ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ሃታ ' የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፲፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ - የካቲት ፳፱ ቀን ፲፱፻፶፫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩ / ፲፱፻፶፫ ዓም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ( ማሻሻያ ) ገፅ ፩ሺ፪፻፻፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩ / ፲፱፻፫ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ( ማሻሻያ ) ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፯ አንቀጽ ፭ እና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ፳፰ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ( ማሻሻያ ) ደንብ ቁጥር ፪፩ / ፲፱፻፶፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ደንብ ቁጥር ፲፯ዥ፱ ( እንደተ ሻሻለ ) እንደሚከተለው እንደገና ተሻሽሏል ፤ ፩ ከአንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፳፪ ) ቀጥሎ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፳፫ ) ተጨምሯል ፤ “ ፰ “ የታከለ ዋጋ ” ማለት ከጠቅላላ የማምረቻ ወጪ ላይ ከውጭ አገር ለሚመጡ ጥሬ ዕቃዎች እና ሌሎች አቅርቦቶች እንዲሁም ከውጭ አገር ለተገኘ አገል ግሎት የተደረገ ወጪተቀንሶየሚቀረው ወጪሲሆን ፤ በምርት ላይ የሚከፈሉ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶችን አይጨምርም ። ፪ . የአንቀጽ ፳፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተተክቷል ፤ ያንዱ ዋጋ ብር 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፭ሺ፬ደኞቿ ፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ - የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻ ዓም የአገር ውስጥ ምርቶች እና ሥራ ተቋራፎች ከውጭ አገር ምርቶች እና ሥራ ተቋራጮች ጋር ለጨረታ ውድድር በሚቀርቡበት ጊዜ በጨረታ ግምገማ ወቅት ለአገር ውስጥ ምርቶች እና ሥራ ተቋራጮች ልዩ አስተያየት ይደረጋል ። ” ፫ ከአንቀጽ ፳፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና ( ፱ ) ተጨምረዋል ። “ ፫ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ለአገር ውስጥ ምርቶች እና ሥራ ተቋራጮች የሚደረገው ልዩ አስተ ያየት ከምክር አገልግሎት በስተቀር ከሥራው ጋር የተያያዘ የትራንስፖርት ፤ የመድን ፤ የተከላ ሥራ ! የሥልጠና ፣ የጥገና እና አንድን ፕሮጀክት ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ሌሎች አገልግሎቶችን ይጨምራል ። ” ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ አፈፃፀም ፩ ማናቸውም ዕቃ ቢያንስ ከዋጋው ፳ ፐርሰንት ( ሃያ በመቶ ) በኢትዮጵያ ውስጥ የታከለ ከሆነ የአገር ውስጥ ምርት እንደሆነ ይቆጠራል ። ከዚህ በላይ የተነገረው ቢኖርም የመሠረታዊ ብረታ ብረት እና የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ውጤቶች የአገር ውስጥ ምርት እንደሆኑ የሚቆጠረው ከዋጋቸው ፲፭ ፐርሰንት ( አሥራ አምስት በመቶ ) ሰኢትዮጵያ ውስጥ የታከለ ሲሆን ነው ። የገንዘብ ሚኒስትሩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ከተመለከተው በላይ በየምርት ዘርፉ ተፈፃሚ የሚሆነውን መቶኛ በመመሪያ ይወስናል ። ” ፬ . ከአንቀጽ፳፰ንዑስ አንቀጽ ፮ ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ) ፣ ( ፰ ) እና ( ፱ ) ተጨምረዋል ፤ “ ማናቸውም ዕቃ በዚህ ደንብ አንቀጽ፳፮ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተደነገገው ልዩ አስተያየት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው አምራቹ ከዕቃው ዋጋ ቢያንስ ፳ ፐርሰንት ( ሃያ በመቶ ) እና ከዚያ በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የታከለ መሆኑን የሚያሳይ በታወቀ ኦዲተር የተረጋገጠ የሂሣብ ሪፖርት ሲያቀርብ ብቻ ይሆናል ። በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተደነገገው ልዩ አስተያየትተጠቃሚ ለመሆን የሚችሉ የአገር ውስጥ ምርቶች እና ሥራ ተቋራጮች ከውጭ አገር ምርቶች እና ሥራ ተቋራጮች ጋር ለጨረታ ውድድር በሚቀርቡበት ጊዜ ለውድድሩ አፈፃፀም ሲባል በጨረታ ግምገማ ወቅት በውጭ አገር ምርቶች እና ሥራ ተቋራጮች የመጫረቻ ዋጋ ላይ ፲፭ ፐርሰንት ( አሥራ አምስት በመቶ ) እንዲ ታከል ይደረጋል ። በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) የተደነገገው የአገር ውስጥ ምርቶችን በሚመለከት ተፈፃሚ የሚሆነው ከውጭ አገር ምርቶች ጋር በጥራት ተመሳሳይ ሆነው ሲገኙ ነው ። ” የሥራ ተቋራጮች የልዩ አስተያየቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚችሉበት መመዘኛ እና በዚህ ደንብ የተደነገገው ልዩ አስተያየት በጨረታ ግምገማ ወቅት ተፈፃሚ የሚደረ ግበት ሁኔታ በገንዘብ ሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፱ ቀን ፲፱፻፫ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