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የኮሚሽኑን ሠራተኞች በፌዴራሉ ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ኮሚሽኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙ ነቶች ሁሉ ኮሚሽኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለ ኮሚሽኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን _ ከሥልጣንና ከተግባሩ በከፊል ለኮሚሽኑ ሌሎች ኃላፊ ዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፲፪ : በጀት የኮሚሽኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ፲፫• የሂሳብ መዛግብት _ ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪• የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ | ይመረመራሉ ። ፲፬• የተሻረ ሕግ የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር ፩፻፸፫ / ፲፱፻፸፪ ( እንደተሻሻለ ) በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። | ፲፭ መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ 9በአዋጅ ቁጥር ፩፻ሮ፫ ፲፱፻ጅ፪ ተቋቁሞ የነበረው የዕርዳታ | ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለኮሚሽኑ ተላልፈዋል ። ፲፮• አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ኣዋጅከነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?