×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 15551

      Sorry, pritning is not allowed

የሰ / መ / ቁ . 15551
ቀን 29/2/98 ዓ.ም
አቶ አብዱልቃድር መሪ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ወ / ሮ ደስታ ገብሩ አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ ወ / ሪት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ዩናይትድ ቴክኒካል ኢኩፕመንት ኩባንያ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ሞተርና መሐንዲስነት ኩባንያ
ተከተለ ውል
ስለ ውል መፍረስ - ህጋዊ ደንብን ያልተከተለ ውል ስለሚፈርስበት ሁኔታ እና የውል መፍረስ በተዋዋይ ወገኖች ላይ የሚያወጣው ውጤት - የፍ / ብ / ህ / ቁ 1716 ( 2 ፡ 1815 ፣ 1816 እና 1817
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የመኪና ሽያጭ ውል ከፈረሠ በኋላ ገንዘቡ ለአመልካች ተመልሶ በመንግስት የተወረሰችዉ መኪና ወደ ጅቡቲ ትመለስ በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል የወሰነውን በማፅናቱ የቀረበ አቤቱታ ፡፡
ው ሳ ኔ ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን በተመለከተ የሰጠው
ውሳኔ እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ጅቡቲ ትመለስ በማለት የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል ፡፡ ውል እንዲፈርስ ከተወሰነ በኋላ ተዋዋዮች ከውሉ ሰፊት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ የሚወሰነው በውሉ ምክንያት የተሰራውን ሥራ ለማፍረስ የማይቻል ወይም አስቸጋሪ ካልሆነ ነው ፡፡
? ” የሰመ / ቁ . 15551 ፡
ቀን 29/2/98 ዓ.ም
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ 3 ,
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ደስታ ገብሩ አቶ መስፍን ዕቁሰዮናስ ወ / ሪት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ዩናይትድ ቴክኒካል ኢኩፕመንት ኩባንያ ተጠሪ፡- የኢዮጵያ ሞተርና መሓንዲስነት ኩባንያ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ ይህ ጉዳይ የጀመረው የኦሁን እመልካች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በተጠሪው ላይ ባቀረበው ክሥ መነሻ ነው ::
ነገር ከሣሽ ላንድክሩዘር መኪና ለመግዛት ፈልጎ ተከሣሽን የመሸጫ ዋጋ ጠይቆ ጥያቄው በተከሣሽ ተቀባይነት በማግኘቱ ተከሣሹ ባቀረበው የመኪና መሸጫ ዋጋ ተስማምተው ከሣሽ ገንዘቡን የኮፈስ . መሆኑን ፤ ነገር ግን መኪናዋ በተከሣሽ ላይሰንስ ጉምሩክ መጋዘን ከገባች በኋላ መኪናዋ በሕገወጥ መንገድ ስለገባች ማውጣት አትችሉም ሲል ጉምሩክ ስለከለከለ ውሉ ገንዘቡን ከነወለዱ እንዲመስስ ይወሰንልኝ የሚል ነው ፡፡
የሥር ተከሣሽ የአሁን ተጠሪም ቀርቦ ከተከራከረ በኋላ ፍ / ቤቱ ውሉ የተደረገው ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡት ዕቃዎች ሐምሌ 12/1988 ከወጣው ደንብ በኋላ የተደረገ ስለሆነ ፤ ውሉም ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን በመሆነ በፍ / ሕ / ቁጥር 1716 / 1 / መሠረት ፈራሽ
ፈራሽ ነው ከተባለ ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት ሁኔታ ሊመለሱ እንደሚገባ የፍ / ሕ / ቁጥር 1815 / 1 / ስለሚደነግግ
