የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፬ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፵፩ ዓም የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ .... ገጽ ፩ሺ፩፻፴፱ 1 ማፍቀፍ ወይም አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፵፩ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለሚደረገው ሕገ መንግሥታዊ አደረጃጀትና ለፖለቲካዊ ሥርዓቱ ዝግጅት አስፈላጊ ስለሆነ ፡ ትክክለኛውን የሕዝብ ብዛት ማወቅ በሀገር በተወሰነ የክልል አስተዳደር እርከን ደረጃ ለሚደረጉ ምርጫዎች አፈጸጸም አስተማማኝ መሠረት በመሆኑ ፡ የተግባሩን አስፈላጊነት፡ ስፋትእናውስብስብነት በማገናዘብ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን እንደሚቋቋም በሕገ መንግሥቱ የተደነገ provision on the establishment of a separate commission , in ገውን በሥራ ላይ ለማዋል ዝርዝር ሕግ ማውጣት አስፈላጊ | consideration of the necessity , extensiveness and complexity በመሆኑ፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፩፻፫ እና አንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር | 2. Definitions በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ዥሺ፩ ገጽ ፩ሺ፩፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም : ፩ . “ የሕዝብ ቆጠራ ” ማለት በሀገር አቀፍ ፣ በክልል ወይም በተወሰነ የክልል አስተዳደር እርከን ስለሚገኘው ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት፡ የጾታ ፡ የዕድሜ ፣ የጋብቻ ፣ የትምህርት ደረጃ ፡ የሰው ኃይል ፣ የሥራዓይነት ፣ የሥራ መስክ፡ የልደት፡ የሞት፡ የፍልሰትና ሌሎች ተመሳሳይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፣ የማጠናቀር ፣ የመገምገምና የማሠራጨት ተግባር ነው ፤ ፪ . “ የቤት ቆጠራ ” ማለት በሀገር አቀፍ ፣ በክልል ወይም በተወሰነ የክልል አስተዳደር እርከን የሚገኘውን የቤት ብዛትና ዓይነት ፡ ያሉትን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንዲሁም ስለቤት ሁኔታ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፣ የማጠናቀር ፡ የመገምገምና የማሠራጨት ተግባር ነው ፣ ፫ . “ የናሙና ጥናት ” ማለት ሀገሪቱን ወይም የተወሰነ ክልልን በሚወክል መልኩ በናሙና ከተመረጡ አካባቢ ዎችና ቤተሰቦች የሕዝብ ብዛት ፣ የጾታ ፣ የዕድሜ ፣ የጋብቻ : የትምህርት ደረጃ የሰው ኃይል ፣ የሥራ ዓይነት፡ የሥራ መስክ፡ የልደት ፣ የሞት ፣ የፍልሰት ፣ የቤት ብዛትና ዓይነት እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፤ የማ ጠናቀር ፡ የመገምገምና የማሠራጨት ተግባር ነው ፤ “ የቆጠራ ካርታ ” ማለት ማንኛውም ሰው ሳይቆጠር እንዳይቀር እንደዚሁም ከአንድ ጊዜ በላይእንዳይቆጠር ለማድረግ የቆጠራው ክንዋኔ ከመጀመሩ በፊት የቆጠራ ቦታና የመቆጣጠሪያ ቦታ ካርታዎች ማዘጋጀት ነው ፣ ፭ “ ምክር ቤት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው ፣ ፮ “ ቆጠራ ” ማለት የሕዝብና የቤት ቆጠራ ነው ፤ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ነው ። ፫ : ስለመቋቋም የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለውና ራሱን የቻለ የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ይሆናል ። ፬ ዓላማዎች የኮሚሽኑ ዓላማዎች የሚከተሉት ይሆናሉ ፣ ፩ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ለምርጫዎች ዝግጅት፡ ለዕቅድ አፈጻጸም ፡ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ለምርምር የሚጠቅሙ ሕዝብና ቤትን የሚ መለከቱ መረጃዎችን መሰብሰብ ፡ ማጠናቀር ፣ መገም ገምና ማሰራጨት ፡ ፪ • የሕዝብ እና የቤቶች ምዝገባ በመላ ሀገሪቱእንዲቋቋምና እንዲሠራበት መሠረታዊ ጥናቶችን በማካሄድ የሚደራ ጁበትን መንገድ መቀየስ ። ፭ የኮሚሽኑ አባላት ፩ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፩፻፫ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በተደነ ገገው መሠረት የኮሚሽኑ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በምክር