የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፬ አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻፳፰ ዓም የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ ገጽ ፻፵ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ ፲፱፻፫፫ዓ.ም የኢትዮጵያ የጤናና ሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፻፴፩ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻ዥ፰ የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት የተቋቋመበትን አዋጅ ቁጥር ፪፻ሮ፩ ፲፱፻ሮቺ መሻር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | 271/1985 ; መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows : አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻፴፰ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ • መሻር የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር | 2. Repeal ፪፻፻፩ ፲፱፻፯ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፫ • መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት መብትና ግዴታ በሚኒስ | 3. Transfer of Rights and Obligations ትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ ፲፱፻ሆኗ ለተቋቋመው የኢት ዮጵያ የጤናና ሥነምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ተላልፋል ። ያንዱ ዋጋ ጎ 2.40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሺ፩ - ፋና ጥበቃ ሚኒስትር ይሆናል ። ገጽ ፻፵፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓም ፬ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅከየካቲት፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ T ፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፰ የኢትዮጵያ የጤናና ሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትየጵያ የጤናና ሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲ | Republic of Ethiopia Proclamation No.4 / 1995 . ትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር | 1. Short Title ፬ / ፲፱፻፳፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ የጤናና የሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን | 2 Establishment የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው መንግሥታዊ ተቋም በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ዋናው መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈ ላጊነቱ በሌሎች ሥፍራዎችም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ለማቋቋም ይችላል ። ፬ • የኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ የበሽታ መንስኤና ስርጭትን ፡ ሥነ ምግብን ፡ የሀገረሰብ መድኃኒትና የሕክምና ዘዴዎችን እንዲሁም ዘመናዊ መድ | 4. Objectives of the Institute ኃኒቶችን በተመለከተ ጥናትና ምርምር በማካሄድ በሀገሪቱ ጤናን ለማሻሻል የሚደረገውን እንቅስቃሴ የማገዝ ፤ ፪ የጤና ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲዳብር አስተዋጽኦ የማድረግ ። ፭ የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ : ለምርምርና ጥናት የሚረዱ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፡ የማጠናቀር ፤ ፪ • ለጤና ምርመራ ፡ ለበሽታ መከላከያና ለሕክምና የሚያስ | 5. Powers and Duties of the Institute ፈልጉንጥረነገሮችዝግጅትን በተመለከተ ጥናትና ምርምር የማድረግ ፤ ፫ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማከናወን ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ወይም ተቋሞች ጋር ቅንጅታዊ አሠራር እንዲቀየስ ፡ እንዲጠናከርና እንዲዳብር የጋራ ምርምር እንዲፈጠር የመጣር ፤ ፲፬ • የንብረት ባለቤት የመሆን ፡ ውል የመዋዋጮ እ ገጽ ፻፵፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ፩ የምግብ እጥረትና ያለመመጣጠን የሚያስከትላቸው በሽታዎች የሚወገዱበትን መንገድና በቤተሰብ ደረጃ የአመጋገብ ሁኔታ እንዲሻሻል ጥናትና ምርምር የማድረግ ፤ ፭ የበሽታዎችን መንስዔ፡ የሚያስከትሉትን ጠንቅና ሥርጭት በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር ጥናትና ምርምር የማካሄድ ፤ በሀገረሰብ መድኃኒትና ህክምና እንዲሁም በዘመናዊ መድኃኒቶች ላይ ምርምር የማካሄድ ፡ አጥጋቢ የምርምር ውጤት ያሳዩ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው የሀገረሰብ መድኃኒቶችና የህክምና ዘዴዎች በጤና አገልግሎት ውስጥ የሚገቡበትን ሁኔታ የማጥናት ፤ ፯ ከሌሎች አግባብ ካላቸው አካሎች ጋር በመተባበር በአገሪቱ ውስጥ የሥነ ምግብ ምርምርና ጥናት የማካሄድ ፤ ፰ በላቦራቶሪና በክሊኒካል ጥናቶች ፈዋሽነታቸው የተረ ጋገጠ የባህል መድኃኒቶች ሊመረቱ የሚችሉበትን ሁኔታ የማጥናት ፤ ፱ ፍቱን የሀገረሰብ መድኃኒቶችን አጠቃቀም ፡ ጥራትና ብቃትየሚገልጽ መነሻ መጽሐፈ መድኃኒት የማዘጋጀት ፤ ፲ . የሀገረሰብ መድኃኒትና ሕክምና ባለሙያዎች ስለሙያው መጐልበትና ስለሚከተሉት የጤና አገልግሎት ጥራትና ብቃት