×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 98/1990 ዓም ስለንግድ ተቋም የዋስትና መማእቱ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፲፯ አዲስ አበባ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፰ ፲፱፻፮ ዓ . ም ስለንግድ ተቋም የዋስትና መያዝ የወጣ … . . . . . . ገጽ ፮፻፸፯ አዋጅ ቁጥር ፲፰ ፲፱፻፲ ስለንግድ ተቋም የዋስትና መያዣ የወጣ አዋጅ የንግድ ተቋሞች በዋስትና መያዣነት ስለሚመዘገቡበት መዝገቦች አያያዝና አፈጻጸም ፡ ዋስትናውን ከመዝገብ ስለመሰረዝና ስለሥርዓቱ በሕግ እንደሚደነገግ በንግድ ሕጉ አንቀጽ ፩፻ዥኜ የተመ ለከተ በመሆኑ ፡ በንግድ ሕጉ አንቀጽ ፩፱፪፱ በንግድ ተቋም ላይ የሚሠጡ መያዣዎችን ስለማስመዝገብ የተመለከቱት ድንጋጌዎች የሚጸኑት ወደፊት በነጋሪት ጋዜጣ በሚነገረው ቀንና ሁኔታ መሠረት እንደሚሆን በዚሁ የንግድ ሕግ አንቀጽ ፩ሺ፩፻፭፭ ( ፩ ) የተደነገገ በመሆኑ ፣ ለኢኮኖሚው እንቅስቃሴ አመች ሁኔታ ለመፍጠር የንግድ ተቋሞቻቸውን አባንክ በዋስትና ካስያዙ ባለዕዳዎች ላይ የሚፈለጉ ዕዳዎችን በተቀላጠፈ መንገድ ማሰባሰብና ለወደፊቱ ጥሩ የንግድ አሠራር ባሕል እንዲዳብር ማድረግ በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት | the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia , አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ያንዱ ዋጋ 2 , 80 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፴ሺ፩ ገጽ ፮፻ሮቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፶ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 17 19 February , 1998Page 678 ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ስለንግድ ተቋም የዋስትና መያዣ የወጣ አዋጅ ቍጥር ፲፫ / ፲፱፻፵ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ ፩ . “ የንግድ ተቋም ” ማለት በ፲፱፻፶፪ ዓ . ም . በወጣው የንግድ ሕግ የተመለከተው የንግድ መደብር ነው ፡ ፪ . “ ቢሮ ” ማለት የክልል ወይም የከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም በዋስትና የተሰጡ መያዣዎችን እንዲመዘግብ ሥልጣን የተሰጠው የክልል ወይም የከተማ አካል ነው ፤ ፫• “ ከተማ ” ማለት አዲስ አበባ ፡ ድሬዳዋ ወይም ሌላ ለፌዴራሉ መንግሥት ተጠሪ የሆነ ከተማ ነው . ፬ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፵፯ ውስጥ የተመለከተ ክልል ነው ፡ ፭ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ሁለት ስለንግድ ተቋም ዋስትና መያዣ ምዝገባ መዝገብ ስለማቋቋም ፩ በንግድ ተቋም ላይ የሚደረግ የዋስትና መያዣ መዝገብ በያንዳንዱ ክልል ወይም ከተማ ይቋቋማል ። ፪ የዋስትና መያዣ መዝገብ አደረጃጀትና አቀማመጥ በክልል ወይም በከተማ አስፈጻሚ አካል ይወሰናል ። ፬ . ስለንግድ ፈቃድ አስፈላጊነት የንግድ ተቋምን በመያዣነት ለመስጠት በቅድሚያ የንግድ ተቋሙ አግባብ ባለው የፌዴራል ወይም የክልል አካል ተመዝግቦ የንግድ ፈቃድ ያወጣ መሆን አለበት ። ለምዝገባ ስለማመልከት ፩ . ማናቸውም የዋስትና መያዣ ጥያቄ ጉዳዩ በሚመለከተው ሰው አመልካችነት ሊቀርብ ይችላል ። ፪• የዋስትና መያዣ ለማስመዝገብ ጥያቄ የሚቀርበው በቢሮው የተዘጋጀውን የምዝገባ ማመልከቻ ቅጽ በሁለት ኮፒ ሞልቶ በማቅረብ ይሆናል ። ፫ . አመልካቹ ከቅጹ ጋር ለምዝገባው ጥያቄ መነሻ የሆነውን የውል ሰነድ ወይም ሌላ ማስረጃ አያይዞማቅረብ ይኖርበታል ፬ . ቢሮው ቅጹ ተሞልቶ ሲቀርብለት ትክክለኛነቱን ካረጋገጠ በኋላ እንደአመጣጡ ለቅጹ ተከታታይ ቁጥር ይሰጠዋል ። ፮ ስለምዝገባ ማመልከቻ ቅጽ ይዘት ፩ : ቢሮው ለዋስትና መያዣ ምዝገባ ማመልከቻ ቅጽ አዘጋጅቶ ያወጣል ። ፪• የምዝገባ ማመልከቻ ቅጽ የሚከተሉትን ይጨምራል ፤ ሀ ) የምዝገባ ጥያቄ ያቀረሰው ሰው ወይም ወኪል ስምና አድራሻ : ለ ) የንግድ ተቋሙ አስቀድሞ በመያዣነት የተሰጠ ከሆነ የመዝገቡ ቁጥርና ቀን ፡ ገጽ ፮፻ሮሀ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ሐ ) የዋስትና መያዣው ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ መሆኑ ፡ መ ) የምዝገባው ጥያቄ አዲስ ምዝገባ ለማድረግ ወይም ቀድሞ የተደረገ ምዝገባን ለማሻሻል የቀረበ መሆኑ ፡ ሠ ) ቅጹ የተሞላበት ቀን ፡ ወር እና ዓመተ ምህረት ። ፯ የንብረት መለያ ምልክት ስለመስጠት _ ፩ በንግድ ሕጉ አንቀጽ ፩የሮ፭ ( ፩ ) ( ሰ ) እና አንቀጽ ፩፻፸፰ ( ፩ ) ( ሠ ) መሠረት በዋስትና መያዣነት በተሰጡት የንግድ ተቋም ንብረቶች ላይ የዋስትና መያዣ የተሰጠው ገንዘብ በር ጠያቂ መለያ ምልክት ሊያደርግባቸው ይችላል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የተሰጡት መለያ ምልክቶች በመዝገብ ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል ። ፰ በመዝገብ ስለሚጻፉ መግለጫዎች ፩ . በመዝገብ ውስጥ የሚገቡ አስፈላጊ መግለጫዎች ፡ በተለይም ፡ ሀ ) የዋስትና መያዣው በመዝገብ የገባበት ቀን ፣ ወርና ዓመተ ምህረት ፡ ለ ) ማናቸውም የገንዘብ መጠን ወይም ሌላ ድምር በአኃዝና በፊደል ፡ በማሻያማ ሁኔታ በግልጽ መጻፍ ይኖርባቸዋል ። ፪ . በመዝገብ ላይ የሚጻፉ መግለጫዎች በማይጠፋ ቀለም መጻፍ ይኖርባቸዋል ። ፬ . ስለመመዝገብና ስለምዝገባ ክፍያ ማንኛውም የዋስትና መያዣ ምዝገባ ማመልከቻ ቅጽ ከአስፈ ላጊው ሰነዶች ጋር ቀርቦ የተሟላ መሆኑን ቢሮው ካረጋገጠ አመልካቹን የምዝገባ ክፍያ በማስከፈል ይመዘግባል ። ፲ በመዝገብ የገቡ መግለጫዎችን ስለማረም ፩ . በመዝገቡ ውስጥ የገባ ማንኛውም መግለጫ ያልተሟላ ወይም ትክክል ያልሆነ ሆኖ ከተገኘ ሊታረም ይችላል ። " ፪ ቢሮው በመዝገብ የገቡ መግለጫዎች ስለሚታረሙበት ሁኔታ መመሪያ ያወጣል ። ፲፩ ቁጥጥር ስለማድረግ ቢሮው በዋስትና መያዣነት የተመዘገበውን የንግድ ተቋም ስለሚገኝበት ሁኔታ ለማጣራት ወይም ለመመርመር በቦታው ተገኝቶ ለመቆጣጠር ወይም መግለጫ እንዲሰጥበት ለመጠየቅ ይችላል ፡ ባለንብረቱም ተገቢውን ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት ። ፲፪ ስለመሰረዝ ሥርዓት ፩ የዋስትና መያዣው ከመዝገብ እንዲሰረዝለት የሚጠይቅ ሰው መያዣው እንዲለቀቅለት የተደረገበትን ስምምነት ወይም በፍርድ ቤት የተሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ ማቅረብ ይኖርበታል ። ፪ መዝጋቢው የቀረበውን ሰነድ ትክክለኛነት በማረጋገጥ መያዣውን ከመዝገብ ይሰርዛል ። ክፍል ሦስት በዋስትና የተሰጠን የንግድ ተቋም በሐራጅ ስለመሽጥ ፲፫ : የዋስትና መያዣ ስምምነት የ፲፱፻፵፪ ዓ . ም . የንግድ ሕግ አንቀጽ ፩፻፳፱ ቢኖርም ፣ የዋስትና መያዣ ያለው ገንዘብ ጠያቂ ባንክ የሚፈልገው ገንዘብ ሳይከ ፈለው ቢቀር ከሠላሳ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ ለባለዕዳው በመስጠት ለባንክ ብድር ዋስትና በመያዣ የተሰጠን የንግድ ተቋም በሐራጅ ለመሸጥና የንግድ ተቋሙን የባለቤትነት መብት ለገገር ለማዛወር ወይም ለሁለተኛ ጊዜ በወጣ የሐራጅ ማስታ | ። ወቂያ መሠረት ገገር ካልቀረበ ንብረቱን በብድር ውሉ ውስጥ በሰፈረው የዋጋ ግምት መሠረት ለመውሰድና የባለቤትነት መብቱ በስሙ እንዲዛወርለት ለማድረግ ከባለዕዳ ጋር የሚያደ ርገው ስምምነት ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። ገጽ ፮፻፰ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፲፩• በንግድ ተቋም ላይ ያለ የዋስትና መብት ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት የንግድ ሕጉ የንግድ ተቋም መያዣ እንዲመዘገብ በማስገደዱ በአንቀጽ ፩ሺ፩፻፸፭ ( ፪ ) መሠረት በአውራጃ ፍርድ ቤት የተመዘገበ የዋስትና መያዣ ያለውና ገንዘቡ ያልተከፈለው ገንዘብ ጠያቂ ባንክ ለባለዕዳው ከሠላሳ ቀናትያላነሰማስጠንቀቂያ በመስጠትየንግድተቋሙን በሐራጅ ለመሽጥና ባለቤትነቱንም ለገዢው ለማዛወር ወይም ለሁለተኛ ጊዜ በወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ መሠረት ገዢ ካልቀረበ ንብረቱን በብድር ውሉ ውስጥ በሰፈረው የዋጋ ግምት መሠረት ለመውሰድና የባለቤትነት መብቱ በስሙ እንዲዛወርለት ለማድረግ ይችላል ። ፲፭ በባንክና በባለዕዳው መካከል ስለሚኖር ግንኙነት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ እና፲፬ መሠረት በባንክ የተደረገ ሽያጭ ባለዕዳውን በመወከል እንደተፈጸመ ይቆጠራል ። ፲፮• በሐራጅ ሽያጭ ላይ የፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ሕግ ተፈጻሚ ስለመሆኑ ባንክ በዋስትናመያዣ የያዘውን የንግድተቋም በሐራጅየመሽጥ | 16 . Application of the Civil Procedure Code to Auction ሥልጣኑን በሥራ ላይ በሚያውልበት ጊዜ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ከቁጥር ፫፻፲፩ - ፬፻፱ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደአግባብነታቸው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል ። ስለባንክ ተጠያቂነት ባንክ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፮ የተጠቀሱትን አግባብ ያላቸውን | 17 . Liability of the Bank የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች በመተላለፍ ሽያጩን በመፈጸሙ ባለዕዳው ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት በኃላ ፊነት ተጠያቂ ይሆናል ። ፲፰ የቢሮው ሥልጣንና ኃላፊነት ፩ . የዋስትና መያዣውን የመዘገበው ቢሮ ለሐራጅ ሽያጭ አፈጻጸም የሚረዱ አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ሥልጣንና ኃላፊነት አለው ። ፪ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ቢሮው ለሚወ ስደው እርምጃ የፖሊስ ኃይል መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ያገኘው እንደሆነ ፖሊስን ማዘዝ ይችላል ። ፲፬ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ስላሉ ጉዳዮች የንግድ ተቋምን በዋስትና በያዘ ባለገንዘብ ባንክ አመልካችነት ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ክስ ወይም አፈጻጸም ተቋርጦ በዚህ አዋጅ መሠረት ባንኩ የንግድ ተቋሙን በሐራጅ ለመሽጥና የባለቤትነቱንም መብት ለገዢ ለማስተላለፍ ይችላል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳ ስለንግድ ሕግ አፈጻጸም ፩ አግባብ ያላቸው የ፲፱፻፶፪ ዓም የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች በንግድ ተቋም የዋስትና መያዣዎች ላይ ተፈጻሚነት ይኖራ ፪ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በንግድ ሕጉ የንግድ ተቋምን በዋስትና ማስያዝን በሚመለከቱት ድንጋጌዎች ውስጥ ፣ ሀ ) ክልልን የሚመለከት ከሆነ “ ጠቅላይ ግዛት ” የሚለው ክልል ” እንዲሁም “ የንግድ ሚኒስቴር ” የሚለው “ ቢሮ ” ፡ ወይም ገጽ ፮፻፷፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ለ ) ከተማን የሚመለከት ከሆነ “ ጠቅላይ ግዛት ” የሚለው “ ከተማ ” እንዲሁም “ ንግድ ሚኒስቴር ” የሚለው “ ቢሮ ” ተብሎ ይነበባል ። ፳፩ - ስለ ክፍያ በንግድ ሕጉና በዚህ አዋጅ መሠረት ለዋስትና መያዣ ምዝገባና ለተዛመዱ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያ በክልል ወይም በከተማ ሕግ ይወሰናል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ በንግድ ተቋም ላይ ስለሚሰጡ መያዣዎች ምዝገባ የንግድ ሕጉ አንቀጽ ፩፻ኞ፱ እና የዚህ ኣዋጅድንጋጌዎችየሚጸኑት ከየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ጀምሮ ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፵ ዓ . ም . ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?