የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፲፯ አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፭ / ፲፱፻፲፬ ዓም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ገጽ ፩ሺ፯፻፲ አዋጅ ቁጥር ፪፻፻፲፱፻፵፬ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ በርካታ የውጭ ዜጎች ከትውልድ አገራቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚፈልጉ መሆናቸውን በመገንዘብ ፤ እነዚህ የውጭ ዜጎች ተለይተው አንዳንድ የመብት አጠቃቀ | of origin ; ሞችን የሚመለከቱ የሕግ ገደቦች ቢነሱላቸው ለሀገሪቱ እድገትና ለወገኖቻቸው ኑሮ መሻሻል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያ | contribute to the development and the prosperity of the ደርጉ በመታመኑ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፭ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ዝሺ፩ ፈጻሚ ገጽ ፩ሺ፯፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ ማለት ” ፡ የሌላ ሀገር ዜግነት ከመያዙ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ዜግነት የነበረው ፡ ወይም ከወላጆቹ ፡ ከአያቶቹ ወይም ከቅድመ አያቶቹ ቢያንስ አንዱ በማናቸውም ጊዜ የኢትዮጵያዊ ዜግነት ይዞ የነበረ የውጭ ዜጋ ሲሆን ፣ የኢትዮጵያን ዜግነት በመተውየኤርትራ ዜግነትን መርጦ የያዘ ሰውን አይጨምርም ፤ ፪ . “ የኢትዮጵያ ሚስዮን ” ማለት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፡ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ / ቤት ወይም ቆንስላ ጽ / ቤት ማለት ፫ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማለት ነው ፤ ፬ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የደህንነት ; የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ማለት ነው ፤ በዚህ አዋጅ በወንድ ጾታ የተደነገገው የሴትን ጾታ ያካትታል ። ፫ . የአዋጁ ዓላማ የዚህ አዋጅ ዓላማ ፡ ፩ . በኑሮና በሕይወት አጋጣሚዎች እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የሌላ አገር ዜግነት የወሰዱ የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆኑትን በመለየት የኢትዮጵያ ዜግነታቸው በመቅረቱ የተጣለባቸውን የሕግ ገደቦች በማላላት የተለያዩ ባለመብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች ባለቤቶች ማድረግ ፤ ፪ • የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆኑ የውጭ ዜጐች ለወገኖ ቻቸው ኑሮ መሻሻል ፡ ለትውልድ ሀገራቸው ዕድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ማስቻል ነው ። ፬ . የተፈጻሚነት ወሰን በዚህ አዋጅ በክፍል ሁለት የተመለከቱት መብቶች የሚሆኑት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) ትርጓሜ የሚሸፈን ሆኖ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብ መሠረት የተሰጠና የኢትዮጵያ ተወላጅ መሆኑን የሚገልጽ የጸና መታወቂያ ወረቀት ለያዘ የውጭ ዜጋ ነው ። ክፍል ሁለት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ የውጭ ዜጐች መብቶችና ገደቦች ፭ መብቶች በዚህ አዋጅ መሠረት የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት | 5. Rights መታወቂያ ካርድ ያለው ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በዚህ አንቀጽ ሥር የተዘረዘሩት መብቶች ተጠቃሚ ይሆናል ፤ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባትና ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆ የትም ሆነ ለመኖር የመግቢያ ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲኖረው አይጠየቅም ፤ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፪ ) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የሥራ ፈቃድ እንዲያወጣ ሳይገደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥሮ መሥራት ይችላል ፤ ፫ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ የውጭ ዜጐች የመብት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚገድበው ድንጋጌ ተፈጻሚ አይሆንበትም ፤ ለሆኑ የውጭ ዜጐች የመታወቂያ ካርድ " መመዘኛ | ገጽ ፩ሺ፯፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓም ፬ . የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፵፫ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለቤትነት በሚመለከት በፍት ሐብሔር ሕግ አንቀጽ ፫፻፰ ፫፻፫ የተመለከቱት ገደቦች አይመለከቱትም ፣ ፭ እንደ ሀገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር ከፈለገ በሀገሪቱ የኢንቬስትመንት ሕግ መሠረት ለሀገር ውስጥ ባለሀብት በተፈቀዱ የኢንቬስትመንት መስኮች መሳተፍ ይችላል ፤ ፮ የኢኮኖሚ ፡ የማኅበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በመጠቀም ረገድ በውጭ ዜጐች ላይ በሕግ ፡ በመመሪያ ወይም በአሰራር ልምድ የተጣሉ ገደቦችና የሚደረጉ ልዩነቶች አይመለከቱትም ። በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተደነገገው ቢኖርም ፣ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዘ የውጭ ዜግነት ያለው ፩ በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በሚካሄድ ምርጫ የመ ምረጥና የመመረጥ መብት አይኖረውም ፣ ፪ . በማናቸውም የሀገር መከላከያ ፡ የሀገር ደህንነት ወይም በውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኛነት ተቀጥሮ መሥራት አይችልም ። ክፍል ሦስት የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆኑ የውጭ ዜጐች መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ ፯ የመታወቂያ ካርድ በዚህ አዋጅ የተደነገጉትን መብቶች ጥቅማ ጥቅሞችና ሀላፊነቶች ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ተወላጅ አዋጅ በተመለ ከተው መሠረት ሊሰጣቸው ይችላል ። ፰ መታወቂያ ካርዱ ለማን እንደሚሰጥ ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ / ፩ / የተመለከተውን የሚያሟላ ማንኛውም ሰው የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ መሆኑን የሚገልጽ የመታወቂያ ካርድ ይህን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣ ደንብ መሠረት ማመልከቻ በማቅረብ የማግኘት ሙሉ መብት አለው ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ቢኖርም ፣ ማንኛውም አመልካች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ ( ፫ ) ወይም ፲፬ ( ፬ ) ውስጥ ከተጠቀሱት ምክንያቶች አንዱ የሚመለከተው ከሆነ የመታወቂያ ካርዱ አይሰጠውም ። ፫ . በዚህ አዋጅ መሠረት የኢትዮጵያ ተወላጅ መሆኑን ዋን የሚገልጽ መታወቂያ ካርድ የተቀበለች የውጭ ዜግነት ያለው ላት ሰው የሌላ ሀገር ዜግነት ያለው ላት ሚስት ወይም ባል የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ ሚስት ባል መሆኑን ወይም መሆኗን የሚገልጽ የመታ ወቂያ ካርድ የማግኘት ሙሉ መብት አለው / ላት ። ይህ መብት የኢትዮጵያ ተወላጅ ከሆኑ የውጭ አገር ዜጐች ጋር ጋብቻ የፈጸሙ የኤርትራ ዜጐችንም ይጨምራል ። ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት የሚሰጠውን የመታወቂያ ካርድ የያዘች ሰው በዚህ አዋጅ የተጠ ቀሱት መብቶችና ግዴታዎች ይመለከቱታል ። ገጽ ፩ሺ፯፻፲፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓ • ም • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት የሚሰጠው የመታወቂያ ካርድ የሚያገለግለው የመታወቂያ ካርዱ በአንቀጽ ፲፫ መሠረት እስካልተመለሰ ወይም በአንቀጽ ፲፬ መሠረት እስካልተሰረዘ ድረስ ወይም ጋብቻቸው እስካልፈረሰ ድረስ ብቻ ይሆናል ። ዕድሜው ፲፰ ዓመት ያልሞላው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የተቀበለ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው ልጅ፡ ሌላ መታወቂያ እንዲያወጣ አይገደድም ። ልጁ የመታወቂያ ካርድ ባወጣው ወላጁ ወላጆቹ ፣ ካርድ ላይ ብቻ በመመዝገብ በዚህ አዋጅ የተጠቀሱት መብቶች ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል ። ፯ . ከላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ቢኖርም ፣ ዕድሜው ፲፰ ዓመት ያልሞላው በዚህ አዋጅ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋን ትርጓሜ የሚያሟላ ማንኛውም ሰው የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ሕግ ስለ አካለ መጠን ስላላደረሱ ሰዎች በሚደነግገው መሠረት ይህን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣ ደንብ የሚወሰነውን ክፍያ በመክፈል በግሉ የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማውጣት ይችላል ። በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) የኢትዮጵያ ተወላጅ ስለሆነ የውጭ ዜጋ የተሰጠ ትርጓሜ ቢኖርም ፣ ሚኒስቴሩና ባለሥልጣኑ ሲያምኑበት በኢትዮጵያ ኗሪ ለሆኑ የውጭ አገር ዜጐች በልዩ ሁኔታ በዚህ አዋጅ የኢትዮጵያ ተወላጅ ለሆኑ የውጭ ዜጐች የተሰጡ መብቶችንና ጥቅሞችን መስጠት ይችላሉ ። አፈጻጸሙ በመመሪያ ይወሰናል ። ፱ • የመታወቂያ ካርድ የሚሰጠው አካል መታወቂያ ካርዱን ከኢትዮጵያ ውጭ ለመስጠት ሥልጣን ያለው ሚኒስቴሩ ሲሆን ፣ በሀገር ውስጥ ደግሞ ባለሥልጣኑ ይሆናል ። ፲ • መታወቂያ ካርዱ እንዲሰጥ ስለሚቀርብ ማመልከቻ የመታወቂያ ካርድ አሰጣጥ ሁኔታ አዋጁን ተከትሎ በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፲፩ . መታወቂያ ካርዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በዚህ አዋጅ መሠረት የተሰጠ መታወቂያ ካርድ የማደሻ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በሚወጣው ደንብ ይወሰናል ። ፲፪ ክፍያ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚሰጠውን መታወቂያ ለማግኘት እንዲሁም መታወቂያውን ለማሳደስ የሚከፈለው ክፍያ መጠን በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች መታወቂያ ካርዱን ስለመመለስ ማንኛውም የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዘ የውጭ አገር ዜግነት ያለው ሰው በማናቸውም ጊዜና ምክንያት መታወቂያ ካርዱን መመለስ ይችላል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንዳለ ሆኖ ፣ የመታ ወቂያ ካርዱን የመለሰ ሰው ካርዱን በተጠቀመባቸው ጊዜያት የገባቸውን ውሎች ወይም ሌሎች ግዴታዎችን የማክበርና የመፈጸም ኃላፊነት አለበት ። ገጽ ፩ሺ፯፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፯ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም : ፲፬ • የመታወቂያ ካርድ ስለሚሰረዝበት ሁኔታ ሚኒስቴሩና ባለሥልጣኑ በጋራ ሲወስኑ የመታወቂያ ካርዱ ከሚከተሉት ምክንያቶች ባንዱ ሊሠረዝ ይችላል ፣ ፩ . መታወቂያው የተገኘው ሌላ ሰው መስሎ በመቅረብ ወይም ስለራሱ ትክክለኛውን ነገር በመደበቅ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ በማቅረብ ከሆነ ፣ ፪ የመታወቂያው ባለቤት በሽብርተኝነት ወይም የተከ ለከሉ ዕጾችን ወይም የጦር መሣሪያዎችን በማዘዋወር ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ፣ ፫ : የመታወቂያው ባለቤት ከኢትዮጵያ ጋር በጦርነት ላይ ያለ አገር ዜጋ ከሆነ ወይም ይህን ዓይነቱን አገር በፈቃደኝነቱ የሚረዳ ሰው ከሆነ ፣ ፬ • የመታወቂያው ባለቤት ለሌላ አገር መንግሥት በመደበኛ ውትድርና ወይም በደህንነት ሥራ ማገልገሉ ከተረጋገጠ ፣ ፭ መታወቂያውን ይዞ መቆየቱ ለሕዝብና ለአገር ጥቅም ተገቢ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ። ፲፭ ተፈጻሚ ስለማይሆኑ ሕጐች ይህን አዋጅ የሚቃረኑ ሕጐች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያዎች ፣ | 15. Inapplicable Laws ውሳኔዎች ወይም አሠራሮች ይህን አዋጅ በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፲፮ የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ወይም ሰው ለዚህ አዋጅ ተግባራዊነት የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፲፯ ደንብና መመሪያ ስለማውጣት ፩ : ይህን አዋጅ በሚገባ ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ | 17. Regulations and Directives ደንቦችን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያወጣ ይችላል ። ፪ : ይህን አዋጅ በሚገባ ለማስፈጸም ኣስፈላጊ የሆኑ መመሪ ያዎችን ሚኒስቴሩ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፰ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