የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፯ አዲስ አበባ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፱ ፲፱የጤ፰ ዓም | የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶና ልማት ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር ፲፬ ፲፱፻፳፰ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶና ልማት ፈንድ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የገጠሩ ድሀ ሕብረተሰብ መሠረታዊ የሆኑ ማኅበራዊ አገልግ ሎቶች የማግኘት በሩ እንዲከፈትለትና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶች ተዘርግተውለት ገቢውን ማሳደግ እንዲችል መርዳት አስፈላጊ በመሆኑ ፤ _ ይህ ዓላማ ግብ እንዲመታ በሙከራ መልክ ተቋቁሞ የነበ | infrastructure and services ; ረውን የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶ ፈንድ ወደ አገር አቀፍ ፕሮግራም ደረጃ ማስፋፋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ ይህን ፕሮግራም በሥራ ላይ ለማዋልና ፕሮጀክቶችን በማመ ንት ፣ በመቅረጽና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከታች ወደ ላይ የአሰራር ሥልትን በመከተል ለመስራት የሚችል የማኔጅመንት አካል መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶና ልማት ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፱ ፲፱፻T፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ | 1 . Short Title ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ . ቁ : ዥሺ፩ ገጽ ፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም ፪• ስለ መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶና ልማት ፈንድ ( ከዚህ በኋላ | 1 ) There is hereby established the Ethiopian Social “ ፈንዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ፥ ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ፪ የፈንዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፫• የፈንዱ ዓላማዎች የፈንዱ ዓላማዎች የሚከተሉት ይሆናሉ ፡ ፩ መሠረታዊ የሆኑ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማቅረብና | በማጠናከር በዋነኛነት የገጠሩን ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ፣ ፪• የኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶችንና አገልግሎቶችን በመዘር ጋትና በማቅረብ የድሃውን ሕብረተሰብ ገቢ የማግኘት አቅም ማሳደግ ፣ ፫ . ማኅበረሰብን መሠረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችን የመለየት ፡ የማዘጋጀትና የመተግበር ፡ የማስተዳደርና የመንከባከብ ዘይቤን በሕብረተሰቡ ውስጥ ማራመድ ፡ ፬• ቀጣይነት ያለው አነስተኛ ብድር ለድሃው ሕብረተሰብ መስጠት የሚችሉ አነስተኛ ብድር ሰጪ ድርጅቶች እንዲፈጠሩና እንዲዳብሩ መርዳት ፡ ፭ ሕብረተሰቡን አግዘው የሚሰሩ መሠረታዊ ድርጅቶችንና ማኅበረሰቦችን በፕሮጀክት ሥራዎች ቴክኒካዊና የሥራ አመራር ብቃት እንዲያዳብሩ መርዳት ። ፬• የፈንዱ ሥልጣንና ተግባር ፈንዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ መሠረታዊ የሆኑ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለማቋቋምና | ለማጠናከር እርዳታ መስጠት ፡ ፪• በአካባቢ ደረጃ በሚከናወኑ ንዑስ ፕሮጀክቶች አማካይነት የሥራ ዕድል መፍጠርና በሙከራ ደረጃ በሚከናወነው የአነስተኛ ብድር አገልግሎት አማካይነት ድሃው የገጠር ሕዝብ ቀጣይነት ባለው የገቢ ማግኛ ሥራ ላይ እንዲሰማራ መርዳት ፡ ፫ የሥልጠናፕሮግራሞችለሕብረተሰቡ በማዘጋጀት መሠረታዊ የሕብረተሰብ ድርጅቶችንና ሕብረተሰቡን በማንኛውም የፕሮጀክት ሥራ ላይ ለመሳተፍ ያለውን አቅምማጎልበት ፣ ፬ . ሴቶች በማንኛውም የፕሮጀክት ሥራ እንቅስቃሴ እንዲ ሳተፉማበረታታት ፡ ፭ የንብረት ባለቤት መሆን ፡ ፮ . ውል መዋዋል ፡ – በስሙ መክሰስና መከሰስ ፡ ፰ ዓላማውን ከግቡ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባ ሮችን ማከናወን ። ፭ የፈንዱ አደረጃጀት ፩ . በማዕከላዊ ደረጃ ፡ ሀ ) የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶና ልማት ፈንድ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፡ ለ ) ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ፡ ሐ ) የፈንዱዋናሥራአስኪያጅ ፡ ምክትል ዋና ሥራአስኪያጅ እና አስፈላጊው የሰው ኃይል ይኖሩታል ። ገጽ ፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ፪ በእያንዳንዱ ክልል ! ሀ ) የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ ' ለ ) የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ' ሐ ) የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ' እንደ አስፈላጊነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና አስፈ ላጊው የሰው ኃይል ይኖሩታል ። ክፍል ሁለት የፈንዱ ማዕከላዊ አካላት ፮• የቦርዱ አባላት ቦርዱ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፣ ፩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ተወካዩ . . . . . . . . ፪• በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የክልል ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ . . . . . . . . . . . . . . . . ፫ የገንዘብ ሚኒስትር . . . . . . . . . ፬• የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስትር . . . ፭ . የውሀ ሀብት ሚኒስትር ፮ የግብርና ሚኒስትር . . . ፯ የፈንዱ ዋና ሥራ አስኪያጅ . . . . . . . . . . . . . . . . አባልና ፀሐፊ ፯ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ፩ ቦርዱ የፈንዱን አጠቃላይ አስተዳደርና የሥራ ክንውን | 7 . ይመራል ፡ ይቆጣጠራል ። ፪ ከላይ የተጠቀሰው አጠቃላይ ሁኔታ ሳይወሰን ፡ ቦርዱ ፣ ሀ ) ፖሊሲዎች ፣ የአፈጻጸም መመሪያና በመመሪያው ላይ | የሚደረጉ ማሻሻያዎችን ጭምር ያወጣል ፡ ለ ) ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም ያጸድቃል ፡ ሐ ) ዓመታዊ የሂሣብ ሪፖርት ያጸድቃል ፡ መ ) የሠራተኞችን የደመወዝ ስኬል ይወስናል ፡ ሠ ) የፈንዱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተቀላጠፈና በሰከነ ሁኔታ ሊፈጸም ይችል ዘንድ የክልል መስተዳድሮ ችንና የልዩ ልዩ የፌዴራሉ መንግሥት ተቋማትን ትብብር ያስገኛል ፡ ረ ) ፈንዱን በሚመለከቱ ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ። ፰ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ። ሆኖም | 8 . Meetings of the Board በሰብሳቢው ጥሪ የቦርዱ አስቸኳይ ስብሰባዎች በማን ኛውም ጊዜ ሊደረጉ ይችላሉ ። ፪ ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ላይ ሲገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይኖራል ። ፫• የቦርዱ ውሳኔ በስብሰባው ላይ በተገኙ አባላት በድምፅ ብልጫ ይሰጣል ። ድምዕ እኩል ለእኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ድምዕ ይኖረዋል ። [ ፬ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፬ . የማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ሥልጣንና ተግባር የፈንዱ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ የፈንዱ እንቅስቃሴዎች በመላው አገሪቱ እንዲታወቁ ማድረግ ፡ ፪• በፕሮጀክቶች ዝግጅት : ማስተዋወቅ ፡ ግምገማ ፡ | አፈጻጸም ፡ ቁጥጥርና ክትትል ረገድ ብቃታቸውን ከፍ እንዲያደርጉ የክልል ጽሕፈት ቤቶችን መርዳት ፣ ፫ የፈንዱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ | በማጠናቀር ለቦርዱ ማቅረብ ፡ ገጽ የ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ የካቲት ፭ ቀን ፲፱የተ፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 7 - 13 February 1996 – Page 109 0 የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤቶችን የበጀትና የሥራ ፕሮግራም አፈጻጸም እንዲሁም የፋይናንስ እንቅስቃሴ መከታተልና በፈንዱ የሥራ መመሪያ መሠረት መከናወናቸውን ማረጋገጥ ፣ ፭ ለማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት በጸደቀው በጀት መሠረት ክፍያዎችን መፈጸም : ፮ . ከክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤቶች የሚቀርቡ የመተኪያ ክፍያ ጥያቄዎችን ገምግሞ ለፋይናንስ አቅራቢ ምንጮች ማስተ ላለፍ ፡ ጊ ከውጭ አገር የሚያስፈልጉ ግዥዎችን ማከናወንና ክፍያ _ ዎችን መፈጸም ፣ ፲ - የፈንዱን የሥራ ፡ የፋይናንስ እንቅስቃሴና ወጪዎችን በተመለከተ የሩብ ዓመት ፡ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ሀ - አጠቃላይ የፈንዱን አቅም ግንባታ ፡ ሥልጠናና ምርምር መርሐ ግብሮችን ማስተዳደር ፡ 1 . ፈንዱን የሚመለከቱ የፖሊሲ ሃሳቦችን ለቦርዱ ማቅረብ ፡ 16 - የፈንዱን እንቅስቃሴዎች አፈጻጸም በበላይነት መከታተል ። 