×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 267/1994 የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፲፬ አዲስ አበባ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፯ ፲፱፻፶፬ ዓ.ም የእንሰሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ ገጽ ፩ሺ፮፻፲፬ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፯ ፲፱፻፲፬ የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ የሀገሪቱ የእንስሳት ሃብት ለእርሻ ተግባር ፣ ለምግብነት ፣ ለኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ፣ ለውጭ ምንዛሬ ማስገኛ በጠቅላላው ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት ከሆኑት ዋና ሃብቶች አንዱ | try's livestock resource is a source of draft power for መሆኑን በመገንዘብ ፣ ከዚህ ሰፊ የእንስሳት ሃብት የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ | foreign exchange and is generally considered as one of the በቅድሚያ የእንስሳት በሽታዎችን በሚገባ መከላከልና መቆጣጠር | important assets for the economic growth of the country ; ወሣኝ እየሆነ በመምጣቱ ፣ ለዚህም ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ፣ ከሀገር ውስጥ ወደ | ወ be derived from this extensive livestock resource ; ውጭ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ከቦታ ቦታ የእንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ዝውውር ሥርዓት በመዘርጋት የእንስሳት | establishment of a system to control the movement of በሽታዎችን መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በአጠቃላይ የእንስሳት በሽታዎችን በመቆጣጠርና በዓለም | of the county አቀፍ ደረጃ የተደረሱትን የእንስሳት ጤና ስምምነቶች በመጠበቅ የእንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎችን ኤክስፖርትንግድ | products by controlling animal diseases and by observing ማስፋፋት አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጠቃላይ ድንጋጌዎች ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆ ጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፯ ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የግብርና ሚኒስትር ወይም ሚኒስቴር ነው ፥ ያንዱ ዋጋ " [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፮፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ፪ . “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) የተመለከ ቱትን ማለት ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደርንም ይጨምራል ፣ ፫ . “ እንስሳ ” ማለት ለዚህ አዋጅ ዓላማ ሲባል የቤትና የዱር እንሳሳ ሲሆን እንዲሁም የባህር እንስሳትና ንብን ያጠቃ ፬ . “ የእንስሳት ውጤት ” ማለት ሥጋና የሥጋ ውጤቶች ፣ ወተትና የወተት ውጤቶች ፣ እንቁላል ፣ ማር ፣ እንዲሁም ሚኒስቴሩ ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም ሲባል የእንሳሳት ውጤቶች ብሎ የሚሰይማቸውን ሁሉ ያጠቃልላል ፣ ፭ . “ የእንስሳት ተዋጽኦ ” ማለት ቆዳ ፣ ሌጦ ፣ ጠጉር ፣ ላባ ፣ ዝባድ ፣ ቀንድ ፣ ሰም ፣ ሽሆና ፣ አጥንት ፣ ሞራና ከነዚህ የሚገኙትን መኖን እንዲሁም ሚኒስቴሩ ወደፊት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የእንስሳት ተዋጽኦ ብሎ የሚሰይ ማቸውን ሁሉ ይጨምራል ፣ ፮ . “ በሽታ ” ማለት