×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 255/1994 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት መተዳደሪያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፩ [ አዲስ አበባ መስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ / ፲፱፻፲፬ ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት መተዳደሪያ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፮፻፳፮ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ / ፲፱፻፲፬ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት መተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ / ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት ምዕራፍ ሰባት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት የተመለከቱትን | implementation of the provisions of Chapter Seven of the ድንጋጌዎች ዝርዝር አፈጻጸም መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ የፌዴራሉን ፕሬዚዳንታዊ ተቋም ህገመንግሥታዊ አቋም | with regard to the President of the Republic ; ለማጠናከር እና የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሥራ ዘመኑ ካለቀ በኋላ ያገለገለበትን ዘመን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊጠበቁለት | strengthen the Constitutionality of the presidential institution የሚገባቸውን መብቶችና ጥቅሞች ማስከበር አስፈላጊ ሆኖ | and to respect the rights and benefits of the Ex - President of በመገኘቱ ፤ በህገመንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት መተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፭ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ ፩ “ ፕሬዚዳንት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ ህገመንግሥት አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የተሰየመ ሰው ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፮፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓ • ም • ፪ . “ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ተሰይሞ ሲያገለግል የቆየና በህመም ፣ በሞት ፣ የሥራ ዘመኑን በመጨረስ ፣ ወይም ማናቸውም ምክንያቶች የፕሬዚዳንትነት ሥራውን ያቋረጠ ነው ። ፫ “ የፕሬዚዳንት ጽ ቤት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ተቋምን ለማገ ልገል በአዋጅ ቁጥር ፩፻፴፩ ፲፱፻፲፩ የተቋቋመው ጽ / ቤት ክፍል ሁለት የፕሬዚዳንቱ ተቋም ፫ . ፕሬዚዳንቱ የሚመረጠው ለስድስት ዓመታት ሲሆን ፣ ይህ የሥራ ዘመን የሚያበቃው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴ ሬሽን ም ቤቶች ከተመረጡ በኋላ ባለው ሁለተኛ ዓመት በሚያደርጉት የመጀመሪያ የጋራ ስብሰባ ላይ ይሆናል ። ፬ ፕሬዚዳንቱ በሥራው ዘመን የሕዝብ ተወካዮች ም ቤት የሚያጸድቀው ወርሃዊ ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ይኖሩታል ። ለፕሬዚዳንቱ ጽ ቤት የሚያስፈልገው ማናቸውም ወጭ በፕሬዚዳንቱ ጽ / ቤት ተዘጋጅቶ በሕዝብ ተወካዮች ም ቤት በሚጸድቀው ዓመታዊ በጀት መሠረት ይፈጸማል ። ፮ ፕሬዚዳንቱ በአገሪቷ ከሚገኙት የፖለቲካ ኃይሎች ገለልተኛ ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ በህገመንግሥቱ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ፕሬዚዳንትነቱን የሚቀበል ዕጩ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ድርጅታዊ ግንኙነት የሌለው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ፯ ፕሬዚዳንቱ በሥራ ዘመኑም ሆነ የሥራ ዘመኑ ካበቃ በኋላ ወገንተኝነት ካላቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች የመገለል ኃላፊነት ይኖረዋል ። ፕሬዚዳንቱ የሥራ ዘመኑን ሳይጨርስ በህመም ፣ በሞት ወይም በግል ፈቃዱ ወይም በህጋዊ ውሳኔ በሚነሳበት ጊዜ በሕዝብ ተወካዮች ም / ቤት አፈጉባዔና በፌዴሬሽን ም / ቤት አፈጉባዔ ወይም በአፈጉባኤዎቹ በጋራ በሚጠራ ልዩ የጋራ ስብሰባ በሚወሰነው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሊተካው ይችላል ። ፬ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ መሠረት የሚሰየመው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፫ መሠረት ሁለቱ ም / ቤቶች በሚያደርጉት የጋራ ስብሰባ ለሚመረጠው ፕሬዚ ዳንት ኃላፊነቱን ያስረክባል ። ክፍል ሦስት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ተቋም ሕጋዊ አካል ነው ። ፲፩ . የቀድሞ ፕሬዚዳንት በሕይወቱ ዘመን ፕሬዚዳንታዊ ተቋሙ ለቆመላቸው ዓላማዎች ተገዥ ነው ። ፲፪ . የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከዚህ የሚከተሉት ኃላፊነቶችና | 12. ል- Ex - President shall have the following respon ግዴታዎች ይኖሩታል ፤ ሀ ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥቱን መደገፍና መከላከል ፤ ለ ) በፕሬዚዳንትነት ባገለገለበት የሥራ ዘመኑ ያገኛ ቸውን አገራዊ ጉዳዮችና መረጃዎች መጠበቅ ፤ ሐ ) የሪፐብሊኩን ፕሬዚዳንታዊ ተቋም ከሚያንቋሽሹ ሥነምግባራዊ ተግባራት መቆጠብ ፤ መ ) በግል የሚያካሂዳቸው ሥራዎችና እንቅስቃሴዎች በዚህ አዋጅ ከተቀመጡት መርሆዎችና ድንጋጌዎች የማይጻረሩ መሆኑን ማረጋገጥ ። ፲፫፡ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሚጠበቁለት መብቶች ፩ : የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከዚህ የሚከተሉት መብቶች | 13. Rights and Benefits of an Ex - President ይኖሩታል ፤ ሀ ) በመንግሥት ወጭ የሚተዳደር አንድ መደበኛ መኖሪያ ቤት ፣ ገጽ ፩ሺ፮፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ለ ) ለግል ወጭ የሚሆን በየወሩ ብር ፭ ሺህ ( አምስት ሺህ ብር ) የሚከፈለው ሲሆን ፣ ይህ ክፍያ በየጊዜው ከኑሮ ውድነት ጋር እየታየ በምክር ቤቱ የሚሻሻል ይሆናል ። ሐ ) በመንግሥት ወጭ የግል ደህንነቱን የሚጠብቁ ሠራተ ኞችና አገልግሎቶች ፣ መ ) ለራሱና ለቤተሰቡ ነፃ የህክምና አገልግሎቶች ፣ ሠ ) የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ ፣ ወርሀዊ ክፍያው ለባለቤቱና ለአቅመ ኣዳም ላልደረሱ ልጆቹ የማሳደጊያና የመተዳደሪያ ክፍያ ሆኖ ይቀጥላል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌዎች ቢኖሩም ፣ በሕግ የተወገደ የቀድሞ ፕሬዚዳንት በዚህ አንቀጽ የተዘረዘሩት መብቶች ኣይጠበቁለትም ። ክፍል አራት የቀድሞ ፕሬዚዳንትነት መብቶችን ስለማቋረጥ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፣ ሀ ) በዚህ ኣዋጅ አንቀጽ ፲፫ በተጠቀሱት መብቶች ተጠቃሚ ላለመሆን የመረጠ እንደሆነ ፤ ውሳኔውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጽሑፍ በማሳወቅ የመብቶቹ ተጠቃሚነቱን ሊያስቀር ይችላል ። ለ ) በዚህ አዋጅ መሠረት ግዴታዎቹን ሳይወጣ ከቀረ በአንቀጽ ፲፫ የተመለከቱት መብቶቹ ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ የጋራ ውሳኔ ወይም በአፈጉባኤዎቹ በሚጠራ ልዩ የጋራ ስብሰባ ውሳኔ ሊቋረጡ ይችላሉ ። ፲፭ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከመስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፬ ይሆናል ። ጀምሮ የፀና አዲስ አበባ መስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?