የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር 3 አዲስ አበባ- ኅዳር ፳፩ ቀን ፲፱፻ዥ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፬ ፲፱፻፶፫ ዓም ለባለብዙ ዘርፍ የኤችአይቪ ኤድስ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ........ ገፅ ፩ሺ፬፻፴፭ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፬ / ፲፱፻፲፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ለባለብዙ ዘርፍ የኤችአይቪ / ኤድስ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ኤስ - ዲ - አር ፭ ሚሊዮን ፪፻ ሺህ ( አርባ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ኤስዲ - አር ) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ኦክቶበር ፲፪ ቀን ፪ ሺህ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ ፣ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆ ናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው፡ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኅዳር ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለባለብዙ ዘርፍ የኤችአይቪ ኤድስ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፬ / ፲፱፻፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ.ቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፭ሺ፬፻፴፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፭ ኅዳር ፳፩ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ኦክቶበር ፲፪ ቀን ፪ ሺህ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመው ቁጥር ፫ሺህ፱፻፲፮ ኢት . የብድር ስምምነት ነው ። - የገንዘብ ሚኒስትሩ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በብድር ስምምነቱ የተገኘውን ኤስዲአር ፵፭ ሚሊዮን ፪፻ ሺህ ( አርባ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ኤስዲ - አር ) በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከኅዳር ፳፩ ቀን ፲፱የን ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፳፩ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