ነጋሪት ጋዜጣ የሚተዳደር በመሆኑና ይህንኑ የተመለከተ መሠረታዊ የ 1 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፳፮ አዲስ አበባ ግንቦት ፳፫ ቀን ፲፱፻፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፰ ፲፱፻፶፫ ዓም : የኢትዮጵያ ግብርና ቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ ገጽ ፭ሺ፭፻፲፩ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፪ / ፲፱፻፲፫ የኢትዮጵያ ግብርና ቆጠራ ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ መረጃ በማስፈለጉ ፤ ዝርዝር የሆኑ የግብርና መረጃዎች መኖር በአገር አቀፍና በክልሎች ፣ ከዚያም በታች ባሉ የአስተዳደር እርከኖች ለሚቀየሱ | regarding the agricultural sector is essential for policy and ፖሊሲዎችና የልማት ፕሮግራሞች አፈጻጸም ፣ ክትትልና ቁጥጥር | evaluation at national , regional and at lower administrative አስተማማኝ መሠረት በመሆኑ ፤ ይህንኑ የቆጠራ ሥራ በተቀላጠፈና በአስተማማኝ ሁኔታ | operations efficiently and effectively , it is found necessary to ለመምራት በአገር አቀፍ ፣ በክልሎችና ከዚያም በታች ባሉ የአስተ | establish acommission that have a life span of upto five years , ዳደር እርከኖች ደረጃ በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብር እስከ | and responsible for the overall management and coordination አምስት ዓመት ዕድሜ ያለው ኮሚሽን ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ግብርና ቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፰ / ፲፱፻፶፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ.ቁ : ፰ሺ፩ ) ” ..ራ ኮሚሽን / ከዚህ በኋላ ገጽ ሺ፩ሺ፭፻፲፪ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳ኘግንቦት፳፫ ቀን ፲፱፻፶ዓም ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ የግብርና ቆጠራ ” ማለት በአገር አቀፍ ደረጃ ወይም በተወሰነ ብሔራዊ ክልል በተለይም ስለእርሻ መሬት ይዞታና የሰብል ምርት መጠን ፣ ስለቤት እንስሳትና ንብ በግብርና ሥራ ስለተሰማራው የሰው ኃይል ፣ ስለግብርና መሣሪያዎች ይዞታና አጠቃቀም ፣ ስለ መስኖ ሥራ፡ ምርጥ ዘር ፣ ማዳበሪያ ፣ ፀረ ተባይና ሌሎች ተመሳሳይ * ረጃዎችን አጠቃቀም በተመለከተ ወካይነት ባለው ከፍተኛ የናሙና መጠን በመጠቀም መሠረታዊ መረጃ ዎችን የመሰብሰብ፡ የማጠናቀር የመገምገም ፣ የመተን ተንና ውጤቱንም ለተጠቃሚዎችየማሠራጨትተግባር ፪ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥ ልጣን ነው ፤ ፫ ኮሚሽን ” ማለት የግብርና ናሙና ቆጠራውን ሥራ በበላይነት እንዲመራና እንዲያስተባብር በማዕከል ፣ በክልል ፣ በዞንና በወረዳ የሚቋቋመው ኮሚሽን ነው ፤ ፬ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ የተጠቀሰው ማንኛውም ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የአዲስ አበባና የድሬዳዋ መስተዳድርንም ይጨምራል ፤ ፭ “ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ” ማለት ማናቸውም የሚኒ ስቴር የኮሚሽን፡ የባለሥልጣን ፣ የጽሕፈት ቤት ፣ ተቋም ወይም ማናቸውም ሌላ የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥት መሥሪያ ቤት ነው ፮ “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ነው ። ፫ ስለመቋቋም ፩ የኢትዮጵያ ግብርና “ ኮሚሽን ” ተብሎ የሚጠራ / በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሆናል ። ፫ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቆጠራውን ሥራ ለማስፈጸም ደንብ የማውጣት ሥልጣን ይኖረዋል ። ፬ • የኮሚሽኑ አቋም ፩ • ኮሚሽኑ ፤ ሀ ) ማዕከላዊ ኮሚሽን ፣ ለ ) የብሔራዊ ክልል ኮሚሽን ሐ ) የዞን ኮሚሽን ፤ መ ) የወረዳ ኮሚሽን ፤ እና ሠ ) እንደ አስፈላጊነቱ የቀበሌ ኮሚቴዎች ፡ ይኖሩታል ። ፪ ባለሥልጣኑ የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ሆኖ ያገለግላል ። የማዕከላዊ ኮሚሽኑ አባላት ማዕከላዊ ኮሚሽኑ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፤ ፩ ጠቅላይ ሚኒስትር ተወካይ ፪ የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስትር አባልና ም / ሰብሳቢ ፫ . የግብርና ሚኒስትር ፬ . የማስታወቂያና ባሕል ሚኒስትር ፭ የገንዘብ ሚኒስትር የግብርና ምርምር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ፯ . የኢንቨስትመንት ጽ / ቤት ኃላፊ ..... ማለፉ \ ገጽ ፭ሺ፭፻፲፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ግንቦት ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም • ፯ የትምህርት ሚኒስትር የውሀ ሀብት ሚኒስትር ፱ . የተፈጥሮ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ፲ . የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ገበያ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ . ” ፲፪ . በጠቅላይ ሚ / ር ጽ / ቤት የክልል ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ፲፫ . የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ .... አባልና ፀሐፊ ። ፮ . የማዕከላዊ ኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ማዕከላዊ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፤ ፩ . የኢትዮጵያ ግብርና ቆጠራን በሚመለከት የፖሊሲ መመሪያ ማውጣትና አፈጻጸማቸውን መከታተል ፤ ቆጠራ የሚከናወንበትን ጊዜና የሚሰበሰበውን የመረጃ ዓይነት መወሰን ፤ ፫ . ስለግብርና ቆጠራ ተግባር ለሕዝብ ማሳወቅ ፤ እና ፬ . ከብሔራዊ ክልል ኮሚሽን በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት ። ፯ . የብሔራዊ ክልል ኮሚሽን አባላት የብሔራዊ ክልል ኮሚሽኑ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፤ ፩ የክልሉ መንግሥት ፕሬዚዳንት .. .. ፪ . የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ... አባልና ም / ሰብሳቢ የግብርና ቢሮ ኃላፊ 6 • የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ፭ . የማስታወቂያ ቢሮ ኃላፊ ፮ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ... ፰ የፖሊስ ኮሚሽነር ፱ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ጽ ቤት ; በክልሉ በግብርና እንቅስቃሴ ላይ የተሠማሩ ሌሎች ድርጅቶች ኃላፊ ....... የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽ / ቤት ኃላፊ አባልና ፀሐፊ ። በዞንና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ ኮሚሽኖች አባላት በዞንና በወረዳ የሚቋቋሙት ኮሚሽኖች አባላት ከክልል ኮሚሽኑ በሚወጣው መመሪያ መሠረት ይወሰናል ። የዞንና የወረዳ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ሊቃነመና ብርት እንደአግባቡ በዞንና በወረዳ ደረጃ ለሚቋቋሙ ኮሚሽኖች ሰብሳቢዎች ይሆናሉ ። ፫ . በየደረጃው የሚገኝ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥ ልጣን ኃላፊ ወይም ተጠሪ እንደአግባቡ በዞንና በወረዳ ለሚቋቋመው ኮሚሽን ፀሐፊ ይሆናል ። በብሔራዊ ክልል ፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ ኮሚሽኖች ሥልጣንና ተግባር ፩ . በብሔራዊ ክልል ፣ በዞንና በወረዳ የሚቋቋመው ኮሚሽን ተጠሪነቱ በደረጃ ቀጥሎ ለሚገኘው የበላይ ኮሚሽን ሆኖ በየደረጃው የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፣ ገጽ ሺ፩ሺ፭፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፲ግንቦት፳፫ቀን ፲፱፻፫ዓ • ም • ሀ ) ከደረጃውቀጥሎከሚገኘው የበላይኮሚሽን የሚተ ላለፉ መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን የማረ ለ ) ለግብርናቆጠራው አፈጸጸም በየአስተዳደር እርከኑ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝብ እንደዚሁምመ / ቤቶችና ድርጅቶች የመቀስቀስና የማስተባበር ፣ ሐ ) በየአስተዳደር እርከኑ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ ለቆጠራው አፈጻጸም ስልቶችን የመቀየስ ፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታትና ለቆጠራው ስኬታማነት ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፣ መ ) ከደረጃ ቀጥሎ ከሚገኘው