የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ አዲስ አበባ ጥር ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ጠባቂነት የወጣ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻፲ ዓ.ም ዝቋላ ስቲል ሮሊንግ ሚል ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፮፻፳፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻፲ ዝቋላ ስቲል ሮሊንግ ሚል ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱ T ፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፲፬ አንቀጽ ፯ ፩ ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ ዝቋላ ስቲል ሮሊንግ ሚል ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ : መቋቋም ፩ ዝቋላ ስቲል ሮሊንግ ሚል ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅቁጥር፳፭ ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥ ልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ብር 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ : T ሺ፩ ገጽ ፮፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ጥር ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በደብረዘይት ይሆናል ፤ እንዳስፈላጊ ነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ የድርጅቱ ዓላማ የአርማታ ( ሪንፎርስመንት ) ብረቶችና ስትራክ ቸራል ስቲል ማምረትና ለገበያ ማቅረብ፡ በተጨማሪም ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መሥራት ነው ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደለት ካፒታል ብር ፪፻፴፫ሚሊዮን፰፻፵፩ሺህ ፮፻፲፪ብርጀ፩ ( ሁለት መቶ ሠላሳ ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም ) ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ዥ፫ሚሊዮን፰፻፵፩ሺህ፮፻፯ ፪፻፩ ( ሰማንያ ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ : ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ • ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