የሰበር ችሎት መቁ . 2 ዐ 772
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሠ
2. ›› ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. ›› ተገኔ ጌታነህ
4. ›› መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካቾች፡- 1. አቶ ኃ / ገብርኤል አያሌው
2. ወ / ት ምስራቅ ወ / ማርያም
ተጠሪዎች : - 1. ወ / ሮ የውብድንበር ሀ / ማርያም
2. ወ / ሮ አምሣለ ደምሴ
3. ዲያቆን ኤልሣዕ ደምሴ
የአሁኑ ተጠሪዎች አመልካቾችን ጨምሮ በሶስት ተከሣሾች ላይ ባቀረቡት ክስ አውራሻቸው አጋፋሪ ደምሴ ገ / ሥላሴ በወረዳ 15 ቀበሌ 27 ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቁጥር 459 የሆነውን ቤት ወ / ሮ የሹምነሽ ማንተጋፍቶት በህይወት እስካሉ ድረስ እንዲኖሩበትና ለተጠሪዎች እንዲመለስ በመስማማት ፈቅደውላቸው የነበረ ሲሆን ወ / ሮ የሹምነሽ ሲሞቱ ግን አመልካቾች ቤቱን ይዘው ለማስረከብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዲያስረክቡ እንዲወሠንላቸው ጠይቀዋል ፡፡
ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት ሟች አጋፊሪ ደምሴ ባደረጉት ስጦታ ከፍ ሲል ቁጥሩና አድራሻው የተጠቀሠውን ቤት ወ / ሮ የሹምነሽ እንዲገለገሉበት ብቻ የሠጧቸው በመሆኑ ወ / ሮ የሹምነሽ ሲሞቱ የነበራቸው በቤቱ የመጠቀም መብት ስለሚቋረጥ ወራሽነታቸው በቤቱ ላይ መብት አይኖራቸውም በማለት አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪዎች እንዲያስረክቡ ወስኗል ፡፡
ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት ደግሞ በማይንቀሣቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የስጦታ ውል በግልፅ በሚደረግ የኑዛዜ አሠራር አይነት መቅረብ ያለበት በመሆኑና የቀረበው የስጦታ ውል ግን በግልፅ የሚደረግ የኑዛዜ አሠራር ( ፎርማሊቲ )
ትካል ኅ ?
የፃፉትን ሠነድ መሠረት አድርገው ነው ፡፡ ይህም ሠነድ ክርክር የተነሣበትን ቤት ወ / ሮ የማያሟላ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም ፡፡ ተጠሪዎችም ይህንን የሥጦታ ውል
መሠረት አድርገው አመልካቾች ቤቱን እንዲመልሱላቸው ሊጠይቁ አይችሉም በማለት የሥር ፍ / ቤት ውሣኔን ሽሮታል ፡፡
የፌ / ጠቅላይ ፍ / ቤት ደግሞ በአስረጅነት የቀረበው ሠነድ በየትኛውም መልኩ የሥጦታ ውል የሚል ትርጉም ሊሠጠው የማይችል ነው ፡፡ ውሉ ለወ / ሮ የሹምነሽ በቤቱ የመጠቀም መብት ብቻ የሚሠጥ ነው ፡፡ እሳቸው ከሞቱ በኋላ ቤቱን የመጠቀም መብት በፈቀዱት ለደምሴ ገ / ሥላሴ ተወላጆች ተመላሽ ይሆናል ፡፡ እንዲህ አይነቱ በንብረት የመጠቀም መብት መፈቀድ ደግሞ በህጉ የተለየ የውል ፎርም አይጠይቅም በማለት የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤትን ውሣኔ በመሻር የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤትን ውሣኔ አፅንቷል ፡፡
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው ይህ ችሎትም በአስረጂነት የቀረበው ሠነድ የሥጦታ ውል ስላልሆነ የተለየ ፎርም አያስፈልገውም በሚል የተሠጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር እንዲቀርብ በማድረግ የግራ ቀኙ የፁሁፍ ክርክር ተቀብሏል ፡፡ አቤቱታ የቀረበበትን አግባብነት ካለው ህግ ጋር አገናዝቦ መርምሯል ፡፡
