የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፫ አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻1 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፩ ፲፱፻፲ ዓ . ም ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምም | ነት ማጽደቂያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፮፻ዛ አዋጅ ቁጥር ፲፩ ፲፱፻ኝ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል የተደረገውን _ የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮግራም ( ኤስሲፒ II ) ማስፈጸሚያ የሚውል ፳፪ ሚሊዮን ፮፻ ሺህ ( ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ) የአሜሪካን ዶላር የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮ ጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል እኤአ ጁላይ ፲፮ ቀን ፲፱ያን በሮም የተፈረመ በመሆኑ ፡ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፣ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ይህ አዋጅ “ ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፩ / 1ህየፕ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 2 : 30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፮፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፲፱፻፲ ዓም በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል እኤአ ጁላይ ፲፮ ቀን ፲፱፻፲፯ በሮም የተፈረመው የብድር ስምምነት ነው ። የገንዘብ ሚኒስትሩ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በስምምነቱ የተገኘውን ፳፪ ሚሊዮን ፮፻ ሺህ ( ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ) የአሜሪካን ዶላር በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትታተመ