የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፃ አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፷፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፮ / ፲፱፻፷፱ ዓም ስለኤሌክትሪክ የወጣ አዋጅ አዋጅ ቁጥር ፳፮ / ፲፱፻፳፱ ስለኤሌክትሪክ የወጣ አዋጅ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚስፋፋበትን ሁኔታ ማመቻቸት የሀገሪቱን ኢኮኖሚና ማኅበራዊ እድገት ለማፋጠን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ ብቁና አስተማማኝየኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል አገልግሎት የሚሰጡትን አካላት ሥራዎች የሚቆጣጠር ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማቋቋምና ቁጥጥሩ የሚካሄድበትን ሁኔታ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ስለ ኤሌክትሪክ ( የወጣ ) አዋጅ ቁጥር ፰፮ / ፲፱፻፴፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ ክፍያ ” ማለት ደንበኛው ለተጠቀመበት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚጠየቅ ክፍያ ነው ፤ ፪ . “ ደንበኛ ” ማለት ከባለፈቃዱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያገኝ ሰው ነው ፡ “ ማከፋፈል ” ማለት በመካከለኛ እና በአነስተኛ ቮልቴጅ መስመሮች አማካይነት ለደንበኞች የሚቀርብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው : ፬ . “ ኤሌክትሪክ ” ማለት ከውሃ ፣ ከማዕድናት ፤ ከፀሐይ ወይም ከሌሎች ምንጮች የሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ነው ፤ ፭ “ ማመንጨት ” ማለት ኤሌክትሪክ ማምረት ነው ፤ ያንዱ ዋጋ 2 : 40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ዥሺ፩ | ገጽ ፮፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓም : Federal Negarit Gazeta - No . 50 74 July , 1997 - - Page 605 - ፮ “ ፈቃድ ” ማለት ለንግድዓላማኤሌክትሪክን ለማመንጨት ፤ ለማስተላለፍ ለማከፋፈልና ለመሸጥ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚሰጥ ፈቃድ ነው ፣ ፯ . “ ባለፈቃድ ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ የተሰጠው ሰው ነው ፡ ፰ . “ ሚኒስትር ” እና “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር እና ሚኒስቴር ነው ፤ ፱ . “ ሰው ” ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፣ ፲ . “ ደንብ ” ማለት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጣ ደንብ ፲፩ . “ ታሪፍ ” ማለት በመንግሥት የጸደቀ የኤሌክትሪክ አገልግ ሎት ዋጋ ተመን ዝርዝር ነው ፣ “ ማስተላለፍ ” ማለት ከፍተኛ መጠን ያለውን ኤሌክትሪክ የማጓጓዝ ተግባር ነው ። ክፍል ሁለት | ስለኤሌክትሪክ ኤጀንሲ ፫ መቋቋም _ ፩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤጀንሲ ( ከዚህ በኋላ “ ኤጀንሲ ” ተብሎ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥ ሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ : ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ፬ . ዋናው መሥሪያ ቤት _ የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊ ነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። የኤጀንሲው ዓላማ የኤጀንሲው ዓላማ ብቁ ፡ አስተማማኝ ፣ ጥራት ያለውና ኤኮኖሚ ያዊ የሆነ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲስፋፋ ማድረግ ይሆ _ ፮ የኤጀንሲው ሥልጣንና ተግባር ፩ የኤሌክትሪክ ማመንጨት ፣ ማስተላለፍ ፣ ማከፋፈልና ሽያጭ ሥራዎች በዚህ አዋጅ ፡ አዋጁን ለማስፈጸም በወጡደንቦችና መመሪያዎች መሠረት መካሄዳቸውን መቆጣጠርና ማረጋ ፪• የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ጥራትና ደረጃ መወሰን ፡ ተግባራዊነታቸውን ማረጋገጥ ፣ ፫ ለኤሌክትሪክ ሥራ ተቋራጮች የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀት መስጠት ፡ በዚህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም በወጡ ደንቦችና መመሪያ ዎች መሠረት የኤሌክትሪክ ማመንጨት ፣ ማስተላለፍ ፡ ማከፋፈልና መሸጥ ፈቃድ መስጠት ፡ ማገድና መሠረዝ ፣ ፭ ታሪፍን አጥንቶ ለውሳኔ ማቅረብ ፤ ሲፈቀድም ተግባራዊነ ቱን መቆጣጠር ፣ ፮ በደንብ በሚወሰነው መሠረት የፈቃድ ክፍያዎችን መሰብ ሰብ ፡ በኤሌክትሪክ ቴክኒካዊ እድገት