×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 6092 የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲን ማቋቋሚያ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲ህየን፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፰ ህየን፪ ዓ.ም. የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገጽ ፩ሺ፩፻፲፬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፰ ፲፱፻፲፪ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱የዝጊ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ | Duties of the Executive Organs of the Federal Democratic አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፰ ህየን ! ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። በዚህ ደንብ ውስጥ፡ “ መንግሥት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነው፡ ፪ “ ቦርድ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ መሠረት የተቋቋመው የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ነው፡ ፫ “ ጉባዔ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ መሠረት የተቋቋመው የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ነው፡ ( “ የአካዳሚክ ሠራተኛ ” ማለት በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሠማራ ሠራተኛ ነው ፡፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፩፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፭ . “ ፕሬዚዳንት ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲ መሠረት የሚሾም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ነው ፡፡ ፮ “ ዩኒቨርሲቲ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፫ መሠረት የተቋቋመው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው፡ ፫ . መቋቋም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ( ከዚህ በኋላ “ ዩኒቨርሲቲውን ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞችን ያካትታል፡ ሀ ) ባህር ዳር ፖሊቴክኒክ ኢንስቲትዩት፡ ለ ) ባህርዳር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፡ ሐ ) ወደፊት በቦርዱ የሚቋቋሙ ሌሎች ፋኩልቲ ዎችና ኮሌጆች ። ፫ . የዩኒቨርሲቲው ተጠሪነት ለትምህርት ሚኒስቴር ይሆናል ። ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡ ፩ ዕውቀትን ማዳበር፡ ማስፋፋትና ማስተላለፍ፡ ከር፡ ከብሔር፡ ከፆታ፡ ከሃይማኖትና ከመሳሰሉት ኣድል ዖዎች ነፃ የሆነ፡ በመከባበር፡ መተማመን፡ መተሳሰብና መቻቻል ላይየተመሰረተናሁለንተናዊ ስብዕናን የሚያበ ለዕግና የሰው ልጅ ክቡርነትን የሚያጠናክር ትምህርት መስጠት፡ የሥራ ክቡርነትንና የኅብረተሰብ ብልዕግናን የሚያ ራምድ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ ማድረግ፡ 0 የኢትዮጵያን ሕዝብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን በሳይንስ በቴክኖሎጂ፡ በሥነ ጥበባትና በልዩ ልዩ ሙያዎች የሠለጠኑ፡ ኅብረተሰብን በሚገባ ሊያገ ለግሉ የሚችሉ ሰዎች ማፍራት፡ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የሚረዳ ጥናትና ምርምር ማካሔድ፡ ጠቃሚ ውጤቶችን ማሠራጨት፡ የክልሉን ሕዝብም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን የሚረዱ ሙያዊ ግልጋ ሎቶች ማበርከት፡ ጊ የአገልግሎት ክፍያን በመቀበል የምክርና ሥልጠና አገልግሎት መስጠት ። የዩኒቨርሲቲው ሥልጣንና ተግባር ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ ፋኩልቲዎች፡ ኮሌጆችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ተቋሞች ማቋቋምና ማካሔድ፡ ፪ የቅድመ ምረቃና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም መቀየስና ሥራ ላይ ማዋል፡ I የምስክር ወረቀት፡ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሁም ለከፍተኛ ውጤትና ኣስተዋጽኦ ኣካዳሚክ ሜዳይ፡ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት፡ ሴሚናሮች ወርክሾፖችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋጀትና ማካሔድ፡ . . ንግሥት አቅርቦ ገጽ ፭ሺ፩፻፷፮ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ታኅሣሥ፲፪ ቀን ፲፱፻፪ ዓ.