የኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፴፰ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፬ / ፲፱፶፬ ዓም የኢትዮ ጅቡቲ'የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀምና በትራንዚት ላይ ያለ ጭነት አገልግሎት ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ ገጽ ፭ሺ፰፻፴ አዋጅ ቁጥር ፳፬ / ፲፱፻፲፬ የኢትዮ ጅቡቲ'የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀምና በትራንዚት ላይ ያለቅነት አገልግሎት ስምምነትን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ : እና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረገው የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀምና በትራንዚት ላይ ያለ ጭነት አገልግሎት ስምምነት ሚያዝያ ፭ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም በጅቡቲ ላይ የተፈረመ ስለሆነ ፣ ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው ተዋዋይ ሀገሮች በየሕጎ ቻቸው መሠረት ስምምነቱ መጽደቁን ኣንዱ ለሌላው ሲያሳውቅ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተገለጸ በመሆኑ ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ባደረገው ስብሰባ ስምምነቱን ያፀደቀው በመሆኑ ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / እና / ፲፪ መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ “ ይህ አዋጅ “ የኢትዮ ጅቡቲ ፣ የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀምና በትራንዚት ላይ ያለ ጭነት አገልግሎት ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅቁጥር የተ፬ / ፲፱፵፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። # ስምምነቱ ስለመፅደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ሚያዝያ ፭ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም በጅቡቲ የተፈረመው የጅቡቲ ወደብ አጠቃ ቀምና በትራንዚት ላይ ያለ ጭነት አገልሉት ስምምነት ፀድቋል ። ያንቆዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣፖማቁ ተሺ፩ ገጽ ፭ሺ፰፻፴፩ ፌዴራል ነጋሪት ቁጥር 94 ሰኔ ፳፮ ቀን ፲ደዛውም ፫ ስለአስፈጻሚ አካላት ሥልጣን መንግሥት የሚወክላቸው አስፈጻሚ አካላት፡ በሥራ መስካቸው ይህ ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን በዚህ አዋጅተሰጥቷቸዋል ። ፬ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ኣዋጅከሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፵፬ ዓ ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፵፬ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያመርትታተመ