ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ° ማሻሻያ ) ► የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፵፩ አዲስ ኣበባ - መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፩ / ፲፱፻፲፭ ዓም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ኣዋጅን ለማሻሻል የወጣ ገጸ ፪ሺ፩፻፴ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፩ / ፲፱፻፲፭ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ኣዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፰ እንደተ ሻሻለ እንደገና ማሻሻል በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ ) አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቁጥር ፫፻፳፩ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ ) ማሻሻያ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻ዥ፰ እንደሚከ | 2. Amendment ተለው ተሻሽሏል ። ፩ . የአንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል ። “ ፩ . በመንግሥት ግዛት ሀገር ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች፡ ” ፪ . የአንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል ፤ “ ፱ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ሕጎችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተበዳይ ወይም ተከሳሽ የሆኑባቸው ወንጀሎች ፡ እንዲሁም የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና እንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ከ፭ ዓመት ጽኑ እሥራት በላይ ሊያስቀጡ የሚችሉ የውጭ ሀገር ዜጎች ተበዳይ ወይም ተከሳሽ የሆኑባቸው ወንጀሎች፡ ” ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ሺ፩ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም በአንቀጽ ፪ ሥር የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፲፫ ) እና ( ፲፬ ) ተጨምረዋል ፣ “ ፲፫ ) በተለያዩ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች፡ ጎሣዎች ፡ በሃይማኖት ተከታዮች ወይም በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች ፤ ፲፬ ) በፌዴራል መንግሥቱ ንብረቶች ላይ በሚፈጸሙ እና የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ከ፭ ዓመት ጽኑ እሥራት በላይ ሊያስቀጡ የሚችሉ ወንጀሎች፡ ” ፬ ) የአንቀጽ ፲፪ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፲፪ | 4 ) Article 12 is deleted and replaced by the following new ተተክቷል ፣ “ ፲፪ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል የዳኝነት ሥልጣን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡ ፩ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፡ ( ፪ ) ( ፫ ) ፡ ( ፰ ) ፡ ( ፬ ) እና ( ፲፫ ) በተመለከቱት የወንጀል ጉዳዮች፡ ፪ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የውጭ ሀገር ዜጎችን እንዲሁም አንቀጸ ( 10 ) ን በሚመለ ከቱና በሥራ ላይ ባሉት ሕጎች ለከፍተኛ ፍርጅ ቤት በተሰጡ የወንጀል ጉዳዮች፡ ፫ ) በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች ውስጥ በሚነሱና በሥራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰጡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች ። ” ፭ አንቀጽ ፲፭ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፲፭ ተተክቷል ፤ “ ፲፭ . የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የወንጀል የዳኝነት ሥልጣን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚከተሉት የወንጀል ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡ ፩ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ፡ ( ፭ ) ፡ ( ፩ ) እና ( ፯ ) በተመለከቱት የወንጀል ጉዳዮች፡ ፪ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የውጪ ሀገር ዜጎችን እንዲሁም ንዑስ አንቀጽ ( ፲፬ ) ን በሚመ ለከቱና በሥራ ላይ ባሉት ሕጎች ለወረዳና ለአውራጃ ፍርድ ቤት በተሰጡ የወንጀል ጉዳዮች፡ ፫ ) በሕግ ለሌሎች ኣካላት የተሰጠው የዳኝነት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በአዲስ አበባ እና ደሬዳዋ ከተሞች ውስጥ በሚነሱና በሥራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለወረዳና ለአውራጃ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች ። ” በክልል ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ ስላሉ ጉዳዮች ይህ አዋጅ ከመፅናቱ በፊት በክልል ፍርድ ቤቶች በመታየት | 7 . Effective Date ላይ ያሉ በዚህ አዋጅ የተሻሻለውን ኣንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፡ ( ፱ ) ፡ ( ፲፫ ) ኣና ( ፲፬ ) የሚመለከቱ፡ የወንጀል ጉዳዮች ሥልጣን ወደአላቸው ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተዛውረው ይታያሉ ። ፯ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከመጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