×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤትደንብ ቁጥር 41/1991 የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲ ትዩት ማቋቋሚያ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፩ አዲስ አበባ መስከረም ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፩ / ፲፱፻፲፩ ዓ.ም የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፰፻፵፰ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፵፩ / ፲፱፻፲፩ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፩ ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። ፫ መቋቋም የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” ተብሎ የሚጠራ / የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዥሺ፩ ኢሎች ተግባ ገጽ ፰፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፳፪ ቀን ፲፱፻፷፩ ዓም • ፪ • የኢንስቲትዩቱ ተጠሪነት ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ፬ • የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ይሆናል ፡ እንደአስፈላጊነቱም በሌሎች ቦታዎች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ማቋቋም ይችላል ። ፭ የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የኢንስቲትዩቱ ዓላማ ስለተለያዩ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች አሠራር፡ከቆዳና ከቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ ጋር ስለተገናኙጥሬ ዕቃዎች : ኬሚካልና መካኒካል አሠራሮች እና ስለጥራት ቁጥጥር ዘዴዎች የተግባርና የፅንሰ - ሀሣብ ሥልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም በመስኩ የምርምርና የምክር አገል ግሎት ሥራዎች በማካሄድ ለዘርፉ የሠለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ይሆናል ። ፮ . የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር ለሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕግ ተለይተው የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች እንደተጠበቁ ሆነው ኢንስቲ ትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . በተለያዩ ደረጃዎች የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ሥልጠናዎችን በመስጠት በዘርፉ የሙያተኞችን ብዛት ማሳደግ ፡ ፪ • የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን ጥራትና ብዛት ለማሳደግ የሚያስችሉ የምርምርና ልማት ተግባራትን ማከናወን ፤ ፫ የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን የጥራት ደረጃ ለማሳደግ የሚያ ስችሉ የምክር አገልግሎቶችን መስጠት ፡ ፬ የዘርፉን ልማት ለማሳደግ የሚያስችሉ የመረጃ አገልግሎ ቶችን መስጠት ፡ ፭፡ ለሚያሰለጥናቸው ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት መስጠት ፡ ፮ : ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ክፍያ ማስከፈል ፤ ፯ የንብረት ባለቤት መሆን ፡ ውል መዋዋል ፣ በራሱ ስም መክሰስ እና መከሰስ ፡ ፰ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ራትን ማከናወን ። ፯ . የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ፡ የሥራ አመራር ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፡ ፪ • በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ዲሬክተር ፡ ፫ አካዳሚክ ካውንስል ፡ እና ፬ አስፈላጊ ሠራተኞች ፡ ይኖሩታል ። ፰ : የቦርዱ አባላት ቦርዱ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ በመንግሥት የሚሰየሙ ሰባት ኣባላት ይኖሩታል ፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ከአባላቱ መካከል በመንግሥት ይመደባል ። ገጽ ፰፻፶ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፱ • የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች በበላይነት የመቆጣጠር ፣ የመከታተል እና ኢንስቲትዩቱ በዓላማው መሠረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረጉን የማረጋገጥ ፤ ፪ • የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ መርሆዎች በመከተል የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚተዳደሩበትን መመሪያዎች የማፅደቅ ፡ የሠራተ ኞችን የደመወዝ ስኬልና ሌሎች የማነቃቂያ ክፍያዎችን የመወሰን ፣ ተግባራዊነታቸውንም የመከታተል ! ፫ ለዲሬክተሩ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ ኃላፊዎችን ቅጥር ፣ ምደባና ስንብት የማፅደቅ ፣ ፬ • ኢንስቲትዩቱ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍ ለውን የክፍያ ተመኖች የመወሰን ፤ ፭ ኢንስቲትዩቱ ከአገር ውስጥ ወይም ከውጭ አገር ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን ስምምነቶች የማፅደቅ ፤ ፮ የኢንስቲትዩቱን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ለሚኒስቴሩ የማቅረብ ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን የመቆጣጠር ፤ ፯ ይህንን ደንብ መሠረት በማድረግ የሚዘጋጁ የኢንስቲት ዩቱን የውስጥ ደንቦች የማፅደቅ ፣ ተግባራዊነታቸውንም የመከታተል ፤ ፰ በኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር በሚቀርቡ ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የመምከር ፣ የመወሰን ፣ ፬ ለኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር አጠቃላይ የሥራ መመሪያ የመስጠት ፣ ፲ የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በየሩብ ፲ የቦርዱ ስብሰባ ፩ : ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ ስብሰባ ይኖረዋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ። በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ውሳኔ የሚሰጠው በድምፅ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምፅ እኩል ለእኩል የተከፈለ ከሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ። የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዲሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢን ስቲትዩቱን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዲሬክተሩ፡ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የኢንስቲት ዩቱን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የኢንስቲትዩቱን የሠራተኞች አስተዳደር መመሪያ ፣ የደመወዝ ስኬልና ሌሎች የማነቃቂያ ክፍያዎች አጥንቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፡ ገጽ ፰፻፶፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. ሐ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል : ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፡ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ኢንስቲትዩቱን ይወክላል ፤ ረ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈፃፀምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፫ ዲሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስ ፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኢንስቲ ትዩቱ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪ . ስለአካዳሚክ ካውንስል አባላት የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ካውንስል የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡ ፩ . የኢንስቲትዩቱ ዳሬክተር ፪ . ሬጅስትራር . ፫ የተማሪዎች ተወካይ የመምህራን ተወካይ ፭ . ከኢንስቲትዩቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች በቦርዱ የሚሰየሙ ተወካዮች ፲፫፡ የአካዳሚክ ካውንስሉ ሥልጣንና ተግባር የአካዳሚክ ካውንስሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተገባሮች ይኖሩታል፡ ፩ . የኢንስቲትዩቱን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራምና ካሌንደር መርምሮ ለቦርዱ የማቅረብ ፡ ፪ • ዲፕሎማ ፡ ሠርቲፊኬትና ልዩ ሽልማት የሚሰጥበትን ሁኔታ እያጠና ለቦርዱ የማቅረብ ፡ ፫ . የተማሪዎችና ሠልጣኞች አቀባበልን ፡ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን : ምዘናን፡ የዲሲፕሊንና የምረቃ ጉዳዮችን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን አዘጋጅቶ ለቦርዱ የማቅረብ ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ የማድረግ ፡ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎ ችንና ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ፡ ፬ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ዘዴና ሁኔታን የመወሰን ፡ ፭ . ስለአካዳሚክ እድገቶች ጉዳይ አጥንቶ የማቅረብ፡ ወደሚቀጥለው የትምህርት እርከን የሚሸጋገሩ ተማሪ ዎችን ዝርዝር መርምሮ የመወሰን ፡ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ የመወሰን ፡ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች የማከናወን ። ፲ 0 በጀት የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፡ ፩ በፌዴራል መንግሥት ከሚመደብለት የገንዘብ ድጎማ ፡ ፪ ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ፡ እና ፫ • ከዕርዳታ፡ ከስጦታ እና ከማናቸውም ሌሎች ምንጮች ከሚያገኘው ገቢ ። የሂሣብ መዛግብት ፩ . ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ገጽ ፰፻፶፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ • ም • ፪ የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መስከረም ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም • መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?