ማንኛውም በሚኒስቴሩ የተመዘገበ ወይም የሚመዘገብ የእንስሳት በሽታ ነው ፤ ፯ . “ ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት ” ማለት ኢትዮጵያ አባል የሆነችበትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የእንስሳት በሽታዎችን ቁጥጥር ለማስተባበር የተቋቋመ ድርጅት ነው ፣ ፰ “ ተዛማች የእንስሳት በሽታ ” ማለት በእንስሳት ላይ ከፍተኛ እልቂት እና ወይም በሽታ የሚያስከትል ፣ ከእንስሳ ወደ ሰው የሚተላለፍ ፣ ከባድ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያደርስ ወይም በዓለም አቀፍ የእንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ንግድ ላይ ተጽእኖ የሚያደርስ የተመዘገበና ባስቸኳይ መገለጽ ያለበት ማንኛውም ተላላፊ የእንስሳት በሽታ ነው ፣ ፱ ክትባት ” ማለት የተዳከመ ወይም ሕይወት የሌለው የበሽታ መንስኤ ተዋህስያን ውጤት ሆኖ እንስሳትን ከበሽታዎች ለመከላከል ለጤነኛ እንስሳት የሚሰጥ ነው ፣ ፲ . “ ቁስ ” ማለት ከበሽተኛ እንስሳት ጋር በሚኖረው ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ ንክኪ በመበከል በሽታን ማስተላለፍ የሚችሉ ማናቸውም የእንስሳት ጉዝጓዝ ፣ መኖ ፣ ግርግም ፣ ውሃና የውሃ መጠጫ ገንዳዎች ፣ በረቶች ፣ ልዩ ልዩ የመገልገያ ቁሳቁሶች ፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ከበሽታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች ያጠቃልላል ፣ ፲፩ . “ የባዮሎጂካል ውጤት ” ማለት ሪኤጀንት ፣ የደም ቅራሪ ፣ የተዳከመ ወይም የሞተ ክትባትና የጀርም ጀነቲክ ውጤት ሆኖ የእንስሳት በሽታን ለመመርመር ፣ ለመከላከልና ለማከም ተግባር የሚውል ነው ፣ ፲፪ . “ የፓቶሎጂካል ናሙና ” ማለት የተፈጥሮ ሂደትን ያል ተከተለ የሴል እድገት ወይም በበሽታ አስተላላፊ ወይም ተህዋስ ወይም ጥገኛ ከተበከለ ወይም መበከሉ ከተጠ ረጠረ ሕይወት ካለው ወይም ከሞተ እንስሳ ተወስዶ ለምርመራ ወደ ላቦራቶሪ የሚላክ ነገር ነው ፣ ፲፫ . “ ተሕዋስ ማስወገድ ” ማለት ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በበሽታ አስተላላፊ ተሕዋስ ወይም ጥገኛ የተበከለን ቁስ በሚገባ ካጸዱ በኋላ ፀረ ተሕዋስ በመጠቀም የበሽታ መንስኤዎችን የማስወገድ ተግባር ፲፬ . “ የአስተዳደር ባለሥልጣን ” ማለት በብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሮች በማናቸውም ደረጃ ሕዝቡን ለማስተ ዳደር የተመረጠ ኃላፊ ነው ፤ ፲፭ . “ የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪ ” ማለት የእንስሳት በሽታን ለመቆጣጠር በሚኒስቴሩ ወይም በክልል መስ ተዳድሮች የተመደበና ኃላፊነት የተሰጠው የእንስሳት ጤና ባለሙያ ነው ፣ ፲፮ . “ የእንስሳት ጤና ባለሙያ ” ማለት በየደረጃው የሚሰ ጠውን የእንስሳት ሕክምና ትምህርት ተከታትሎ ዲግሪ ፣ ዲፕሎማ ወይም ሰርቲፊኬት ያለው ሙያውን ለመተ ግበር የተፈቀደለት ነው ፣ ገጽ ፩ሺ፮፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ፲፯ . “ የእንስሳት ጤና ተጠሪ ” ማለት በእንስሳት ጤና አጠባበቅ መሠረታዊ የእንስሳት ጤና ክብካቤ ሥልጠና የተሰጠው የገበሬ ማኅበር ፣ የኅብረት ሥራ ማኅበር ወይም የአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ የእንስሳት ጤና ተወካይ የሆነ ሰው ነው ፣ “ የእንስሳት ጠባቂ ” ማለት የማንኛውም እንስሳ ባለቤት የሆነ ወይም ለእንስሳው ኃላፊ የሆነ ማንኛውም ሰው ነው ፣ ፲፱ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡ ፳ . “ የኳራንቲን ጣቢያ ” ማለት እንስሳትን እንደአስፈላ ጊነቱ ለተወሰነ ጊዜ ኣግልሎ በማቆየት፡ ከሌሎች እንስሳት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዳይ ገናኙ በማደረግ ጤንነታቸውን በመከታተል እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ የክትባት ምርመራዎችንና ሕክምና ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ መሰናዶዎችን ያሟላ የተለየ ሥፍራ ነው፡ “ የመውጪያ ወይም የመግቢያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ” ማለት ለዓለም አቀፍ ትራፊክ ክፍት የሆነ ማንኛውም ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ወይም የባህር ወደብ፡ የየብስ ወይም የባቡር የወሰን ጣቢያ ነው ፣ ፳፪ . “ ዓለም አቀፍ የሳኒተሪ የምስክር ወረቀት ” ማለት ለሰው ምግብነት ፣ ለእንስሳት መኖ ወይም ለሌሎች ተግባሮች የሚውሉ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ጥራትና ሀይጂን ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ መሆኑን በማረጋገጥ በላኪው አገር የእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚሰጥ ወይም የገ፯ዥውን አገር ፍላጎት ያሟላ የምስክር ወረቀት ነው ፣ ፳ . “ ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና የምስክር ወረቀት ” ማለት ወደ ውጭ ሀገር የሚላኩ እንስሳትን ፣ የእንስሳን አባለዘር፡ ጽንስና የለማ እንቁላልን ጤንነትና ደህንነት መርምሮ በማረጋገጥ በላኪው አገር የእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው፡ ፳፬ . “ የእንስሳት ጤና አገልግሎት አስተዳደር ጽ ቤት ” ማለት በየደረጃው በፌዴራልና በክልል የእንስሳት በሽታን ለመከላከል፡ ለመቆጣጠር፡ ክትባትና ሕክምና ለመስጠት፡ በተጨማሪም ሌሎች የእንስሳት ጤና ነክ ሥራዎችን ለመሥራት የተቋቋመ አካል ነው ። ክፍል ሁለት የእንስሳት በሽታዎችን ስለመከላከልና መቆጣጠር ፫ . የእንስሳት በሽታ መከሰቱን ስለማሳወቅ ፩ . የእንስሳት በሽታ ሲከሰት የእንስሳት ጠባቂው ወዲያውኑ በአካባቢው ለሚገኝ የእንስሳት ጤና ተጠሪ ወይም የአስተዳደር ባለሥልጣን ወይም ለእንስሳት በሽታ ተቆጣጣሪ በቃልም ሆነ በጽሁፍ የማሣወቅ ግዴታ አለበት ። ፪ . ማንኛውም የእንስሳት ጤና ባለሙያ በሥራው ላይ እያለ ተዛማች የእንስሳት በሽታ መኖሩን ሲያረጋግጥ ይህንኑ በአስቸኳይ በአቅራቢያው ለሚገኝ የእንስሳት ጤና አገል ግሎት ኣስተዳደር ጽ ቤት ማሳወቅ አለበት ። ፫ የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው ሪፖርት የተደረገለት የእን ስሳት በሽታ መኖሩን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ በሽታው መኖሩን ሲያረጋግጥ ለሚመለከተው የእንስሳት ጤና አገልግሎት አስተዳደር ጽ ቤት ወዲያውኑ ሪፖርት ማድረግ አለበት ። . የእንስሳት በሽታ ስለመከሰቱ ሪፖርት የተደረገለት ክልልም በአፋጣኝ ለሚኒስቴሩ ሪፖርት ማድረግ ይኖር ፭ . ሚኒስቴሩም ስለተከሰተው ተዛማች የእንስሳት በሽታ በዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት አማካይነት ለሌሎች አገሮች መረጃ እንዲደርስ ያደርጋል ። • የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው የእንስሳት በሽታ በአካ ባቢው ሲከሰት ሪፖርት የሚደረግበትን ሥርዓት ለመከታ ቀደምችነት ኃላፊነትና ተጠያቂነት አለበት ። ገጽ ፩ሺ፮፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፯ የእንስሳት ጤና ተጠሪ እና የአስተዳደር ባለሥልጣን ለዚህ አዋጅ ተግባራዊነት አስፈላጊውን የመፈፀም ግዴታ አለባቸው ። ፰ የተዛማች የእንስሳት በሽታዎች ዝርዝርና ስለሚገለ ጹበት ሁኔታ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይገለጻል ። ፬ • የእንስሳት በሽታየገባባቸውን አካባቢዎች የማሳወቅ ሥልጣን ፩ ሚኒስቴሩ አንድ አካባቢ ተዛማች የእንስሳት በሽታ የተከሰተበት መሆኑን በሕዝብ መገናኛ እንዲገለጽ ያደርጋል ። ፪ • ማስታወቂያውም በሽታው ያለበትን ሥፍራና አለ የተባ ለውን የበሽታ ዓይነት እንዲሁም መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች ለይቶ የሚገልጽ መሆን አለበት ። ፫ . ሚኒስቴሩ በሽታው ተከስቶበታል የተባለውን አካባቢ ስፋት እንደበሽታው ስርጭት ሁኔታ መጨመር ፣ መለወጥ ወይም መቀነስ ይችላል ። ፭ የእንስሳት በሽታ የተከሰተባቸውን አካባቢዎች ስለሚመ 5. Provisions Applying to Areas Infected by Animal ለከቱ ጉዳዮች ፩ . የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው