የሰበር መ / ቁ . 19967
ቀን ሚያዝያ 4/1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የአምቦ ማዕድን ውሃ ፋብሪካ
ተጠሪዎች፡- እነ ጌትነት ብርሃኑ / 16 ሠዎች /
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን /
ይወሰንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / Cause of
action / አለው ? ወይስ የለውም ? ጉዳዩንስ ለመዳኘት የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
ቦርድ ስልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
የም / ኦሮሚያ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ
እንደተቀጠርኩ / ን / ይወሰንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውሣኔ
ሰጥቷል ፡፡ በውሣኔው ላይ ይግባኝ የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ
የተመለከተውን የህግ ነጥብ ሳይመረመር አልፎታል ፡፡
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር
ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተጠሪ / ዎች ቀርበው መልስ ሰጥተዋል ፡፡
ፌዴራራ በቅሳያ ፍርድ ቤት
ከ 1919 y
ችሎት ተቀብለው ወ l 18180 አግባብነት ያላቸው የአሰሪና ሠራተኛ
ችሎቱም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወሰንልኝህን / የሚል ዳኝነት በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of action / አለው ? ወይስ የለውም ? የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ መርምሯል ፡፡
ይህ ችሎት በመ.ቁ. 16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውሣኔ አግባብነት ያላቸውን የህጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሠራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሠራተኛ ሕጉ አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበት ጥቅም ካለ የቀረበት ጥቅም እንዲሰጠው መጠየቅ / ክስ ማቅረብ / የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ በሚል ብቻ የሚቀርብን ክስ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድም ሆነ የሥራ ክርክር
ሊያዩ የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የሕግ ትርጉም
በሌላም በኩል ቢሆን
አዋጅ ድንጋጌዎችን በመተርጎም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን
የተሰጠው የወል የሥራ ጉዳዮችን ነው ፡፡ አንድ የሥራ ክርክር የወል የሥራ ክርክር ነው
የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ
አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፡፡ በአንፃሩ አንድ የሥራ ክርክር
የወል ሳይሆን የግል የሥራ ክርክር
ጉዳይ ነው
የሚባለው የክርክሩ ውጤት
በተከራከረው ሠራተኛ / ሠራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሲገኝ ነው በማለት የህግ
ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
በዚህ ጉዳይም የም / ኦሮሚያ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪዎች
ያቀረቡት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወስንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ምክንያት የሌለው ከመሆኑም በአሻገር
የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ
አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የሥራ ክርክር
አይደለም ፡፡ በመሆኑም በሁለቱም ምክንያቶች የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባው
ጉዳዩን አከራክሮ በመወሰኑ መሠረታዊ የህግ ስህተት ፈጽሟል ፡፡
ው ሣ ኔ
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመቁ . ጂቢ.ኤም 9-24 / 1778 መጋቢት
16 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ .
24769 በሚያዝያ 07 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌዴራ 6 ቀሳ ገርድ ቤት
You must login to view the entire document.