የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፲፮ አዲስ አበባ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፬ / ፲፱፻፶፬ ዓ.ም የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፯፻፯ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፱ / ፲፱፻፲፬ የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከልን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ አገሪቱ የምትከተለው ገጠሩን ማዕከል ያደረገ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሆኑ እና በዚህም ፖሊሲ መሠረት የገጠሩን ዘላቂ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የኢነርጂ ልማት | economic policy , and the development of energy plays a ወሳኝ በመሆኑ ፤ ለገጠሩ ተስማሚ የሆኑ የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎች | of the rural areas , ጥናትና ልማት ሥርዓት ባለውና በተቀናጀ ሁኔታ መካሄድ ያለበት በመሆኑ ፤ በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን ልማዳዊ | for the rural areas in a systematic and coordinated manner ; የኢነርጂ አጠቃቀም በዘመናዊ ዘዴ መተካት አስፈላጊ በመሆኑ ፤ እነዚህን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ ተገቢው ሥልጣንና | modern methods the traditional energy utilization system ተግባር ያለው አንድ ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ | which has caused negative impact on the environment ቤት ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ | of the Constitution of the Federal Democratic Republic of ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፱ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ ኢነርጂ ” ማለት ከባዮማስ ፣ ከውኃ ፣ ከጂኦተርማል ፣ ከፀሐይ ፣ ከነፋስ ፣ እንዲሁም ታዳሽ ካልሆኑ እንደ ነዳጅ ፣ ማዕድናት የመሳሰሉ ምንጮች እና ከሌሎች የተለያዩ ቁሳቁሶች የሚገኝና ለገጠሩ ኅብረተሰብ የሚያገለግል ኃይል ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፕሺ፩ ) ገጽ ፩ሺ፯፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ጥር ፳፫ ፲፱፻፲፬ ዓም ፪ . “ ሚኒስትር ” እና “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የገጠር ልማት ሚኒስትር እና ሚኒስቴር ነው ። ፫ . መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል | ከዚህ በኋላ “ ማዕከል ” እየተባለ የሚጠራ ራሱን የቻለና የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ • ማዕከሉ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊኖሩት ይችላል ። ፭ ዓላማ የማዕከሉ ዓላማ ለገጠሩ የሚያገለግሉ የኢነርጂ ምንጮች እና ቴክኖሎጂዎች የሚለሙበትንና የሚስፋፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይሆናል ። ፮ • የማዕከሉ ሥልጣንና ተግባር ማዕከሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ . ለገጠሩ ተስማሚ የሆኑ የኢነርጂ ምንጮችን መለየትእና ለልማት የሚረዳ ጥናት ማካሄድ ፣ ከውጭ ሀገር የሚገኙትን የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች ከአገሪቱ ፍላጎት ጋር በማጣጣም ማላመድ እና አገር በቀል የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግ ፣ ፫ የኢነርጂ ጥናት ሥራዎችን ማስተባበር ፣ ማበረታታት እና መደገፍ ፣ ፬ • የገጠሩን የኢነርጂ ፍላጎት ፣ አቅርቦት እና ፍጆታ ማጥናት እና በየጊዜው መረጃ ማጠናቀር ፣ ፭ የአካባቢ ጥበቃን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ፣ ተመጣ ጣኝ ዋጋና ብቃት ያላቸውን የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎ ጂዎች ልማት ፡ ሥርጭት ፣ አጠቃቀም ቁጠባ ማጥናት እንደነገሩ አግባብነት በግል ባለሀብቶች ፣ በመንግሥትእና በሌሎች ዘርፎች በኩል ለገጠሩ ኅብረተሰብ ማስተዋወቅ ፣ ፮ የተለያዩ የኢነርጂ ምንጮጮችና ቴክኖሎጂዎችን መጠ ቀም የሚያስከትለውን ማኅበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባ ቢያዊ ተጽዕኖ መገምገም ፣ ፯ በኢነርጂ ዘርፍ እንደአስፈላጊነቱ በክፍያ ወይም ያለክፍያ የማማከር አገልግሎት መስጠት ፣ ፰ የኢነርጂ ጥናትን በሚመለከት መረጃ መሰብሰብ ፣ በባለቤ ትነት መያዝ ፣ እንደአስፈላጊነቱ ዋጋ በማስከፈል ወይም ያለክፍያ ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ፡ እንዲሁም መጽሄ ቶችን ማዘጋጀትና ማሠራጨት ፣ ፀ • ከሥራው ጋር አግባብ ያለውን መረጃ ሁሉ ከማንኛውም ምንጭ መጠየቅና ማግኘት ፣ ፲ የኢነርጂ ልማት ፣ ሥርጭት ፣ አጠቃቀምና ቁጠባን በተመ ለከተ የገጠሩን ሕብረተሰብ ግንዛቤ ማዳበር ፣ ሥልጠና መሥጠትና እንዲሁም ከክልሎች ጋር መተባበር ፣ ፲፩ ከሥራው ጋር አግባብነት ባላቸው የኢነርጂ ጥናት እና ምርምርን በሚመለከቱ ማናቸውም ግንኙነቶች ከሌሎች ጋር በመተባበር መሳተፍ እንዲሁም ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ከአገር በቀል ፣ ከውጭ አገር እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር መተባበር ፣ ፲፪ • የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል ፣ መክሰስና መከሰስ ፤ እና ፲፫ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ሕጋዊ | 7 . Organization of the Center ተግባራትን ማከናወን ። ፯ የማዕከሉ ድርጅታዊ አቋም ማዕከሉ ፣ ፩ . በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ዲሬክተር ፣ እና ፪ • አስፈላጊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ቿ የዋናው ዲሬክተር ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ዲሬክተር የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከሚኒስትሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአዋጁ ኣፈ ga ም የሚረዳ ደንብ ገጽ ፩ሺ፯፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ፪ : ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ / ፩ / የተጠቀሰው ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ዲሬክተር ፣ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የማዕከሉን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረታዊ መርሆዎች ተከትሎ መንግሥት በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳ ድራል ፣ ያሰናብታል ፣ ሐ ) የማዕከሉን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ መ ) የማዕከሉን የሥራ ክንውንና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ ሠ ) ተጠሪነታቸው ዲሬክተር የሆኑትን የማዕከሉ ኃላፊዎች በመምረጥ ለሚኒስትሩ አቅርቦ ያሾማል ፣ ረ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ማዕከሉን ይወክላል ፣ ፫ ዋናውዲሬክተር ለማዕከሉየሥራቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለማዕከሉ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፱ . የበጀት ምንጭ የማዕከሉ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የሚገኝ ይሆናል ፣ ፩ በመንግሥት ከሚመደብለት ዓመታዊ በጀት ፣ ፪ • ማዕከሉ ከሚያስከፍለው የአገልግሎት ዋጋና ሌሎች ክፍያዎች ፣ ፫ : ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገንዘብ ። ፲ . የሂሣብ መዛግብት ፩፡ ማዕከሉ የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ • የማዕከሉ የሂሣብ መዛግብትእና ሌሎችገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም በዋናው ኦዲተር በሚሰየም ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፩ ደንብ ስለማውጣት ሊያወጣ ይችላል ። ፲፪ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም : ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