×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 68/1989 ዓ•ም• የፌዴራል ዋናው ኦዲተርመሥሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ [ አዲስ አበባ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፷፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ . አዋጅ ቁጥር፳፯ / ፲፱፻፳፱ ዓም• የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . … . … . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፫፻፳፭ አዋጅ ቁጥር ፰፰ ፲፱፻፷፱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኦዲት ሥርዓትን ማጠናከር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በሚገባ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስፈልገውን አስተማማኝ መረጃ [ country plays an important role in providing reliable data ፣ በማግኘት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ፤ _ በልዩ ልዩ የልማትና አስተዳደር መስኮች የተሰማሩ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የገንዘብ | አስተዳደር ተገቢውን የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት የተከተለ የገቢ አሰባሰባቸው ፡ የወጪ አፈቃቀዳቸውና የንብረት አስተዳደራቸው የመንግሥት ሕግና መመሪያ ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑና ዕቅድና | ፕሮግራማቸውንም በቅልጥፍና እና ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ በማከናወን የሚጠበቅባቸውን ግብ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ፤ በመንግሥት አወቃቀር በየደረጃው ፌዴራላዊ መንግሥት | attaining their objectives ; መሥሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች ሊኖር የሚገባውን ተጠያቂነት በማረጋገጥ የዲሞክራሲን ሥርዓት ለማስፈን ኦዲት ዓይነተኛ | ting the new democratic system by ensuring Proper accoun መሣሪያ በመሆኑ ፤ የኢፌዲሪ መንግሥት አዲሱ የኢኮኖሚ ፖሊሲን በሚገባ ተግባራዊማድረግ ይቻል ዘንድ በፌዴራላዊ መንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙ የአስተዳደር ' የልማትና የአገልግሎት ተቋማትን በብቃት ለመቆጣጠር በተጠናከረና ዘመናዊ በሆነ የኦዲት ተግባር መታገዝ ያለበት በመሆኑ ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ ገጽ ፫፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ የካቲት ፳፯ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta – No . 26 6 * March 1997 – Page 386 ለዚህ ተግባራዊነት የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤትን አጠናክሮ ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት | ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፰፻፲፱፻፷ፁ ” ተብሎ ሊጠቀስ | 2 . Definition ይችላል ። : ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ” ማለት ሚኒስቴር ፡ ኮሚሽን ፥ ባለሥልጣን ፡ ተቋም ወይም ማናቸውም ሌላ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ነው ፤ ፪• “ ድርጅት ” ማለት ማናቸውም በሙሉ ወይም በከፊል የፌዴራል መንግሥት የሆነ የማምረቻ ፡ የማከፋፈያ ፡ | 3 . Establishment የአገልግሎት ሰጭ ወይም ሌላ የንግድ ድርጅት ነው ። ፫• መቋቋም ፩ . በኢፌዲሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፩፻፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በተመለከተው መሠረት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መን ግሥት ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ( ከዚህ በኋላ “ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ ለሥራው አስፈላጊ በሆነ ቦታ ሁሉ ቅርንጫፍ | 4 . Objectives of the Office መሥሪያ ቤቶች ይኖሩታል ። - ፩ . የመሥሪያ ቤቱ ዓላማዎች ፩ የፌዴራሉን መንግሥት ዕቅዶችና በጀት በሚገባ ለመም ራትና ለማስተዳደር የሚያስፈልገውን አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት የሚረዳ የኦዲት ሥርዓትን ማጠናከር ፤ _ የፌዴራል መንግሥት ገንዘብና ንብረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጡት ሕጎችና ደንቦች መሠረት መሰብሰቡን ፡ መጠበቁንና በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥና የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ሪፖርት ማቅረብ ፤ በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የፋይናንስና የክንዋኔ ኦዲት ማካሄድ ፤ ፬ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የሂሣብ አያያዝና የኦዲት ሙያ እንዲያድግና እንዲጠናከር ጥረት ማድረግ ፤ ፭ በሂሣብ አያያዝና በኦዲት ሙያ ላይ ለተሠማሩት - ለክልልና ለፌዴራል መንግሥት ሠራተኞችና ድርጅቶች ሙያዊ እገዛና ምክር መስጠት ፤ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ሂሣብ የሚመረመርበትን የኦዲት ደረጃ ( እስታንዳርድ ) | 5 Appointment and Accountability of the Federal Auditor ማውጣትና ተግባራዊ መሆኑን መከታተል ። ፭ ስለፌዴራል ዋናው ኦዲተር አሿሿምና ተጠሪነት ፩ . የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤትን የሚመራ ዋናው ኦዲተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማል ። የፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሆናል ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ በማይሆንበት ጊዜ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ይሆናል ። ጽ ፫፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፰፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta - No . 26 6ሓ March 1997 - Page 387 ስለ ምክትል ዋናው ኦዲተር አሿሿም የፌዴራል ዋናው ኦዲተሩን የሚረዳና እርሱ በሌለ ጊዜ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ሥራ የሚመራ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ፅሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚሾም አንድ የፌዴራል ምክትል ዋናው ኦዲተር ይኖራል ። ክፍል ሁለት የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሥልጣንና ተግባር የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሥልጣንና ተግባር የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት በሕግ የተሰጠውን ተግባር ለማከናወን የሚያስፈልገው ሥልጣን ሁሉይኖረዋል ። በዚህ አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ፤ ፩ . የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን እና ድርጅቶችን ሂሣብ ኦዲት ያደርጋል ፡ ያስደርጋል ፤ ፪• የፌዴራሉ መንግሥት ለክልል መንግሥታት የሚሰ ጠውን የበጀት ድጋፍና ልዩ ድጎማዎችን ኦዲት ያደ ርጋል ፡ ያስደርጋል ፤ የፌዴራል መንግሥት ከብር ፭፻ ሺህ ( አምስት መቶ ሺህ ብር ) በላይ የሚጠይቅ ሥራ የግል ሥራ ተቋራጮች እንዲሠሩ በውል የሰጠ እንደሆነ ይህንኑ የመንግሥት ነክ የሆነ የግል ሥራ ተቋራጮች ሂሣብ ኦዲት ያደርጋል ፤ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ያስገኙት ውጤት ሕጉን የተከተለ ፡ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አሠራር የተፈጸመ መሆኑንና ተፈላጊውን ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ እንደአስፈላጊቱ የፕሮግራምና የአሠራር ቅልጥፍናና ምርመራ ወይም ክዋኔ ኦዲት ያደርጋል ፡ ያስደርጋል ፤ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፡ ( ፪ ) ፡ ( ፪ ) ፡ እና ( ፬ ) በተመለከተው መሠረት ያከናወነው የምርመራ ውጤት እንደነገሩ ሁኔታ ለፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቱ እና ለድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ያሳውቃል ፡ የፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ የምርመራው ውጤት ወንጀል መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ከሆነ ወዲያውኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ያደርጋል ፤ , ፮ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሂሣብና የንብረት ምርመራ ሥርዓትና ደረጃን የሚመለከቱ መመሪያዎችን ያወጣል ፤ ፯ ማናቸውም የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት እና ድርጅት የውስጥ ኦዲተር ከመመደቡ በፊት ተመዳቢው አስፈላጊው የሙያ ብቃት ያለው መሆኑን አረጋግጦ ምስክርነት ይሰጣል ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የማናቸውም ፌዴራል መሥሪያ ቤት የውስጥ ኦዲተሮች የመሥሪያ ቤታቸውን ሂሣብና ንብረት በመመርመር ውጤቱን እንዲገልጹለት ሊያደርግ ይችላል ፤ ፀ• ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንደአስፈላ ጊነቱ ለውስጥ ኦዲተሮች ሥልጠና ይሰጣል ፤ አንድ ሂሣብ ወንጀል ባለበት ሁኔታና ታማኝነት በጎደለው አኳኋን መያዙን ለማመን ምክንያት ያለው እንደሆነ ይህንን ሂሣብ በሚመለከቱ መጽሐፎች ! መዘክሮች ፡ መዝገቦች ፡ ሰነዶችና ሌሎች መረጃዎች ላይ ያሽጋል ፤ ፲፩ የገንዘብ ሚኒስቴር ስለገንዘብናየሂሣብ አጠባበቅ በሚያ ዘጋጀው ደንብ ላይ አስፈላጊውን ምክር ይሰጣል ፤ ገጽ ፫፻ኞቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፯ቀን ፲፱፻፱ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta No . 26 6 March 1997 - - Page 388 ፲፪ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሂሣብ አያያዝና የኦዲት ሙያ እንዲዳብር ጥረት ያደርጋል ። የፌዴራሉ መንግሥት የኦዲትና የሂሣብ አያያዝ ሙያ ትክክለኛውን ፈር ይዞ እንዲዳብር አስፈላጊውን ቁጥጥር ያደርጋል ፤ ፲፫ ከክልል የኦዲት እና ቁጥጥር ቢሮዎች ጋር የኦዲት ተግባር የሚዳብርበትን ሁኔታ በተመለከተ የቅርብ የሥራ ግንኙነትና ትብብር ያደርጋል ፣ ፲፬• የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ፤ ሀ ) በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት ሥር በሆኑ ድርጅቶች ፥ ለ ) በሕግ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የጋራ ይዞታ ሥር እንዲሆኑ በተወሰኑ ድርጅቶች ፡ በሕግ የመቆጣጠር መብት የፌዴራል መንግሥት በሆነባቸው የሥራ ዘርፎች ፡ መ ) የማስተዳደር ኃላፊነትና ሥልጣን በሕግ ተለይቶ ለፌዴራል መንግሥት በተሰጡ የሥራ መስኮች ። የፌዴራልና የክልል መንግሥታት እንዲሁም የፌ ዴራልናየውጭም ሆነ የሀገርውስጥ የግል ኢንቨስ ተሮች በጋራ በሚያካሂዷቸው ሥራዎች ፡ ሌሎች የፌዴራል መንግሥት የማስፈጸም ኃላፊነት የወሰ ደባቸው የሥራ መስኮች ላይ ኦዲት ለሚያከናውኑ ኦዲተሮችና የሂሣብ አያያዝ ሥራ ለሚያከናውኑ የሂሣብ አዋቂዎች በሥራው መስክ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን የምስክር ወረቀት ይሰጣል ፡ ያድሳል ፡ ያግዳል ፡ ይሠርዛል ። ፲፭ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት የምስክር ወረቀት ሲሰጥና ሲያድስ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወጣውን ደንብ በመከተል ተገቢውን ዋጋ ያስከፍላል ። ክፍል ሦስት የፌዴራል ዋናው ኦዲተርና ምክትል ዋናው ኦዲተር ሥልጣንና ተግባር ተግባር ( ፰ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ሥልጣንና ተግባር የፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር | 8 . Powers and Duties of the Federal Auditor General መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ በመሆን በዚህ አዋጅ ፤ በአንቀጽ ፯ ለፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ከማዋል ! - በተጨማሪ ከዚህ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባርይኖረ { በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፡ ( ፪ ) ፡ ( ፪ ) እና ( ፬ ) መሠረት ስለሚከናወነው ምርመራና ስለመሥሪያ ቤቱ ሥራዎች አጠቃላይ ዓመታዊ ዘገባ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል ። ምክር ቤቱ በሥራ ላይ በማይሆንበት ጊዜ ለፌዴራል ሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ያቀርባል ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የፌዴራል መንግሥት ያለፈውን በጀት ዓመት ገቢና ወጪ ፡ ሀብትና ዕዳ ፡ እንዲሁም የመንግሥት ገንዘብ ነክ የሆኑ መረጃዎችን ሂሣብ የበጀት ዓመቱ እንደተጠናቀቀ በተቻለ ፍጥነት ዘግቶ ለምርመራ ለፌዴራል ዋናው ኦዲተር ይልካል ። ዋናው ኦዲተሩም የሂሣብ ዘገባው በደረሰው በ፬ ወር ጊዜ ውስጥ መርምሮና አጥንቶ ሪፖርቱን ከነአስተያየቱ ለሚኒስቴሩ ፡ ይልካል ፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያቀርበው ዓመታዊ ዘገባ ውስጥ ሪፖርቱ እንዲካተት ያደርጋል ፤ ገጽ ፫፻፳፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፯ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta No . 