ለመወያየት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን የማመ ቻቸት፡ ሥልጠናና ትምህርትም እንዲያገኙ ከሚመለከ ታቸው ጋር በመተባበር የመሥራት ፤ ፲፩ : በሀገረሰብ መድኃኒትነት የሚያገለግሉ ዕፅዋቶችና የሕክምና ቅርሶች እንዳይጠፉ የኣካባቢ ጥበቃ እንዲደረ ግላቸው ከሚመለከታቸው ድርጅቶች ጋር በመተባበር ኣስፈላጊውን ጥረት የማድረግ ፤ ፲፪ : እንደ አስፈላጊነቱ የሙያ ምክር የመስጠት ፡ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ተቋሞች ለከፍተኛ ምርመራ ጥያቄዎች ሲቀር ቡለት የሚላኩለትን ናሙናዎች በመቀበል የላቦራቶሪ ምርመራዎችን የማከናወን ፤ ፲፫ : ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ የማስከፈል ፤ ፲፭ በራሱ ስም የመክሰስ ፡ የመከሰስ ፣ ፲፮ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉትን ሌሎች ተግባ ሮችን የማከናወን ። ፮ : የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፤ ፩ . የዲሬክተሮች ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፤ ፪ በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም ኣንድ ዲሬክተር ፤ ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፯ • የቦርዱ አባላት ፩ • የጤና ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር ...... ሰብሳቢ ፪ • የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ተወካይ . እባል ፫ • የሕክምና ትምህርት ከሚካሄድባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች የሚወከሉ ባለሙያዎች ፬ • በመንግሥት የሚሰየም አንድ ኣባል ፭ የኢትዮጵያ የጤናና ሥነምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ዲሬክተር ..... አባልና ፀሐፊ ገጽ ፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ • ም • ፳ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬እና፭ የተመለከቱት የኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች እንዲሁም ስልጣንና ተግባሮች በሚገባ ሥራ ላይ መዋላቸውን የመከታተል ፤ ፪ በኢንስቲትዩቱ ተቀርጸው የሚቀርቡትን ፖሊሲና መመሪ ያዎች የመገምገምና የማፅደቅ ፤ ፫ የኢንስቲትዩቱን የምርምር ፕሮግራሞችገምግሞ የማጽደቅ፡ በሥራ መተርጐማቸውን የመከታተልና የመቆጣጠር ፤ ፬ ለኢንስቲትዩቱ ዲሬክተርተጠሪ የሆኑኃላፊዎችን ሹመት የማጽደቅ ፤ ፭ በቴክኒክና በሳይንቲፊክ ሥራዎች ላይ የተሠማሩ ሠራተ ኞችን መተዳደሪያ ደንብ የማጽደቅ ፡ ደሞዝና አበላቸውን የመወሰን ፤ ፮ . የኢንስቲትዩቱን ረቂቅ በጀት የማጽደቅ ' አመዳደቡን የመመጠንና አወጣጡን የመወሰን ። ፱ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል ። | 9 Meetings of the Board ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ ከቦርዱ አባላት አብዛኞቹ በስብሰባው ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሣኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ። ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዲሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት ኢንስቲ ትዩቱን በሚገባ የማስተዳደርና ሥራውንም የመምራት ኃላፊነት አለበት ። ፪ • ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ ኣነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዲሬክተሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ለኢንስቲትዩቱ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ የማዋል ፤ ለ ) በኢንስቲትዩቱ በቴክኒክ እና በሳይንቲፊክ ሥራ ላይ የተሠማሩ ሠራተኞችን ቦርዱ ባፀደቀው መመሪያ መሠረት የመቅጠር ፡ የማስተዳደር እንዲሁም የኢንስ ቲትዩቱን ሌሎች ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት የማስተዳደር ፤ ሐ ) የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ'ፕሮግራም ኣዘጋጅቶ ለቦርዱ የማቅረብ ፤ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ የማድረግ ፤ ሠ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ ክንውን የሚያሳይ ዓመታዊ ሪፖርት ለቦርዱ የማቅረብ ። ፫ የኢንስቲትዩቱን ተግባሮች በሚገባ ለማከናወን ባስፈለገ መጠን ሥልጣኑን በከፊል ለኢንስቲትዩቱ ምክትል ዲሬክተር ወይም ለሌሎች የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በውክልና ሊሠጥ ይችላል ። ገጽ ፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት 3 ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ፲፩ በጀት ፩ የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል ፤ -ሀ ) ከፌዴራል መንግሥቱ የሚመደብ በጀት ፡ ለ ) በዚህ ደንብ መሠረት የሚሰበሰብ የአገልግሎት ሐ ) ከሌሎች ምንጮች ። ፪ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከተው ገንዘብ በኢንስቲትዩቱ ስም ባንክ ተቀማጭ ሆኖ የኢንስቲት ዩቱን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ የመንግሥትን የበጀት አሠራር መመሪያ በማድረግ ወጪ ያደርጋል ። ፲፪ የሂሣብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት | 12. Books of Accounts . ይይዛል ። ፪ የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፫፫ : ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