በክሥ አቤቱታው ላይ የተመለከተውን ብር 177,184.23 7 አንድ መቶ ሰባ
ሠባት ሺህ አንድ መቶ ሠማንያ አራት ብር ከሃያ ሦስት ሣንቲም /
የኢትዮጵያ ብር ወይም 26037,36 / ሃያ ስድስት ሺህ ሠላሣ ሰባት ብር ከሠላሣ ስድስት ሣንቲም / የአሜሪካን ዶላር ተከሣሽ ለከሣሽ ይክፈል ፣ ዳኝነት ስታሪፉ ልክ ፣ የጠበቃ አበል 15 % ልዩ ልዩ ወጪ 1 ዕዕ / አንድ መቶ ብር ጨምሮ ለከሣሽ እንዲከፍል ሲል ወስኗል ፡፡
የኣሁን ተጠሪም በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ሰማቅረቡ ፍ / ቤቱ የይግባኙን ክርክር መርምሮ ስፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት ውሉ ሊፈርስ ይገባል በማለት የተሰጠውን የውሣኔ ክፍል በማጽናት ነገር ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት ይመለሱ ሲባል ከሣሽ ለመኪናው የከፈለው ገንዘብ ይመለስለት ማለት ሲሆን ፤ ተከሣሹም ከውሉ በፊት ወደነበረበት ሁኔታ የሚመለሰው ሰውሉ ምክንያት ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባው መኪና ወደ ጅቡቲ ሲመለስለት በመሆኑ የሥር ፍ / ቤት አንዱን ወገን ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ አድርጊ ሌላውን ወገን ባለበት ሁኔታ በመተው የሰጠውን ውሣኔ አሻሽለን ከላይ በተገለፀው ሁኔታ ወደነበረበት ይመለሱ ሲል ውሣኔ ሠጥቷል ።
በዚህ ውሣኔ የሥር ከሣሽ ቅር በመሰኘት ለፌ / ጠ / ፍ / ቤት የይግባኝ ቅሬታ ሲያቀርብ ተከሣሹም መስቀለኛ ይግባኝ አቅርቧል ፡፡
የፌ / ጠ / ፍ / ቤት ዋናውን ይግባኝ በተመለከተ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር መሠረት የለውም በማለት ፤ መስቀለኛ ይግባኙም ፍ / ቤቶች ተመሣሣይ ውሣኔ የተሰጠበት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 9 መሠረት በይግባኝ ደረጃ ሊታይ አይችልም በማለት መዝገቡን ዘግቶ መልሶለታል ፡፡
እንግዲህ የሥር ከሣሹ ማለትም የእሁን አመልካች በ 25 / 8 / 96 ጽፎ ያቀረበው የሀሰር ኣቤቱታ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት መኪናዋ ወደ ጅቡቲ ትመለስ የሚለው ተጨማሪ የውሣኔ ክፍል አፈፃፀሙን የተወሣሠበ ስላደረገውና የፌ / ጠ / ፍ / ቤትም ይህንኑ ማረም ሲገባው ማለፉ ሥነ ሥርዓትን የሚቃረን በመሆኑ ይህ ተሻሽሎ የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት ውሣኔ ይፀናልን በማለት በዝርዝር አመልክቷል ፡፡
የማመልከቻ ግልባጭ ለተጠሪው ደረሶ ጥር 19/1997 ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካቹ የፌ / ጠ / ፍ / ቤት ውሣኔ ከሰጠ በኋላ አፈፃፀመ እንዲቀጥል ማቅረሳቸ By Af
ሸማኔጅ WA እንደተሰማበት
የሚቆጠር ነው ለዚህ ችሎት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም ውሣኔው መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን ኣላሣዩም ፣ ውሉ ሊፈርስ ይገባዋል ሲባል ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት ሁኔታ ይመለሱ መባሉም ትክክል ነው አመልካች መኪናውን አልተረከቡም ለሚሉት አስቀድሞ ያስተላት ክርክር ስለሆነ ኣሁን ሊነሣ አይገባውምና እቤቱታው ተሠርዞ ተገቢው ኪሣራ ተቋርጦልን እንሠናበት በማለት የተከራከረ አመልካችም አቤቱታውን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ ሰጥቷል ፡፡