በጽሁፍ ካልፈቀደ በስተቀር የእንስሳት በሽታ ከገባበት አካባቢ እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ወደ ሌላ ሥፍራ መጓጓዝ አይኖርባቸውም ። ፪ • በሽታ አለበት በተባለ ሥፍራ ላይ የሚገኙት እንስሳት ሁሉ በተቻለ መጠን ከሕዝብ መተላለፊያ መንገድ ርቀው መጠበቅ ይኖርባቸዋል ። ፫ የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው በሽታው አለበት በተባለው ሥፍራ የሚገኝን ማንኛውንም በእንስሳት በሽታ የተያዘን ወይም መያዙ የተጠረጠረን እንስሳ እንዲለይና ተስማሚ ነው ብሎ የሚያምንበትን ምልክት ሊያደርግ ይችላል ። ፬ • በሽታው አለበት በተባለው ሥፍራ ዙሪያ ለሚገኙ እንስሳት እንዳስፈላጊነቱ የከበባ ክትባት እንዲሰጥ ይደረጋል ። ፭ በእንስሳት በሽታታመው የሞቱ ወይም በበሽታ መያዛቸው የተጠረጠሩ እንስሳት በድን የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መወገድ ይኖርበታል ። ፮ • የእንስሳት በሽታ የተከሰተበት አካባቢ ከበሽታ ነጻ መሆኑ የሚገለፅበት አኳኋን ፩ . ተዛማች የእንስሳት በሽታ አለበት ተብሎ ማስታወቂያ የወጣበት ኣካባቢ በሚኒስቴሩ ከበሽታው ነፃ ነው ተብሎ እስካልተገለጸ ድረስ ከበሽታው ነፃ እንደሆነ አይቆ ፪ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) መሠረት የእንስሳት በሽታው ተዛምቶበታል የተባለ አካባቢ ከበሽታው ነፃ መሆኑ በሚኒስቴሩ ሲረጋገጥ ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል በሽታው መኖሩን ባስታወቀበት መንገድ አካባቢው ከበሽታው ነፃ መሆኑን ያሳውቃል ። ፯ የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስለሚ ወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ወቅትና ቦታ የእንስሳት በሽታዎች እንዳይከ ሰቱና እንዳይዛመቱ እንደአስፈላጊነቱ ሚኒስቴሩ እና ወይም ጉዳዩ የሚመለከተው ክልል ፤ ፩ . የእንስሳት በሽታ መኖሩ ከተረጋገጠበት ወይም ከተጠ ረጠረ አካባቢ ወይም አገር ፣ እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤት ፣ የእንስሳት ተዋጽኦ እና ቁስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ይከላከላል ፣ ይቆጣጠራል ። ፪ . የእንስሳት በሽታ መኖሩ ከተረጋገጠበት ወይም ከተጠ ረጠረ ክልል እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶች ፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች እና ቁስ ወደ ሌላ ክልል እንዳይዘዋወሩ ይከላከላል ፣ ይቆጣጠራል ። ፫ • የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ ድንበርን አቋርጠው እንዳይዘዋወሩ ይቆጣ ፬ ኢትዮጵያ የገባችባቸውን ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የእን ስሳት ጤና ስምምነቶች በሀገሪቱ ውስጥ እንዲከበሩ ገጽ ፩ሺ፮፻፶፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ፭ ከሰው ወደ እንስሳትና ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ይሠራል ፣ ፮ ከዱር እንስሳት ወደ ቤት እንስሳት ፣ ከቤት እንስሳት ወደ ዱር እንስሳት ፣ የሚተላለፉ ተዛማች የእንስሳት በሽታ ዎችን ለመቆጣጠር አስፈላጊ የሆኑ የመከላከያ እርምጃ ዎችን ይወስዳል ፣ ፯ . ለእንስሳት ፣ ለእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ኢምፖር ተሮች ፣ ኤክስፖርተሮች ፣ አምራቾች ፣ ተመጋቢዎችና በአ ጠቃላይም ለኅብረተሰቡ በየጊዜው ስለእንስሳት በሽታዎች ሁኔታ አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ፣ ፰ የእንስሳት በሽታዎች እንዳይስፋፉና ባዕድ በሽታዎች ወደ ኣገሪቱእንዳይገቡ የአጣዳፊ ጊዜ ዝግጁነትና የበሽታ ክትትል ሥርዓት ይዘረጋል ፣ ፱ . የእንስሳት በሽታዎች በኅብረተሰቡ ማኅበራዊ ፣ ኢኮኖ ሚያዊ እና ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት መሠረት በማድረግ ቅደም ተከተል በማውጣት የቁጥጥር ፕሮግራም ያካሂዳል ፣ ፲ አገሪቱን ደረጃ በደረጃ ከተዛማች የእንስሳት በሽታዎች ነጸ ለማድረግና የአገሪቱን የእንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች የውጭ ንግድን ለማስፋፋት ከበሽታ ነጻ የሆኑ ቀጣናዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲቋቋሙ ያደርጋል ። ፰ የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪ ሥልጣን የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ፣ የእን ስሳት ጤና ተቆጣጣሪ ፣ ፩ . የመከላከያ ፣ የህክምና ወይም እንደአስፈላጊነቱ የኳራ ንቲን እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እንስሳትን የመመርመር ፣ ፪ . . እንስሳት ከመጓጓዛቸው በፊት ፣ በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ ፣ ከተጓጓዙም በኋላ የመመርመርና እንዲሁም እንዳስፈላ ጊነቱ ዝውውራቸውን የመቆጣጠር ፣ ፫ እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ወይም የእንስሳት መኖ የሚገኙባቸውን ማናቸውም ቅጥር ግቢ ወይም አካባቢ ገብተው የመመርመር ፣ የእንስሳት በሽታን ለመለየት ሲባል ከማንኛውም እንስሳ ፣ የእንስሳት ውጤቶች ወይም ተዋጽኦዎች ናሙና የመውሰድ ፣ ፭ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በማንኛውም ወቅት እንስሳት እንዲመረመሩ ፣ እንዲከተቡ ፣ እንዲታከሙ ፣ በፀረ ተባይ መድሃኒት እንዲረጩ ወይም በኳራንቲን እንዲቆዩ የማድረግ ፣ ፮ እንስሳት እንዲለዩ፡ እንዲታረዱ ወይም እንዲወገዱ ትእዛዝ የመስጠት ፣ ፯ በመግቢያና በመውጫ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ተገቢውን ቁጥጥር የማድረግ ፣ ፰ የሞቱ እንስሳት በድን ፣ የበድን ቅሪቶች ፣ የተበላሹ የእንስሳት ውጤቶች ፣ በእርድ ወቅት የሚወዳድቁ ቅንጥ ብጣቢዎች ፣ አዛባ ፣ እበት እና ጉዝጓዝ በተገቢው ሁኔታ መወገዳቸውን የመከታተል ፤ ፱ ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ሳይወሰን የእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው የእንስሳት ህክምና ሙያ አስፈላጊ የሚያደ ርጋቸውን ሌሎች እርምጃዎች የመውሰድ ፣ ሥልጣን ይኖረዋል ። ፱ : ስለ እንስሳት ጤና መረጃ ልውውጥ ፩ . የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ፣ ውጤታማ የሆኑ የበሽታ ቁጥጥር ፖሊሲና ስልቶችን ለመንደፍ ፣ አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅባትን ግዴታዎች ለመወጣት ሚኒስቴሩ አገር አቀፍ የእንስሳት ጤና የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ይዘረጋል ። ፪ ሚኒስቴሩ በየጊዜው በዓለም አቀፍ ደረጃ በእንስሳት ሕክምና ሳይንስ በኩል የሚገኙትን አዳዲስ ውጤቶች በሙያው ለተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ያሳውቃል ። ፫ ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆ ጣጠር እያንዳንዱ ክልላዊ መንግሥት ከአጎራባች ክልሎችና ከሚኒስቴሩ ጋር አስፈላጊ መረጃዎችን መለዋወጥ ይኖርበታል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፶፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ፲፱፻፵፬ ዓም ክፍል ሶስት ፲ የእንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ዝውውር የኳራንቲን ጣቢያዎች ስለማቋቋም እና ስለመቆጣጠር ፩ የኳራንቲን ጣቢያ እንስሳትን ለማቆየትና ለማጓጓዝ በሚያመች ቦታ ላይ አስፈላጊ የሆኑ መሰናዶዎችን አሟልቶ መቋቋም ይኖርበታል ። ፪ የኳራንቲን ጣቢያዎች ስለሚቋቋሙባቸውና ስለሚያሟ ሊቸው መስፈርቶች በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወስናል ። ፫ . ሚኒስቴሩ ፣ የሚቋቋሙ የኳራንቲን ጣቢያዎችን ከሚሰጠው የእንስሳት ጤና አገልግሎት አንጻር ይቆጣ ጠራል ፣ እንደ አስፈላጊነቱም ሥልጣኑን ለክልሎች በውክልና ይሰጣል ። ፲፩ . የመውጪያ እና የመግቢያ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን ስለማ ፩ . ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን ፣ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ የሚወጡበትን የመውጪያ እና የመግቢያ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ይወስናል ። • ከተዛማች የእንስሳት በሽታዎች ቁጥጥርና ከበሽታ ነፃ የሆኑ ቀጣናዎችን ከማቋቋም አንጸርእንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ከክልል ወደ ክልል አግባብ ካላቸው ክልሎች ጋር በመሆን ይወሰናል ። ፲፪ • እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችንና ተዋጽኦዎችን ወደ ውጭ ሀገር ስለመላክ ወደ ውጭ አገር የሚላኩ እንስሳት በቅድሚያ ኳራንቲን ጣቢያ ውስጥ ገብተው ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆዩ መደረግ አለበት ። ወደ ኳራንቲን ጣቢያ የሚገቡት እንስሳት ተዛማች የእንስሳት በሽታ ካልተከሰተበት አካባቢ የመጡና የዝውውር ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል ። ፫ እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤትና ተዋጽኦዎችን ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ የሚያጓጓዙ ሰዎች የማጓጓዣ መስፈርቶችን ጠብቀውማጓጓዝና እንዲሁም የተሰየሙትን የመውጪያ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መጠቀም ይኖርባቸዋል ። ፲፫ እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎችወደ ሀገር ውስጥ | 13. Importation of Animals , Animal ስለማስገባት ፩ . ማንኛውም ሰው እንሰሳትን ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋ ጽኦዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባቱ በፊት በቅድሚያ ስለሚገቡት እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽ ኦዎች ዓይነትና ዝርያ ፣ ብዛት ፣ የመጓጓዣ ሁኔታ ፣ የመድረሻ ቀን የመግቢያ በር እንዲሁም ከየት ሀገር እንደሚመጡ የሚያቋርጧቸውን ሀገሮች ለሚኒስቴሩ በማሳወቅ የመግቢያ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የተፈቀደ ላቸው እንስሳት ፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ሲገቡ በመግቢያ ጣቢያ ላይ በእንስሳት ጤና ተቆጣጣ ሪዎች መታየት ይኖርባቸዋል ። ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤናና የሳኒተሪ የምስክር ወረቀት ፩ . ማናቸውም እንስሳ ፣ የእንስሳ አባለዘር ፣ ጽንስ ፣ የለማ እንቁላል ፣ የእንስሳት ውጤቶች የእንስሳት ተዋጽኦዎች ሲገቡ በመግቢያ ጣቢያ ላይ በእንስሳት ጤና ተቆጣጣ ሪዎች መታየት ይኖርባቸዋል ። ፪ . የእንስሳት ጤናና የሳኒታሪ የምስክር ወረቀቶች ሊይዟቸው ስለሚገቡ ዝርዝሮች በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፲፭ የእንስሳት የዝውውር ፈቃድ ፩ . ማንኛውም ሰው እንስሳትን ከወረዳ ወደ ወረዳእና ወይም | 15. Animals Movement Pemit ከክልል ወደ ክልል ለማዘዋወር ከእንስሳቱ መነሻ ቦታ ከበሽታ ኣንፃር ፈቃድ መያዝ ይኖርበታል ። ፪ የሚሰጠው የእንስሳት የዝውውር ፈቃድ የእንስሳቱን መነሻና መድረሻ ቦታ ፣ የጉዞ አቅጣጫ ፣ የእንስሳቱን ዓይነትና ብዛት ፣ የእንስሳቱን የጤንነት ሁኔታና ሌሎች አስፈላጊ ዝርዝሮችን የሚገልጽ መሆን ይኖርበታል ። ገጽ ፩ሺ፯፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ክፍል አራት ስለ እንስሳት ጤና ባለሞያዎች ምዝገባና አገልግሎት አሰጣጥ ፲፮ ምዝገባ ፩ . የእንስሳት ጤና ባለሞያካልተመዘገበናየምዝገባ ምስክር ወረቀት ካላገኘ በስተቀር በእንስሳት ጤና ጥበቃ ሥራ ላይ መሠማራት አይችልም ። ፪ . ሚኒስቴሩ ያልተመዘገቡ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ባለሙያ ያልሆኑ ተጠቃሚዎች ሊያከናውኗቸው ስለሚችሉ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ሥራዎች መመሪያ ያወጣል ። ፫ . የእንስሳት ጤና ባለሞያዎችን