የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፴፱ | [ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ግንቦት ፲፭ ቀን ፲ሀየን | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፫ / ፲፱፻፲ ዓ ም | ለንግድ ሥራ ፈቃድ ማሳደሻ ልዩ የጊዜ ገደብ መፍቀጂያ አዋጅ . . . . . አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፫ ፲፱፻፲ ለንግድ ሥራ ፈቃድ ማሳደሻ ልዩ የጊዜ ገደብ ለመፍቀድ የወጣ አዋጅ የ፲፱የ1 በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሣትን በተመ ለከተ ልዩ የጊዜ ገደብ መፍቀድ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለንግድ ሥራ ፈቃድ ማሳደሻ ልዩ የጊዜ ገደብ | መፍቀጂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፫ ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ : ልዩ የጊዜ ገደብ ስለመፈቀዱ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻ዥ፬ አንቀጽ ፳፭ የተደነገገው ቢኖርም ፡ የንግድ ሥራ ፈቃድማሳደሻ ልዩ የጊዜ ገደብ በዚህ አዋጅ ተፈቅዷል ። የተፈጸሚነት ወሰን በዚህ አዋጅ መሠረት የተፈቀደው ልዩ የጊዜ ገደብ ተፈጻ | ሚነት የሚኖረው ፡ የ፲ህየን በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ፈቃድ ዕድሣትን በሚመለከት ብቻ ይሆናል ። | ያንዱ ዋጋ . . ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፯፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፱ ግንቦት ፲፭ ቀን ፲፱፻፶ ዓም . Federal Negarit Gazeta No . 39 23 May , 1998 - ~ Page 748 ፩ . የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኃላፊነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፡ ፩ ፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የተፈቀደው ልዩ የጊዜ ገደብ የሚያበቃበትን ወቅት ፣ ፪ በልዩው የጊዜ ገደብ ውስጥ የንግድ ሥራ ፈቃድ ዕድሣት የሚከናወንበትን ዝርዝር የአፈጸጸም ሁኔታ ፡ እና ፫ አግባብ ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮች መመሪያ በማውጣት ይወስናል ። ፭ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግንቦት ፲፭ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ግንቦት ፲፭ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