×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 273/1994 የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዩሽን ባለሥልጣን እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፳ አዲስ አበባ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፫ ፲፱፻፲፬ ዓም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እንደገና ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፯፻፵ አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፫ ፲፱፻፲፬ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቀልጣፋ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ኢኮኖሚያዊ የአየር ትራንስ ፖርት አገልግሎት እንዲኖር ፣ እንዲሁም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ | safety and an economic air transport services and promote the ልማት በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ Federal Democratic Republic of Ethiopia shall operate in a አውሮፕላኖች ሥራ ላይ በዋሉ ተገቢ ሕጐች ፣ ደንቦችና መመሪ ያዎች መሠረት ደህንነት እና ብቃት ባለው ሁኔታ እንቅስቃሴ | laws , regulations and directives in force ; ማድረጋቸው አስፈላጊ በመሆኑ ፣ የቺካጐ ኮንቬንሽንና ተቀጽላዎቹ እንዲሁም የዓለም አቀፍ | Convention and the Annexes thereto , and to the Standards and ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ያወጣቸውን ደረጃዎችና ተመራጭ | Recommended Practices issued by the International Civil የአሠራር ልምዶች ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጇል ። | of the Constitution of the Federal Democratic Republic of ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፫ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም እንዲሰጠው ካላስፈለገ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ አይሮፕላን ማረፊያ ” ማለት በመሬትም ሆነ በውሃ ላይ በከፊልም ሆነ በሙሉ ለአይሮፕላን ማረፊያ ፣ መነሻ፡ መንቀሳቀሻ ፣ ወይም መገልገያ የተከለለ ቦታንና በዚህ ክልል ውስጥና በአዋሳኙ ለነዚሁ ተግባሮች የሚውሉትን ሕንጻዎች ፣ ድርጅቶችና መሣሪያዎች ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ " .. የአይሮፕላን | ገጽ ፩ሺ፯፻፵፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፯ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓ • ም • ፪ . “ አይሮፕላን ” ማለት በጠፈር ውስጥ በአየር ለመንሳፈፍ የሚያስችለውን ድጋፍ ከመሬቱ ገጽታ ሳይሆን ፣ ከአየሩ ሁኔታ የሚያገኝ ማንኛውም በራሪ መሣሪያ ነው ፤ ፫ . “ አደጋ ” ማለት አውሮፕላን ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም አንድ ሰው በአውሮፕላን ለመሄድ በማሰብ በአውሮፕላን ከተሳፈረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ወረደበት ጊዜ ድረስ ከአውሮፕላኑ ጋር ግንኙነት ያለውና ፣ ሀ ) አንድ ሰው ከታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሲሞት ወይም ብርቱ የአካል ጉዳት ሲያጋጥመው ፣ ፩ . በአይሮፕላን ውስጥ በመሆኑ ፣ ወይም ፪ . ከአይሮፕላን አካል ጋር ወይም ከአይሮፕላን ከተገነጠሉ አካላት ጋር በቀጥታ በመነካካት ፣ ፫ ጉዳቱ በተፈጥሮ ምክንያት ፣ በራስ ወይም በሌሎች የተደረገ ወይም ለመንገደኞች ወይም ለአይሮፕላን መንገደኞች ወይም ሠራተኞች ከሚገባው ቦታ ውጭ በሚጓዙድብቅ ተጓዦች ላይ ከሚደርስ ጉዳት በስተቀር ለጀት ፍንዳታ ቀጥታ መጋለጥ ፣ ወይም አይሮፕላኑ ጉዳት ወይም አካላዊ ውድቀት ደርሶበት በዚሁ ምክንያት ፣ ፩ . አካላዊ ጥንካሬውን ወይም የበረራ ብቃት ሲያጣ ፣ እና ፪ • የተጐዳው ክፍል ትልቅ ጥገና ወይም ለውጥ ሲያስፈልገው ሞተር ብልሽት ወይም ጉዳት ደርሶበት ጉዳቱ በሞተሩ ፣ በካውሊንግስ ወይም ኣባሪ ክፍሎች ፣ በተሽከርካሪ አካሉ ፣ በአን ቴናው ፣ በጐማው ፣ በፍሬኑ ፣ በውጭ አካሉ ላይ የሚደርሱ ትንንሽ ቀዳዳዎች ሲሆን ፣ ወይም ሐ ) የአይሮፕላኑ መጥፋትን ወይም ጨርሶ ከማይደረ ስበት ቦታ መውደቅን ፣ የሚያጠቃልል ነው ። ፬ • “ አጋጣሚ ” ማለት ከአይሮፕላን አደጋ እንቅስቃሴን ደህንነት የሚያቃውስ ወይም ሊያቃውስ የሚችል ክስተት ነው ፤ ፭ “ የአየርናቪጌሽን ” ማለት አይሮፕላንን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መምራትና አይሮፕላኑ በኣየር ላይ ባለ ጊዜ ትክክለኛ ቦታውን የማወቅን ተግባር የሚጨምር ነው ፤ ፮ . “ የአየር ናቪጌሽን መገልገያ ” ማለት ማንኛውንም ቦታ ፣ የብርሃን መሣሪያ ፣ የአየር ሁኔታ ፣ ዜና ማከፋፈያ ሬዲዮና ሌላ በኤሌክትሪክ የሚሠራ መገናኛ ፣ የአቅጣጫ መፈለጊያ መሣሪያ ወይም አይሮፕላኑ ሲበር ፣ ሲያርፍ ፣ ወይም ሲነሳ ለመቆጣጠር የሚያገለግለው መሣሪያና ሌላ ይህን የመሳሰለው መገልገያ ነው ፤ “ የአየር መንገድ ” ማለት የአገር ውስጥ ወይም የዓለም አቀፍ መደበኛና መደበኛ ያልሆነ የኣየር ማመላለሻ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውም የንግድ ድርጅት ነው ፤ ፰ “ የበረራ መስመር ” ማለት ባለሥልጣኑ ለአይሮፕላን በረራ ምቹ ነው ብሎ የወሰነው የአየር መስመር ነው ፤ ፱ . “ የአየር ትራፊክ ቁጥጥር አገልግሎት ” ማለት የአይሮ ፕላን ከአይሮፕላን ወይም ከአደናቃፊ ነገር ጋር ግጭት እንዳይደርስበትና የኣየር ትራፊክ እንቅስቃሴ በሚገባ እንዲካሄድና እንዲጠበቅ የማድረግ አገልግሎት ነው ፤ ፲ . “ የአየር ማመላለሻ አገልግሎት ” ማለት በኣየር መንገ ደኛን ፣ ጭነትን ወይም ፖስታን የማመላለስ አገልግሎት ገጽ ፬ሺ፯፻፵፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፲፩ . “ ለመብረር ብቁ መሆን ” ማለት አንድ አይሮፕላን አስፈላጊ ከሆኑት መሣሪያዎችና ክፍሎች ጋር ባለሥ ልጣኑ በሚወስነው ዓይነት ተግባሩን በበቂ ሁኔታ ለማከናወን መቻሉ ነው ፤ ፲፪ . “ የአቪዬሽን ፐርሶኔል ” ማለት የበረራ አዛዥ ፣ ረዳት አብራሪን ወይም የበረራ መሐንዲስን ወይም የማንኛ ውንም የበረራ ቡድን ኣባል ወይም በአይሮፕላን ፣ በአይሮፕላን ሞተሮችና ውልብልቢቶች ወይም በማን ኛውም የአይሮፕላን አካላት ላይ ምርመራ ፣ ዕድሳት ፣ ጥገና ፣ የአካላት ቅየራ የሚያካሂድና እንዲሁም እንደ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሆኖ የሚያገለግለውን ያጠቃ ፲፫ “ የቺካጐ ኮንቬንሽን ” ማለት ለዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን በዲሴምበር ፲፱፻፵፬ የተፈረመው ኮንቬ ንሽን ነው ፤ ፲፬ . “ አደገኛ ቦታ ” ማለት ለተወሰኑ ጊዜዎች ለአይሮ ፕላን በረራ አደጋ ምክንያት ሊሆኑየሚችሉእንቅስቃ ሴዎች ሊገኙበት ይችላል ተብሎ የተከለለ የአየር ክልል ነው ፤ ፲፭ “ የውጭ አገርአይሮፕላን ” ማለት በኢትዮጵያ ያልተ መዘገበ ማንኛውም አይሮፕላን ነው ፤ ፲፮ . “ ጠቅላላ የአይሮፕላን አገልግሎት ” ማለት ከአየር መንገድ አገልግሎት ሌላ ማናቸውም አገልግሎት ፲፯ . “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ማለት የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይም ሚኒስቴር ማለት ነው ፤ ፲፰ “ አገልግሎት ሰጭ ” ማለት ከአይሮፕላን ጋር በተያያዙ የአይሮፕላን አስተዳደር ወይም ሥራ ለጊዜው የሚያካሂድ ማለት ነው ፤ “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ሰው ማለት ነው ፤ ፳ “ የተከለከለ ቦታ ” ማለት ለአይሮፕላን በረራ ክልክል ሆኖ የተከለለ የአየር ክልል ነው ፤ ፳፩ “ ባለገደብ ቦታ ” ማለት አንዳንድገደቦችን በማክበር አይሮፕላን እንዲበር ተፈቅዶ የተከለለ የአየር ክልል ፳፪ . “ የመንግሥት አይሮፕላን ” ማለት ለወታደራዊ ፣ ለቀረጥና ለመሳሰሉት ሌሎች ሕዝባዊ ግልጋሎቶች የሚውል አይኖፕላን ማለት ነው ። የተፈጸሚነት ወሰን ፩ . ይህ አዋጅ በሚከተሉት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ፤ ሀ ) በሁሉም የሲቪል አውሮፕላን ማረፊያዎች ፣ ለ ) በኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋሙ ወይም በሚንቀ ሳቀሱ ኣየር መንገዶችና በጠቅላላ የአቪዬሽን አገልግሎት ፣ ሐ ) በማንኛውም በባለሥልጣኑ በተመዘገበ አይሮ መ ) በማንኛውም በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ባለ የውጭ ኣይሮፕላን ሠ ) ለሁሉም የአቪዬሽን ፐርሶኔል እና ማሠልጠኛ ተቋማት ፣ እና ረ ) በአይሮፕላን እና በአይሮፕላን ክፍሎች ዲዛይን ፣ ፍብረካ ፣ እድሳት ፣ ጥገና እና ማሻሻያ ሥራ ላይ በተሠማሩ ድረጅቶች፡ ፪ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጡ ደንቦች ካልተወሰነ በስተቀር ይህ አዋጅ በመንግሥት አይሮፕላን ላይ ተፈጻ ምነት አይኖረውምታ hive.com ገጽ ፩ሺ፯፻፵፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ክፍል ሁለት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፬ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እንደገና ስለመቋቋሙ ፩ . የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ “ ባለሥልጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ የራሱ የሕግ ሰውነት ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ እንደገና ተቋቁሟል ። ፪ . ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ፭ የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በኣዲስ ኣበባ ሆኖ ቅርንጫፍ ጽ / ቤቶች በሌሎች ቦታዎች እንደ አስፈላጊነቱ ሊቋቋሙ ይችላሉ ። ፮ ዓላማዎች የባለሥልጣኑ ዓላማዎች የሚከተሉት ይሆናሉ ፤ ፩ ቀልጣፋና ኢኮኖሚያዊ የሲቪል የአየር ማመላለሻና ጠቅላላ የአውሮፕላን አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄና ደህንነት እንዲኖረው ማረጋገጥ ፤ ፪ . የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ የአየር ማመላለሻ መስመሮች እንዲዘረጉና እንዲደራጁ ፣ እንዲሁም አስተ ማማኝና ዘለቄታ ያለው የአየር ማመላለሻ አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ ፣ ፫ • የኢትዮጵያን አየር ክልል ደህንነትና ቀልጣፋ አጠቃቀም መቆጣጠርና ማረጋገጥ ፣ ፬ . የሲቪል አቪዬሽን ሕጐችን ፣ ደንቦችን ፣ መመ መመሪያዎችን እንዲሁም ኢትዮጵያ ስለ ሲቪል አቪዬሽን ጉዳዮች የገባችባቸውን ስምምነቶችና ውሎችን ማስከበርና ማስፈጸም ። ፯ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ ሕግን ተከትሎ ዓላማዎቹን ከግቡ ለማድረስ የሚያስፈልገው ሥልጣን ሁሉ ይኖረዋል ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ባለሥልጣኑከዚህ በታች በተለይ የተዘረዘሩት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ . የማንኛውንም አውሮፕላን ሥራ ፣ ይዞታ ፣ በሥራ ላይ መዋል ፣ ሽያጭ ፣ ወደ ሀገር መግባትና ከሀገር መውጣት ሕጋዊ መሆኑን ይቆጣጠራል ፤ ፪ • ለአቪዬሽን ፐርሶኔል የሥራ ፈቃድ ይሰጣል ፤ ፫ • የአይሮፕላን ማረፊያዎችን ይመረምራል ፣ የሥራ ፈቃድም ይሰጣል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ፬ . በኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ እና ከኢትዮጵያ የአየር ክልል ውጭ የአየር ትራፊክ ፣ የናቪጌሽን ፣ የኤሮኖቲካል መገናኛና መረጃ አገልግሎቶችን ይሰጣል ፤ ፭ ለአየር ማመላለሻ አገልግሎት ሰጪዎች እና ለጠቅላላ የአይሮፕላን አገልግሎቶች የሥራ ፈቃድ ይሰጣል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ፮ ማንኛውንም የሥራ ፈቃድ ወይም የምስክር ወረቀት በበቂ ምክንያት ይሠርዛል ወይም ያግዳል ፤ ፯ መንገደኞች ፣ ዕቃዎችና ፖስታዎች በአይሮፕላን የሚጓ ዙበትን ሁኔታ ይወስናል ፤ ፰ አይኖፕላን በሚያርፍበትና በሚነሳበት መሥመሮችና አካባቢዎች ለበረራ አደገኛ የሆኑትን ነገሮች ለመከ ላከል ፣ ለማንሳት ፡ ለማስነሳት ወይም አስፈላጊው ምልክት እንዲደረግ ማስገደድ ይችላል ፤ ፬ . የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስለሚያድግበት ሁኔታ ምርምር ያካሂዳል ፣ ፕላንና ፕሮግራም ያዘጋጃል ፣ የአየር ክልሉንና ፣ ሌሎች ከአቪዬሽን ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን ጥቅም ላይ ስለሚውሉበት ሁኔታ ፖሊሲ ያዘጋጃል ፤ ፲ የአይሮፕላን በረራ የሚካሄድባቸውን የአየር ትራፊክ ሥርዓቶችና ደንቦች ያወጣል ፤ ፲፩ ለሕዝብ የሚሰጠው የአየር ማመላለሻ አገልግሎት ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ ብቁና የተሟላ መሆኑን ያረጋ የ ፩ሺ፯፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፲፪ ኢትዮጵያ በገባችው ዓለም አቀፍ ስምምነት መሠረት በመንግሥት የሚወጣ የብሔራዊ አቪዬሽን ፀጥታ ፕሮ ግራምን ያስፈጽማል ፤ ፲፫ : ማናቸውንም የሲቪል አይሮፕላን ከነመብቱ ይመዘ ግባል ፣ የመለያ ምልክት ይሰጣል ፣ የአውሮፕላን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ፣ ለመብረር ብቁ መሆኑን መርምሮ የብቁነት ምስክር ወረቀት ይሰጣል ፣ አይሮፕላኑ የሚውልበትን ተግባር ይወስናል ፣ አይሮ ፕላኑ የሚታደስበትና የሚጠገንበትን ሁኔታ ይወስናል ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠራባቸውን የበረራ መስመሮች በመለየት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ሁኔታዎች ይወስናል ፣ እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የሚገቡ ትንና የሚወጡትን አይሮፕላኖች የበረራ ሁኔታዎች ይወስናል ፣ ከሌሎች ከሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር በረራ የተከለከለባ ቸውን ባለ ገደብና የአደጋ ቦታዎች እና የአየር መስመ ሮችን በመለየት ተግባራዊነታቸውን ያስፈጽማል ፤ ፲፭ የሲቪል አቪዬሽን ሙያ ማስተማሪያ ትምህርት ቤቶች ፣ የአይሮፕላን ማደሻና መጠገኛ ጣቢያዎችና እንዲሁም ሌሎችም ለአይሮፕላን አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን ደረጃቸውን ይመረምራል ፣ ይወስናል ፣ ለድርጅቶችና ለምሩቃን የምስክር ወረቀት ይሰጣል ፣ ለራሱ ኣገል ግሎት የሚያስፈልጉትን ባለሙያዎች ለማፍራት ማሠልጠኛ ተቋሞችን ያቋቁማል ፤ ፲፮ : ባለሥልጣኑ ለሰጠው አገልግሎት ወይም መረጃ መሣሪ ያዎች ተገቢውን ዋጋ ፣ ኪራይ ወይም የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል ፤ ፲፯ አይሮፕላን ለሲቪል አቪዬሽን ሥራ በሚውልበት ጊዜ በድምፅ ፣ በንቅናቄ ፣ በአየር ብከላ ወይም በማናቸውም ምክንያት በሕብረተሰቡ ላይ ወይም በአካባቢው ላይ የሚፈጥረውን ችግር እንዲቀንስ እርምጃ መውሰድ ይችላል ፤ ፲፰ : ማንኛውም የሲቪል አይሮፕላን ቢጠፋ ወይም በበረራ ላይ እንዳለ አደጋ በደረሰበት ጊዜ የፍለጋና የአስቸኳይ ዕርዳታ ተግባሮችን ያካሂዳል ፤ ያስተባብራል ፣ የአይሮ ፕላን አደጋን ይመረምራል ፣ የአደጋ ምርመራ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያወጣል ፤ ብሔራዊ የፈልጐ ማዳን ክፍልን ያደራጃል ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የአውሮፕላን ፈልጐ ማዳን ተግባርን ለማከናወን የሰው ኃይልና ንብረትን በጋራ መጠቀም እንዲቻል መንግ ሥታዊ ድርጅቶችን ፣ ሚኒስቴር መ / ቤቶችንና ሌሎች ድርጅቶችን ያስተባብራል ። ለዚህ ዓላማም ከአጐራባች አገሮች ጋር ስምምነት ይፈራረማል ፤ ፲፱ . በኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ በሲቪል አቪዬሽን መስክ በሚሰማሩ ሁሉ ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ቋሚ የኤሮኖቲካል መረጃዎችን በኤሮኖቲካል መረጃ ህትመት ኤ አይፒ መልክ አዘጋጅቶ ያወጣል ፤ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ግዴታ ያረፈባቸውን የኤሮኖ ቲካል ካርታዎችና ቻርቶችን አዘጋጅቶ ያሰራጫል ፤ ፳ ሲቪል አቪዬሽንን የሚመለከት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን ኮንቬንሽኖችና ስምምነቶችን ፣ እንዲሁም ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወ ጡትን ደንቦችና መመሪያዎች ያስፈጽማል ፣ ያስከብራል ፤ ፳፩- ውል ለመግባት ፣ ለመክሰስና ለመከሰስ እንዲሁም ክርክሮችን ለግልግል ማቅረብ ይችላል ፤ ፳፪ ለሥራው የሚያስፈልገውን የሚንቀሳቀስና የማይንቀ ሳቀስ ንብረት ለመግዛት ፣ ለመሽጥ ፣ ባለቤት ለመሆን ፣ ገጽ ፩ሺ፯፻፵፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ፳፫ ባለሥልጣኑ ግዴታዎቹን ለመወጣት ይህ አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡ ደንቦች ወይም መመሪ ያዎች ተጥሰዋል ወይም ሊጣሱ ይችላሉ ብሎ ካመነ በሕጋዊ ወኪሉ አማካኝነት በማንኛውም አይሮፕላን ውስጥ ዘልቆ መግባት ፣ ምርመራዎችን መፈጸም ፣ ማንኛውንም ሠነድ በቁጥጥር ሥር ማዋል እና አይሮፕ ላኑን እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ወይም ማንኛውንም መረጃ መጠየቅ ይችላል ። ፰ የባለሥልጣኑ ሥራ አመራር ፩ . ባለሥልጣኑ ፤ ሀ ) ዳይሬክተር ጄኔራል ፣ እና ለ ) ለሥራው የሚያስፈልጉት ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፪ ዳይሬክተር ጄኔራሉ በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመን ግሥት ይሾማል ። ፬ . የዳይሬክተር ጄኔራሉ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዳይሬክተር ጄኔራሉ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ፣ ከሚኒስቴሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳ ድራል ። ፪ • ከላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዳይሬክተርጄኔራሉ ሕግን ተከትሎ የሚከተሉትን ይፈጽማል ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ የተመለከቱትን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) የባለሥልጣኑን ፕሮግራምና ያዘጋጃል ። ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ሐ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ መ ) ሲቪል አቪዬሽንን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችን እያዘጋጀ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፤ ሠ ) በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት ሠራተኞችን ያስተዳድራል ፤ ረ ) ተጠሪነታቸው ለእርሱ የሆኑትን የባለሥልጣኑን ኃላፊዎች መርጦ ለሚኒስትሩ በማቅረብ ያሾማል ፣ ሰ ) በባለሥልጣኑ የሚሰበሰቡትን ክፍያዎች መጠን አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ በመንግሥት ሲፀድቅም ክፍያውን ያስፈጽማል ፣ ሸ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ። ቀ ) የባለሥልጣኑን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም እና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፤ በ ) ሚኒስትሩ በየጊዜው የሚሰጣቸውን ሌሎች ተግባሮች ይፈጽማል ። ፫ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልገው መጠን ከሥልጣኑና ተግባሩ በከፊል ለባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ሆኖም ዳይሬክተር ጄኔራሉ በሌለበት ጊዜ ስለእርሱ ተወክሎ የሚሰራው ሰው ሚኒስትሩ የሚስማማበት መሆን ይኖርበታል ። ፲ . የባለሥልጣኑ የገንዘብ ምንጮች ባለሥልጣኑ የሚከተሉት የገቢ ምንጮች ይኖሩታል ፤ ፩ . በባለሥልጣኑ የሚሰበሰበው የአገልግሎት ዋጋ ፣ የሥራ ፈቃድ ክፍያ የንብረት ኪራይ ወይም ሽያጭእናከሌላም ክፍያ የሚገኝ ገንዘብ ፣ ፪ . የባለሥልጣኑን ተግባር ለማስፈጸሚያ የሚያገኘው ።። መ እ ዓ ብ ፣ እና በስተቀር በክፍያ መሰማራት | ገጽ ፩ሺ፯፻፵፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ፫ • እንደ አስፈላጊነቱ ከመንግሥት የሚመደብ በጀት ። ስለ በጀትና የበጀት ዓመት ፩ የባለሥልጣኑ ዓመታዊ በጀት በመንግሥት ይፀድቃል ። ፪ . የባለሥልጣኑ የበጀት ዓመት ከሐምሌ ፩ ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ ፴ ቀን ድረስ ይሆናል ። ፫ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ሰ ) የተጠቀሰው ገቢ በባለሥልጣኑ ስም በተከፈተው የባንክ ሂሣብ ውስጥ ገቢ ይደረጋል ። እንዲሁም በተፈቀደው ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት መሠረት ወጪ ይደረጋል ። ፬ . ባለሥልጣኑ ከዓመቱ ገቢ ወጪውን ችሎ የሚተርፈውን ለመንግሥት ገቢ ያደርጋል ። ስለ ሂሣብና ዓመታዊ ሪፖርት ባለሥልጣኑየተሟሉና ትክክለኛ የሂሣብ መዛግብት በመያዝ እያንዳንዱ የበጀት ዓመት በተፈፀመ በስድስት ( ፮ ) ወር ጊዜ ውስጥ በኦዲተር የተረጋገጠ ያለፈውን ዘመን የገቢና የወጪ መግለጫ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ። ፲፫ ስለ ሂሣብ መርማሪዎች የባለሥልጣኑ የሂሣብ ሰነዶች ፣ መዛግብትና ገንዘብ ነክ የሆነ ነገር ሁሉ በዋናው ኦዲተር ወይም በእርሱ በሚወከሉየሂሣብ መርማሪዎች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ውሳኔዎች ክልከላዎችና የአየር ክልል አጠቃቀም ፩ ማንኛውም ሰው በባለሥልጣኑ ፈቃድ መሠረት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም አይሮፕላን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ፣ ከአገር ለማስወጣት ፣ ለመፈብረክ ፣ ለማደስ እና የጥገና ሥራ ለማካሄድ አይችልም ። ፪ • አንድ ኢትዮጵያዊ አገልግሎት ሰጪ በባለሥልጣኑ በሚሰጠው የአየር በረራ አገልግሎት መስጫ የምስክር ወረቀት ካልሆነ አይችልም ። ፫ • መደበኛ ወይም መደበኛ ያልሆነ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በባለሥልጣኑ ፈቃድ እና ባለሥልጣኑ በሚያስቀምጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ወይም ተገቢው ሥልጣን ባለው አካል በሚወጣ ደንብ መሠረት ብቻ ይከናወናል ። መደበኛ ያልሆነ የአየር በረራን በክፍያ ወይም በኪራይ የሚያካሂድ የውጭ ኣገር አገልግሎት ሰጪ በኢትዮጵያ ውስጥ ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር መንገደኞችን ፣ ፖስታን ለማመላለስ አይችልም ። ፪ . ኣንድ የውጭ አገር አገልግሎት ሰጪ ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገር ፣ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ መንገደኞች ፣ ጭነትና ፖስታ የማመላለስ መብት ፣ ሥልጣን ባለው አካል በሚወጡ ደንቦች መሠረት ይሆናል ። ፭ በዚህ አዋጅ በሚወጡ ደንቦች መሠረት ብቃቱና በማን ኛውም መልኩ የተገለጸ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ ወይም ኢትዮጵያ በገባችባቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ ወይም የምስክር ወረቀት ከሌለው በስተቀር የአቪዬሽን ፐርሶኔል አገልግሎት መስጠት አይችልም ። ፮ በዚህ አዋጅ ወይም ኢትዮጵያ በገባቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት የበረራ ብቁነት የምስክር ወረቀት የያዘ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም አይሮፕላን በኢት ዮጵያ ክልል ውስጥ መብረር አይችልም ። ገጽ ፩ሺ፯፻፵፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም በዚህ አዋጅ ወይም በስሩ በሚወጡ ደንቦች መሠረት በባለሥልጣኑ የተሰጠ ውክልና : ፈቃድ ወይም የምስክር ወረቀት በትክክል ሥራ ላይ አለመዋላቸው ሲታመን ወይም ውክልናው ፡ ፈቃዱ ፣ ወይም የምስክር ወረቀቱን የያዘው ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ባለሥልጣኑ ውክልናውን ፣ የሥራ ፈቃዱን ወይም የምስክር ወረቀቱን ሊያግደው ይችላል ። ባለሥልጣኑ ከምርመራ በኋላ በቂ ምክንያት ካገኘም የሥራ ፈቃዱን ወይም ሠርተፊኬቱን ( የምስክር ወረቀቱን ) ሊሰርዘው ይችላል ። በሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ ወይም በልዩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ፣ ማንኛውም የውጭ መንግሥት አይሮፕላን በኢትዮጵያ ውስጥ መብረር አይችልም ። መሬትን ስለመውሰድ ባለሥልጣኑ ለራሱ ጥቅም የሚውል መሬት ሕግ በሚፈ ቅደው መሠረት ሊወስድ ይችላል ። ፲፮ ኃላፊነትና ግዴታ ማንኛውም የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ወይም የጠቅላላ የአይሮፕላን አገልግሎት ሰጪ እና ማንኛውም አይሮፕላን ወይም የአይሮፕላን አካሎችንና ዕቃዎችን የሚያ ንቀሳቅስ ፣ የሚመረምር ፣ የሚያድስ ፡ ወይም የሚጠግን ሰው በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡትን ደንቦች ፣ መመሪያዎች ፣ ሕጐች እና ሥርዓቶች ማክበር አለበት ። ፲፯ ቅጣት ሀ ) ይህን አዋጅና በአዋጁም መሠረት የወጡትን ደንቦች ወይም መመሪያዎች የሚተላለፍ ማንኛውም ሰው ጥፋተኛ መሆኑ ሲረጋገጥበት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ይቀጣል ። ለ ) አንድ ሰው ይህን አዋጅ ወይም በአዋጁ መሠረት የወጡትን ደንቦች ወይም መመሪያዎች ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የተሰጠውን የሥራ ፈቃድ ወይም የምስክር ወረቀት ዝርዝር ሁኔታዎች ቢጥስ ዳይሬ ክተር ጄኔራሉ የሥራ ፈቃዱን ወይም የምስክር ወረቀቱን ሊያግደው ወይም ሊሰርዘው ይችላል ። ሐ ) በዳይሬክተር ጄኔራሉ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ሰው ለሚኒስትሩ ይግባኝ ማለት ይችላል ። የሚኒስትሩ ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል ። ፲፰ : ደንብና መመሪያን ስለማውጣት ሀ ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑትን ደንቦች ሊያወጣ ይችላል ። ለ ) ሚኒስትሩ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጣውን ደንብ ለማስፈጸም መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፲፱ . የተሻረ ሕግ የአየር ትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፩ ፲፱፻፷፱ በዚህ ኣዋጅ ተሽሯል ። ፳ እንደፀና የሚቆይ ደንብ የአይሮፕላን አመዘጋገብ ደንብ ቁጥር ፫፻፮ ፲፱፻፵፯ እንደተ ሻሻለ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደወጣ ተቆጥሮ የፀና ይሆናል ። አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓም ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። ኣዲስ ኣበባ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓ.ም. ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?