የበላይ ኮሚሽን የሚሰጡ ሌሎች ተግባሮችን የማከናወን ። ፪ • በቀበሌ ደረጃ የሚቋቋመው ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይወሰናል ። ፲ የስብሰባና የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ፩ በየደረጃው የሚቋቋመው ኮሚሽን በሰብሳቢው ጥያቄ ወይም ከግማሽ በላይ የሆኑ የኮሚሽን አባላት ሲጠይቁ ይሰበሰባል ። ፪ ከኮሚሽኑ አባላት አብዛኛዎቹ ሲገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ • የኮሚሽኑ ውሳኔ በድምፅ ብልጫ ይሆናል ። ድምፁ እኩል ለእኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ። ፬ • ኮሚሽኑ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ። ነ፩ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ በማቋቋሚያ ሕግ ከተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት በተጨማሪ የግብርና ቆጠራው አስፈጸሚ ድርጅት ነው ። ይህ አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ባለሥ ልጣኑ የግብርና ቆጠራውን ለማከናወን የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ለግብርና ቆጠራው ሥራ የሚያስፈልጉ መጠይቆች ፣ መመሪያ ዎችና የመስክ መገልገያ ዕቃዎች የማዘጋጀት ፣ የግብርና ቆጠራውን የሚመለከቱ መረጃዎች የመሰ ብሰብ ፣ ለዚህም አግባብ ያላቸው ሠነዶችና መዛግብት የመመርመርና ምርመራውንም ለማከናወን አግባብ ባለው ጊዜ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ወደ ማንኛውም ሰው ቅጥር ግቢ ወይንም ይዞታ የመግባት ፣ በግብርና ቆጠራ የተሰበሰበውን መረጃ ማደራጀት ፣ መተ ንተንና ሪፖርቱን አዘጋጅቶ ለማዕከላዊ ኮሚሽኑ የማቅ ረብና ሲፈቀድም የማሠራጨት ፣ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፲፩ ( ፪ ) መሠረት ቆጠራው እንዲ ካሄድ በተወሰነበት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አግባብ ካለው አካል ጋር በመመካከር በማንኛውም የመንግሥት መ / ቤት ሠራተኞች ፣ ንብረትና አገልግሎት ትብብር በመጠየቅ የመጠቀም ፣ ፭ የግብርና ቆጠራውን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ አግባብ ያላቸው ሌሎች አስፈላጊ ተግባሮችን የማከናወን ። ገጽ ሺ፩ሺ፭፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፮ ግንቦት ፳፫ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም ፲፪ : የመተባበር ግዴታ ፩ . ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ መሠረት ለሚከናወነው የግብርና ቆጠራ ሥራ የመተባበር ግዴታ አለበት ። በዚህ አዋጅ መሠረት መረጃ እንዲሰጥ የተጠየቀ ማንኛውም ሰው የባለሥልጣኑን መታወቂያ ለሚያሳይ መረጃ ሰብሳቢ ወይም ተቆጣጣሪ ትክክለኛውን መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት ። ፫ . ማንኛውም የቅጥር ግቢ ፣ የእርሻ ማሳ ፣ የከብቶችና የእርሻ መሣሪያዎች ባለንብረት ወይም ባለይዞታ ወይም ጠባቂ ወይም ወኪል ከባለሥልጣኑ የተሰጠውን መታወቂያ ለሚያሳይ የግብርና ቆጠራ መረጃ ሰብሳቢ ወይም ተቆጣጣሪ ወደ ተባለው ንብረት ወይም ይዞታ እንዲገባ የመፍቀድ ግዴታ አለበት ። ፲፫ የመረጃዎች ምሥጢራዊነት በፍርድ ቤት ካልታዘዘ በስተቀር ከግለሰቦችና ከድርጅቶች | 13. Confidentiality of the Information የተሰበሰቡትን የግብርና ቆጠራ ዝርዝር መረጃዎች ባለሥ ልጣኑ በምሥጢር ይጠብቃል ። ፲፬ . ቅጣት ማንኛውም ሰው ፣ ፩ . የግብርና ቆጠራን መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ ወይም ይህንኑ በሚመለከት ሐሰተኛመረጃ የሰጠ ፤ ወይም ፪ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ር ) የተደነገገውን በመተላለፍ መረጃ ሰብሳቢው ወይም ተቆጣጣሪው ወደተባለው ንብረት ወይም ይዞታ እንዲገባ ያልፈቀደ ፣ እንደሆነ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝከ፩፻፲ብር ( አንድ መቶ ሃምሳብር ) ወይም ከአንድ ወር በማይበልጥ እሥራት ይቀጣል ። ፲፭ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ተፈጻሚነት አይኖ ፲፮ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግንቦት ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ግንቦት ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