×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 200/92 የሕዝብ ጤና አጠባበቅ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፰ አዲስ አበባ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፲፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፱፻፲፪ ዓም የሕዝብ ጤና አጠባበቅ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፪፻፻፬ አዋጅ ቁጥር ፪፻ ፲፱፻፲፪ የሕዝብ ጤና አጠባበቅ አዋጅ በሀገሪቱ የወጣውን ጤና ፖሊሲ ለመተግበር ሕብረትሰቡን ] health sector has become necessary for the implementation of በጤና አጠባበቅ ዘርፍ እንዲሳተፍ ማድረግ በማስፈለጉ ፤ አብዛኛው የጤና ችግር በመሠረታዊ የጤና ክብካቤ የሕዝቡን ስነልቦናዊ አመለካከት በመለወጥ ሊፈታ እንደሚችል | the society through primary health care approach can solve በመታመኑ፡ በዚህም ከግል ንጽሕና አንስቶ ኅብረተሰቡ በየደረጃው ጤናውን እንዲጠብቅና የወደፊቱም ትውልድ ጤናው ተጠብቆ ኃላፊነቱን እንዲረከብ ለማስቻል የጤና አጠባበቅ ህግን መቅረጽ | health of the society and for the Creation of healthy environ በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕዝብ ጤና አጠባበቅ አዋጅ ቁጥር ፪፻ ፲፱፻፲፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ የምግብ ጥራት ” ማለት በብሔራዊና በዓለምአቀፍ ደረጃ ለምግብ ጥራት መለኪያነት የተመደቡ ሥነ ሕይወታዊ ፣ ኬሚካላዊና ፊዚካላዊ መስፈርቶችን ማሟላት ነው፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • T ሺ፩ ጽ ፩ሺ፪፲፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱ዓም “ ምግብ ” ማለት ማንኛውም በከፊል ወይም በሙሉ የተዘጋጀ ወይም በጥሬነቱ ለሰው ምግብነት የሚውል ነገር፡ መጠጥ ፣ የሚታኘክ ማስቲካ እንዲሁም ምግብን ለማምረት፡ ለማቀናበር፡ ለማዘጋጀትና ለማከም አስፈላ ጊነቱ ታምኖበት የታከለን ማንኛውንም ንጥረ ነገር የሚያካትት ሆኖ ትንባሆን፡ ኮስሞቲክስንና ለመድኃኒ ትነት ብቻ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮችን አይጨምርም ፣ ፫ . “ የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ” ማለት እንደአግባቡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም የብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ወይም ተጠሪነቱ ለፌዴራሉ መንግሥት የሆነ ከተማ የጤና ቢሮ ነው ፤ ፬ . “ የምግብ ጭማሪ ” ማለት እንደ ምግብ ኣካል ተቆጥሮ ምግብን ለማጣፈጥ፡ ለማቅለም፡ ሳይበላሽ ለማቆየትና ለማሳመር የሚጨመር ማንኛውም ንጥረ ነገር ነው ፣ “ ጤና ” ማለት በበሽታ አለመያዝ ብቻ ሳይሆን ፍፁም የሆነ የአካል፡ የአዕምሮና የማኅበራዊ ኑሮ ደህንነት ፮ . “ የሥራ ነክ ጤና አጠባበቅ ” ማለት በሥራ አካባቢ የሚከሰቱ ወይም ከሥራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ኬሚካላዊ፡ ፊዚካላዊና ሥነ ሕይወታዊ ጐጅ ንጥረ ነገሮችን በመከላከልና በመቆጣጠር ሠራተኞች ለአደጋ እንዳይጋለጡ በማድረግ ሣይንሳዊ፡ ቴክኖሎ ጂካዊና አስተዳደራዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የሠራተ ኞችን ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ሣይንስ ነው ፤ ፯ . “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ወይም