ለመመዝገብና ፈቃድ ለመስጠት የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ምክር ቤት ይቋቋማል ። ፬ . ምዝገባው ስለሚካሄድበትና የእንስሳት ጤና ባለሞያዎች ምክር ቤት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፲፯ . የእንስሳት ጤና አገልግሎት ለመስጠት ፩ . ማንኛውም ሰው አስፈላጊዎቹን መስፈርቶች አሟልቶ እስከቀረበ ድረስ የእንስሳት ጤና አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ፣ ማዕከል ወይም ተቋም ማቋቋም ይችላል ። ፪ . ማንኛውም ሰው ለእንስሳት ጤና አገልግሎት ጣቢያ ፣ ማዕከልና ተቋም የንግድ ሥራ ፈቃድ ለማግኘት በቅድሚያ ከሚኒስቴሩ ወይም ጉዳዩ ከሚመለከተው ክልል የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል ። ፫ . ሚኒስቴሩ የግል የእንስሳት ጤና አገልግሎት እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ። ፬ . ሚኒስቴሩ እንደየአገልግሎቶቹ ባህርይ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚኖራቸውን ሚናና ኃላፊነት ይለያል ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፰ : ስለ ካሣ ፩ . የእንስሳት በሽታ እንዳይዛመት ለመከላከልና ለመቆ ጣጠር በእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው ትዕዛዝ መሠረት የታመመ እንስሳ የተወገደ ወይም የታረደ ከሆነ ለጠባቂው ምንም ዓይነት ካሣ አይከፈልም ። ፪ . በእንስሳት ጤና ተቆጣጣሪው ትዕዛዝ መሠረት የእን ስሳው በድን እንዲቀበር ወይም እንዲቃጠል ከተደረገ የበድኑ ማስወገጃ ወጪ ለጠባቂው ኣይከፈልም ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ተዛማች የእንስሳት በሽታን ከመላ ሀገሪቱ ወይም ከተወሰነ የሀገሪቱ ክፍል ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል ሚኒስቴሩ እንስሳት እንዲታረዱ ወይም እንዲወገዱ ትእዛዝ ከሰጠ እንደአስፈላጊነቱ ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ያመቻቻል ። ፬ • በኳራንቲን ጣቢያ ውስጥ በተዛማች የእንስሳት በሽታ መከሰት ምክንያት ለሚታረዱት እንስሳት ካሣ አይከ ፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ) ኣፈጸጸም የሚረዳ እና ባለሙያው በእንስሳት ጤና አገልግሎት ሥራ ላይ እያለ ለሚደርስበት ጉዳት ስለሚ ከፈል ካሣ ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፱ • የመተባበር ግዴታ ማንኛውም የሚመለከተው ሰው ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መተባበር ይኖርበታል ። ፳ የአገልግሎት ክፍያ ስለመሰብሰብ ሚኒስቴሩ ለሚሰጠው አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ መሠረት ክፍያዎችን ይሰበስባል ። ፳፩ . ቅጣት ይህን አዋጅና በአዋጁ መሠረት የሚወጡ ደንቦችንና መመሪ ያዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ገጽ ፩ሺ፯፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ፳፪ . የተሻሩና ተፈጻሚነት የሌላቸው ሕጎች ፩ . የከብት በሽታዎችን ስለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር ፩የሮ፩ ፲፱፻ፃር በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፪ ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ፡ ደንብና መመሪያ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳፫ : ደንብና መመሪያ ስለማውጣት ፩ . የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአዋጁ አፈጻጸም የሚረዱ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል ። ፪ ሚኒስቴሩ ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፳፬ . አዋጁ የሚጸናበት ቀን ይህ አዋጅ ከጥር ፳ ቀን ፲፱፻፲፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?