×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 66/92 የውጭ ሀገር ዜጐች በኢትዮጵያ ፊልም ስለሚያነ ሱበት ሁኔታ የወጣ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ መጋቢት ፲፱ ቀን ፲፱፻፵፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፮ ፲፬፻፲፪ ዓ.ም. የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ ፊልም ስለሚያነሱበት ሁኔታ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፩ሺ፪፻፳፬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፮ ፲፬፻፲፪ የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ፊልም ስለሚያነሱ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱የተ፯ አንቀጽ ፭ መሠረት የሚከተ ለውን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የውጭ ሀገር ዜጐች በኢትዮጵያ ፊልም ስለሚያነ ሱበት ሁኔታ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፰፮ ፲፱የን፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የማስታወቂያና ባሕል ሚኒስቴር ” ማለት በሴሉሎስ ወይም በማግኔቲክ ቴፕ የሚቀረጽ ተንቀሳቃሽ ሥዕል ነው፡ ፫ . “ ተራኪ ፊልም ” ማለት በልቦለድ ድርሰት ላይ ተመስርቶ ተዋንያንን በማሳተፍ የሚቀረጽ ፊልም ነው፡ ፬ . “ ዘጋቢ ፊልም ” ማለት ተፈጥሮን፡ ባህልን፡ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን እና የመሳሰ ሉትን ነገሮች በቴሌቪዥን፡ በሲኒማ፡ ወይም በሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ስክሪን ማስተላለፊያዎች ለማሰ ራጨት ዓላማ የሚቀረጸ ፊልም ነው፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪፻፳፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ መጋቢት ፲፱ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፭ . “ የፊልም ማንሳት ፈቃድ ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት በተወሰነ ጊዜና ቦታ ተራኪ ወይም ዘጋቢ ፊልም ለማንሳት ብቻ ለሚመጡ የውጭ ዜጎች በሚኒስቴሩ የሚሰጥ ፈቃድ ነው ። ፫ . የተፈጻሚነት ወሰን የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች፡ ፩ . ኢትዮጵያ ውስጥ የፊልም ተቋም እንዲያቋቁሙ ቋሚ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሰዎች በስተቀር ዓላማቸው ትርፍ የሆነ ወይም ያልሆነ ተራኪ ወይም ዘጋቢ ፊልም ለማንሳት በሚመጡ የውጭ ዜጎች ላይ፡ • በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች፡ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። የደንቡ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡ ፩ በውጭ ዜጎች የሚካሔደው የፊልም ማንሳት ሥራ የሀገሪቱን ታሪክ፡ ባህል፡ የተፈጥሮ ውበት፡ ሀብት፡ ፖለቲካዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ፡ ማህበራዊ ሁኔታ እና የመሳሰ ሉትን ለውጭው ዓለም በማስተዋወቅ ጉልህ ሚና የሚጫወት ስለሆነ ሥራው የሚመራበትን ሥርዓት ግልጽና ቀልጣፋ በማድረግ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፡ የሀገሪቱ ዜጎችና ድርጅቶች ከሚነሳው ፊልም ማግኘት የሚገባቸውን መብትና ጥቅም ማስከበር፡ የፊልም ማንሳቱ ሥራ የሀገሪቱን ሕጎች እና የሕዝቦቿን ባህል በማክበር እንዲካሔድ ማድረግ ። ፭ ፈቃድ ስለማስፈለጉ ኢትዮጵያ ውስጥ ተራኪ ወይም ዘጋቢ ፊልም ለማንሳት የሚፈልግ ማንኛውም የውጭ ዜጋ ከሚኒስቴሩ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ። ፊልም ለማንሳት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ . ኢትዮጵያ ውስጥ ፊልም ለማንሳት የሚፈልግ የውጭ ዜጋ ሥራው ከሚጀምርበት ከ፲ ቀን በፊት ማመልከ ቻውን ለሚኒስቴሩ በጽሑፍ ማቅረብ ይኖርበታል ። ፪ . ማመልከቻው በተለይም የፊልሙን ዓላማና ርዕስ፡ ፊልም ማንሳቱ የሚቆይበትን ጊዜ፡ ፊልም ማንሳቱ የሚካሔድበትን ትክክለኛ ሥፍራ እና ለፊልሙ ሥራ የሚውለውን ጠቅላላ ወጪእንዲሁም ከጠቅላላው ወጪ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ላይ የሚውለውን ገንዘብ መግለጽ ይኖርበታል ። ፫ አመልካቹ ከማመልከቻው ጋር፡ . ሀ ) ተራኪ ፊልም ከሆነ የፊልሙን ስክሪፕት አንድ ቅጂ ከነአጭር መግለጫው ወይም ዘጋቢ ፊልም ከሆነ አጭር መግለጫውን፡ ለ ) በፊልሙ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ገጸ ባህርይ የሚካተት ከሆነ ግለሰቡ ወይም ሕጋዊ ወራሾቹ የማይቃወሙ መሆኑን የሚያመለክት ውሎችንና ሰነዶችን ለማረ ጋገጥ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ሐ ) በኢትዮጵያዊና በውጭ ዜጋ በጋራ የሚሰራ ፊልም ሲሆን የእያንዳንዱን ወገን ግዴታና ኃላፊነት የሚያ መለክት በሁለቱ መካከል የተደረገ ስምምነት ፡ እና መ ) በፊልም ሥራውላይየሚሰማሩትን ሰዎች ዜግነት፡ የፓስፖርቱን ቁጥር ፡ ፓስፖርቱን የሰጠው አገር ፡ ቋሚና ጊዜያዊ አድራሻ : እንዲሁም ሌሎች በሚኒ ስቴሩ የሚጠየቁ መረጃዎችን፡ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል ። ፯ ፈቃድ ስለመስጠት ሚኒስቴሩ በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፮ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው መቅረባቸውንና በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፪ ውስጥ የተወሰነው የፈቃድ ክፍያ መፈጸሙን በማረጋገጥ ማመልከቻው በቀረበለት በ፫ ቀናት ውስጥ ለአመልካቹ ፈቃድ ይሰጣል ። ገጽ ፩ሺ፪፻፳፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ መጋቢት ፲፬ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta - በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሰረት በተሰጠ ፈቃድ ላይ ከተገለጹ ቦታዎች መካከል ፊልም ለማንሳት የተከ ለከሉ ቦታዎች ካሉ ለመከልከል ሥልጣን ያለው አካል መብት የተጠበቀ ነው ። ስለ በረራ ፈቃድ ፩ አመልካቹ ለፊልም ማንሳቱ ሥራ አይሮፕላን መጠቀም | 8. Flight Pemit ከፈለገ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የበረራ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ። ፪ አመልካቹ ከፈለገ የበረራ ፈቃድ ማመልከቻውን በሚኒ ስቴሩ አማካኝነት ሊያቀርብ ይችላል ፡ ለፊልሙ ሥራ አይሮፕላን ለመጠቀም የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ሆኖ ከተገኘ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንማመልከቻ በቀረበለት በ፲ ቀናት ውስጥ የበረራ ፈቃድ መስጠት አለበት ፡ ጥያቄው ተቀባይነት የሌለው ከሆነም ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ለአመልካቹ ወይም ለሚኒስቴሩ በጽሑፍ ያስታውቃል ። ፬ • የአመልካቹ ግዴታ አመልካቹ ከዚህ በታች የተመለከቱት ግዴታዎች ይኖሩታል ፣ ፩ የተሰራውን ፊልም ሁለት የቪ - ኤችኤስ ቪዲዮ ካሴት | 9. Obligations of the applicant የእንግሊዝኛ ቅጂ ለሚኒስቴሩ የማስረከብ ፡ ፪ • በግንባር በመቅረብ በፈቃድ ግዴታው መሠረት ለመሥ ራትና የአገሪቱን ሕግ ለማክበር ግዴታ የመግባት ። ፲ ፈቃድን ስለመሰረዝ በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፱ ፪ በተመለከተው መሠረት ባለፈቃዱ የገባውን ግዴታ ያላከበረ እንደሆነ ሚኒስቴሩ ፈቃዱን ሊሰርዝበት ይችላል ። የቀረጥ ነፃ መብት ፩ . , አመልካቹ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት ይዟቸው የሚመጣውን ለፊልሙ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ መሣሪያዎችን ዝርዝር ለሚኒስቴሩማቅረብ አለበት ። ፪ • አመልካቹ በዝርዝሩ የተመለከቱትን እቃዎች ከአገር እንደሚያስወጣ ግዴታ ሲገባም እነዚህ መሣሪያዎች የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው እንዲገቡ ይደረጋል ። ፲፪ ስለ ፈቃድ ክፍያ ፩ ኢትዮጵያ ውስጥ ፊልም ለማንሳት የሚፈልግ የውጭ ዜጋ ከዚህ የተመለከተውን የፈቃድ ክፍያ ለሚኒስቴሩ ይከፍላል ፡ ሀ ) ለፊልሙ ሥራ ከሚወጣው ወጪ ለመጀመሪያብር ፩፻ሺ አንድ መቶ ሺህ ብር ፡ ብር ፩ሺ ኣንድ ሺህ ብር ፡ እና ለ ) ከብር ፩፻ሺ አንድ መቶ ሺህ ብር በላይ ለሆነው ለተጨማሪው የፊልም ወጪ ደግሞ ተጨማሪ 0 ፪ በመቶ ( ዜሮ ነጥብ ሁለትፐርሰንት ) የፊልም ማንሳቱ ሥራ የሚካሄደው ፊልም ለማንሳት ክፍያ በሚያስከፍል ቦታ የሆነ እንደሆነ በሚመለከተው አካል የሚጠየቀውን ክፍያ መክፈል ይኖርበታል ። መመሪያ ለማውጣት ሚኒስቴሩ ፡ የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ መመሪያዎችን ለማውጣት ይችላል ። ውክልና ስለመስጠት ሚኒስቴሩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ማናቸውም የፊልም ማንሳት ፈቃድ የተሰጠባቸው ግዴታዎች መጠበቃቸውን ለማረ ጋገጥ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንዲችሉ ውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ገጽ ፩ሺ፪፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ መጋቢት ፲፱ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : Federal Negarit Gazeta – ፲፭ ቅጣት የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች ተላልፎ የተገኘ ሰው አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌ መሠረት ይቀጣል ። ፲፮ : ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፲፱ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?