26 6 March 1997 – Page 389 በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፯ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ውጤቱን እንዲያውቁ የተደረጉት አካላት የሰጡት አስተ | ያየትና ያቀረቡት ተቃውሞ አጥጋቢያለመሆኑን የገመተ እንደሆነ ይህን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተጠ ቀሰው ዘገባ ውስጥ ያስገባል ፤ ፬ ተግባሩን በሚገባ ለማከናወን መሥሪያ ቤቱን ያደረጃል ፤ ፭ የመሥሪያ ቤቱን በጀት አዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግና ደንብ ውስጥ የተመለከ ቱትን መሠረታዊ ዓላማዎችን ጠብቆ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሠረት ለመሥሪያ ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን ይቀጥራል ያስተዳድራል ፤ ቪ• ለሥራው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በቂ መመሪያ በመስጠት የኦዲት ምርመራ እንደአግባቡ በግል ኦዲተሮች ወይም በሌሎች ባለሙያዎች እንዲከናወን ይወክላል ። ፱ የምክትል ዋናው ኦዲተር ሥልጣንና ተግባር ፩ ከፌዴራል ዋናው ኦዲተር በሚሰጠው መመሪያ | 9 . Powers and Duties of the Deputy Auditor General መሠረት ፤ ሀ ) የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ተግባ ሮችን በማቀድ ፡ በማደራጀት | በመምራትና በማስተባበር የፌዴራል ዋናው ኦዲተርን ይረዳል ፡ ለ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር በማይኖርበት ጊዜ ለፌዴራሉ ዋናው ኦዲተር የተሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል ። ፪ በፌዴራል ዋናው ኦዲተር የሚሰጡትን ሌሎች ሥራዎች ያከናውናል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲ በጀትና ሂሣብ ምርመራ _ ፩ ለፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ከተፈቀደው በጀት ውስጥ የየሶስት ወር ድርሻ የሆነው የሥራማስኬጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ስም በተከፈተውሂሣብ ውስጥ በአንድጊዜ በቅድሚያ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ፪ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሂሣብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፡ ምክር ቤቱ በሥራ ላይ በማይሆ ንበት ጊዜ በፌዴራል ሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በሚሰየም አካል ይመረመራል ። ፲፩ ስለኦዲት ሥርዓትና የጊዜ ገደብ ፩ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር አንድ ሂሣብ ኦዲት ሲያደርግ | ለጉዳዩ አስፈላጊ እንደመሰለው ; አንድ በአንድ በዝርዝር ፡ ወይም በአልፎአልፎየኦዲት ዘዴ ሊመረምር ይችላል ። ቢሆንም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) መሠረት ሂሣቦችን መርምሮ በሚያቀርበው ዘገባ ውስጥ ለእያንዳንዱ ሂሣብ ያመራመሩን ሁኔታና ጥልቀት መግለጽ አለበት ። . የፌዴራል ዋናው ኦዲተር የሚያደርጋቸው ምርመራዎች ከሚመረመረው የበጀት ዓመት ወደኋላ ከሁለት የበጀት ዓመታት ማለፍ የለባቸውም ። ነገር ግን በእርሱ ግምት ወንጀል መፈጸሙን ያመነ እንደሆነ ከተባሉት ሁለት የበጀት ዓመታት ወደኋላ አልፎ ሊመረምር ይችላል ። ጽ ፫፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta No . 26 6 March 1997 - Page 390 ይ የተመርማሪዎች ግዴታ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ' የመሥሪያ ቤቱ ኦዲተሮች ወይም የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ወኪሎች ለምርመራ ጠቃሚና አስፈላጊ የሚመስሏቸውን መጻሕፍት : መዘክሮች ፡ መዝገቦች ፡ ሰነዶችና ሌሎች የጽሑፍና የቃል መረጃዎች ሁሉ ሲጠይቁ የተጠየቀው ግለሰብ ፡ ሠራተኛ ወይም ባለሥልጣን በትክክልና በተሟላ አኳኋን ወዲያውኑ የማቅረብ ግዴታ አለበት ። የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት እንዲቆጣጠ ራቸው በዚህ አዋጅሥልጣን የተሰጠው አካላትን ገንዘብ ወይም ንብረት የተረከበ ፡ ወጪ ያደረገ * የከፈለ ወይም ለሂሣቡ ኃላፊ የሆነ ማንኛውም ሰው ሲጠየቅ ሂሣቡን ኦዲት የማስደረግግዴታ አለበት ። ተመርማሪ መሥሪያ ቤቶች በፌዴራል ዋናው ኦዲተር በተላኩ ሪፖርቶች በተገለጹ ግኝቶች ላይ ተገቢውን እርምት እርምጃ እንዲወስዱ በተሰጡ የማሻሻያ ግቦችና አስተያየቶች መሠረት ከ፴ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እርምጃ የመውሰድ ግዴታ አለባቸው ። እርምጃ ለመውሰድ ካልቻሉ ምክንያቱን በመግለጽ ለፌዴራል ዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት በዚሁ የጊዜ ገደብ ውስጥ ማሳወቅ አለባቸው ። ፩ . የፌዴራሉ ዋናው ኦዲተር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያቀርበው ሪፖርት ውስጥ ድክመት የታየባቸው መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎች በታዩት ድክመቶች ላይ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ወስደው ይህንኑ ለምክር ቤቱና ለፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ። ፫ የማስታወቅ ግዴታ የፌዴራሉ ዋናው ኦዲተር ኦዲት ሲያከናውን በጉዳዩ ላይ ወንጀል መሠራቱን ያመነ እንደሆነ ይህንኑ ለፍትሕ ሚኒስቴር እና ለሚመለከተው አዲት ተደራጊ መሥሪያ ቤት ወይም ድርጅት የበላይ ኃላፊ ማስታወቅ አለበት ። ፲፬ ጥፋትና ቅጣት ፩ . ማንኛውም ሰው } ሀ ) የፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ በቀጥታ ወይም በኦዲ ተሮቹ ወይም በወኪሎቹ አማካይነት ለምርመራ እንዲቀርብለት የሚጠይቀውን መጻሕፍት : መዘከሮች ' መዛግብት ሰነዶችና ሌሎች የጽሑፍ ወይም የቃል መረጃዎች ያላቀረበ ' ወይም ላ ለፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ ) ለመሥሪያ ቤቱ ኦዲተሮች ወይም ለወኪሎች ሀሰተኛ መሆኑን እያወቀ ሀሰተኛ መረጃ የሰጠ ወይም አውነተኛ መሆኑን ለማመን ምክንያት ሳይኖረው ማናቸ ውንም መረጃ የሰጠ ' ወይም ሐ ) የፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ ሥራ በሚገባ እንዳይከ ናወን ያሰናከለ ፡ ወይም መ ) ያለበቂ ምክንያት በፌዴራል ዋናው ኦዲተሩ በቀረቡ ኦዲት ሪፖርቶች በተሰጡ የማሻሻያ አስተ ያየቶችና ሃሳቦች ላይ በወቅቱ እርምጃ ያልወሰደ ፡ ወይም በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሠረት መፈፀም ሲኖርበት ለመፈጸም ፈቃደኛ ሆኖ ያልተገኘ ፤ እንደሆነ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ እሥራት ወይም ብር ፲ ሺህ ( አሥር ሺህ ብር የገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ገጽ ፫፻፵፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፯ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta No . 26 6ቃ March 1997 - Page 391 ፪ . ማንኛውም ኦዲተር ፣ ሀ ) የሥራ ግዴታውን ለመፈጸም ወይም በኃላፊነቱ ወይም በሥራግዴታውማድረግ የሚገባውን ላለማ ድረግ ወይም ማድረግ የማይገባውን ለማድረግ ስጦታ ፡ ገንዘብ ወይም ሌላ ጥቅም እንዲሰጠው የጠየቀ ፡ የተስፋ ቃልየተቀበለ ወይም የቀረበለትን የወሰደ ፡ ወይም ለሚያደርገውየሂሳብ ምርመራተመርማሪውያቀረ በለት ሰነድ ሐሰተኛ መሆኑን እያወቀ እንደ ትክክለኛ ሰነድ ከያዘለት ወይም ትክክለኛነቱን እያወቀ ሊይዝለት የሚገባውን ሰነድ ሳይቀበለው የቀረ ፡ ወይም ሐ ) የፌዴራል መንግሥት ገንዘብ ያጭበረበረ ወይም ሌላ ሰው እንዲያጭበረብር ሁኔታዎችን በማመ ቻቸት የተባበረ ወይም ያሴረ ፥ ወይም መ ) ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት ወይም ሌላ ሰውን ለመጉዳት በማሰብ ፡ በተመርማሪው የቀረቡለትን መጸሕፍት : መዘክሮች መዝገቦች ሰነዶችና ሌሎች ማናቸውንም መረጃዎች እንዲጠፉ ያደረገ ወይም ወደ ሐሰት የለወጠ ወይም እንዲለወጡ ያደረገ - እንደሆነ ከአምስት እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከብር ፲ሺህ እስከ ብር ፲፭ሺህ ( ከብር አሥር ሺህ እስከ ብር አሥራ አምስት ሺህ ) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ፩ . የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር ፲፫ / ፪፻ዥ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፪• ይህን አዋጅ የሚጻረሩ ሌሎች ሕጎችና ደንቦች በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸ ፲፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓም ጀምሮ የጸና | ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?