መስክ ከማሰልጠኛ ተቋማት ጋር መተባበር ፣ የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋልና በስሙ መክሰስና መከሰስ ፡ ፀ• ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ሕጋዊ ተግባራትን ማከናወን ። - ገጽ ፳ድ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ሰኔ ፴ቀን ፲ህደr፱ ዓም = ፯ የኤጀንሲው አመራር 3 ፩ ኤጀንሲው በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም | 7 . Management of the Agency አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅና አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩ ፪ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከሚኒስቴሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠ ረት የኤጀንሲውን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( የተጠቀሰው ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል : ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች ተከትሉ መንግሥት በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ የኤጀንሲውን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩያቀርባል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፡ በጸደቀው የኤጀንሲው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነት ሁሉ ኤጀን ሲውን ይወክላል ፡ ረ ) የኤጀንሲውን የሥራ ክንውንና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋ ጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ። ፬ . ዋና ሥራ አስኪያጅ ለኤጀንሲው የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈ ልግ መጠንሥልጣንና ተግባሩን ለኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎ ችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ሆኖም እርሱ በማይኖር ጊዜ ተክቶ እንዲሠራ የሚወከል ሰው ከ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ በሚኒስትሩ መፈቀድ አለበት ። _ ፰ በጀት ፩ . የኤጀንሲው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆ ሀ ) በመንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፡ ለ ) ከሚሰበሰበው የፈቃድ ክፍያ : እና ሐ ) ከሌሉች ምንጮች ከሚገኝ ገንዘብ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ገንዘብ በኤጀንሲው ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ሆኖ የፌዴራሉን መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሠ ረት በማድረግ የኤጀንሲውን ሥራዎች ለማስፈጸም ወጪ ይሆናል ። _ B የሂሣብ መዛግብት ፩ ኤጀንሲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብትን ይይዛል ። ፪ . የኤጀንሲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ክፍል ሦስት ፈቃድና የፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታዎች 3 ፲ የፈቃድ አስፈላጊነት - ፩ . ማንኛውም ሰው ከኤጀንሲው የተሰጠ ፈቃድ ሳይኖረው ለንግድ ዓላማ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ፡ ማስተላለፍ : ማከፋፈል ወይም መሸጥ አይችልም ። | ) No person may generate , transmit , distribute or sell ገጽ ፭፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፪ . ማንኛውም ሰው ለንግድ ላልሆነ ዓላማ ኤሌክትሪክ ለማመን ጨት ፡ ለማስተላለፍ ወይም ለማከፋፈል በቅድሚያ ኤጀንሲ ውን ማሳወቅና የአካባቢ ጥበቃና የአደጋ መከላከያ ሁኔታዎ ችን ማሟላቱን በኤጀንሲው ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መረጃ ዎችን ማቅረብ አለበት ። ፫• የመጠባበቂያ ኃይል ማመንጫ መሣሪያ ተክሎ ኤሌክትሪክ የሚያመነጭማንኛውም ሰው ከሚመለከተው ባለፈቃድ ጋር ስምምነት አድርጐ በአካባቢው በሚገኘው የማከፋፈያ መስ መር ሊጠቀም ይችላል ። ፲፩ ፈቃድ ለማግኘት ብቁ ስለመሆን ፩ ማናቸውም ሰው በዚህ አዋጅ ፡ አዋጁን ለማስፈጸም በሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች እና በኢንቨስትመንት ሕግ የተገለጹ ትን ፈቃድ ለማግኘት ብቁ የሚያደርጉ መሥፈርቶችን ያሟላ ከሆነ እንዲሁም በንግድ ሕግ መሠረት የንግድ ሥራ ማካሄድ የሚችልና የፈቃድ ግዴታዎችን ለመወጣት የሚያስችል የገንዘብ ምንጭ ፡ የቴክኒክ ችሎታ ፡ ሙያና ልምድ ያለው መሆኑ በኤጀንሲው ሲረጋገጥ ፈቃድ ይሰጠዋል ። ፪ . ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት የኤሌክትሪክ ማመንጨት ፡ ማስተላለፍ ፡ ማከፋፈል እና መሽጥ ሥራዎችን ሲሠራ የቆየ ማናቸውም ሰው አስፈላጊውን ዝርዝር የያዘ ማመልከቻ በማቅረብ ፈቃድ ማውጣት አለበት ። ፲፪ ፈቃድ ስለማስተላለፍ በዚህ አዋጅ የተሰጠ ፈቃድ በደንብ በሚወሰን መሠረት የኤጀንሲውን ስምምነት አስቀድሞ በማግኘት ለሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል ። _ _ ፲፫• የፈቃድ ግዴታዎች ማንኛውም ባለፈቃድ ፡ ፩ የኤሌክትሪክ ማመንጨት : ማስተላለፍ : ማከፋፈልና መሸጥ ሥራዎችን ፡ ይህን አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም የወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን ፡ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት የወጡ ሕጐችን ፡ ድንጋጌዎችንና በኤጀንሲው የተወሰኑትን የጥራት ደረጃዎች አክብሮ ያከና ውናል ፡ ፪• ስለሥራው አግባብ ያላቸውን ሪኮርዶች ይይዛል ፡ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ሪፖርቶችንና መረጃዎችን ለኤጀንሲው ያቀርባል ፡ መዛግብቱና ሪኮርዶቹ በአግባቡ ሥልጣኑ በተሰጣቸው የኤጀንሲው ኃላፊዎች እንዲመረመሩ ሲጠየቅ ለምርመራ ያቀርባል ። ፲፬ . ፈቃድ ስለማገድና ስለመሠረዝ ፩ ባለፈቃዱ በዚህ አዋጅ ፡ በአዋጁ መሠረት በወጡ ደንቦች ፡ መመሪያዎችና በፈቃዱ ላይ የተጠቀሱትን ግዴታዎች ሳያከብር ሲቀር ኤጀንሲው ፈቃዱን ሊያግድ ወይም ሊሰርዝ ይችላል ። ፪ : ኤጀንሲው አንድን ፈቃድ ከመሰረዙ በፊት ባለፈቃዱ ስህተቱን እንዲያርም በቂ ይሆናል ብሎ የሚገምተውን ጊዜ ይሰጠዋል ። የወራሾች መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ባለፈቃዱ ሲሞት ወይም የንግድ ድርጅት ከሆነ ሲፈርስ ወይም አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የመክሰር ውሳኔ ሲሰጥበት ፈቃዱ ይሰረዛል ። ፲፭ የኤሌክትሪክ ክፍያዎች | ማንኛውም ባለፈቃደ ለሰጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከታ | 5 cha - ope ሪፍ በላይ ክፍያ ሊጠይቅ ኣይችልም ። ገጽ ፭የቷ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፲፮ በባለፈቃዱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ፩ ባለፈቃዱ በሚከተሉት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር የኤ ሌክትሪክ አገልግሎት ሊያቋርጥ አይችልም ፡ ሀ ) የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችና መስመሮችን ለመፈተሽ ፡ ለመጠገን ፡ ፡ ለማደስ ፡ ለማስተካከል ወይም ከኤሌክት ሪክ መሣሪያዎችና መስመሮች ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ሥራዎችን ለማካሄድ ፡ ለ ) እንደውሃ መጥለቅለቅ ፡ የመሬት መናድ ወይም መንቀ ጥቀጥ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ወይም ከባለፈቃዱ አቅም በላይ የሆኑ ሌሎች ሁኔታዎች ሲከሰቱ : ሐ ) ደንበኛው የኤሌክትሪክ ክፍያ ሳይፈጽም ሲቀር ፡ መ ) ደንበኛው ከገባው ስምምነት ውጪ ያልተፈቀደለትን ኤሌክትሪክ ሲጠቀም : ፪ . ባለፈቃዱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ( ሀ ) የተመለከቱት ምክንያቶች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከመቋረጡ ከ፳፬ ሰዓት በፊት ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ ማሳወቅ አለበት ። ፲ጊ ብሔራዊ ግሪድ ፩ - መንግሥት በማስታወቂያ ማንኛውንም የቮልቴጅ መጠኑ ከ፩፻፴፪ ኬ · ቪ ያላነሰን የኤሌክትሪክ የማስተላለፊያ መስ መር ብሔራዊ ግሪድ ብሎ ሊሰይም ይችላል ። ፪ . ባለፈቃዶች በብሔራዊ ግሪድ ላይ የሚጠቀሙበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል ። ፲፰ ኤሌክትሪክ ወደ ሀገር ውስጥ ስለማስገባት ወይም ወደውጪ አገር ስለመላክ ፩ . ማንኛውም ባለፈቃድ ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ኤሌክትሪክ አስገብቶ ማከፋፈል ቢፈልግ በቅድሚያ ከኤጀ ንሲው ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ። ፪ . ማንኛውም ባለፈቃድ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመነጨውን ኤሌክትሪክ ወደ ውጪ መላክ ቢፈለግ በቅድሚያ ከኤጀን ሲው ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ። • ኤሌክትሪክ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ወደ ውጪ ሀገር መላክ የሚቻልበት ሁኔታ በኤጀንሲው በሚቀርበው ጥናት መሠረት በሚኒስቴሩ ይወሰናል ። ፲፱ ስለመቆጣጠር በኤጀንሲው የተወከለ ኃላፊ ለህሊና ግምት ተገቢ በሆነ በማንኛ ውም ሰዓት