1 - የፈንዱ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፩ የፈንዱ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በቦርዱ ይሾማሉ ። ፪ . የቦርዱ አጠቃላይ ኣመራር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዋናውሥራ አስኪያጅ የፈንዱ እንቅስቃሴዎች በፈንዱ የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት በአግባቡ ተግባራዊ ለመሆናቸው ኃላፊ ይሆናል ። - ከላይ የተጠቀሰው አጠቃላይ ሁኔታ ሳይወሰን ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ለማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ይፈጽማል ፡ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የፈንዱን ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳ ደራል ፡ ሐ ) ለማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያዎችን ይፈጸማል ፡ መ ) በማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት ደረጃ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ፈንዱን ይወክላል ፡ ሠ ) የፈንዱን እንቅስቃሴዎች በብቃት ለማከናወን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሥልጣኑን ለማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፬ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ በሌለበት ጊዜ ፡ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ የተሰጠውን ተግባር ሁሉ ያከናውናል ። ክፍል ሦስት የፈንዱ የክልል አካላት ፲፩ የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ ኣባላት እያንዳንዱ የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል : ፩ የክልል ምክር ቤት ሰብሳቢ ወይም ተወካዩ ፪ : የማኅበራዊ ልማት ዘርፍ ኃላፊ . . . . . . . . . . . . . . . ኣባል • የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ኃላፊ 0 የፕላንና የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ . . . . ፭ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ፮ . የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፍ ተወካይ . . . . . ፯ የሲቪክ ድርጅቶች ተወካዮች ፰ የክልሉ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ . . አባልና ፀሐፊ ገጽ ያ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፮ የካቲት ፩ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 7 13 February 1996 – Page 110 ፲፪ የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር እያንዳንዱ የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ በክልሉ ውስጥ የሚካሄደው የፈንዱ እንቅስቃሴ በዚህ አዋጅ ፡ በፈንዱ የሥራ አፈጻጸም መመሪያና በቦርዱ ውሳኔዎች መሠረት መከናወኑን ያረጋግጣል ፡ ፪• የክልለ ፈንድ ጽሕፈት ቤት አዘጋጅቶ የሚያቀርበውን የክልለን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት በማጽደቅ በፈንዱ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት አማካይነት ለመጨረሻ ውሳኔ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ • የክልሉን ጽሕፈት ቤት የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸምና የፋይናንስ ሪፖርቶች ያጸድቃል ፡ ፬ ከክልሉ ፈንድ ጽሕፈት ቤት በሚቀርቡት ፕሮጀክቶች ፡ እቅዶችና በሌሎች ከፈንዱ የክልል የሥራ ፕሮግራም አፈጻጸም ጋር በተዛመዱ ነጥቦች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ። ፲፫ የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ፩ የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ። ሆኖም የኮሚቴው አስቸኳይ ስብሰባዎች | በሰብሳቢው ጥሪ በማንኛውም ጊዜ ሊደረጉ ይችላሉ ። ፪• ከኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ላይ ሲገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይኖራል ። ፫ የኮሚቴው ውሳኔ በስብሰባው ላይ በተገኙ አባላት በድምፅ ብልጫ ይሰጣል ። ድምዕ እኩል ለእኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ። ፬ ኮሚቴው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፬ የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሥልጣንና ተግባር እያንዳንዱ የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ የፈንዱ እንቅስቃሴዎች በክልሉ ውስጥ እንዲሰራጩ ማድረግ ፡ ፪ የክልሉን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለክልል አስተባባሪ ኮሚቴው ማቅረብና በኮሚቴው ሲጸድቅ ለማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት ማቅረብ ፡ ፫• በአመልካቾች የሚቀርቡ ንዑስ ፕሮጀክቶችን መገም ገምና ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ለክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ማቅረብ ፡ ፬• ፕሮጀክቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትንና አስፈላጊው የአፈ ጻጸም ክትትልና ርክክብ የሚደረግበትን መንገድ ሁሉ ማዘጋጀት ፡ ፭ ለፕሮጀክቶች የተመደበውን ገንዘብ በአግባቡ በሥራ ላይ ማዋል ፡ ፮ . የግማሽ ዓመት የፋይናንስ እና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያዘጋጀ ለክልሉ ኣስተባባሪ ኮሚቴማቅረብናኮሚቴው ሲያጸድቀውም ለማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት ማቅረብ ፡ ቪ ማናቸውንም የፋይናንስና የፕሮጀክት ሬኮርድ ለማዕከ ላዊው ጽሕፈት ቤት ክፍት ማድረግ ፡ ፰ የአፈጻጸም መመሪያው በሚያዘው መሠረት የክፍያ መተኪያ ጥያቄዎችን አዘጋጅቶ ክፍያ እንዲፈጸም ለማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት ማቅረብ ። _ ፲፭ የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ፩ እያንዳንዱ የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ በክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ይሾማል ። ገጽ ፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ የካቲት ፭ ቀን ፲፱ደተቛ ዓም : Federal Negarit Gazeta – No . 7 - 13 February 1996 - Page 111 ፪ በአስተባባሪው ኮሚቴ የሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ሥራ አስኪያጁ የፈንዱ እንቅስቃ ሴዎች በፈንዱ የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት በአግባቡ ተግባራዊ ለመሆናቸውኃላፊ ይሆናል ። ፫ . ከላይ የተጠቀሰው አጠቃላይ ሁኔታ ሳይወሰን ሥራ አስኪያጁ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ ለክልሉ ፈንድ ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ይፈጽማል ! ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የክልሉን ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ይቀጥራል ያስተዳድራል ፤ ሐ ) ለክልሉ ፈንድ ጽሕፈት ቤት በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያዎችን ይፈጽማል ፤ መ ) በክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ደረጃ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ፈንዱን ይወክላል ፣ ሠ ) በክልሉ የፈንዱን እንቅስቃሴዎች በብቃት ለማከ ናወን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሥልጣኑን ለክልሉ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፮ . የአሠራር ወጥነትን ስለማረጋገጥ የፈንዱን የአሠራር ወጥነት ለማረጋገጥ የሥራ አፈጻጸም መመሪያው የፈንዱን አጠቃላይ ተግባራትና እንቅስቃሴዎች | የሚገዛ ይሆናል ። ፲፯ በጀት ፩• የፈንዱ በጀትከፌዴራሉ መንግሥት ፡ ከለጋሽ ድርጅቶችና ከሕብረተሰቡ የሚደረግ የገንዘብ መዋጮና ከዓለም ባንክ የሚገኝ ብድር ይሆናል ። ፪• ከክልሎች ፡ ከፌዴራሉ መንግሥትና ከለጋሽ ድርጅቶች የሚሰጡ ቢሮዎች ፡ መሣሪያዎች ፡ ዕቃዎችና የመሳሰሉት ለፈንዱ ተጨማሪ ገቢዎች ሊሆኑ ይችላሉ ። ፫• በጀቱ የገንዘብ መዋጮዎቹ ከተደረጉበት የብድርና ዕርዳታ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ ተግባራዊ ይሆናል ። ፲፰ የባንክ ሂሣብ ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ ( ፩ ) የተጠቀሰውመዋጮ በፈንዱ ስም በባንክ ተቀማጭ ይሆናል ። ፪• ማዕከላዊው ጽሕፈት ቤት የሚከተሉት የባንክ ሂሳቦች ይኖሩታል ፤ ሀ ) የውጭ ምንዛሪ ሂሣብ ፡ ከውጭ ዕርዳታና ብድር ሰጪዎች ለሚገኘው ገንዘብ ፤ ለ ) የብር ( የአገር ውስጥ ገንዘብ ) ሂሳብ ። የክልል ፈንድ ጽሕፈት ቤት ሁለት የተለያዩ የአገር ውስጥ ገንዘብ የባንክ ሂሳቦች ለሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ይኖሩታል ፤ ሀ ) ለንዑስ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ፡ እና ለ ) ለሥራ ማስኬጃ ፡ የሚውል ። ፲፱ ኦዲት የፈንዱ ሂሣብ በየዓመቱ በውጭ ኦዲተሮች ይመረመራል ። ፳ : የዕቃ ግዥና አጠቃቀም በፈንዱ የሥራ አፈጻጸም መመሪያ ውስጥ በተመለከተው መሠረት ፈንዱ የራሱ የዕቃ ግዥና አጠቃቀም ሥርዓት ይኖረዋል ። ገጽ ፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 7 13 February 1996 – Page 112 ፳፩• የመብትና ግዴታ መተላለፍ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶ ፈንድ መብትና ግዴታ በዚህ | አዋጅ ለፈንዱ ተላልፋል ። ፳፪• የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ግለሰብ ፥ የመንግሥት አካላትና የግል ድርጅቶች ፈንዱ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ የመተባበር ግዴታ አለባቸው ። ፳፫• አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፭ ቀን ፲፱፻T፰ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