×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 231,93 ለሴቶች ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር 70 አዲስ አበባ ጥር ፳፪ ቀን ፲ህየን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻ወ፩ በህየን ዓ - ም ለሴቶች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማዕደቂያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፩ ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማፅደቅ የወጣ አዋጅ ለሴቶች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ ኤስዲ - አር / ሚሊዮን ፳የሺህ ( ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺ ኤስዲ - አር ) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማትማኅበር መካከል እ.ኤ.አ. ኦገስት ፳፯ ቀን ፪ሺ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ፡ መሠረታዊ የኤኮኖሚ ዓለምአቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው፡ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር ፳፪ ቀን ፲፱የን ! ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለሴቶች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ከዓለም አቀፍ የልማትማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማዕደቂያ አዋጅ ቁጥር ፪፻ወ፩ 1 ህየን ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ.ኤ.አ ኦገስት ፳፰ ቀን ፪ሺ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመው ቁጥር ፫ሺ፱የጊ ኢት • የብድር ስምምነት ነው ። ያንዱ ዋጋ ብር 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ : ዥሺ፩ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 18 ጥር ፳፪ ቀን ፲ህየ ፣ ዓ • ም • የገንዘብ ሚኒስትር ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በብድር ስምምነቱ የተገኘውን ኤስዲ - ኣር ፤ ሚሊዮን ፫፻ሺህ ( ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ኤስዲ - ኣር ) በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥር ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፫ ዓም ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?