ቤቱ ይሾማሉ ። ፪ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ የሚሆነው አባል በምክር ቤቱ ተለይቶ ይሰየማል ። ፫ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ድምጽ የመስጠት መብት ሳይኖረው የኮሚሽኑ አባልና ጸሐፊ ሆኖ ይሠራል ። ፮ . የኮሚሽኑ የአባላት ስብጥር የኮሚሽኑ አባላት ከዘጠኙ ክልሎች : ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡ ከፌዴሬሽን ምክር ቤትና ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት የተውጣጡ ይሆናሉ ። ገጽ ፩ሺ፪፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም : ፯ የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር በየአሥር ዓመቱ አጠቃላይ የሕዝብ ቆጠራ እንዲከ ናወን ማድረግ ፡ የቆጠራ ካርታ ሥራ እና የሕዝብ ቆጠራን በሚመለከት የፖሊሲ መመሪያ ማውጣት እና አፈጻጸማቸውን መከታተል፡ የሕዝቡ ብዛት በክልል ፡ በዞን ፡ በወረዳ፡ በከተማ እንዲሁም በከተማና በገጠር ቀበሌዎች ተለይቶ በጾታና በዕድሜ እንዲዘጋጅ ማድረግ ፡ ስለቆጠራ ካርታ ሥራ እንዲሁም ስለቆጠራ ምንነት ለሕዝቡ ማሳወቅ ፡ በሚያወጣው ደንብ መሠረት በክልል በወረዳና አስፈላጊ ሆነው በሚያገኛቸው ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖች ደረጃ ሌሎች ኮሚሽኖችን በቆጠራ ማካሄጃ ወቅት ማቋቋም ፡ እንዲሁም ሥልጣንና ተግባራቸውን፡ የአባላቱን አሰያየምና የስብሰባ ሥነሥርዓታቸውን መወሰን ፡ ፮ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚቀርበው የብሔረሰቦች ዝርዝር መሠረት እና በሕዝብና ቤት ቆጠራ አማካኝነት የብሔረሰቦችን ብዛትና ስርጭት እንዲገኝ ማድረግ ፡ የሕዝብ ቁጥር ዕድገትን ለመተንበይ የሚያስችሉ የናሙና ጥናቶች እንዲከናወኑ ማድረግ ፡ በየክልሉ በሚገኙት ዞኖች ፡ ወረዳዎች፡ ከተማዎችእና የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ያሉት ብሔረሰቦች ብዛት በጾታና በዕድሜ ተከፋፍሎ፡ በገጠርና በከተማ ተለይቶ እንዲዘጋጅ ማድረግ ፡ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚካሄደው ቆጠራ አፈፃፀም ሂደት በስፋቱና በዓይነቱ የቆጠራውን ውጤት ሊያዛባ የሚችል ግድፈት ስለመከሰቱ በቂ መረጃ ካገኘ ለምክር ቤቱ በማሳወቅ ውጤቱን መሠረዝ ፡ እንደገና ቆጠራ እንዲካሄድ ማዘዝ ፡ የቆጠራ ውጤቶችን ማረጋገጥ ፡ ለምክር ቤቱ ማቅረብ ፣ እንዲሁም ለሕዝብ በይፋ እንዲገለጽና በተለያዩ መንገ ዶችም እንዲሰራጭ ማድረግ ፡ ፲፩ የጽሕፈት ቤቱን በጀት ለምክር ቤቱ አቅርቦ ማስፈ ቀድና በትክክል በሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ ፡ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጐችን መሠረተ ሃሳቦች በመከተል ፡ የጽሕፈት ቤቱን ሙያተኛ ሠራተኞች የደመወዝ እስኬል ፡ የቅጥርና የአስተዳደር መመሪያ ማውጣት፡ ስለ ሥራ አፈፃፀሙ በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት ማቅረብ ። ፰ የኮሚሽኑ ስብሰባ ኮሚሽኑ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ። ከኮሚሽኑ አባላት ውሰጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ በስብ ሰባው ላይ ሲገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል ። የኮሚሽኑ ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ ይሰጣሉ ፡ ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። የዚህ አንቀጽ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፡ ኮሚሽኑ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፱ • የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፡ የኮሚሽኑን ስብሰባ ይጠራል፡ ይመራል፡ ፪ የኮሚሽኑ ውሳኔዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋ የኮሚሽኑን ጽሕፈት ቤት የሥራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይቆጣጠራል ። ገጽ ፩ሺ፩፻፴፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፬ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም Federal Negarit Gazeta - No . 64 29 June , 1999 - Page 1142 ፲ ለለኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ፩ ኮሚሽኑ በዋና ጸሐፊእና በምክትል ዋና ጸሐፊ የሚመራ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ይኖረዋል ። ፪ ዋና ጸሐፊው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በምክር ቤቱ ይሾማል፡ ፫ . ምክትል ዋና ጸሐፊው በኮሚሽኑ አቅራቢነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾም ይሆናል ። ፲፩ . የዋና ጸሐፊው ሥልጣንና ተግባር ዋና ጸሓፊው፡ ሀ ) የኮሚሽኑን ጽሕፈት ቤት ያደራጃል፡ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ይመራል፡ ለ ) ከኮሚሽኑ ሰብሳቢ ጋር በመመካከር የኮሚሽኑን የስብሰባ አጀንዳ ያዘጋጃል፡ ሐ ) የኮሚሽኑን ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በሚገባ ይይዛል ፣ መ ) የኮሚሽኑ ውሳኔዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች እንዲተላለፉ ያደርጋል፡ ሠ ) ኮሚሽኑ በሚያወጣው ሙያተኛ ሠራተኞችን ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ ደመወዝና አበላቸውንም ይወስናል፡ የጽሕፈት ቤቱን ሌሎች ሠራተኞችም በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ። ረ ) የኮሚሽኑን ጽሕፈት ቤት የአጭርና የረጅም ጊዜ እንዲሁም ዓመታዊ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለኮሚሽኑ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ። ሰ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች የኮ ሚሽኑን ጽሕፈት ቤት ይወክላል፡ ሸ ) ቆጠራ እንዲሁም የቆጠራ ካርታ ሥራ በዚህ አዋጅና ለአዋጁ አፈፃፀም በሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት እንዲካሔዱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡ ቀ ) በዚህ አዋጅ ለጽሕፈት የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ያስፈጽማል፡ በ ) በኮሚሽኑ መወሰን የሚገባቸውን ጉዳዮተ ያየቱ ጋር ያቀርባል፡ ቸን ስለጽሕፈት ቤቱ የሥራ እንቅስቃሴ በየጊዜው ሪፖርት እያዘጋጀ ለኮሚሽኑ ያቀርባል፡ ተ ) በኮሚሽኑ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከና ለሥራ ቅልጥፍና አስፈላጊ በሆነ መጠን ፣ ዋና ጸሐፊው ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪ የምክትል ዋና ጸሐፊው ሥልጣንና ተግባር ፩ ምክትል ዋና ፀሐፊው ተጠሪነቱ ለዋና ፀሐፊው ሆኖ ፣ ሀ ) የጽሕፈት ቤቱን ቴክኒካዊ ተግባሮች በማቀድ፡ በማደራጀት፡ በመምራትና በማስተባበር ዋና ጸሓፊውን ይረዳል፡ ለ ) በዋና ፀሐፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፪ ምክትል ዋና ፀሐፊው ዋና ጸሐፊው በማይኖርበት ጊዜ ተተክቶ ይሠራል ። ፲፫ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ሥልጣንና ተግባር ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ የቆጠራ ካርታ ሥራ የማከናወን ፣ ገጽ ፩ሺ፩፻፵፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፬ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ፪ የቆጠራና የናሙና ጥናት ዕቅድ አዘጋጅቶ ለኮሚሽኑ የማቅረብ፡ ፫ ቆጠራ እና የናሙና ጥናት ሥራ የማካሔድ ፣ ለዚሁም አፈፃፀም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ( ፩ ) መሠረት የሚቋቋ ሙትን ሌሎች ኮሚሽኖች እንቅስቃሴ የመምራት፡ የማስተባበርና የመቆጣጠር፡ ፬ • ለቆጠራ እና ለናሙና ጥናት አፈፃፀም የሚያስፈልጉ መጠይቆች፡ መመሪያዎችና ልዩ ልዩ ቅጾች እንዲሁም ቁሳቁሶች የማዘጋጀትና የማሠራጨት ፣ ፭ ሕዝብና ቤትን የሚመለከቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ አግባብ ያላቸውን ሰነዶችና መዛግብት የመመርመር ፣ ምርመራውንም ለማከናወን ተገቢ በሆነ ጊዜ ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ወይም ቅጥር ግቢ የመግባት ፣ ለቆጠራ እና ለናሙና ጥናት አፈፃፀም የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል የማሰልጠን ፣ ፯ . በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፣ ( ፪ ) እና ( ፯ ) መሠረት የቆጠራ ካርታ ሥራ ወይም ቆጠራ ለማካሔድ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በማን ኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ፣ ንብረትና አገልግሎት የመጠቀም ፣ የተሰበሰበውን የቆጠራ መረጃ ማደራጀት ፣ መተንተንና ሪፖርቱን አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለኮሚሽኑ የማቅረብ ፣ ፬ • በየጊዜው የሚደረገውን ቆጠራ አፈፃፀም የመገምገም እንዳስፈላጊነቱም የአሠራር ማሻሻያ ጥናቶች እንዲ ካሔዱ የማድረግ ፣ ፲ የንብረት ባለቤት የመሆን ፣ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ ፣ ፲፩ በኮሚሽኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ሌሎች አግባብ ያላቸውን ተግባሮች የማከናወን ። ፲፬ . በጀት ኮሚሽኑ፡ ፩ . በምክር በሚጸድቀው መሠረት መደበኛና የካፒታል በጀት ከመንግሥት ይመደብለታል ። ፪ • በቆጠራ እና በናሙና ጥናት ማካሔጃ ወቅት ከውጭ ዕርዳታ ሊጠይቅ ይችላል ። ፲፭ ግዴታ ፩ . ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ለቆጠራው ሥራ የመተባበር ግዴታ አለበት ። በዚህ አዋጅ መሠረት ለቆጠራ ወይም ለናሙና ጥናት መረጃ እንዲሰጥ የተጠየቀ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን መታወቂያ ለሚያሳይ መረጃ ሰብሳቢ ወይም ተቆጣጣሪ ትክክለኛውን መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት ። ፫ . ማንኛውም የቤት ወይም የቅጥር ግቢ ባለንብረት ፣ ባለይዞታ ፣ ወይም ጠባቂ ከኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን መታወቂያ ለሚያሳይ የቆጠራና የናሙና ጥናት መረጃ ሰብሳቢ ወይም ተቆጣጣሪ ወደተባለው ንብረት እንዲገባ የመፍቀድ ግዴታ አለበት ። ፲፮ የመረጃዎች ምስጢራዊነት በፍርድ ቤት በማስረጃነት እንዲያቀርብ ካልታዘዘ በስተቀር የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት የሰበሰባቸውን የቆጠራና የናሙና ጥናት መረጃዎች በምስጢር ይጠብቃል ። ፲፯ ቅጣት ማንኛውም ሰው፡ ፩ . የቆጠራና የናሙና ጥናት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ ፣ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፬ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፪ • ይህንኑ በሚመለከት ሀሰተኛ መረጃ የሰጠ ፥ ወይም ፫ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ወደተመለከተው ንብረት ገብቶ የቆጠራና የናሙና ጥናት መረጃ የማግኘት ሥራን ያሰናከለ እንደሆነ ፣ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ እስከ ብር ፪ ( ሁለት ሺህ ብር በሚደርስ ገንዘብ ወይም ከ፮ ( ስድስት ) ወር በማይበልጥ እሥራት ይቀጣል ። ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ሲሆን ፣ ከብር፲ሺ ( አሥር ሺ ብር ) በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል ። ፲፰ የተሻሩ እና ተፈፃሚ የማይሆኑ ሕጎች ፩ የሕዝብናየቤትቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅቁጥር ፪ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ። ፫ : ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሌላ ሕግ ፣ ደንብ ፣ መመሪያ ወይም፡ የአሠራር ልምድ በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም ። ፲፬ ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ኮሚሽኑ ይህን አዋጅ በሚገባ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉትን | 20. Transitory Provision ደንቦችና መመሪያዎች ለማውጣት ይችላል ። የመሸጋገሪያ ድንጋጌ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም ፣ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት በሚገባ እስከሚደራጅበት ጊዜ ድረስ አዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፳፭ ተፈጻሚ ሆኖ ይቆያል ። አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፪ ቀን $ 3 አ፩ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓሃ 0 ) ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