የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፴ አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፶ ዓም ለሁለተኛው የኢነርጂ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፯፻፳፪ አዋጅ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ለሁለተኛው የኢነርጂ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ | ኤስዲአር : ፩፻ ሚሊዮን ፩፻ ሺህ ( አንድ መቶ አርባ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ኤስዲአርጎ የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ጃንዋሪ ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፰ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ ፣ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው ፣ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፯፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓም . . . Federal Negarit Gazeta No . 30 5 March 1998 – Page 723 ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለሁለተኛው የኢነርጂ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፮ ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ ኤ . አ ጃንዋሪ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፰ በዋሽንግተን ዲሲ - የተፈረመው ቁጥር፫ ሺህ ፲፱ ኢትየብድር ስምምነት ነው ። የገንዘብ ሚኒስትሩ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በብድር ስምምነቱ የተገኘውን ኤስዲ አር ፩፻፵፮ ሚሊዮን ፩፻ ሺህ ( አንድ መቶ አርባ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ኤስ - ዲ - አር ) በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። 1 ፩ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓም - ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ | የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ድርጅት