እንደተገለፀው ተጠሪዎች የተነሣበትን አመልካቾች እንዲያስረክባቸው የጠየቁት አውራሻቸው አጋፊሪ ደምሴ ገ / ስላሴ ነሐሴ 17/1957
የሹመነሽ ማንተጋፋቶት በህይወት እስካሉ እንዲጠቀሙበት መብት የሚሠጣቸው መሆኑን ከክርክሩ ተረድተናል ፡፡ በመሆኑም ይህ ሠነድ በህጉ መሠረት የስጦታ ውል ነው ሊባል ይችላል ወይስ አይችልም ? የስጦታ ውል ነው ከተባለስ ህጉ የሚጠየቀውን
የአፀፃፍ ፎርም ተከትሏል ? አልተከተለም ? የሚለውን ችሎቱ እንደሚከተለው መርምሯል ፡፡
የፌ / ጠቅላይ ፍ / ቤት ሠነዱ የስጦታ ውል አይደለም በማለት የወሠነ ሲሆን ለዚህም ምክንያት ያደረገው በውሉ ለወ / ሮ የሹምነሽ የተላለፈው የባለቤትነት መብት ሣይሆን በቤቱ የመጠቀም መብት ብቻ መሆኑን ነው ። ስለሆነም በአንድ ንብረት የመገልገል መብት ብቻ በስጦታ ሊተላለፍ መቻል አለመቻሉን ስጦታን በተመለከተ በፍ / ህጉ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መመልከቱ ተገቢ ነው ፡፡ በፍ / ህ / ቁ 2461 ሥር ተቀባዩ የተሠጡትን ንብረቶች ጠብቆ አቆይቶ እሱ ሲሞት ወይም አንድ የተወሠነ ጊዜ
ሥርዐት ተከትላል . …
( መሠረት አድርገው ቤቱ እንዲመለስላቸው ሊጠይቁ ሲያልፍ ወይም አንድ ሁኔታ ሲፈፀም በስጦታ የተቀበላቸውን ንብርቶች ለሚተኩ ሠዎች ማስተላለፍ አለበት የሚል ቃል በስጦታ ውሉ ውስጥ ሊካተት እንደሚችል ተመልክቷል ፡፡ በመሆኑም በዚህ ድንጋጌ መሠረት ስጦታ አድራጊው የባለቤትነት መብትን ብቻ ሣይሆን በንብረቱ የመጠቀም መብትን ብቻ ሊያስተላልፍ መቻሉን እንረዳለን ፡፡ ከዚህ የህጉ ድንጋጌ አኳያም ሲታይ በውሉ የተላለፈው የመጠቀም መብት ብቻ በመሆኑ ሠነዱ የስጦታ ውል አይደለም በማለት ፍ / ቤቱ የደረሠበት መደምደሚያ የተሣሣተ ነው ፡፡
በማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም በማይንቀሣቀስ ንብረት ላይ መብት የሚሠጥ ስጦታ ደግሞ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ አሠራር አይነት ካልተደረገ ፈራሽ እንደሚሆን በፍ / ህ / ቁ 2443 ሥር ተመልክቷል ፡፡ ስለሆነም የማይንቀሣቀስ ንብረትን የሚመለከት የስጦታ ውል ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በስጦታ አድራጊውና በአራት ምስክሮች ፊት ተነቦ ስጦታ አድራጊውና ምስክሮቹ ፈርመውበት የሚዘጋጅ ሠነድ መሆን ይገባዋል ( የፍ / ህ / ቁ 881 ) በተያዘው ጉዳይ ግን በአስረጅነት የቀረበው ሠነድ ይህንን ሥርዐት ያልተከተለ ለመሆኑ በፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት የተረጋገጠ ሲሆን ተጠሪዎችም ሠነዱ ይህንን
በማለት ያቀረቡት ክርክር የለም ፡፡ በመሆኑም ሠነዱ በፍ / ህ / ቁ 2443 መሠረት ፈራሽ ስለሚሆን ህጋዊ ውጤት አይኖረውም ፡፡ ተጠሪዎችም በህግ ፊት ተቀባይነት የሌለውን ሠነድ አይችሉም ፡፡ በመሆኑም በዚህ ሠነድ መሠረት አመልካቾች ቤቱን እንዲመልሱ የተሠጠው ውሣኔ ከፍ ሲል በተዘረዘሩት የህግ ምክንያቶች ሥህተት ያለበት ነው ።
1 ) የፌ / ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ 1876 ዐ በ 16 / 10 / 97 እና የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት
በመ / ቁ 19195 በ 25 / 11 / 95 የሠጡት ውሣኔ ተሽሯል ፡፡ 2 ) የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 23807 በ 11 / 04 / 97 የሠጠው ውሣኔ ፀንቷል ፡፡ 3 ) ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ። ይምለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.