የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፮ አዲስ አበባ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፪ / ፲፱፻፶ ዓም የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፮፻፷፱ አዋጅ ቁጥር ፩፻፪ / ፲፱፻፲ የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣ የኢኮኖሚ ልማትንና ቴክኖሎጂን በማሻሻል የኅብረተሰቡን አኗኗር ለማበልጸግ የሚደረገው እንቅስቃሴ የጥራትን ፡ የሜትሮሎ ጂንና የደረጃዎች ሥራን ማስፋፋትና መተግበርን አስፈላጊ ስለሚያ ደርገው ፣ በዚህ ረገድ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ፡ የደረጃዎችና የጥራት ማስፋፋት ሥራ ኃላፊነት የተጣለበትን መንግሥታዊ አካል እንደገና ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፪ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ጀ• ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር | በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ “ የጥራትማስፋፋት ” ማለት በየደረጃው በሚገኝ የምርት ሂደት ላይ በተመጣጠነ የሀብት አጠቃቀም የጥራት ተፈላጊ ሁኔታዎችንና ዓላማዎችን በማሟላት ፣ የአንድን ድርጅት ብቃት ለማሳደግና ለማሻሻል የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ነው ፣ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ• ሺ ግጽ ፯፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፵ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta - No . 26 3 March , 1998 - Page 700 ፪ . “ ጥራት ” ማለት በቀጥታ የተገለጸንና በተዘዋዋሪ መንገድ የተመለከተን ፍላጎት የማሟላት ችሎታውን የሚገልጽ የአንድ አካል አጠቃላይ ባሕርይ ነው ፡ ፫ . “ የደረጃዎች ሥራ ” ማለት ደረጃዎች የማዘጋጀት ፤ አሳትሞ የማውጣትና የመተግበር ሂደቶችን የሚያካትት እንቅስቃሴ ነው ፣ ፬ . “ ደረጃ ” ማለት ምርቶች ለታቀዱበት ዓላማ የሚስማሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንደ ደንብ ፡ መመሪያ ወይም እንደ ባህሪያት ትርጓሜ በቋሚነት ለማገልገል ቴክኒካዊ ዝርዝር ሁኔታዎችን ወይም ሌሎች መመዘኛዎችን በተመ ለከተ በስምምነት የተዘጋጀ ሰነድ ነው ፣ ፭ “ ምርት ” ማለት የእንቅስቃሴዎች ወይም የሂደቶች ውጤት ሲሆን ይህም አገልግሎት ፡ ሀርድዌር ፡ ሶፍትዌር ፥ ፕሮሴስድ ዕቃዎች ወይም የእነዚህን ጥምር ሊያጠቃልል ይችላል ፡ ፮ “ ሂደት ” ማለት ግብአትን ወደ ውጤት የሚለውጥ የተቀናበረ የሀብትና የእንቅስቃሴዎች ጥምር ነው ፤ ፯ . “ የኢትዮጵያ ደረጃ ” ፡ ማለት ማንኛውም ባለሥልጣኑ አጽድቆ የሚያወጣው ደረጃ ነው ፤ ፰ “ ዓለምአቀፍ የአሀዶች ሥርዓት ( ኤስአይ ) ” ማለት የሚዛንና መስፈሪያ ጠቅላላ ኮንፈረንስ ( ጂፒኤም ) የተቀበለውና በሥራ ላይ እንዲውል ድጋፍ የተሰጠበት የተቀናጀ የአሀዶች ሥርዓት ነው ፣ ፱ . “ ኢታሎን ” ማለት አንድን አሀድ ፡ ወይም አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የመጠን እሴትን ለመወሰን ፡ በተግባር ለመግለጽ : ለመጠበቅ ወይም ለመቅዳት የተመደበ መሠረታዊ መለኪያ ፡ የመለኪያ መሣሪያ ፡ የማመሳከሪያ ስረት ወይም የአለካክ ቅንብር ነው ፤ ፲ “ የተመሰከረለት ማመሳከሪያ ስረት ” ማለት የምስክር ወረቀት ያለው ፡ የአንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የባሕሪዩ እሴቶች የተረጋገጡበት ሥርዓት ባህሪዩ የተገለጸ በትን አሀድ በተዋረድነት በትክክል የሚገልጽ ሆኖ የእያንዳንዱ የተረጋገጠ እሴት እርግጠኛ አለመሆን በተወሰነ አስተማማኝነት ደረጃ የተገለጸ የማመሳከሪያ ስረት ነው ፡ ፲፩ . “ የመለኪያ መሣሪያ ” ማለት ብቻውን ወይም ከአጋዥ መሣሪያዎች ጋር በመጣመር መጠኖችን ለመለካትእንዲያ ገለግል ታቅዶ የተሠራ መሣሪያ ነው ፤ ፲፪ . “ የጥራት ማኅተም ” ማለት ዝርዝር ሁኔታው በባለሥ ልጣኑ የሚገለጽ ከኢትዮጵያደረጃዎች ጋር ተስማሚነትን ለማመልከት የሚያገለግል የጥራት ማረጋገጫ ምልክት ፲፫ “ የተስማሚነት ምስክር ወረቀት ” ማለት አንድን በሚገባ የተገለጸን ምርት ወይም ሂደት ከተወሰነ ደረጃ ጋር ለመስማማቱ በቂ ማረጋገጫ የሚሰጥ ሰነድ ነው ፤ ፲፬• “ የተስማሚነት ምዘና ሥርዓት ” ማለት የራሱ የሆነ የአሰራር ደንብና የማኔጅመንት ዘይቤ ኖሮት አግባብነት ያላቸው የደረጃ ተፈላጊ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ለመወሰን በቀጥታና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት ሥርዓት ነው ፤ ፲፭ “ ስምምነት ” ማለት መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በዋናነት ከሚመለከታቸው ወገኖች ያለማቋረጥ የሚነሳ ተቃውሞ የሌለበት ሆኖ ፣ የሁሉንም ወገን ሃሣብ በማስተና ገድና የሚጋጩ ሃሳቦችን ለማስታረቅ በመፈለግ ላይ የተመሠረተ አጠቃላይ መግባባት ነው ፣ ገጽ ፯፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 26 3 March , 1998 - Page 701 ፲፮ . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ፫• እንደገና መቋቋም ፩• የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ “ ባለሥልጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን የቻለና ሕጋዊ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል ። ፪ . ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፬• ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊ ነቱም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊያቋቁም ይችላል ። ፭ ዓላማ ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ በማኅበራዊውና በኢኮኖሚው ዘርፍ የጥራት ሥራ አመራር ልምድ ከሌሎች የሥራ አመራር ተግባራት ጋር በቅንጅትና እራሱን የቻለ ሆኖ የሚመሰረትበትን ሁኔታ ማስፋፋትና መርዳት ፣ ፪• የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በማስፋፋትና በመተግበር የምርቶ ችንና የሂደቶች ጥራት እንዲሻሻል መርዳት ፣ ፫ . በአገሪቱ ውስጥ በሁሉም ደረጃ : የደረጃዎች ሥራን ማስፋፋትና ማስተባበር ፡ ፬ . ለኢኮኖሚ እድገት እንደ መሠረታዊ መዋቅር ሆኖ የሚያገ ለግል አስተማማኝ የሆነ ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ሥርዓት ማቋቋም ፣ ፭ በአገር አቀፍ ደረጃ አስተማማኝነት ያላቸው የፍተሻ ላቦራ ቶሪዎች እንዲስፋፉ ፡ እንዲጠናከሩና እንዲጐለብቱ ማድረግ ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ _ ፩ የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በብቸኝነት ማጽደቅና ማሳወቅ እንዲሁም ብሔራዊ ኢታሎኖችን መጠበቅ ፣ ፪• እንደአስፈላጊነቱ ለአጠቃላይ ወይም በተለይ ለተወሰነ አገልግሎት የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ማዘጋጀት ፡ ማጽደቅ ፡ ማስታወቅና አሳትሞ ማውጣት ፣ ፫ በብሔራዊ ኣህጉራዊ ወይም ዓለምአቀፍ የደረጃዎች ሥራን | በሚያከናውኑ አካላት የተዘጋጀን ማንኛውንም ደረጃ እንደ | አስፈላጊነቱ እንደ ኢትዮጵያ ደረጃ እውቅናን መስጠት ፣ ፬ . ከአገሪቱ የልማት መርሃ ግብር ጋር የተጣጣመ የጥራት ማስፋፋት ፡ የደረጃ ምደባ ፖሊሲና ስትራቴጂ ማዘጋጀትና ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ ፡ አፈጻጸሙንም መከታተል ፤ ፭ አስተማማኝ የሆነ ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ሥርዓትን ለማቋቋም ፣ ሀ ) ብሔራዊ ኢታሎኖችንና የተመሰከረላቸውማመሳከሪያ ስረቶችን መጠበቅና ማሰራጨት ፣ ለ ) የዓለምአቀፍ አሀዶች ሥርዓትን ( ኤስአይ ) የፊዚካል መጠኖች መለኪያ እንደ ብቸኛ የአለካክ ሥርዓት ማስተዋወቅ ፣ ሐ ) የመለኪያ መሣሪያዎችን ትክክለኝነት ማረጋገጥ እና ወይም ካሊብሬት ማድረግ ፣ ፮ ብሔራዊ የተስማሚነት ምዘና ሥርዓትን ማቋቋምና በሥራ ላይ ማዋል ፡ ፯ ምርቶች አግባብነት ካላቸው ተፈላጊ ሁኔታዎች ጋር መስማ ማታቸውን ለማረጋገጥ ፡ የኢንዱስትሪና የእርሻ ምርም ሮችን ለመርዳትና በአገሪቱ ውስጥ በሁሉም ደረጃ ለሚካሄዱ የጥራት ማሻሻያና የደረጃዎች ሥራ ጥረቶች ድጋፍ ለመስጠት ፡ የፍተሻ ላቦራቶሮችን ማቋቋምና ማካሄድ ፡ ቿ ወደፊት የሚወሰን ቅርጽና እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች ተጨማሪ መለያዎች የሚኖረው የጥራት ማኅተምን መወሰን ፡ ፬ በጥራት ማኅተም ለመጠቀም ፈቃድ መስጠት ፡ ማደስ ፡ ማገድ ፡ ወይም መሰረዝ ፡ ግጽ ፯፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፲ ምርቶች እና ወይም ሂደቶች አግባብነት ካላቸው አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ጋር ተስማሚ ካልሆኑ በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ፋብሪካዎች ወይም የንግድ ተቋሞች እንዲዘጉ ወይም ሥራቸው እንዲቋረጥ ወይም የምርቶች እንቅስቃሴ እንዲታገድ ትዕዛዝ መስጠት ፤ ) ፲፩ ጥራትንና ደረጃን የተመለከተ መረጃ ለመስጠት የሥርዓተ ሰነድና መረጃ ማዕከል ማቋቋም ፤ ፲፪• የጥራትንና የደረጃን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ በተጠቃ ሚውና በኅብረተሰቡ ዘንድ ማስተዋወቅ ፣ ፲፫• የደረጃዎች ሥራን በሚመለከት ማናቸውም ጉባዔዎች ፡ ሴሚናሮች ወይም ስብሰባዎች ላይ መንግሥትን ወክሎ መሳተፍ ፣ ፲፬• ተግባሩን ለማራመድ ከደረጃዎች ሥራ አካሎች ፡ ከሙያ ማኅበሮችና ከጥራት ሥራ ጋር ከተያያዙ ማኅበሮች ፡ ከሰርቲፊኬሽን አካሎችና ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር የሥራ ግንኙነት መፍጠርና መጠበቅ ፡ ፲፭ የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በብቃት በሥራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሥልጣንና ተግባሩን እንደአስፈላ ጊነቱ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ድርጅቶች በከፊል በውክልና መስጠት ፡ ፲፮ ለሚሰጠው ማናቸውም አገልግሎት ዋጋ ማስከፈል ፡ ፲፯ የንብረት ባለቤት የመሆን ፡ ውል የመዋዋል ፡ በራሱ ስም የመክሰስና የመከሰስ ፡ ፲፰ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወን ። ፮ . የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፡ ፩ የሥራ አመራር ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፣ ፪ . በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የቦርድ አባላት ቦርዱ አንድ ሊቀመንበርና ቁጥራቸው ከሰድስት የማይበልጥ | The Board shall have a chairmer በመንግሥት የሚሾሙ አባላት ይኖሩታል ። ፀ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር - ፩ . የባለሥልጣኑን የፖሊሲ ጉዳዮች ይወስናል ፡ ሥራዎቹን በበላይነት ይመራል ፡ ይቆጣጠራል ፡ ፪ . የባለሥልጣኑን የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት በራሱ ደረጃ ያጸድቃል ፣ በተግባር መተርጐሙን ያረጋግጣል ፣ የባለሥልጣኑን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸድቃል ፣ ፬• የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ያጸድቃል ፣ ፭ ባለሥልጣኑ ለሚሰጠው የጥራት ማኅተም ክፍያ እና | ሌሎች የአገልግሎቶች ክፍያዎችን ይወስናል ፣ ፯r ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ፮ እንደአስፈላጊነቱ የፖሊሲ አማካሪ ኮሚቴዎች ያቋቁሟል ፣ ፯ በዋና ሥራ አሰኪያጁ በሚቀርቡ የባለሥልጣኑን አስተዳ ደርና አመራር በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይወስናል ። _ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ። ጀ በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው ከአባሎቹ በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ይሆናል ፣ ሆኖም ድምጹ እኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። [ ፬ የዚህ ኣንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፣ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። - የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር " ፩ ዋናው ሥራ አስኪያጅ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሥራ ያቅዳል ፡ ያስተዳድራል ። - ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ ሃሣብ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፣ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ላይ የተጠቀሰውን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ መርሆዎች ተከትሎ ቦርዱ በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ለባለሥልጣኑ በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ሠ ) ባለሥልጣኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ፣ ረ ) የባለሥልጣኑን የሥራ እንቅስቃሴና ሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣኑና ተግባሩ በከፊል ለባለሥ ልጣኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ስለ በጀት የባለሥልጣኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፣ ፩ በመንግሥት ከሚሰጥ የበጀት ድጋፍ ፣ ፪ ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ፣ እና ፪ ፫ ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገቢ ። ስለሂሣብ መዛግብት አያያዝ ! ፩ ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛ | 1 ) The Authority shall keep complete and accurate books ግብት ይይዛል ። ገጽ ፯፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፲ ዓም - ፪ የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬• ስለቅጣት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ፡ _ ፩ ማንኛውም የባለሥልጣኑ ሹም ወይም ሠራተኞች ፣ ሀ ) በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመቀበል ወይም በዝምድና ግንኙነት በሐሰተኛና በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት የአንድን ምርት ወይም ሂደት ጥራት ወይም ደረጃ በተመለከተ ሐሰተኛ የምስክር ወረቀት ወይም ማረጋገጫ የሰጠ ወይም እንዲሰጥ ያደረገ እንደሆነ ፣ ወይም ለ ) መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመፈለግ ወይም ሰውን ለመጉዳት በማሰብ በኃላፊነቱ የቀረበለትን ውሳኔ ወይም ጉዳይ በወቅቱ ባለመፈጸም ባለጉዳዩን ያጉላላ እንደሆነ ፡ በመደለያ የተቀበለውን ገንዘብ ሦስት እጥፍ ያልበለጠና ፣ ከ፲፭ ዓመት በማያንስ እና ከ፳ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ፪• የኢትዮጵያ የደረጃዎችን ሥራ በሥራ ላይ እንዲያውል ከባለሥልጣኑ ውክልና ወይም ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ፡ ሀ ) በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመቀበል ወይም በዝምድና ግንኙነት በሐሰተኛና በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት የአንድን ምርት ወይም ሂደት ጥራት ወይም ደረጃ በተመለከተ ሐሰተኛ የምስክር ወረቀት ወይም ማረጋገጫ የሰጠ ወይም እንዲሰጥ ያደረገ እንደሆነ ፡ ወይም መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመፈለግ ወይም ሰውን ለመጉዳት በማሰብ በኃላፊነቱ የቀረበለትን ውሳኔ ወይም ጉዳይ በወቅቱ ባለመፈጸም ባለጉዳዩን ያጉላላ እንደሆነ ፡ በመደለያ የተቀበለውን ገንዘብ ሦስት እጥፍ ያልበለጠ እና ከ፲፭ ዓመት በማያንስ እና ከጽ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ፣ እንዲሁም የተሰጠው ውክልና ወይም ሥልጣን ይሠረዝበታል ። ፫• ማንኛውም ሰው ፡ ሀ ) በአንድ ምርት ወይም ሂደት ላይ የማጭበርበር . ድርጊት እንዲፈጸም መደለያ ወይም ሌላ ስጦታ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ እንደሆነ በመደለያ የሰጠውን ወይም ለመስጠት ያቀረበውን ገንዘብ ሦሰት እጥፍ ያልበለጠ መቀጮ እና ከ7 ዓመት በማያንስ እና ከ፲፭ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። የጥራት ማኅተም ፈቃድ ፡ ወይም የተስማሚነት የምስክር ወረቀት ሳይኖረው አንድ አስገዳጅ የኢት ዮጵያ ደረጃ ያለውን ምርት ወይም የመለኪያ መሣሪያ የሽጠ ወይም ለሽያጭ ያቀረበ እንደሆነ ከr ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ከብር ፲ ሺ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል ፡ የተፈጸመው ድርጊት በሰው ሕይወት ወይም ጤንነት ላይ ወይም በኢኮኖሚው ላይ ጉልህ ጉድለት ያደረሰ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ፲ ዓመት ጽኑ እሥራትና እስከ ብር ፳ ሺ መቀጮ ሊደርስ ይችላል ። ገጽ ፯፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፶ ዓም . Federal Negarit Gazeta - No . 