ሚኒስቴር ፰ “ የተጠረጠረ ” ማለት በዚህ ህግ በተሰጡት ድንጋ ጌዎች መሠረት በጤና አጠባበቅ ባለሥልጣኖች አመለካከት ለተላላፊ በሽታ እንደተጋለጠ የሚቆ ጠርና ያለበትን በሽታ የማስተላለፍ ችሎታ ያለው ሰው ነው ፤ • “ ሥልጣን የተሰጠው ኃላፊ ” ማለት አግባብ ባለው ሙያ በቂ ዕውቀት ያለው ሆኖ በአዋጁ የተሰጠውን ተግባር ለማከናወን በሚኒስቴሩ ወይም በክልል የጤናገ ቢሮ በጽሑፍ ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም ሰው ፲ “ ህንፃ ” ማለት ተንቃሳቃሽ ቤቶችን ማንኛውም ጣራና ግድግዳ ያለው ቤት ወይም መጠለያ ነው ፣ ፲፩ . “ ያልታከመ ፍሳሽ ቆሻሻ ” ማለት ከኢንዱስትሪ ከእርሻ ተቋማት እና እንደ ጤና ድርጅት፡ ትምህርት ቤት፡ ንግድ ድርጅት ከመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በምርት ወይም በሥራሂደት በባዮሎጂካዊና በኬሚካላዊ ውህደት ምክንያት የሚፈጠርና በሰው፡ በእንስሳትና በዕፅዋት ላይ የጤና ጠንቅ ወይም ጉዳት እንዳያስከትል በተለያዩ ሣይንሳዊ ዘዴዎች ሳይጣራ በቀጥታ ወደ ውሃ አካል ፥ ዕጽዋት ወይም አፈር እንዲፈስ የተደረገ ፍሳሽ ማለት ነው ፣ ገጽ ፩ሺ፪፻፸፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፪ ዓም : ፲፪ “ የመግቢያ ወይም የመውጫ በር ” ማለት በገቢ ወይም ወጪ ዕቃዎች፡ በመጓጓዣዎች ወይም ሰዎች ላይ ቁጥጥር የሚደረግባቸው የጉምሩክ ኬላዎች ወይም በሚኒስትሩ የሚወሰኑ ሌሎች ስፍራዎች ናቸው ፤ ፲፫ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ሁለት ስለአማካሪ ቦርድ ፫ የአማካሪ ቦርድ መቋቋም ይህን አዋጅ በተገቢው ሁኔታ በሥራ ላይ ለማዋል እንዲቻል አግባብ ያለውን የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን የሚያማክር በፌዴራልና በክልል የጤና አማካሪ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ . በዚህ አዋጅ በተሸፈኑና የጤና አጠባበቅን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣኑን ያማክራል ፤ ፪ የሕዝብ ጤና አጠባበቅ እንቅስቃሴዎችን የሚያግዙ ጥናቶችን አጥንቶ ለጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ያቀርባል፡ በጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፭ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነሥርዓት ደንብ ያወጣል ። ፪ • ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ሲገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይኖራል ። የጉባዔው ውሳኔ በአብዛኛው ድምፅ ይወሰናል፡ ድምፁም እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ። የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሦስት ዓመት ይሆናል ። ክፍል ሦስት ስለ ተቆጣጣሪ ፮ ተቆጣጣሪዎች ስለመሾም የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን የዚህን አዋጅ በጤና አጠባበቅ ላይ የወጡ ሌሎች ሕጐችንና መመሪያዎችን | 6. Appointment of Inspectors ለማስፈጸም አስፈላጊ ችሎታ ያላቸውን ተቆጣጣሪዎች ይሾማል ። ፯ . የተቆጣጣሪው ሥልጣንና ተግባር ተቆጣጣሪው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ጤናን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ሁኔታ ተፈጥሯል የሚያሰኝ በቂ ምክንያት ሲኖረው ወደ ማንኛውም ግቢ ወይም ህንፃ ይገባል፡ ፍተሻ ያካሂዳል፡ ፪ ተቆጣጣሪው ወደ ማንኛውም ግቢ በሚገባበት ጊዜ ፤ ሀ ) ኃላፊነቱን ከመወጣት የሚያግደው ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚያሰኝ ምክንያት ሲኖረው ችግሩን ለመከላከል የሚችል የፖሊስ ኃይል አብሮት እንዲገኝ ይጠይቃል፡ ለ ) ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ ማሳየት ይኖርበታል፡ ሕግን በመጻረር የተፈጸመ ድርጊት ውጤት የሆነ ወይም ድርጊቱን ለመፈጸም ጥቅም ላይ የዋለ ወይም ማንኛውም ከድርጊቱ አፈጻጸም ጋር ግንኙነት ያለውን መሣሪያ ወይም ቁሳቁስ ወይም ዕቃ ይይዛል ፤ ገጽ ፩ሺ፪፲፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የያዛቸውን ቁሳቁሶች ወይም ዕቃዎች አስፈላጊ ለሚሆን ጊዜ በማቆየት ፣ ሀ ) በቁሳቁሶቹ ወይም በዕቃዎቹ ላይ ምርመራ ያካሂዳል ። ለ ) በዚህ አዋጅ ወይም አግባብ ባለው ሕግ ድንጋ ጌዎች መሠረት ለሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃ በማስ ረጃነት ሊቀርብ የሚችል መሆኑን ያረጋግጣል ። ፭ አስፈላጊ ሲሆን የሚገባበት ግቢ ወይም ሕንጻ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ምርመራ የሚካሄድበት መሣሪያ፡ ቁሳቁስ ወይም ዕቃ በአጠቃላይ ወይም በተናጠል በቂ ለሆነ አስፈላጊ ጊዜ ሳይነካካ እንዲቆይ ለማዘዝ ወይም ግቢው ወይም ሕንጻው ለተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ እንዲቆይ ለማዘዝ ይችላል፡ ምርመራ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ልኮችን ይወስዳል ። ፎቶግራፎችን ያነሳል፡ ምዝገባዎችን ያካሂዳል፡ ፯ አስፈላጊ ሲሆን በግቢው ወይም በሕንጻው ከሚገኝ ማናቸውም መሣሪያ፡ ቁሳቁስ ወይም ዕቃ እንዲሁም ከግቢው ወይም ከአካባቢው አየር ናሙና ይወስዳል ። ፰ በግቢው ወይም በሕንጻው የሚገኘው ማንኛውም መሣሪያ፡ ቁሳቁስ ወይም ዕቃ በጤናላይ ጉዳትእንዲሁም የተለያዩ አደጋዎች የሚያስከትል ወይም ሊያስከትል የሚችል ነው የሚያሰኝ በቂ ምክንያት ሲኖረው ዕቃው ተለያይቶ እንዲቀመጥ ለማድረግና ጤናን ሊበክሉ የሚችሉ አላስፈላጊ ቁሳቁሶችም እንዲወገዱ ለማድረግ ይችላል ። ሆኖም ዕቃውን የመለያየትእርምጃው በዕቃው ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆን የለበትም ፤ ፬ ለሚያካሂደው ምርመራ አግባብነት ያለው መረጃ ሊሰጥ ይችላል ብሎ የሚያምንበትን ማንኛውንም ሰው መረጃ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል ። ሥልጣን ባለው አካል ክስ እንዲመሠረት ያደርጋል ። ክፍል አራት ስለጤና አጠባበቅ ፰ የምግብ ጥራት ኣጠባበቅ ፩ . ማንኛውም ምግብ ለጤና በማይስማማና ንጽሕናው ባልተጠበቀ ሁኔታ፡ ጠቃሚ ነገሮችን በሚለውጥ ዓይነት በመቀላቀል ወይም አግባብነት የሌለውን የምግብ ጥራት አጠባበቅ ደረጃን በማያሟላ መልኩ እንዲዘጋጅ፡ ወደ ሀገር እንዲገባ፡ እንዲከፋፈልና በማናቸውም መንገድ ለተጠቃሚ እንዲደርስ ማድረግ የተከለከለ ነው ። ፪ . ማንኛውም ምግብ እንደአግባቡ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ መለያ ምልክት ሊኖረውና አስፈ ላጊው የጤና አጠባበቅ ሊደረግለት ይገባል ። ፫ ማንኛውም ሰው በሚያመርተው ወይም በሚያከፋፍለው የምግብ ጨው ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ አዮዲን ያለበት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ፬ . ማንኛውም ሰው የምግብ፡ የውኃ ጥራትንና የአየር እና የዕጽዋት ብክለትን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያቋ ቁመውን የጤና አጠባበቅ ላቦራቶሪ በተመለከተ ስለመ ሣሪያው ብቃትና ደረጃ ከጤና አጠባበቅ ባለሥልጣንና አግባብነት ካለው አካል ፈቃድ ሳያገኝና ሳያስመዘግብ በሥራ ላይ ማዋል አይችልም ። ገጽ ፩ሺ፪፻፸፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም . የምግብ ጤና አጠባበቅ ደረጃን ስለመጠበቅ ማንኛውም ለሰው ምግብነት የሚውል ምግብን በመሽጥ ወይም ለሽያጭ በማምረት ወይም በማከማቸት ወይም በማዘ ጋጀት ወይም ሳይበላሽ በማቆየት ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው የሕብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ አኳያ በጤና ጥበቃ ሚ / ር የተቀመጠውን መስፈርት ማሟላት አለበት ። ስለመጠጥ ውኃ ጥራት አጠባበቅ ፩ በጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ጥራቱ ካልተረጋገጠ በስተቀርየምንጭ፡ የጉድጓድና የቧንቧ ውኃኣገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው ። ጥራቱ ያልተረጋገጠ የማዕድን ውኃም ሆነ የታሸገ ውኃ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ወይም በማምረት ለሕብረ ተሰቡ ማደልና ማሰራጨት የተከለከለ ነው ። ፫ ከፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ፣ ከማስረጊያዎች፡ ከፍሳሽ ማብላሊያ ስፍራና ከኢንዱስትሪ የሚወጣውን ጤናየሚበክል ያልታከመ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ውኃአካላት ወይም ወደ ውኃ አካላት መገናኛዎች መልቀቅ የተከ ለከለ ነው ። ስለሥራ ነክ ጤና አጠባበቅ እና ስለመሣሪያ አጠቃቀም ፩ . ማንኛውም ሠራተኛን ቀጥሮ የሚያሠራሰው የሥራ ነክ ጤና አጠባበቅ ማድረግ ይኖርበታል ። ፪ • ከመጠን በላይ ድምጽ በሚያሰማ ወይም በሚያወጣ መሣሪያ መጠቀም የተከለከለ ነው ። ይህን መሰል መሣሪያ የሚጠቀም ሰው የድምጽ መቀነሻ ማስገባት ይኖርበታል ። ፲፪ • ስለቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፩ . ማንኛውም ሰው ቆሻሻን ለጤንነት ጐጂ ባልሆነ ሁኔታና ተለይቶ በተዘጋጀ ስፍራ ማከማቸት ይኖር ፪ . ማንኛውም ሰው ደረቅ፡ ፍሳሽ ወይም ሌሎች ቆሻሻ ዎችን አካባቢን ሊበክል በሚችል መልኩ ወይም በጤንነት ላይ ጉዳት በሚያደርስ ሁኔታ ማስወገድ የለበትም ። ፫ ከሆስፒታል የሚወጡ ደረቅ፡ ፍሳሽ ወይም ሌሎች ቆሻሻዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ አለባቸው፡ አወጋገ ዳቸው የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን የሚያወጣቸውን ደረጃዎች ማሟላት ይኖርበታል ። ፲፫ የመጸዳጃ ቤት እንዲኖር ስለማድረግ ፩ . ማንኛውም ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ወይም ድርጅት ንጽሕናው የተጠበቀ በቂ የመጸዳጃ ቤት | 13. Availability of Toilet Facilities የማዘጋጀትና ለደንበኞቹ ክፍት የማድረግ ግዴታ ይኖር ፪ . ማንኛውም የከተማ አስተዳደር የሕዝብ መጸዳጃ ቤት እንዲኖር የማድረግና ንጽህናውም ሁልጊዜ የተጠበቀ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ። ፲፬ • የመታጠቢያ ስፍራዎችንና የመዋኛ ገንዳዎችን ስለመቆ ፩ አግባብ ካለው የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ፈቃድ ካልተገኘ በስተቀር ማንኛውም ሰው መታጠቢያ ስፍራ ወይም የመዋኛ ገንዳ አዘጋጅቶ ለሕዝብ አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም ። የሕዝብ መታጠቢያ ወይም የመዋኛ ቦታ አዘጋጅቶ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውም ሰው አገልግሎቱን ግልጽ የሆነ የቆዳ ሕመም ወይም ቁስል ላለባቸው ሰዎች መፍቀድ የለበትም ። ገጽ ፩ሺ፪፲፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. አግባብ ባለው የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ካልተ ፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ሰው የተፈጥሮ እንፋሎት መታጠቢያ ወይም የፍልውሀ አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም ። ፲፭ አስከሬንን ስለማስወገድ ፩ አስከሬንን ለመቅበር ወይም ለማቃጠል ከተፈቀደው ቦታ በስተቀር ማንኛውንም አስከሬን ወይም አጽም መቅበር ወይም ማቃጠል የተከለከለ ነው ። ጉዳዩ በሚመለከተው የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውንም አስከሬን ቆፍሮ ማውጣት ወይም በማንኛውም ሁኔታ እንዲጋለጥ ማድረግ የተከለከለ ነው ። ፲፮ : በመግቢያና መውጫ በሮች ስለሚደረግ የጤና አጠባበቅ ፩ . ማንኛውም መንገደኛ በተፈቀደለትና በታወቀ የመግ ቢያና መውጫ በር ወደ ሀገር ሲገባና ከሀገር ሲወጣ ፣ ሀገሪቱ በተቀበለቻቸውና በተግባር ባዋለቻቸው ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ መስፈርቶች መሠረት የሚጠየ ቀውን ክትባት መውሰድ፡ የክትባትደብተር የመያዝና ለሚመለከተው የጤናኃላፊየማሳየት ፣ በተላላፊ በሽታ ሲጠረጠር ለምርመራ የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፪ ተገቢ የሆነ የጤና ማስረጃ ያልያዘን ወይም መቅሰፍት ሊያመጣ የሚችል ወረርሽኝ ካለበት ቦታ የመጣ ወይም የተጠረጠረ ሰው ወደ ሀገር እንዳይገባ ሊታገድ ይችላል ። ፫ . ማንኛውም የመግቢያና የመውጫ በር ባለሥልጣን የተጠረጠረ ሰው ሲያጋጥመው ወዲያውኑ በአቅራ ቢያው ለሚገኝ ጤና ድርጅት የማሳወቅ ግዴታ አለበት ። የጤና ምስክር ወረቀት ሳይዝና መከላከያ ሳይበጅለት እንስሳትን ከመንገደኛ ጋር ቀላቅሎ ማጓጓዝ የተከለከለ ፲፯ ስለተላላፊ በሽታዎች ፩ . ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው የተላላፊ መኖር ወይም መከሰት ባወቀ ጊዜ ይህንኑ በቅርቡ ላለው የጤና አገልግሎት ተቋም ወዲያውኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ። የጤና ተቋሙም አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ ለጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን ወዲያውኑ ማስታወቅ ይኖርበታል ። ፪ . ማንኛውም የተጠረጠረ ሰው ለምርመራና ለሕክምና ወይም ለክትባት ፈቃደኛ መሆን አለበት ። ፫ ሚኒስቴሩ የወረርሽኝ በሽታ ሲከሰት እንደአስፈላጊነቱ ወደ ተወሰኑ ሀገሮች የሚደረግ ጉዞን የመከልከል ፥ በበሽታ በተጠቁ ወይም ይጠቃሉ ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች የሚደረጉእንቅስቃሴዎችን የመገደብ ፣ ት ቤቶችን ወይም የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎችን የመዝጋት እና በወረርሽኝ በሽታ የተያዙ ሰዎችን ከሥራ ቦታቸው ለተወሰነ ጊዜ የማግለልና ሌሎች ተመሳሳይ እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል ። ፬ . ተላላፊ በሽታዎችን ስለመከላከልና ለመቆጣጠር ዝርዝር ጉዳይ ይህን አዋጅ መሠረት በማድረግ በሚወጣው ደንብ ይወሰናል ። ገጽ ፩ሺ፪፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም • ፲፰፡ ለግንባታ ሥራዎች ፡ ቅድመና ድህረ የጤና አጠባበቅ ፈቃድና ምዝገባ ስለማስፈለጉ ለሕዝብ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎች ግንባታ የሚያ ካሂድማንኛውም ሰው ከግንባታው ዕቅድ አንስቶእስከ ግንባታው ፍጻሜ ድረስ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣው ደንብና መመሪያ መሠረት ከጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን አስፈላጊውን ፈቃድ የማግ ኘትና የመመዝገብ ግዴታ አለበት ። ፪ . ማንኛውም ሰው የመኖሪያ ቤት፡ የማምረቻና የአገል ግሎት መስጫ ድርጅት ወይም ተቋም ሲገነባ የመጸዳጃ ቤት አብሮ መሥራት ይኖርበታል ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ለዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች አፈጸጸም የመተ ባበር ግዴታ አለበት ፡፡ ፳ ቅጣት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ከባድ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር፡ የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፬ የተጻረረ ማንኛውም ሰው | 20. Penalty ከ፪ሺ፭፻ እስከ ፭ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፪ • ለቆሻሻ ማከማቻነት ከተቀመጡ ማከማቻዎች ውጭ አካባቢን ሊበክል በሚችል መልክ ወይም በጤንነት ላይ ጉዳት ሊያደርስ በሚችል ሁኔታ ቆሻሻን ያስወገደ ማንኛውም ሰው ከሦስት ወር እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ፩ሺ እስከ ፱ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀፅ ( ፩ ) እና ( ፪ ) በመጻረር የወንጀል ድርጊት የፈጸመ ማንኛውም ሰው ከ፩ሺ እስከ ፱ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮና ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ። የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፬ በመጻረር ወንጀል የፈጸመ ማንኛውም ሰው ከ፩ ሺ እስከ ፭ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት ይቀጣል ። ፭ የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፮ በመጻረር ወንጀል የፈጸመ ሰው ከ፭፻ እስከ ፫ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፳፩ . የተሻሩና ተፈጻሚነታቸው የሚቀጥል ሕጐች ፩ ከዚህ በታች የተመለከቱት ሕጐች በዚህ አዋጅ | 21. Repealed and Applicable Laws ተሽረዋል፡ ሀ ) የሕዝብ ጤናጥበቃ አዋጅቁጥር፳፮ / ፲፱፻፴፬ ፣ እና ለ ) የሕዝብ ጤና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፴፱ ። ፪ በአዋጅ ቁጥር ፳፮ / ፲፱፻፴፬ እና በአዋጅ ቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፴፭ መሠረት የወጡ ደንቦች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረኑና በሌሎች ደንቦች እስኪተኩ ድረስ ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል ። ፳፪ ደንብ የማውጣት ሥልጣን ፩ . የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጸጸም ደንብ ለማውጣት ይችላል ። ገጽ ፩ሺ፪፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • የክልል መስተዳድር ወይም ተጠሪነቱ ለፌዴራሉ መንግሥት የሆነ የከተማ መስተዳድር ለዚህ አዋጅ አፈጸጸም ሕግ ማውጣት ይችላል ። መመሪያ የማውጣት ሥልጣን የጤና አጠባበቅ ባለሥልጣን በዚህ አዋጅ መሠረት የወጣውን ደንብ አፈጸጸም የሚመለከቱ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፳፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ጀምሮ የጸና | 24. Effective Date ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : ዶር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?