የኤሌክትሪክ ሥራዎችን ሳያግድ ወይም ላያደናቅፍ በሥፍራው በመገኘት የኤሌክትሪክ ማመንጨት ፡ ማስተላለፍ ፡ ማከፋፈልና መሸጥ ሥራዎችን መመርመርና መቆጣጠር ይች ላል ። ክፍል አራት ለኤሌክትሪክ አቅርቦት ሥራዎች በመሬት ስለመጠቀም ፳ : በመሬት ስለመጠቀም _ _ ፩ . ማንኛወም ባለፈቃድ በማንኛውም ሰው ይዞታ ስር ወደሆነ መሬት ወይም ቅጥር ግቢ በመግባት የኤሌክትሪክ መስመር | 20 . Use of Land ለመዘርጋት ፡ ለመጠገን ፡ ለማሻሻል ፡ ለመመርመር ወይም መስመሩን ለማንሳት የሚያስፈልጉ ተግባሮችን ማከናወን ይችላል ። ፪ . ባለፈቃዱ የኤሌክትሪክ ግንባታዎችንና ሥራዎችን ለማካ ሄድ መሰናክል የሚሆኑ ወይም በኤሌክትሪክ መስመር ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ዛፎችን የመቁረጥና የመመል መል ወይም ሰብሎችን ፡ አትክልቶችንና ሌሎች ነገሮችን የማስወገድ መብት አለው ። 5 ገጽ ፮የሀ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፱ ዓም : 3 ፤ ባለፈቃዱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ወይም ( ፪ ) የተጠቀሱትን ተግባራት ለማከናወን ሲፈልግ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት የመሬቱን ባለይዞታ በቅድሚያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ። ፳፩ ካሣ ስለመክፈል ባለፈቃዱ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳ የተጠቀሱትን ተግባራት ሲያከናውን በባለይዞታው ንብረት ላይ ላደረሰው ጉዳት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ካሣ የመክፈል ግዴታ አለበት ። - ፳፪ መሬትን ስለመስጠት ማንኛውም ባለፈቃድ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በግል የተያዘን መሬት በሕግ መሠረት ሊሰጠው ይችላል ። - ፳፫ ስለከተማ ፕላን ፩ ማንኛውም የከተማ ፕላን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ሲስተ ሙን በግልጽ መለየትና ማሳየት ይኖርበታል ። ፪ . ማንኛውም ባለፈቃድ የኤሌክትሪክ መስመር ሲዘረጋ የከተ ማውን ፕላን ተከትሎ የመዘርጋት ኃላፊነት አለበት ። ስለሌሎች ግንባታዎችና ሥራዎች ከኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ጣቢያዎች ወይም መስመሮች አቅራ | 24 . Other Constructions and Works ቢያ በደንብ ተለይቶ በሚወሰን ርቀት ክልል ውስጥ ግንባታ ዎች ፡ እርሻዎች ፡ አትክልቶች ወይም ማናቸውንም ሌላ የቋሚ ነት ጸባይ ያላቸውን ሥራዎች ለማከናውን አይቻልም ። በነባር መገልገያዎች ስለመጠቀም ባለፈቃዱ በዘረጋው የማስተላለፊያ መስመሮች ሌሎች ባለፈቃ | 25 . ዶች የባለፈቃዱን ሥራዎች በማያደናቅፍ ሁኔታና ኤጀንሲው የሚወስነውን ዋጋ በመክፈል እንዲገለገሉበት ሲጠየቅ መፍ ቀድ አለበት ። _ ፳፮ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት በውኃ ስለመጠቀም ፩ ባለፈቃዱ ያለምንም ክፍያ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት | 26 . Use of Water for the Generation of Electricity በውሃ ለመጠቀም ይችላል ። ፬ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት በውሃ የሚጠቀም ባለፈቃድ በውሃ ሀብት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር ፲፪ / ፲፱፻፳፮ ድንጋጌ ወች መሠረት የሚያስፈልገውን የውሃ መጠቀሚያ ፈቃድ ኤጀንሲው አግባብ ያለውን ባለሥልጣን ወክሎ ይሰጠዋል ። | ፳፯ ቅጣት ፩ ማንኛውም ሰው በኤሌክትሪክ ማመንጫ ተቋሞች ወይም በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ወይም ማከፋፈያ መስመሮች ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌ መሠረት የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ከ፭ ዓመት እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ፪ . ማንኛውም ባለፈቃድ ይህን አዋጅ ወይም አዋጁን ለማስፈ ጸም የወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን የጣሰ እንደሆነ አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌ መሠረት ይቀጣል ። ፳፰ ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩• ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን የሚኒስት ሮች ምክር ቤት ሊያወጣ ይችላል ። ፪ . ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሚኒስትሩ ሊያወጣ ይችላል ። ገጽ የ1 ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፳፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፡ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