አምሳ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፺፫
የአንዱ ዋጋ
ነ ጋ ሪ ት
ጋ ዜ ጣ
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፹፰ ፲፱፻፹፮ ዋልያ የአገር አቋራጭ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፬፻፵፬
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፹፰ ፲፱፻፹፮ ዋልያ የአገር አቋራጭ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅትን
ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርንና የሚ ኒስትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወ ጣው አዋጅ ቁጥር ፪ ፲፱፻፹፫ አንቀጽ ፬፪እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ አንቀጽ ፵ ፩ሀ | መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ።
በ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር መ ን ግ ሥ ት የተወካዮች ምክር ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ « ዋልያ የአገር አቋራጭ አውቶቡስ አገል ግሎት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፹፰ ፲፱፻፹፮ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
፪. መቋቋም
፩. ዋልያ የአገር አቋራጭ አውቶቡስ አገልግሎት ድር ጅት (ከዚህ በኋላ « ድርጅት » እየተባለ የሚጠራ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ።
፪. ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ መሠረት ይተዳደራል
፫. ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን
በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል "
መ ን ግ ሥ ት
አዲስ አበባ ሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ. ም.
የፖስታ ሣጥን ቍ ፹ሺ፩ (80,001)