×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 22833

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር / መ / ቁ . 22833
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
አቶ ጌታቸው ምህረቱ
አቶ መስፍን እቁበዮናስ
ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- አቶ ዋሲሁን ካሣ
ተጠሪ፡- ቄስ ጉባኤ ኃ / ገብርኤል
Af ያ *
ፍ ር ድ
ለሠበር ችሎት የቀረበው የተጠሪ አባት አባ ኃ / ገብርኤል ዋለልኝ
ከአባታቸው በውርስ ተረክበው የነበረውን ቤት በሥር ፍ / ቤት 2 ኛ ተከሣሽ በነበረው
በክፍሉ ቀበሌ ጽ / ቤት እርዳታ
ተነጥቀው አመልካች የቤት ባለቤትነት ደብተር
አውጥተው በቤቱ እንዲጠቀሙ
ያለአግባብ በመሆኑ ቤቱ እንዲመለስላቸው
ተጠሪ ያቀረቡትን ጥያቄ የፌ / መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ተመልክቶ ክርክር ለቀረበበት ቤት
የተሠጠውን የቤት ባለቤትነት ደብተር ዘርዞ ቤቱ ለተጠሪ እንዲመለስ በመወሠኑና
ይህንኑ ውሣኔ የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በማፅናቱ ነው ፡፡
አመልካች ለሠበር ችሎት ባቀረቡት አቤቱታ መንግሥት አጣርቶ የባለቤትነት
ደብተር ከሠጣቸው በኋላ ማስረጃ ለሌለው ግለሠብ ቤቱ እንዲሰጥ መወሠኑና ተጠሪ
መብት አለኝ ቢሉ እንኳን መብቱ በይርጋ በመታገዱ የሥር ፍ / ቤቶች ውሣኔ የህግ
ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዲሻርላቸው ጠይቀዋል ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ

ይህ ክስ የቀረበ
ይህ ችሎትም የሥር ፍ / ቤት በአመልካች በኩል የቀረበው የይርጋ መቃወሚያ
ውድቅ የመደረጉን እና የቤት ባለቤትነት ደብተር የመሠረዙን አግባብነት ለመመርመር
ጉዳዩ ለሠበር እንዲቀርብ በማድረግ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር አድምጧል ፡፡
በመጀመሪያም የተጠሪ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ሊሆን ይገባል ወይስ አይገባም
የሚለውን ነጥብ ስነመለከት ከመዝገቡ እንደተረዳነው የተጠሪ አባት በውርስ ንብረቱን
አግኝተዋል የተባለው በ 1963 ሲሆን ይህ ቤት አዋጅ ቁጥር 47/67 ሲወጣ ቤቱ ከተጠሪ
አባት እጅ ወጥቷል ። ከዚህ በኋላ የተጠሪ አባት ቤቱ እንዲመለስላቸው ያቀረቡት ጥያቄ
ስለመኖሩ የቀረበ ነገር የለም ፡፡ የተጠሪ አባት ከሞቱም በኋላ ተጠሪ የአባታቸውን
ወራሽነት አረጋግጠው ቤቱ እንዲመለስላቸው የጠየቁት በ 1988 ዓ.ም. ነው ፡፡ በአጠቃላይ
ክርክር የተነሣበት የውርስ ንብረት ከተጠሪ አባት እጅ ከወጣ ከ 30 ዓመት በኋላ ነው
ተጠሪ በክሣቸው ላይ የተጠሪ አባትና የአመልካች እናት የአባ
ገ / ማርያም ካሣን የውርስ ንብረት ተከፋፍለው የአሁኑ ተጠሪ አባት ክርክር የተነሣበትን
ቤት አግኝተዋል ብለዋል ። የውርስ ንብረት ደግሞ መብት በሌለው ወራሽ / በተያዘው
ጉዳይ በአመልካች / የተያዘ ከሆነ መብቱን ለማረጋገጥ ጥያቄ ማቅረብ ያለበት የውርስ
ንብረቱ በሌላ
ሠው መያዙን በታወቀ በ 3 ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆኑን በፍ / ህ / ቁ .
1000 / 1 / ሥር ተመልክቷል ፡፡ በተያዘው ጉዳይ የተጠሪ አባት የውርስ ንብረቱ ከእጃቸው
ከወጣ ጀምሮ ክስ ያላቀረቡ ሲሆን ተጠሪ በአባታቸው ወራሽነታቸው በአመልካች ላይ
ክስ የመሠረቱት እንኳን አመልካች የባለቤትነት ደብተር ካወጡ ከ 5 ዓመት ቆይታ በኋላ
ነው ፡፡ / በቃል ክርክሩ ወቅት አመልካች ደብተሩን ያገኙት በ 1983 መሆኑን ገልፀዋል /
በመሆኑም ተጠሪ አመልካች መብት ሣይኖራቸው የያዙትን የውርስ ንብረት ይመልሱ
በማለት ያቀረቡት ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ሊሆን የሚገባው ነው ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ቀን ፳ l ጎ 1 ኛ k
• አረዝ
በሌላ በኩል ይህ የይርጋ ጥያቄ የሚታለፍ ቢሆን እንኳን የአስተዳደር መ / ቤት
የሠጠውን የቤት ባለቤትነት ደብተር ወይም ምስክር ወረቀት መሠረዝ የሚችለው
ማነው የሚለው በቀጣይነት ሊታይ ይገባዋል ፡፡
የአንድ ቤት ባለቤት ማን መሆኑን በማረጋገጥ የቤት ባለቤትነት ማስረጃ
የመሥጠት
የአስተዳደር
የማይነቀሣቀሠውን
ንብረት ባለሀብትነት በማወቅ በአስተዳደር
የባለሀብትነት የምስክር ወረቀትም የያዘም ሠው የዚሁ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ
ይቆጠራል / የፍ / ህ / ቁ / 1195 / 1 / በመሆኑም ይህ የባለሀብትነት ምስክር ወቀረት ካልተሠረዘ
በቀር ሕጉ ምስክር ወረቀቱን የያዘው
የንብረቱ ሕጋዊ ባለቤት መሆኑን
ይገምታል ፡፡ ነገር ግን ምስክር ወረቀቱ የተሠጠው ሀሠተኛ በሆነ መንገድ የሆነ እንደሆነ
ማስረጃው
እና ሕጉ የሚወስደው ግምትም ፈራሽ ሊሆን እንደሚችል
በፍ / ህ / ቁ .1196 እና ተከታዩቹ ቁጥሮች መገንዘብ ይቻላል ፡፡ የአስተዳደሩ ክፍል የሠጠው
የባለቤትነት ደብተር በፍ / ህ / ቁ . 1196 ሥር በተመለከቱት ሁኔታዎች የተገኘ ከሆነም
ይህንን ደብተር ለመሠርዝ ስልጣን የተሠጠው ይኸው ደብተሩን የሠጠው ክፍል
መሆኑንም ከፍ / ህ / ቁ . 1198 / 2 / መረዳት ይቻላል ፡፡
በመሆኑም የቤት ባለቤትነት
ማስረጃው በሀሠተኛ መንገድ የተሠጠ ነው የሚል ወገን ካለ ደብተሩን በያዘው ሠው
ላይ ፍ / ቤት ክስ ከማቅረቡ በፊት ይኸው ደብተር እንዲሠረዝ መጠየቅ የሚገባው
የአስተዳደሩን ክፍል ነው ፡፡ የአስተዳደሩ ክፍል የሠጠው ደብተር እስካልተሠረዘ ግን
ደብተሩን የያዘው ሠው የንብረቱ ባለሀብት መሆኑን ሕጉ በወሠደው ግምት ተጠቃሚ
ነው ፡፡ ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ለአመልካች የሚመለከተው አስተዳደር ክፍል
የቤት ባለሀብትነት ደብተር ሠጥቷቸዋል ፡፡ ይህ ደብተር በሀሠተኛ መንገድ የተገኘ ነው
የሚባል ከሆነ በቅድማያ ደብተሩ እንዲሠረዝ ጥያቄ መቅረብ ያለበት ለዚሁ አስተዳደር ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ክፍል ነው ፡፡ ደብተሩ ሣይሠረዝ ተጠሪ ቤቱን አመልካች እንዲመልሱ ያቀረቡት ጥያቄ
ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም ፡፡ ፍ / ቤቱም ቢሆን ለአመልካች የተሠጠውን የባለቤትነት
ደብተር በአስተዳደር መ / ቤቱ ሥራ ጣልቃ በመግባት መሠረዙ ከሥልጣኑ ውጪ
መስራቱን
ያመለክታል ፡፡ በመሆኑም ለአመልካች የተሠጠው የባለቤትነት ደብተር
ተሠርዞ ቤቱን ተጠሪ እንዲረከቡ የተሠጠው ውሣኔ የህግ ስህተት ያለበት ነው ፡፡
ው ሣ ኔ
1 / የፌ / መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 1472 በ 11 / 02 / 96 የሠጠው እንዲሁም
የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 24803 በ 28 / 4 / 98 የሠጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
2 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልብጭ
311 ] ሃአ_

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?