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር ከፍ ብሎ በዝርገር የተመለከተው ሲሆን ውሣኔ ሊያገኝ የሚገባው ጭብጥ ፤ በአመልካችና በተጠሪው መካከል የነበረው የመኪና ሽያጭ ውል ፈርሶ ወደነበሩበት ይመለሱ ሲባል ለአመልካቹ ገንዘቡ እንዲመለስለት ብቻ ሣይሆን ከጅቡቲ ወደብ መጥታ ጉምሩክ መጋዘን ገብታለች የተባለችውም መኪና ወደ ጅቡቲ መመለስ አለባት ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ? አይደለም ? የሚለው ነው ፡፡
በመሠረቱ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው የመኪና ሽያጭ ውል እንዲፈርስ በሥር ፍ / ቤቶች በተሠጠው ውሣኔ ሳይ ያልቀረበበት ስለሆነ ይህን ነጥብ መመርመሩ አስፈላጊ አይደለም ፡፡ የተጠሪው ክርክር ውሉ ይፍረስ ከተባለ ውጤቱ በፍ / ሕግ ቁጥር 1815 / 1 / መሠረት ተዋዋዮች ወደነበሩበት ይመለሣሉ ሁኔታ መመላለስ ስለአለብን የፌ / ከፍተኛ ከሣሹ ገንዘቡን እንዲያገኝ ከተወሰነ መኪናዋም ወደጅቡቲ እንድትመለስ መወሰኑ ተገቢ ነው ሊል አመልካች በበኩሉ መኪናዋ ወደ ጅቡቲ ትመለስ ከተባለ ውሣኔው ሊፈፀም የማይችል ይሆናል ባይ ነው ፡፡
አከራካሪዋ መኪና ከጅቡቲ ወደብ መጥታ ጉምሩክ መጋዘን ከገባች በኋላ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብታለች ተብሎ ጉምሩክ ለከሣሽ ሊሰጥ አለመቻሉንና በዚሁ ምክንያት በመንግሥት ስለመወረሷ ራሱ የሥር ተከሣሽ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ / ቤት ካቀረበው ክርክር መረዳት ይቻላል ፡፡
እንግዲህ ምንም እንኳን የፍ / ሕ / ቁጥር 1815 / 1 / አንድ ውለታ ሲሠረዝ ወይም ሲፈርስ ተዋዋዮችን በተቻለ መጠን ውለታው ከመደረጉ
በውርስ የገባች መሆኑ እየተረጋገጠ ወደ ጅቡቲ ትመለስ ተብሎ መወሰኑ የተሠራውን ሥራ ለማፍረስ የማይቻል ወይም አስቸጋሪ ያደርገዋል ፡፡
እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ደግሞ የፍ / ሕግ ቁጥር 1816 እና 1817 የፍ / ሕ / ቁጥር 1815 ልዩ ሁኔታ ( exceptions ) ሆነው መፍትሄ ይሰጣሉ ፡፡
ይኸውም በተለይ ለዚህ ጉዳይ ተጠቃሽነት ያለው የፍ / ሕ / ቁጥር 1817 / 1 / ... የተሠራውን ሥራ ለማፍረስ የማይቻል ሲሆነ ወይም እስቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ወይም ከፍ ያለ መሠናክል የሚያመጣ ሲሆን የተሰሩት ሥራዎች እንደረጉ ይቀራሉ ይላል ፡፡
ይሁንና የፌከፍተኛ ፍ / ቤት ይህን ድንጋጌ በሚቃረን መኪናዋ በመንግሥት መወረሱን እየተረዳ ወደ ጅቡቲ ትመለስ ሲል የሰጠው የውሣኔ ክፍል መሠረታዊ የሕግ ሥህተት ያለበት ነው ብለናል ፡፡
የፌ / ጠ / ፍ / ቤትም ይህን ሥህተት እንዲያርም የቀረበለትን ይግባኝ ያለመቀበሉ ሊታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ የፌ / ጠ / ፍ / ቤት ሰፍ / ይ / መ / ቁ 11936 ጥር 26/96 በዋለው ችሎት ዋናውን ይግባኝ በተመለከተ የሰጠው የውሣኔ ክፍል በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 348 // ተሽሯል ፡፡
የፌ / ከ / ፍ / ቤት ሰይ / መ / ቁ . 216/94 በ 24 / 7 / 95 መኪናዋ ወደ ጅቡቲ ትመለስ በማለት የሰጠውን የውሣኔ ክፍል ብቻ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ /
ቁጥር 348 / ተሽሯል ። የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በፍ / መ /
ቁጥር 492/90 በ 4 / 11 / 93 በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሣኔ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁጥር 348 / 1 / መሠረት በማጽናት ወስነናል ። የውሣኔው ለሥር ፍ / ቤት
ፍ / ቤት ይድረሰው ተዘግቷል ፡፡ ለመ / ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?