የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፴ አዲስ አበባ – ሰኔ ፳፰ ቀን ፲ሀየጠቿ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፫፫ ዓ . ም የአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አዋጅ . . . . ገጽ ፪፻፴፭ አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፰ ለአነስተኛ ብድር ኣቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ፈቃድ ስለመስጠትና ሥራቸውን ስለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ - የአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ የገንዘብና የፋይናንስ ፖሊሲዎች ውስጥ ለማካተት | የሚያስችል ሕጋዊ ሥርዓት ሊዘረጋ ስለሚገባ ፣ በሀገሪቱ በሥራ ላይ የዋሉት የገንዘብና የባንክ ሕጎች ዝቅተኛ የገጠር ገበሬዎችንና በሌሎች አነስተኛ የምርትና አገልግሎት ሥራ | not provide for micro financing institutions catering for the የተሰማሩ ሰዎችን የብድር ፍላጎት ለማሟላት የሚችሉ አነስተኛ | credit needs of peasant farmers and others engaged in small ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶችን መቋቋም የማያመቻቹ | scale production and service activities : በመሆኑ ፡ ለአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ፈቃድ ስለመ | licensing and supervision of the business of micro financing ስጠትና ሥራቸውንም ስለመቆጣጠር የሚደነግግ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ : በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻T፰ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 3 - 40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፫ሺ፩ ገጽ ፪የሣኔ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻T፰ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 30 5 " July 1996 – Page 246 ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ ባንክ ” ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው ፣ ፪• “ ኩባንያ ” ማለት በንግድ ሕጉ አንቀጽ ፫፻፬ በተሰጠው ትርጉም መሠረት የተቋቋመ ፡ አክስዮኑ በሙሉ በኢትዮጵያ ዜጎች እና ወይም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ዜጎች ባለሀብ ትነት በተቋቋሙ ድርጅቶች የተያዘ ፥ በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የተመዘገበና ዋና መሥሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ የአክስዮን ማኅበር ነው ፣ “ አነስተኛ ብድር የማቅረብ ሥራ ” ማለት መጠናቸው በባንኩ የሚወሰን ብድሮችን በጥሬ ገንዘብ ወይም በዓይነት ለገጠር ዝቅተኛ ገበሬዎች ወይም በከተማ አነስተኛ የምርትና አገልግሎት ሥራ ላይ ለተሰማሩ የማቅረብ እንቅስቃሴ ነው ፣ ፬ . “ አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ” ማለት | በገጠርና በከተማ አካባቢዎች አነስተኛ ብድር የማቅረብ ሥራ እንዲያካሂድ በዚህ አዋጅ መሠረት የተፈቀደለት ኩባንያ ነው ፣ ፭ “ አባላት ” ማለት በአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ | ድርጅት ውስጥ የማቋቋሚያ አክስዮን የገዙ ወይም | በድርጅቱ የተዘጋጀ ማናቸውም ዓይነት የአባልነት ስምምነት ተፈራራሚዎች ናቸው ፣ “ የቡድን ዋትና ” ማለት ከመካከላቸው በማንኛውም አባል ላልቶ ፡ በድር የተበዳሪዎች ቡድን አባላት በአንድነትና በነጠላ ባለእዳ ለመሆን ግዴታ የሚገቡበት የዋስትና ስልት ነው ፡ ፯ . “ ቁጠባ ” ማለት የአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ | ድርጅት አባላት የሚያስቀምጡት ሊወጣ የማይችል የግዴታ ቁጠባ ወይም መደበኛ ቁጠባ ነው ፤ : ፰ “ ተቀማጭ ” ማለት በሂሳቡ ባለቤት በማናቸውም ጊዜ | በከፊል ወይም በሙሉ ሊወጣ የሚችል መደበኛ ወይም | መደበኛ ያልሆነ ቁጠባ ነው ፡ 6 . “ ዲሬክተሮች ” ማለት የአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት የቦርድ አባላት ናቸው ። ፫ ዓላማና ተግባር ፩ . የአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ዓላማ | ከፍተኛ መጠኑ በባንኩ የሚወሰን ብድር በጥሬ ገንዘብ ወይም በዓይነት መስጠት ነው ። ፪• አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት በዚህ አዋጅ ውስጥ በተደነገጉት ሁኔታዎች መሠረት ፡ የሚከተሉትን ሥራዎች በሙሉ ወይም በከፊል ሊሠራ ይችላል ፣ ሀ ) የቁጠባ ገንዘብ እንዲሁም በተጠየቀ ጊዜ የሚከፈልና በጊዜ ገደብ የሚከፈልን ጨምሮ ፡ ተቀማጭ ገንዘብ | መቀበል ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ ተከፋይ የሚሆኑ የሃዋላ ወረቀቶች ማውጣትና መቀበል ፡ ገጽ የጊ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻r፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 30 5 » July 1996 – Page 247 ሐ ) በንብረቱ ዋስትና ወይም በሌላ አኳኋን ለድርጅቱ ሥራ የሚውል ገንዘብ መበደር ፡ መ ) ዓላማቸው ገቢ ማስገኘት የሆነ እንደ ግምጃ ቤት ሰነዶች ያሉ የንግድ ወረቀቶችን መግዛት ፡ ሠ ) ሥራውን የሚያከናውንባቸውን ሕንፃዎች ጨምሮማና ቸውንም የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት በባለ ቤትነት መያዝ ፡ መንከባከብና ለሌሎች ማስተላለፍ ፡ ረ ) ለደንበኞቹ የምክር አገልግሎት መስጠት ፡ ሰ ) በከተማና በገጠር በኣነስተኛ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች ገቢ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶችን ማበረታታት ፡ ሸ ) ለተበዳሪዎች የሥራ አመራር ፡ የገበያ : የቴክኒክና የአስተዳደር ምክር መስጠትና በነዚህም መስኮች አገል ግሎት እንዲያገኙ መርዳት ፡ አነስተኛ ብድር ለማቅረብ ሥራ ዓላማ የሚውል ገንዘብ ማስተዳደር ፡ እና በ ) በተለምዶ በአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች የሚሠሩ ሌሎች ሥራዎችን መሥራት ። ክፍል ሁለት ለአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ፈቃድ ስለመስጠት አነስተኛ ብድር የማቅረብ ሥራ ለማካሄድ ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ፩ አነስተኛ ብድር የማቅረብ ሥራ ለማካሄድ ከዚህ የሚከ ተሉት ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው ፣ ሀ ) ከባንኩ ፈቃድ ማግኘት ፡ ለ ) በኩባንያ ቅርጽ መቋቋም ፡ ሐ ) በባንኩ የተወሰነውን ዝቅተኛ መነሻ ካፒታል በባንክ ማስቀመጥ ፡ እና መ ) ዲሬክተሮችና ሌሎች ኃላፊዎች ባንኩ የሚያወጣ ቸውን መመዘኛዎች መጥነው መገኝት ። ፪ . አዲስ ዓይነት የሆኑ ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊ አካላት አነስተኛ ብድር በማቅረብ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ለማስ ቻልና ከዚህ አዋጅ ዓላማ ጋር ለሚዛመድ ምክንያት የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ማናቸውም ድንጋጌ በአመልካቹ ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆን ባንኩ የውሳኔ ሀሳብና አስተያየት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል ። ፭ ተጨማሪ ሁኔታዎችን ስለመደንገግ ፩ ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት መሟላት ያለባቸውን ማናቸ ውንም ተጨማሪ ሁኔታዎች ባንኩ በየጊዜው በሚያወ ጣቸው መመሪያዎች ሊደነግግ ይችላል ። ባንኩ ከፈቃድ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ሁኔታዎችን ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል ሲፈልግ ለውጡን ወይም ማሻሻያውን ሥራ ላይ ለማዋል ካሰበበት ዕለት ፵፭ ቀናት አስቀድሞ ለሚመለከታቸው አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ያሳውቃል ። ገጽ ፪፻፵፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 30 5 D July 1996 – Page 248 ፮ ፈቃድ እንዲሰጥ ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፭ . አነስተኛ ብድር የማቅረብ ሥራ ለማካሄድ እንዲፈቀድ የሚቀርብ ማመልከቻ የሚከተሉትን መያዝ ይኖርበታል ፡ ሀ ) ሥራው ሊካሄድ የታሰበበትን ኣካባቢ ( የዋና መሥሪያ ቤቱንና የቅርንጫፎቹን አድራሻ ማመልከት ) ፡ ለ ) የመሥራቾቹን ስም ፡ የሥራ መስክ ፡ የመኖሪያ አድራሻና ዜግነት ፡ ሐ ) ድርጅቱ የተቋቋመበትን ቅርጽ ዓይነት ፡ መ ) ድርጅቱን ለመመሥረት የተደረገውን ስምምነት ፡ ሠ ) ለድርጅቱ ሊሰጥ የታቀደውን ስያሜ ፡ ረ ) የእያንዳንዱን መሥራች አባል ፡ የታሳቢ ዲሬክተሮችና ፡ የኃላፊዎችን የሕይወት ታሪክ መረጃ ፡ ሰ ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት የተደረገውን መዋጮ የድርሻ መጠን እና በዓይነት የተደረገውን መዋጮ አገማመት ፡ ሽ ) ድርጅቱ ሊሠራቸው ያቀዳቸውን ተግባሮችና እነዚ ህኑም ለማከናወን አመልካቹ ሊጠቀምበት ያቀዳቸው ሁኔታዎች ፡ እና | ባንኩ እንዲቀርብለት የሚጠይቃቸው ሌሎች አግባ | ብነት ያላቸው መረጃዎች ። ፪• ፈቃድ እንዲሰጠው የሚጠይቅ አመልካች ማመልከቻውን በሚያቀርብበት ወቅት ባንኩ የሚወስነውን የሠነድ መመ ርመሪያ ክፍያ ይከፍላል ። ፫ ፈቃድ የተሰጠው አመልካች ፈቃዱ ከተሰጠው ጊዜ _ አንስቶ በአሥራ ሁለት ( ፲፪ ) ወራት ውስጥ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል ። ፬ ከባንኩ በቅድሚያ ይሁንታ ሳያገኝ ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ከተፈቀደለት አካባቢ ውጪ ለመስራት አይችልም ። ፭ ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ባንኩ የሚወስነውን ዓመታዊ የፈቃድ ማደሻ ክፍያ ይከፍላል ። ፯ ሥራ እንዲጀመር ስለመፍቀድ ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ባንኩ በሚያወጣቸው መመሪ ያዎች የተመለከቱ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ ሊጠየቅ ይችላል ። ቿ ፈቃድ ከሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብና የሚተላለፉ የገንዘብ ሠነዶችን ስለማስመለስ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ መሠረት የሚካሄዱ ሥራዎችን ያለፈቃድ ከሠራና በዚሁ ድርጊት አማካይነት የተቀበለው ገንዘብ ወይም ንብረት ካለ ባንኩ ይህ ገንዘብና ንብረት ምን ሊደረግ እንደሚገባ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ለፌዴራሉ ከፍተኛ | ፍርድ ቤት ለማመልከት ይችላል ። ፍርድ ቤቱም ገንዘቡና ንብረቱ ለአስቀማጮች ወይም ለባለንብረቶች በአፋጣኝና በተቀላጠፈ መንገድ እንዲመለስ የሚያስችል ትዕዛዝ ይሰጣል ። ፈቃድ ስለመሠረዝ ኣነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ከዚህ በሚከተሉት ማናቸውም ምክንያቶች ፈቃዱ በባንኩ ሊሰረዝበት ይችላል ፣ ፩ ፈቃድ በተሰጠው በአሥራ ሁለት ( ፲፪ ) ወራት ውስጥ ሥራውን ሳይጀምር ሲቀር ፡ ፪ ሥራውን ሲያቆም ፡ ፫ የመክሰር ውሳኔ ሲሰጥበት ወይም እንዲፈርስ ሲወሰን ፣ ገጽ ፪፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 30 5 5 July 1996 – Page 249 ፬ ባንኩ በቅድሚያ በጽሑፍ ሳይፈቅድ ከሌላ አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ወይም ባንክ ጋር ሲዋሃድ ፡ ፭ በተሳሳተ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተመዘገበ መሆኑ ሲረጋገጥ ። ፲ እንደገና ለመመዝገብ ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት የሚያንቀሳ ቅሰው የቁጠባ ገንዘብ ብር ፩ ሚሊዮን ( አንድ ሚሊዮን ብር ) ሲደርስ እንደገና ለመመዝገብ ማመልከት አለበት ። ፪• ድርጅቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ሲያመለክት ፡ ባንኩ ባወጣቸው መመሪያዎች ውስጥ የተጠቀሱ ተጨማሪ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ ሊገደድ ፲፩ . ስለ ድጋፍ _ ፩ ባንኩ ተገቢ ነው ብሎ ሲያምንበት ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት በሚቋቋምበት ወይም ሥራውን በሚያካሂድበት ወቅት የሚጠይቀውን ቴክኒካዊ ድጋፍ ይሰጣል ። ፪• አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች መልሶ ለማበደር ወይም ለካፒታል ማስፋፊያ የሚያውሉት የብድር አገልግሎት ወይም ማናቸውንም እርዳታ ከውጪ ሀገር ለማግኘት ይችላሉ ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የሚገኝ ብድር ወይም እርዳታ በቅድሚያ የገንዘብ ሚኒስቴርን ይሁንታ ማግኘት አለበት ። ክፍል ሦስት የፊናንስ ግዴታዎችና ደንቦች ፲፪• ዝቅተኛ የካፒታል መጠን ፡ የባንኩ ሥልጣንና ተግባር ፩ አነስተኛ ብድር ለማቅረብ ሥራ ፈቃድ ለማግኘት የሚጠ የቀው ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን ባንኩ በሚያ ወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ፪ . ባንኩ ከዚህ የሚከተሉትን ጉዳዮች በሚመለከት መመሪያ | ዎችን ለማውጣት ይችላል ፣ ሀ ) ኣነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ለማን ኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን ስለሚሰጡት ከፍተኛ የብድር መጠን ፡ ለ ) ስለብድር መክፈያ ጊዜና የአሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ፡ ሐ ) ስለወቅታዊ ሪፖርት አቀራረብ ፡ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ እና የሂሣብ መዝገብ አያያዝ ሥርዓት ፡ መ ) ብድርን አስመልከቶ በየጊዜው ስለሚደረግ ጥቅል ምርመራና ስለኦዲት ፡ ሠ ) ስለተጠያቂነት ፡ ስለመዋቅር ፡ ስለቁጠባ ዘዴና ስለገ ንዘብ ክንውን ደረጃዎች ፡ እና ረ ) ለአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ስለሚውል ልዩ የወለድ ተመን አወሳሰን ። ፫ ባንኩ ከዚህ የሚከተሉትን የማከናወን ኃላፊነት አለበት ፣ ሀ ) ባንኮችና ሌሎች የገንዘብ ድርጅቶች አነስተኛ ብድር በማቅረብ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ወይም በዚህ መስክ ሥራቸውን እንዲያስፋፉማበረታታት ፣ ለ ) ለአነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ሠራተኞች ሥልጠና መስጠት ወይም ሥልጠና እንዲ ያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፤ ገጽ ጀTH ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . ሐ ) ዝቅተኛ ገቢ ያለው የኅብረተሰቡ ክፍል የበለጠ ጥቅም እንዲያገኝባቸው ፡ እንደ እቁብ የመሳሰሉ ባሕላዊ የቁጠባ ተቋሞችን ማበረታታትና ማዳበር ፤ መ ) በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አነስተኛ ብድር በማቅረብ የሥራ መስክ ላይ የሚውለው ኢንቨስትመንት በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንዲያድግ ማድረግ ። መጣመርና መቀላቀል በተጎራባች አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የአነስተኛ ብድር | 13Consolidation and Merger አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች መጣመርና መቀላቀል የሚበ | ረታታ ይሆናል ፤ ባንኩም ተገቢ ነው ብሎ የሚያምንበትን | ማበረታቻ ለእንዲህ ዓይነቶቹ ድርጅቶች ይሰጣል ። ፲፬ . ቅርንጫፎችን ስለመክፈት ፩ . ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት | 14 . Opening of Branches ቅርንጫፉ ሥራውን በጀመረ በአሥራ አምስት ( ፲፭ ) ቀናት ውስጥ የቅርንጫፉን መከፈት ማሳወቅ አለበት ። አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ስለሚከፍትበትና ሥራቸውን ስለሚያካሂድበት ሁኔታ ባንኩ አጠቃላይ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ክፍል አራት ጠቅላላ ሁኔታዎች የብድር አገልግሎት አሰጣጥ አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ለአባላትና | 15 . Extending of Loan Services አባል ላልሆኑም ብድር ሊሰጡ ይችላሉ ። ሆኖም በቡድን ዋስትና የሚካሄዱ የብድር መርሀ ግብሮች ' ተበዳሪዎችን የድርጅቶቹ አባል ለማድረግ መጣር ይኖርባቸዋል ። ፲፮ መሠረታዊ የጥንቃቄ ሥርዓት አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች በአጠቃላይ ሊከተሉት የሚገባ መሠረታዊ የጥንቃቄ ሥርዓት ባንኩ | 16 . Minimum Operational Pndence በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል ። ፲፯ ክልከላዎች ከባንኩ በቅድሚያ ይሁንታ ካላገኘ በስተቀር ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ፤ ፩ በመቀላቀል ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ የንግድ ሥራውን መሸጥ ወይም የባለሀብትነት መተላለፍን የሚያ ስከትሉ ማናቸውንም ዓይነት ስምምነቶች ወይም ውሎች ማድረግ ወይም አወቃቀሩን መቀየር ፤ በመደበኛ የሥራ ተግባሩ አፈጻጸም ካልሆነ በስተቀር ንብረቱን በሙሉ ወይም በከፊል በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ | በውጭ ሀገር ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ወይም በሌላ መንገድ ባለቤትነቱን ማዛወር ፣ ፫ የካፒታሉን መጠን መቀነስ ፡ ወይም ፬ . የመመስረቻ ጽሑፉን ማሻሻል ወይም ሥራውን እንዲያ ካሂድ ፈቃድ ያገኘበትን ስም መቀየር ፣ አይችልም ። ፲፰ . ለሥራ መሪነት ፈቃድ ስለሚያስፈልግበት ሁኔታ ከዚህ በታች የተመለከቱት ዓይነት ግለሰቦች ከባንኩ በቅድሚያ በጽሑፍ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር ፡ የእነ ስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅትን ሥራ ለመምራት አይችሉም ፣ ገጽ የሃ፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 30 5 July 1996 - Page 25 1 ፩ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የመክሰር ውሳኔ የተሰጠባቸው ወይም ስለኪሳራው ከገንዘብ ጠያቂዎቻቸው ጋር ስምምነት ያደረጉ ፡ ወይም ፪ . በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር እምነት በማጉደል ወይም በአታላይነት ወንጀል የተፈረደባቸው ። _ ፲ ) የግብር ነፃነት አነስተኛ ብድር ኣቅራቢ የገንዘብ ድርጅቶች ከገቢ ግብር ነፃ የሚሆኑበትን ጊዜና አፈጸጸሙን የመወሰን ሥልጣን በዚህ አዋጅ ለገንዘብ ሚኒስቴር ተሰጥቶታል ። ፳ ልዩ ኃላፊነት ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት ዝቅተኛ ገቢ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል ፡ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ፡ ብድር ሊያገኝ የሚችልበትን ፖሊሲ በማውጣት መፈጸም እና ለዚሁም ዓላማ የቡድን ዋስትና የንብረት ዋስትናን የሚተካባቸውን መንገዶች ሥራ ላይ ማዋል ይኖር ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፩ . የመተባበር ግዴታ ይህን ኣዋጅ ሥራ ላይ በማዋል ረገድ ባንኩ ሲጠይቅ | የሚመለከታቸው አካላት የመተባበር ግዴታ አለባቸው ። ፳፪ . ስለ ሂሳብ ምርመራ ማናቸውም አነስተኛ ብድር አቅራቢ የገንዘብ ድርጅት | ከተጣራ ዓመታዊ ትርፉ ላይ ለባለአክስዮኖቹ ከማከፋፈሉ | በፊት ሂሳቡ በባንኩ ተቀባይነት ባለው ነፃ ኦዲተር መመርመር አለበት ። _ ፳፫ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ሕጎች በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮቸን በተመለከተ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። _ ፳፬• ተፈጻሚነት ስላለው ሌላ ሕግ በዚህ አዋጅ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ የባንክ ሥራ ስለመፍ | ቅድና ስለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር ዥ፬ ፲፱፻፫፮ | እንዳስፈላጊነቱ እየተቃና ተፈጻሚ ይሆናል ። መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ባንኩ ይህን አዋጅ በሚገባ በሥራ ላይ ለማዋል መመሪያ ዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፳፮ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ፩ ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት አነስተኛ ብድር በማቅረብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ከአዋጁ ድንጋጌዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ እስኪዋቀሩ ድረስ በነበሩበት ሁኔታ ሊቀጥሉ ይችላሉ ። ፪• አዋጁ በተጠቀሱት ደርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ሳይሆን ሊቆይ የሚችልበት ሁኔታና የጊዜ ገደብ ባንኩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይወሰናል ። ገጽ ፪፻፶፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ፳፯ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፫፫ ዓም ጀምሮ የጸና | ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻T፰ ዓ•ም• ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