×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
ዋጅ ቁጥር ፪፻፶፬/፲፱፻፶፭ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ አዲስ አበባ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፱ / ፲፱፻፶፭ ዓም የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ ገጽ ፲፱፻፶፩ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፱ / ፲፱፻፲፭ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ፣ የልማት ሃሣብ ንድፍ ሲዘጋጅ | to predict and manage the evironmental effects which a ቦታው ሲመረጥ ፣ ሲገነባ ወይም ሲተገበር እንደዚሁም በመተግበር | Proposed development activity as a result of its design sitting , ላይ ያለ እንቅስቃሴ ሲሻሻል ወይም ሲቋረጥ የሚያስከትለውን | Construction , operation , or an ongoing one as a result of its ተፅዕኖ በመተንበይና አስቀድሞ በማረም በውል የታሰበበትን [ modification termination , entails and thus helps to bring ልማት ለማምጣት የሚያግዝ በመሆኑ ፣ መንግሥታዊ ሰነድ በአካባቢ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን | environment prior to the approval of a public instrument ተፅዕኖ ለመለየት ገና ከመፅደቁ በፊት መገምገም ፣ የመፅደቂያው | provides an effective means of harmonizing and integrating ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት አካባቢያዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ባህላዊና | environmental , economic , cultural and social considerations ማህበራዊ ታሳቢዎችንና ግቦችን ዘላቂ ልማትን ለማምጣት | into a decision making process in a manner that promotes በሚያመች ሁኔታ እንዲዋሃዱና እንዲቀናጁ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ፣ አሉታዊ የአካባቢ ተፅዕኖዎችን መተንበይ ፣ የመፍትሔእርም | fostered by the prediction and management of likely adverse ጃዎችን መውሰድና ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቃሚነታቸውን | environmental impacts , and the maximaization of their socio ማዳበር በሕገ መንግሥት የተደነገጉትን የኣካባቢ ደህንነት መብቶ | economic benefits . ችንና ዓላማዎችን የመተግበርን ሂደት የሚያግዝ በመሆኑ ፣ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ኣስተዳደራዊ ግልፅነትና በኃላፊነት | to bring about administrative transparency and accountablity , ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ፣ በአጠቃላይ ራሱንና አካባቢውን በሚመለከቱ የልማት እቅዶች አወጣጥና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሕዝቡን ፣ በተለይም ደግሞ ማሕበረሰቦችን ለማሳተፍ የሚረዳ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows : -መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፱ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ፲፱፻፶፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta No. 11 3December , 2002 Page 1952 ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ማለት ነው ፤ ፪ . “ እካባቢ ” ማለት በመሬት ፣ በከባቢ አየር ፣ በአየር ሁኔታ እና በአየር ንብረት ፣ በውሃ ፣ በህያዋን ፣ በድምፅ ፣ በሽታ ፣ በጣእም ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች እና በስነ ውበት ሳይወሰን ፣ በተፈጥሮአዊ ሁኔታቸው ወይም በሰው አማካኝነት ተሻሽለው ወይም ተለውጠው የሚገኙ ነገሮች በሙሉና ያሉበት ቦታ ፣ እንዲሁም መጠናቸውን ወይም ሁኔታ ቸውን ወይም ደግሞ የሰው ወይም የሌሎች ሕያዋን በጎ ሁኔታን የሚነኩ ተስተጋብሮቶቻቸው ድምር ነው ፤ ፫ . “ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ” ማለት አንድ ፕሮጀክት ወይም መንግሥታዊ ሠነድ ተግባራዊ ሲሆን የሚያስከት ለውን ገንቢም ሆነ አፍራሽ ውጤት በቅድሚያ ለይቶ የማወቂያና የመመዘኛ ዘዴ ነው ፤ ፬ • “ ተፅዕኖ ” ማለት በአካባቢ ወይም በንዑሳን ክፍሎቹ ላይ በሚፈጠር ለውጥ ምክንያት ማንኛውም በሰው ጤና ወይም ደህንነት ፣ በዕፅዋት ፣ በእንስሳት ፣ በአፈር ፣ በአየር ፣ በውሃ ፣ በአየር ንብረት ፣ በተፈጥሮአዊ ወይም በባህላዊ ቅርስ ፣ በሌላ ቁሳዊ ቁም አካል ፣ ወይም በአጠቃላዩ ሲታይ በአካበቢያዊ ፣ በማሕበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊ ወይም በባሕላዊ ገፅታዎች ላይ የሚከሰት ተከታይ ለውጥ ነው ፤ ፭ “ የፈቃድ ሰጪ መሥሪያ ቤት ” ማለት እንደሁኔታው የኢንቨስትመንት ፣ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ለመስጠት ወይም`የንግድ ድርጅት ለመመዝገብ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም የመንግሥት አካል ነው ፤ ፮ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፤ ፯ . “ በካይ ” ማለት ፈሳሽ፡ ጠጣር ወይም ጋዝ የሆነ ፣ በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ፤ ሀ ) ያረፈበትን የአካባቢ ክፍል ጥራት በመለወጥ ጠቀሜታ የመስጠት አቅሙን የሚያጓድል ፣ ወይም ለ ) በሰው ጤና ወይም በሌሎች ሕያዋን ላይ ጉዳት የሚያደርስ ወይም ሊያደርስ የሚችል መርዝን፡በ ሽታን ፣ ክርፋትን ፣ ጨረርን ፣ ድምፅን ፣ ንዝረትን ፣ ሙቀትን ወይም ሌላ ክስተትን የሚያመነጭ ፣ ማንኛውም ነገር ነው ፤ ፰ “ ፕሮጀክት ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ በማንኛውም መመሪያ ውስጥ በተጠቀሰ ርዕስ የሚካተት ማንኛውም አዲስ የልማት እንቅስቃሴ ፣ ወይም በነባር ድርጅት ላይ የሚደረግ ጉልህ መስፋፋት ወይም ለውጥ ፣ ወይም ደግሞ ተቋርጦ የነበረ ሥራን መልሶ ለመጀመር የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው ፤ ፱ . “ የፕሮጀክት ባለቤት ” ማለት ፕሮጀክቱ በመንግሥት የተወጠነ ሲሆን የሚመለከተው የመንግሥት አካል ፣ ወይም በግሉ ዘርፍ የተወጠነ ሲሆን ባለሀብት የሆነው ሰው ነው ፤ ፲ “ መንግሥታዊ ሠነድ ” ማለት ፖሊሲ ፣ ስልት ፣ መርሐ ግብር ፣ ሕግ ወይም የዓለም አቀፍ ስምምነት ነው ፤ ፲፩ . “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ፩ የተመለከቱት የአገሪቱ ክፍሎች ማለት ሲሆን ፣ ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም የድሬዳዋ አስተዳደሮችንም ይጨምራል ፤ ፲፪ . “ የክልል የአካባቢ መ / ቤት ” ማለት ለአካባቢና ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ወይም ቁጥጥር በክልሉኃላፊነት የተሰጠው ማንኛውም የክልል የመንግሥት አካል ነው ። ገጽ ፲፱፻፶፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ • ም • ክፍል ሁለት ፫ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ፩ ማንም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ በወጣ መመሪያ መሠረት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ፕሮጀክት ፣ ከባለሥልጣኑ ወይም ከሚመለ ከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ይሁንታ ሳያገኝ ተግባራዊ ለማድረግ አይፈቀድለትም ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ከሚያስፈልገው ማንኛውም ፕሮጀክት የሚከተለውን ተፅዕኖ ኢምንት ነው ብሎ ከገመተ የፕሮጀክቱን ባለቤት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲያካሂድ ላያስገድደው ይችላል ። ፫ . ማንኛውም ፈቃድ ሰጪ መሥሪያ ቤት የኢንቨስት መንት ፣ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ከመሥጠቱ በፊት ከባለሥልጣኑ ወይም ከሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንዲሆን ይሁንታ መሰጠቱን ማረጋገጥ አለበት ። ፬ • የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ ተቀባይነት ማግኘቱና ከባለሥልጣኑ ወይም ከሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ይሁንታ መሰጠቱ የፕሮጀክቱን ባለቤት ጉዳት በማድረስ ከሚከተል ኃላፊነት ነፃ አያደርገውም ። ፭ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተጠያቂነት ነፃ መሆን የሚቻለው ጉዳቱ በተጎጂው በራሱ ወይም ደግሞ የፕሮጀክቱ ባለቤት ኃላፊነት በሌለበት በሦስተኛ ወገን መድረሱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው ። የተፅዕኖ መወሰኛታሳቢዎች ፩ . የፕሮጀክት ተፅዕኖ ከፕሮጀክቱ መጠን ፣ ከመካሄጃ | 4. Considerations to Determine Impact ሥፍራው ፣ ከባህሪዩ ፣ ከክልል ተሻጋሪነቱ ፣ ከሌሎች ተፅዕ ኖዎች ወይም ክስተቶች ጋር ከሚኖረው ተዳማሪነት ፣ ከቆይታው ፣ ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ከመቻሉ ወይም ካለመቻሉ ፣ እንደዚሁም ከሌላ ተዛማጅገጽታዎች አኳያ መገምገም አለበት ። ፪ ጠቃሚና ጎጂ ውጤቶች ካሉት ፣ ነገር ግን ጠቃሚ ጎኑ በትንሹ ብቻ ከሚያመዝን ወይም መብለጥ አለመብለጡ ከሚያወዛግብ አንድ ፕሮጀክት ሊከተል የሚችልን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲወስን ባለሥልጣኑ ወይም የሚከ ተለው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ወደ ጥንቃቄ እርምጃ በማዘንበል ፕሮጀክቱ ጉልህ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያስከትል ይችላል በማለት መወሰን አለበት ። ፭ . የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ስለሚያስፈልጋቸው ፕሮጀክቶች ፩ . በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ በማንኛውም መመሪያ በተጠቀሰ ርዕስ በሚካተት በማንኛውም ፕሮጀክት ሁሉ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መካሄድ አለበት ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው መመሪያ፡ ሀ ) አሉታዊ ተፅዕኖ ያስከትሉ ይሆናል ተብለው ስለማ ይታሰቡ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የማያስፈልጋ ቸውን ፕሮጀክቶች ' እና ለ ) አሉታዊ ተፅዕኖ ያስከትሉ ይሆናል ተብለው ስለሚ ታሰቡ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የሚያስፈልጋ ቸውን ፕሮጀክቶች ለይቶ ማመልከት አለበት ። ፮ ክልል ተሻጋሪ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አንድ የፕሮጀክት ባለቤት ክልል ተሻጋሪና ተፅዕኖ ሊያስከትል የሚችል ፕሮጀክትየአካባቢተፅዕኖ ግምገማ ሲያካሂድ ' ጉዳት ይደርስባቸው ይሆናል ተብለው የሚገመቱ በየትኛውም ክልል የሚገኙ ማሕበረሰቦችን ማሳተፍ አለበት ። ገጽ ፲፱፻፶፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም • ፪ ክልል ተሻጋሪ ተፅዕኖ ሊያስከትል የሚችል ፕሮጀክት በሚካሄድበት ክልል ውስጥ የሚገኝ የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት፡ የፕሮጀክቱን የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባ ለባለሥልጣኑ እንዲቀርብ ማድረግ አለበት ። ባለሥልጣኑ ክልል ተሻጋሪ የአካባቢ ተፅዕኖ ሊያስከትል የሚችል ፕሮጀክት የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባን መመርመር ከመጀመሩ በፊት ጉዳት ይደርስባቸው ይሆናል የሚባሉት በየሚመለከተው ክልል የሚገኙት ማሕበረሰቦች አስተያየት ተጠይቆ የተካተተ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ክፍል ሦስት ፯ . የፕሮጀክት ባለቤት ግዴታዎች ፩ አንድ የፕሮጀክት ባለቤት የፕሮጀክቱን የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አካሂዶ፡ የፕሮጀክቱን አሉታዊ ተፅዕ ኖዎች በቅድሚያ ለይቶና ተፅዕኖዎቹን የማስቀሪያ ወይም የመቋቋሚያ ዘዴን በጥናቱ ውስጥ አካትቶ ባለሥ ልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ተገቢነታቸውን ከወሰነባቸው ሠነዶች ጋር የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባውን ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤትማቅረብ ኣለበት ። ፪ . በፕሮጀክቱ ላይ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የሚካሄደው፡ የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባም የሚዘጋጀው ባለሥ ልጣኑ በሚያወጣው ማንኛውም መመሪያ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በሚያሟሉ ባለሙያዎች መሆኑን የፕሮ ጀክት ባለቤቱ ማረጋገጥ አለበት ። ፫ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማን ለማካሄድና የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባን ለማዘጋጀት የሚያስፈልገውን ወጪ የፕሮ ጀክቱ ባለቤት መሸፈን አለበት ። ፬ . አንድ የፕሮጀክት ባለቤት ፕሮጀክቱን ሲተገብር በተሰጠው ፈቃድ ውስጥ የተዘረዘሩ ግዴታዎችን ማሟላት አለበት ። የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ ፩ የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባ ባለሥልጣኑ ወይም የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት የፕሮጀክቱን መካሄድ ወይም አለመካሄድ ተገቢነት እንዲሁም ሲካሄድ ሊኖረው የሚገባውን ሁኔታ ለመወሰን የሚያስችለውን በቂ መረጃ የያዘ መሆን አለበት ። ፪ • የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ ቢያንስ የሚከተሉትን ዝርዝሮች የያዘ መሆን አለበትተነ፡ የፕሮጀክቱን ባህሪ በጥቅም ላይ የሚውለውን ቴክኖሎጂና አጠቃቀም፡ ለ ) ፕሮጀክቱ ሲተገበር እንዲሁም ቋሚ ሥራው ሲከናወን ወደ አካባቢ የሚለቀቀውን የበካይ ይዘትና መጠን፡ ሐ ) የሥራው እንቅስቃሴ የሚጠይቀውን የኃይል ፍጆታና ምንጭ ሊከተል ስለሚችል ክልል ተሻጋሪ የአካባቢ ተፅዕኖ መረጃ፡ ሠ ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይከተላሉ ተብለው የተተመኑ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተፅዕኖዎች ባህሪያትና የሚቆዩበት ጊዜ ረ ) አሉታዊ ተፅዕኖን ለማስወገድ ' ለመቀነስ ወይም ለማቃለል የታቀዱ እርምጃዎች፡ ሰ የአካባቢ አያያዝ ችግርን ለማቃለል የተነደፉ እቅዶች፡ የአደጋ መከላከያ ዝግጁነት እና ሽ ) ፕሮጀክቱ በሚተገበርበትና እንደዚሁም ቋሚ ሥራው በሚከናወንበት ወቅት የውስጥ የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎች የሚካሄዱባቸውን መንገዶች ። ፫ . ባለሥልጣኑየአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባን ለማዘጋጀትና ዘገባውን ለመመርመር የሚረዱ ሃሳቦችን የሚዘረዝሩ መመሪያዎችን ማውጣት ኣለበት ። ፫ : ልዩ ሁኔታ ካላስገደደው በስተቀር ልጣኑ ወይም ገጽ ፲፱፻፶፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ፀ • የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ ምርመራ ፩ ምርመራ እንዲካሄድበት ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመለ ከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በሚቀርብ የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባ፡ ማንም ሊረዳው በሚችል ቋንቋ በአጭሩ የተዘጋጀ የጥናቱን መግለጫ የያዘና እንደዚሁም የጥናቱ መረጃ መሟላትንና ትክክለኛነቱን የሚያመላክት፡ አጭር መግለጫ መያዝ ኣለበት ። ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ የሕዝብ አስተያየትንና የባለሙያዎች አስተሳሰብን በማመዛዘን የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናቱን ዘገባ ከመረመረ በኋላ፡ ሀ ) ጎጂ ተፅዕኖ የማያስከትል መሆኑን ካመነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፕሮጀክቱን ይቀበላል ፥ እንዲተገ በርም ይሁንታውን ይሰጣል ፥ ለ ) ጎጂ ተፅዕኖዎቹን ለማስቀረት ወይም በበቂ ሁኔታ ለመቋቋም የሚቻል መሆኑን ካመነ ለማስቀረት ወይም ወደ ኢምንትነት ለመቀነስ የሚያስፈል ጉትን ቅድመ ሁኔታዎች ዘርዝሮ እንዲሟሉ በማዘዝ ፕሮጀክቱ እንዲተገበር ይሁንታ ይሰጣል፡ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚሆንበት በአካባቢ ላይ የሚከተለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በአጥጋቢ ሁኔታ ለማስቀረት እንደማይቻል ካመነ ትግበራውን ይከለክላል ። የፀደቀ የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ፩ እንዲተገበር ይሁንታ የተሰጠው የፕሮጀክት የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባው ይኸው ይሁንታ ሲሰጥ አብሮ የተመለከተውን የጊዜ ገደብ ተከትሎ ካልተተገበረ ተቀ ባይነቱ ይቀራል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ አተገባበር ተገቢ አለመሆኑን ሊያስረዳ የሚፈልግ የፕሮጀክት ባለቤት እንደአግባቡ ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመለ ከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ማመልከት ይችላል ። የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ማመልከቻውን ከተቀበለበት ዕለት ጀምሮ በሰላሣ ቀናት ውስጥ የዘገባው ተቀባይነት ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘም ወይም የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማው እንዲከለስ ወይም እንደገና እንዲካሄድ መወሰን አለበት ። ክፍል አራት ፲፩ የአዲስ ሁኔታ መከሰት የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባ ከቀረበ በኋላ ከባድ እንድምታ ያለው ቀደም ሲል ያልተጤነ እውነታ ቢከሰት ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት እንድ ምታውን ለማጤን እንዲቻል የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማው እንደአስፈላጊነቱ እንዲከለስ ወይም እንደገና እንዲካሄድ ማዘዝ ይችላል ። ፲፪ የትግበራ ክትትል ፩ . የፕሮጀክቱ ባለቤት ፣ ፕሮጀክቱን በመተግበር ላይ የሚገኘው ለፕሮጀክቱ ትግበራ ይሁንታ በተሰጠበት ወቅት በገባው ቃል እና በተጣለበት ግዴታ ሁሉ መሠረት መሆኑን ለመገምገም ባለሥልጣኑ ወይም የሚ መለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በፕሮጀክቱ አተገባበር ላይ ክትትል ማድረግ ኣለበት ። ለው ተፅዕኖ እቲ 4 ፡ ገጽ ፲፱፻፶፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፪ አንድ የፕሮጀክት ባለቤት እንዲተገብረው ይሁንታ የተሰ ጠውን ፕሮጀክት በገባውቃል ወይም በተጣለበት ግዴታ መሠረት ካልተገበረ ፣ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት መወሰድ ያለበትን የእርምት እርምጃ በመግለጽ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ይችላል ። ፫ እንደአግባቡ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ማንኛውንም ፕሮጀክት እንዲተ ገበር በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ( ፪ ) ሀ ወይም ( ለ ) መሠረት የሰጠውን ይሁንታ ሲያግድ ወይም ሲሰርዝ ሌላ ማንም ፈቃድ ሰጪ መሥሪያ ቤት ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሰጠውን ፈቃድ ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ ማገድ ወይም መሠረዝ አለበት ። ፲፫ የመንግሥት ሠነድ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት በወጣ በማንኛውም መመሪያ በሚገለጽ መደብ ውስጥ የሚካተት ማንኛውም የመንግሥት ሠነድ ከመፅደቁ በፊት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲካሄድበት መደረግ አለበት ። ፪ በባህሪያቸው ቸል ሊባል የማይችል አካባቢያዊ ተፅዕኖ ያስከትሉ ይሆናል ተብለው የሚገመቱ የመንግሥት ሠነዶች መደብን ለመለየትና የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲካሄድባቸው ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ባለሥ ልጣኑማውጣት አለበት ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በወጣ በማንኛውም መመሪያ መሠረት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ በሚያስፈ ልገው መደብ የሚካተትን ማንኛውም የመንግሥት ሠነድ የሚያዘጋጅ የመንግሥት አካል በሠነዱ ላይ የኣካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የተካሄደበት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ፬ • ማንኛውም የመንግሥት የሚያዘጋጀው ማናቸውም የመንግሥት ሠነድ ሊያስከትለው የሚች ለማስቻል ከባለሥልጣኑ ጋር ፲፬ የኃላፊነት ክፍፍል ፩ ፈቃድ የመስጠቱ ፣ የመተግበሩ ወይም የአተገባበር ቁጥጥሩድርሻ የፌዴራል መንግሥት አካል ከሆነ ወይም ፕሮጀክቱ ክልል ተሻጋሪ የአካባቢ ተፅዕኖ ያስከትል ይሆናል ተብሎ የሚታሰብ ከሆነ ፣ የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባውን የመመርመር ፣ ፕሮጀክቱ እንዲተገበር ይሁንታ የመስጠትና ክትትል የማካሄድ ኃላፊነት የባለ ሥልጣኑ ነው ። ፪ : ፈቃድ የመስጠቱ ፣ የመተግበሩ ወይም የአተገባበር | ቁጥጥር ድርሻ የክልል መንግሥት አካል ከሆነና ፕሮጀክቱ ክልል ተሻጋሪ የአካባቢ ተፅዕኖ ያስከትል ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ ከሆነ ፣ የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባውን የመመርመር ፣ ፕሮጀክቱ እንዲተገበር ይሁንታ የመስጠትና አተገባበሩን የመከታተልኃላፊነት የክልሉ የኣካባቢ መሥሪያ ቤት ነው ። ክፍል አምስት ፲፭ ስለሕዝብ ተሳትፎ ፩ . ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ማንኛውንም የአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ በዘገባው ላይ አስተያየት መጠየቅ አለበት ። ፪ . ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በአጠቃላዩ የሕዝብ ፣ በተለይም ደግሞ የፕሮጀክቱ አተገባበር ጉዳት ያስከትልባቸው ይሆናል ተብለው የሚገመቱ ማኅበረሰቦች አስተያየት ፣ በአካባቢ መካተቱን ፣ እንደዚሁም ምርመራው በሚካሄድበት ወቅት መጤኑን ፣ ማረጋገጥ አለበት ። ገጽ ፲፱፻፶፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፲፮ ስለማበረታቻ ፩ . ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት የተጎዳ አካባቢን መልሶ እንዲያገግም ለማስደረግ የተዘጋጀ ፕሮጀክት አተገባበርን ኣቅሙ በሚ ፈቅደው መሠረት ማገዝ አለበት ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የተጎዳ አካባቢን እንዲያገግም ለማድረግ ወይም ብክለትን ለማስቀረት ወይም የተበከለን ለማጽዳት ለተዘጋጀ ፕሮጀክት ባለሥልጣኑ ኣቅሙ በፈቀደ መጠን ተጨማሪ ወጪዎችን ለመሸፈኛ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፎች ማድረግ ይችላል ። ፲፯ • የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት ፩ . ለፕሮጀክት ትግበራ በተሰጠ ይሁንታ ወይም በክትትል ፣ ወይም ፕሮጀክቱን በሚመለከት ከባለሥልጣኑ ወይም ከክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በተሰጠ በማንኛውም ሌላ ውሣኔ ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ሰው ቅሬታውን እንዳግባቡ ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ማቅረብ ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተደነገገው መሠረት ፣ የባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የአካባቢ መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊ ቅሬታው በደረሰው በሰላሣ ቀናት ውስጥ ውሣኔ መስጠት አለበት ። ክፍል ስድስት ፲፰ ስለ ጥፋትና ቅጣት ፩ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፣ ይህን አዋጅ ወይም ሌላ አግባብ ያለውን ሕግ ወይም መመሪያ የሚተላለፍ ማንኛውም ሰው ጥፋት ፈጽሞ አልና ቅጣት ይጣልበታል ። ፪ . ማንኛውም የፕሮጀክት ባለቤት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲካሄድበት የተደነገገበትን ማንኛውም ፕሮጀክት ፣ ከባለሥልጣኑ ወይም ከሚመለከተው የክልል የአካባቢመሥሪያ ቤት ይሁንታ ሳያገኝተግባራዊ ያደረገ እንደሆነ ወይም በአካባቢ ተፅዕኖ የጥናት ዘገባው ውስጥ ሀሰተኛ መግለጫ ያቀረበ እንደሆነ ጥፋት ፈጽሟልና ከሃምሣ ሺ ብር በማያንስና ከአንድ መቶ ሺ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፫ . ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ ሲሰጠው የተጣለበትን ግዴታ ካልተወጣ ፣ ወይም ተፈላጊ ዝርዝ ሮችን በመዝገብ ሳያሰፍር ከቀረ ጥፋት ፈፅሞአልና ከአስር ሺ ብር በማያንስና ከሃያ ሺ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፬ . በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ጥፋት ሲፈጽም ድርጅቱ እንዲከፍለው ከተፈረደበት መቀጮ በተጨማሪ የሕጉን መከበር ለማረጋገጥ መፈጸም የሚገ ባውን ተግባርበትጋትያልተወጣ በመሆኑየሥራመሪው ከአምስት ሺ ብር በማያንስና ከአሥር ሺ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፭ ይህን አዋጅ ወይም በሥሩ የሚወጣውን ማንኛውም ደንብ ወይም መመሪያ በመጣስ ጥፋተኛነቱ የተረጋገጠ ሰው ፣ ከሚወሰንበት ከማንኛውም ቅጣት በተጨማሪ የደረሰውን ጉዳት በሙሉ በራሱ ወጪ እንዲያስተካክል ወይም እንዲተካ ፍርድ ቤቱ ማዘዝ ይችላል ። ገጽ ፲፱፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ክፍል ሰባት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፱ • ደንቦችን የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል ። ፳ መመሪያዎችን የማውጣት ሥልጣን ባለሥልጣኑ ይህን አዋጅ በተሟላ ሁኔታተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፳፩ . የመተባበር ግዴታ ለዚህ አዋጅ አተገባበር ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፳፪ ተፈጻሚነት የሌላቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር ተቃራኒ የሆነ ሕግ ወይም አሠራር በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት | 23. Effective Date አይኖረውም ፣ ፳፫ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅካኅዳር፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?