26 3 March , 1998 _ Page 705 ሐ ) ወቅታዊ ካሊብሬሽን ማረጋገጥ የሚያስፈልጋ ቶውን የመለኪያ መሣሪያዎች ያለምስክር ወረቀት የተጠቀመ ከ፫ ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ከብር ፲ሺህ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል ፣ የተፈጸመው ድርጊት በሰው ሕይወት ወይም ጤንነት ላይ ወይም በኢኮኖሚው ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ፲ ዓመት ጽኑ እሥራትና እስከ ብር ፳ሺህ መቀጮ ሊደርስ ይችላል ። የተስማሚነት የምስክር ወረቀት ወይም የጥራት ማኅተም ተሰጥቶት የምስክር ወረቀቱን ወይም ማኅተሙን በፈቃዱ ላይ ከተመለከተው ሁኔታ ውጥ የተጠቀመ ወይም ፈቃዱ ከተሰረዘ በኋላ አገልግሎት መስጠቱን የቀጠለ ከ፫ ዓመት ባልበለጠእሥራትናከብርቨሺህ ባልበለጠ መቀፎ ይቀጣል ። በሐሰት ኢንስፔክተር ነኝ ብሎ እራሱን ያቀረበ ወይም ኢንስፔክተሩ ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት እንቅፋት ወይም መሰናክል የሆነ እንደሆነ ከ፫ ዓመት ባልበለጠ እሥራት ይቀጣል ። ረ ) ስለቅድመ እሽግ የወጣውን ደንብ ባለመከተል የቅድመ እሽግ ሽቀጥ የሸጠ እንደሆነ ከ፩ ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ከብር ፭ሺህ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል ። ፬ . በዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሠ ) ፣ ( ፪ ) ( ሀ ) እና ( ፫ ) ( ሀ ) የተመለከቱትን የወንጀል ድርጊቶች በመፈጸም ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ስለተፈጸመው ጥፋትና ስለተባባሪዎቹ ሚና ጠቃሚ መረጃ የሰጠን ሰው የፍትሕ ሚኒስቴር በዚህ ሕግ መሠረት እንዳይከሰስ ሊያደርግ ይችላል ። ፲፭ የተሻሩና ጸንተው የሚቆዩ ሕጐች ፩• የኢትዮጵያ ደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ | ) The Ethiopian Authority for Standardization Es አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፰ ፲፱፻፪፬ እና የሚዛንና የመስፈሪያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፰ ፲፱፻፶፭ በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ። ፪ የደረጃዎችማኅተም እና የአገልግሎት ዋጋ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻ዥ፪ ፡ የሚዛንና የመስ | ፈሪያ ደንብ ቁጥር ፬፻፴፩ / ፲፱፻፷፭ ፣ የኢትዮጵያ ደረጃዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፪ / ፲፱፻ዥ፪ በሌላ ሕግ እስኪተኩ ድረስ እንደጸኑ ይቆያሉ ። ፲፮ አግባብነት የሌላቸው ሕጐች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑማናቸውም ሕጐች በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ገዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻ሮü የተቋቋመው የኢትዮጵያ | ደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለባለሥልጣኑ ተላልፈዋል ። ፲፰ የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የመተባበር ግዴታ | አለበት ። ገጽ ፯፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፲ ዓም . Federal Negarit Gazeta - - No . 26 3 March , 1998 - ~ Page 706 አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻ ዓ ም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት