×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 25 1 93 የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፴ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፬ቀን ፲፱፻፲፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲ / ፲፱፻፫ ዓም የፌዴራሉ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲ / ፲፱፻፶፫ የፌዴራሉ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አዋጅ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ፤ የሕጐች ሁሉ የበላይ የሆነውን የፌዴራሉን ሕገ መንግሥት ለመተርጐም ሥልጣን ለተሰጠው የፌዴሬሽን ም / ቤት የሙያ ድጋፍ ለመስጠት | sional support to the House of the Federation which has been በፌዴራሉ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፪ ፩ የተቋቋመ በመሆኑ ፤ የሕገ መንግሥት ትርጉም አሠራር ይበልጥ እንዲጐለብት ፣ ብቃትና ጥራት ያለው የሙያ አገልግሎት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት | and strengthen the Council of Constitutional Inquiry so as to ለመስጠት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን ማደራጀትና | further consolidate the task of interpreting the constitution ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ፤ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባላትን የሥራዘመን ፣ መብትና ግዴታቸውን መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራሉ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አዋጅ ቁጥር ፪፻፶ ፲፱፻፲፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጉም የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ ሕገ መንግሥት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክ ራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ * ጽሕፈት ቱ ተጠሪነቱ ለአጣሪ ጉባኤም ' ' - ገጽ ፩ሺ፮፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻ ዓ • ም • ፪ . “ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ” ማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፴፫ መሠረት የተቋቋመ የፌዴራሉ መንግሥት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው ፤ ፫ . “ አጣሪ ጉባኤ ” ማለት የፌዴራሉ መንግሥት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ነው ፤ ፬ . “ ክልል ” ማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) መሠረት በክልልነት የታወቁት ሲሆኑ እንዳስፈላጊነቱ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና የድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስልን ይጨምራል ፤ ፭ “ ሕግ ” ማለት በፌዴራሉ መንግሥት ወይም በክልል መንግሥታት አካላት የሚወጡ አዋጆች ፣ ደንቦች እንዲሁም ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነ ቶችን ያካትታል ፤ ፮ . “ የመንግሥት አካል ” ማለት የፌዴራሉም ሆነ የክልል ሕግ አውጪ ፣ ሕግ አስፈጸሚ፡ የዳኝነት አካል ወይም በሕግ የዳኝነት ሥልጣን የተሰጠው ሌላ አካል ነው ፤ ፯ . “ ፍርድ ቤት ” ማለት በማናቸውም ደረጃ የሚገኝ የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ነው ። ፫ የአጣሪ ጉባኤው አደረጃጀት አጣሪ ጉባኤው ፣ የጉባኤ ሊቀመንበር ፣ ምክትል ሊቀመንበር ፣ አባላት የጽሕፈት ቤት ኃላፊና ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፬ . የአጣሪ ጉባኤው አባላት አጣሪ ጉባኤው የሚከተሉት አሥራ አንድ አባላት ይኖሩታል ፤ ፩ . የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት .... ሰብሳቢ ፪ . የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ሰብሳቢ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢነት በሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት የሚሾሙ በሙያ ብቃታቸውና በሥነ ምግባ ራቸው የተመሰከረላቸው ስድስት የሕግ ባለሙያዎች ፬ . የፌዴሬሽኑምክር ቤት ከአባላቱ መካከል የሚወክላቸው ሦስት ሰዎች . ፭ መቋቋም ፩ . የአጣሪ ጉባኤው ጽሕፈት ቤት ( ከዚህ በኋላ “ ጽሕፈት ቤቱ ” ተብሎ የሚጠራ ) ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፮ የአጣሪ ጉባዔው ሥልጣንና ተግባር አጣሪ ጉባኤው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ አጣሪ ጉባዔው ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን በማጣራት ሕገ መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባል ። ፪ • በፌዴራሉ መንግሥትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጎች ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳ እና ጉዳዩም በሚመለ ከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሣኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል ። በፍርድ ቤቶች የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ ፣ ሀ ) ሕገ መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ይመልሳል ፤ ለ ) የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሣኔ ያቀርባል ። ፯ . የአጣሪ ጉባዔው አባላት የሥራ ዘመን ፩ . የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚወክላቸው አባላት የሥራ ዘመን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሥራ ዘመን ነው ። ገጽ ፩ሺ፮፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም. ፪ በሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት የሚሾሙ አባላት የሥራ ዘመን ስድስት ዓመት ይሆናል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ድንጋጌዎች ቢኖሩም፡ የአጣሪ ጉባዔው አባላት በድጋሚ አባል ሆነው ሊመረጡ ይችላሉ ። ፫ የአጣሪ ጉባዔው አባላት ከሥራ ስለሚነሱበት ሁኔታ ፩ . ከሰብሳቢውና ከምክትል ሰብሳቢው በስተቀር ፣ የአጣሪ ጉባዔ አባል በወከለውና በሾመው አካል በበቂ ምክንያት ሊነሳ ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚሰጠው ውሣኔ ተግባራዊ የሚሆነው ውሣኔው በፌዴሬሽን ምክር ቤት በድምጽ ብልጫ ተቀባይነት ያገኘ እንደሆነ ብቻ ነው ። የአጣሪ ጉባዔው አባላት የሥራ ሁኔታና የአገልግሎት ክፍያ ምክትል ሰብሳቢው ፤ የአጣሪ ጉባዔው አባላት በአጣሪነ ታቸው ለሚያበረክቱት አገልግሎት በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የሚወሰን አበል ወይም ደመወዝ ይከፈላቸዋል ። ፪ . አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከአጣሪ ጉባዔው አባላት መካከል በከፊል በዋናው ጽሕፈት ቤት በቋሚነት እንዲሰሩ ይደረጋል ። የአጣሪ ጉባዔው ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር የአጣሪ ጉባኤው ሰብሳቢ ፣ ፩ . የአጣሪ ጉባዔውን ስብሰባ ይጠራል ፤ ይመራል ፤ ፪ ለአጣሪ ጉባዔው የሚቀርቡለትን ጉዳዮች በሥርዓት አቀናብሮ ለአጣሪ ጉባዔው አባላት እንዲደርሱያደርጋል ፤ ምልዓተ ጉባዔ መኖሩን ያረጋግጣል ፣ ከአጣሪ ጉባዔው አባላት መካከል ለአጣሪ ጉባዔው በቀረበ ጉዳይ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ የውሣኔ አስተያየት እንዲያ ቀርቡ ወይም የውሣኔ ረቂቅ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል ፤ ፭ የአጣሪ ጉባዔው ውሣኔዎች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲተላለፉ ያደርጋል ፤ ፮ የአጣሪ ጉባኤውን ጽሕፈት ቤት በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፤ የአጣሪ ጉባዔውን ደንብና ሥርዓት ያከብራል ፤ ያስከ የአጣሪ ጉባዔውን የሥራ ክንውን ሪፖርት በየስድስት ወሩ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል ። ፲፩ . የአጣሪ ጉባዔው ም ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር ምክትል ሰብሳቢው ፣ ፩ . የአጣሪ ጉባኤው ሰብሳቢ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል ፣ ፪ . በሰብሳቢው የሚሰጡትን ተግባራት ይፈጽማል ። ፲፪ • የአጣሪ ጉባዔው አባል ተግባርና ኃላፊነት ማንኛውም የአጣሪ ጉባኤው አባል ፣ ፩ . ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጠመው በስተቀር አጣሪ ጉባዔው በሚጠራው ማንኛውም ስብሰባ ላይ መገኘት ይኖርበታል ፤ ፪ • ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ስብሰባ ላይ የማይገኝ ከሆነ ይህንኑ ለሰብሳቢው አስቀድሞ ማሳወቅ አለበት ፤ ፫ በአጣሪ ጉባዔው ወይም በኮሚቴ ስብሰባ ላይ በአጀንዳ በሚቀርበው ጉዳይ ተካፋይ በመሆን የጉባዔው ሥራ የተሟላ ውጤት እንዲያገኝ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ይኖርበታል ፣ የአጣሪ ጉባዔውን ደንብና ሥርዓትማክበር ይኖርበታል ። ፲፫ : የአጣሪ ጉባዔው ስብሰባ ፩ አጣሪ ጉባዔው በየሦስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ። ፪ . እንደ አስፈላጊነቱ ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ። ፲ 0 የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፩ ለአጣሪ ጉባዔው የጽህፈት አገልግሎት ይሰጣል፡ ፪ • ለአጣሪ ጉባዔውና ለልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ያዘጋጃል፡ ገጽ ፩ሺ፮፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም : ፫ የአጣሪ ጉባዔውን ቃለ ጉባዔ፡ ውሣኔ እና ሌሎች ሰነዶች በሚገባ ተመዝግበው እንዲጠበቁ ያደርጋል ። ፬ ኣጣሪ ጉባዔው የሚያወጣውን መጽሔትና ጽሁፎች ሕት መታቸውንና ስርጭታቸውን ይከታተላል ። ፭ ባለጉዳዮች ተገቢውን መስተንግዶ እንዲያገኙ ያደርጋል፡ ፮ ለአጣሪ ጉባኤው አባላት የምርምርና ጥናት አገልግሎት ይሰጣል፡ ፯ የንብረት ባለቤት ይሆናል፡ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል፡ ይከሰሳል፡ ፰ : ሌሎች ለአጣሪ ጉባኤው ሥራ ስኬታማነት የሚረዱ ተግባሮችን ያከናውናል ። ፲፭ የጽሕፈት ቤቱ አቋም የአጣሪ ጉባዔው ጽሕፈት ቤት ፣ ፩ በአጣሪ ጉባዔው አቅራቢነት በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሾም አንድ ሀላፊ፡ እና ፪ . አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፫ የአጣሪ ጉባኤው ዋና ጽሕፈት ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ። ፲፮ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባር የጽሕፈቱ ቤቱ ኃላፊ ፣ ፩ የጽሕፈት ቤቱን ሥራዎች ይመራል፡ ያስተዳድራል፡ ፪ • የአጣሪ ጉባዔውን ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፡ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡ ፫ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ የተመለከቱትን የጽሕፈት ቤቱን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል፡ ፬ ጽሕፈት ቤቱ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ጽሕፈት ቤቱን ይወክላል፡ ፭ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ህግ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሰራተኞች ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ ፮ የጽሕፈት ቤቱን የስራ እንቅስቃሴና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለአጣሪ ጉባኤው ሰብሳቢ ያቀርባል ። ፯- ሌሉች በአጣሪ ጉባዔውና በሰብሳቢው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል ። ክፍል ሁለት ሕገ መንግሥትን ስለመተርጎም ፲፯ መሠረቱ ፩- ኣጣሪ ጉባዔው ሕገመንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን ይኖረዋል ። ፪ አጣሪ ጉባዔውማናቸውም ሕግ ወይም የመንግስት አካላት ወይም የባለስልጣን ውሣኔ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሣኔ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል ። ፫ አጣሪ ጉባዔው በምርመራው ሂደት ህገ መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውሣኔውን ጥያቄ ላቀረበው አካል ያሳውቃል ። ፲፰ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ ስለማቅረብ ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ንዑስ አንቀጽ ፫ መሠረት አጣሪ ጉባዔው በሰጠው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ ቅሬታውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በይግባኝ ማቅረብ ይችላል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚቀርብ ይግባኝ ውሣኔው ለባለጉዳዩ በደረሰ በ፰ ቀናት ውስጥ ሊቀርብ ይገባል ። ፲፱ • የውሣኔ ሃሣብ ስለመላክ ፩ አጣሪ ጉባዔው የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋል ብሎ ሲያምን የውሣኔ ሃሣቡንና ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ መረጃ ዎችና ሰነዶችን አያይዞ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይልካል ። ፪ . አጣሪ ጉባዔው የውሣኔ ሃሣቡንና ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ መረጃዎችንና ሰነዶችን የውሣኔ ሃሣቡን ካፀደቀበት ቀን ጀምሮ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲደርሰው ያደርጋል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻ ዓ • ም • ፳ • በህገ መንግሥት ትርጉም ተፈጻሚ ስለሚሆኑ መርሆዎች ፩ አጣሪ ጉባዔው የሚቀርቡለትን የሕገ መንግሥት ነክ ጉዳዮች መርምሮ ለመወሰን ጠቃሚ ናቸው ብሎ የሚያምን ባቸውን የህገ መንግሥት አተረጓጎም መርሆዎች መለየትና በሥራ ላይ ማዋል ይችላል ። ፪ • ለአጣሪ ጉባዔው የቀረበው ጥያቄ በህገ መንግሥቱ የሰፈ ሩትን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች የሚመለከት ሲሆን ትርጉሙ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግጋት፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነ ቶችና አለም አቀፍ ሰነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ ይተረጎማል ። ፳፩ . በፍርድ ቤት ስለሚነሳ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ፩ በፍርድ ቤት በተያዙ ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጥያቄው ጉዳዩን በያዘው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ለአጣሪ ጉባዔው ሊቀርብ ይችላል ። ፪ : ጉዳዩን የያዘው ፍርድ ቤት የትርጉም ጥያቄ ለአጣሪ ጉባዔው የሚልከው ጉዳዩን ለመወሰን ሕገ መንግሥቱን መተርጎም ያስፈልጋል ብሎ ሲያምን ብቻ ነው ። ፫ ፍርድ ቤቱ ለአጣሪ ጉባዔው የሚልከው የሕገ መንግሥት ትርጉም ለመስጠት አስፈላጊ የሆነውን የሕግ ነጥብ ብቻ ፍርድ ቤቱ ለአጣሪ ጉባዔ የላከው የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ውጤት እስኪደርሰው ድረስ የቀረበለትን ጉዳይ በእንጥልጥል እንዲቆይ ያደርጋል ። ፳፪- በፍርድ ቤት በተያዙ ጉዳዮች ስለሚቀርብ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ፩ በፍርድ ቤት ክርክር ያለው ማንኛውም ባለጉዳይ ጉዳዩ ለመወሰን የሕገ መንግሥት ትርጉም አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነ እንደሆነ ጥያቄውን ለአጣሪ ጉባዔው ማቅረብ ይችላል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው አጠቃላይ ድንጋጌ ቢኖርም ፣ ባለጉዳዩ ጥያቄውን ለአጣሪ ጉባዔው ከማቅረቡ በፊት ጉዳዩን ለያዘው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል ። ፫ ጥያቄው የቀረበለት ፍርድ ቤት ጥያቄውን ያልተቀበለ እንደሆን ባለጉዳዩ ውሣኔውን ባወቀ በ፯ ቀን ውስጥ ለአጣሪ ጉባዔው ማቅረብ ይኖርበታል ። ፬ . ባለጉዳዩ ለአጣሪ ጉባዔው የሚያቀርበው ጥያቄ የሕገ መንግስት ትርጉም ለመስጠት አስፈላጊ የሆነውን የሕግ ነጥብ ብቻ ነው ። ፭ አጣሪ ጉባዔው ከባለጉዳዩ የቀረበለትን የትርጉም ጥያቄ መርምሮ ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ ፍርድ ቤት ያለው ጉዳይ በእንጥልጥል እንዲቆይ ሊያዝ ይችላል ። ፳፫ • ከፍርድ ቤት ውጪ ስለሚቀርብ የሕገ መንግስት ትርጉም ፩ . በማንኛውም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን የመጨረሻ ውሳኔ በሕገ መንግስቱ የተደነገገው መሠረታዊ መብቴና ነጻነቴ ተጥሷል የሚል ማንኛውም ሰው የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ለአጣሪ ጉባኤው ማቅረብ ይችላል፡ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ለአጣሪ ጉባዔው የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ የሚቀርበው የመብት መጓደል አቤቱታው መጀመሪያ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን በየደረጃው ስልጣን ላለው የመንግስት አካል ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት ከሆነ ብቻ ነው ። ፫ . በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ውስጥ የመጨረሻ ውሣኔ ማለት ታይቶ ያለቀና ይግባኝ የሌለው ውሣኔ ነው ኣባላት ሁለት ገጽ ፩ሺ፮፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፵፫ ዓ • ም • ፬ • በፍርድ ሊወሰን በማይችል በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ፣ አንድ ሦስተኛው ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ በፌዴራሉ ወይም በክልል ምክር ቤት አባላት ወይም በፌዴራሉም ሆነ በክልል አስፈጻሚ አካላት ለአጣሪ ጉባኤው ሊቀርብ ይችላል ። ፳፬ ስለ ጥያቄ አቀራረብ አንድ ሕግ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል የሚል ወይም የሕገ መንግሥት ትርጉም አስመልክቶ ለአጣሪ ጉባዔ የሚቀርብ ጥያቄ ዘርዘር ባለ ሁኔታ በጽሁፍ መቅረብ ይኖር ፳፭ : መልስ ስለመስጠት ለአጣሪ ጉባዔው የቀረበው ጥያቄ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ካለ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ሆኖ በአንደኛው ተከራካሪ ወገን የቀረበ እንደሆነ እንደአስፈላጊነቱ ሌላው ወገን ፣ አስተያየቱን እንዲሰጥ ወይም ማስረጃዎቹን እንዲያቀርብ ዕድል ሊሰጠው ይችላል ። ፳፮ ሕገ መንግሥታዊነትን ስለሚያስረዳ አካል የአንድ ሕግ ሕገ መንግሥታዊነት አከራካሪ ሆኖ ሲገኝ የማስረዳት ግዴታ የሚጣለው እንደነገሩ ሁኔታ የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥቱን በሕግ ጉዳዮች ላይ የማማከር ሥልጣንና ተግባር በተሰጠው የመንግሥት አካል ይሆናል ። ፳፯ የሞያ አስተያየት ስለማሰባሰብ አጣሪ ጉባዔው የሕገ መንግሥት ትርጉም ከመሰጠቱ በፊት አግባብነት አላቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ተቋማት ወይም ባለሙያዎች ቀርበው አስተያየት እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል ። ፳፰ ውይይት ፩ አጣሪ ጉባዔው በቀረቡለት ጉዳዮች ላይ እንደ አቀራረ ባቸው ቅደም ተከተል ውይይት ያደርግባቸዋል ። ፪ የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ( ፩ ) ቢኖርም አጣሪ ጉባዔው አጣዳፊ ነው ብሎ ላመነበት ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ ሊወያይ ይችላል ። ፳፱ • የአጣሪ ጉባዔው አሰራር አጣሪ ጉባዔው የያዘውን ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ ሊያይ ይችላል ። ፴ ስለ ውሣኔ አሰጣጥና የስብሰባ ሥነሥርዓት ፩ የአጣሪ ጉባዔው ምልዓተ ጉባኤ የሚኖረው ሶስተኛ የተገኙ እንደሆነ ነው ። ፪ አጣሪ ጉባኤው የቀረበለትን ጉዳይ በአግባቡ ከመረመረ በኋላ የሚሰጠው ውሣኔ በተባበረ ድምጽ ሊሆን ይችላል ። ፫ • በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተቃውሞ የሌለ እንደሆነ ጉዳዩ በአጣሪ ጉባዔው አባላት የተባበረ ድምፅ እንደተወሰነ ይቆጠራል ። ፬ • አጣሪ ጉባኤው በተባበረ ድምዕ መወሰን ያልቻለ እንደሆነ የውሳኔ ሀሳብ የሚሆነው በስብሰባው ከተገኙት አባላት በአብላጫ ድምፅ የተደገፈው ሀሳብ ነው ። የኣነስተኛ ድምፅ አስተያየቶች ወይም የማስማሚያ ሀሳቦች ከአጣሪ ጉባዔው ውሳኔ ጋር ይያያዛሉ፡ ፭ የተሰጠው ድምፅ በሁለቱም ወገን እኩል በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ይሆናል ። ፴፩ : የውሣኔው ይዘት የአጣሪ ጉባዔው ውሣኔ ወይም የውሣኔ ሃሣብ የቀረበውን ጉዳይ ዝርዝር መግለጫ ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈ ልጋል ወይም አያስፈልግም ያለበትን ምክንያትና የደረሰ በትን መደምደሚያ በግልጽ የሚያሳይ መሆን ይኖርበታል ። ፴፪ ጉዳዮችን በአጭር ጊዜ ስለመወሰን የአጣሪ ጉባዔው የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮ በአፋጣኝ ውሣኔ መስጠት ይኖርበታል ። ፴፫ ስለ ክፍያ ፩ ለሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ የሚቀርብ ሕገ መንግ ሥታዊ ጥያቄ ከክፍያ ነጻ ነው ። ገጽ ፩ሺ፮፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ፪ • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው ቢኖርም | 2. Notwithstanding the Provisions of sub - Article / 1 / of this እንደአስፈላጊነቱ አጣሪ ጉባዔው በሚመራበት ደንብ መሠረት አቤቱታ አቅራቢው ክፍያ እንዲፈፅም ሊደረግ ይችላል ። ክፍል ሶስት ስለ በጀት የአጣሪ ጉባዔው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) በመንግሥት የሚመደብ በጀት ለ ) ከሚያገኘው ስጦታና ዕርዳታ ሐ ) ከማንኛውም ሌላ ህጋዊ ምንጭ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ገቢ በአጣሪ ጉባዔው የባንክ ሂሣብ ተቀምጦ የአጣሪ ጉባዔውን ሥራዎች ለማከናወን ብቻ ወጭ ይሆናል ። አጣሪ ጉባዔው የበጀት አጠቃቀሙን የሚያሳይ ትክክለኛ የሂሣብ ሰነድ መያዝ ይኖርበታል ። ፬ • የጽሕፈት ቤቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፴፭ : የመተባበር ግዴታ ማንኛውም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን አጣሪ ጉባዔው የሥልጣን ክልሉ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚሰጠውን ትዕዛዝ የማስፈፀም ግዴታ አለበት ። ፴፮ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?