ም ፭ የአገልግሎት ክፍያ በመቀበልና በገበያ ውስጥ በመግባት የማማከርና የሥልጠና አገልግሎት መስጠት፡ ፮ . በሀገሪቱ ውስጥና በሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ አቻ ዩኒቨርሲቲዎች : የምርምር ተቋሞችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ጋር ግንኙነት መመሥረት፡ ፯ የትምህርት መጽሔቶችና ጋዜጦች ማቋቋምና ማሠራጨት፡ ፰ የንብረት ባለቤት የመሆን ፣ ውል የመዋዋል፡ ፲ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ፡ ዓላማውን የሚያራምዱ ተግባሮችን ማከናወን ክፍል ሁለት ስለዩኒቨርሲቲው የፖሊሲና የሥራ አስፈፃሚ አካላት ፮ : ስለዩኒቨርሲቲው ቦርድ መቋቋም ፩ ዩኒቨርሲቲው በመንግሥት የሚሰየሙ አንድ ሊቀመን በርና ቁጥራቸው እንደአስፈላጊነቱ የሚወሰን አባላት የሚገኙበት ቦርድ ይኖረዋል ። ቦርዱ የራሱ ፀሐፊ ይኖረዋል ። ፯ . የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክና የአስተዳደር አጠቃላይ ፖሊሲ ያወጣል ፡ ከመንግሥት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር በተገናዘበ መልኩ ይወስናል፡ ፪ የዩኒቨርቲውን አደረጃጀት ይወስናል፡ ፫ ዩኒቨርሲቲው ወደፊት የሚደራጅበትንና የሚተዳደር በትን ቻርተር እንዲዘጋጅ በማድረግ ለመንግሥት ያቀርባል፡ ፬ • የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያፀድቃል፡ ፭ የዩኒቨርሲቲውን ዕቅድና በጀት ያስፀድቃል፡ ፮ የዩኒቨርሲቲውን ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመት ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ ያስጸድቃል፡ ፯ . የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚቀጠሩበ ትንና የሚተዳደሩበትን ሁኔታ የሚወስን የውስጥ አስተ ዳደር ደንብ ከመንግሥት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር በማገናዘብ ያወጣል፡ ዩኒቨርሲቲውን በሚመለከት በማንኛውም የዩኒቨር ሲቲው አካል ወይም በዩኒቨርሲቲው በተሰጠ ውሳኔ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል፡ ፱ . ዩኒቨርሲቲው ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን የአካዳሚክ ስምምነቶች መርምሮ ያፀድቃል፡ ፲ የዩኒቨርሲቲው መለያ ምልክት የሚሆነውን ዓርማ ያጸድቃል፡ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ይወስናል፡ ዩኒቨርሲቲው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች በመን ግሥት በፀደቀው መመሪያ መሠረት ይወስናል፡ የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። * ለርሱ ሃሳብ ገጽ፳ቪልጿረይራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ታኅሣሥ ፲ ቀን ፲ E ዓም ፰ : የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ( ኔት ) መቋቋም ፩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘ የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ይቋቋማል ። ሀ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት . ለ ) የዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች . ሐ ) የየፋኩልቲው ዲኖች ... መ ) የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ሠ ) በተቋሙ የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚመረጡ ሁለት ወኪሎች ረ ሁለት የተማሪዎች ተወካዮች . … .... ሰ ) ቦርዱ የሚሰይማቸው አግባብነት ያላቸው ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላት . ጅ የጉባኤው ተጠሪነት ለቦርዱ ይሆናል ። ፪ • የጉባኤውሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚያወጣው አጠቃላይ መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉባኤው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ካለንደር ያጸድቃል፡ ያ የዩኒቨርሲቲውን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያጸድቃል፡ ፫ ዲግሪዎች ፣ ዲፕሎማዎችና የምስክር ወረቀቶች እንዲሁም ማጻይና ሽልማቶች የሚሰጡበትን ሁኔታ ይወስናል ፣ ፩ የተማሪዎች አቀባበልን ፣ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን፡ የዲሲፕሊን ጉዳዮችንና ምረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል፡ በነዚህም ጉዳዮችላይየሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ፣ ፭ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥና ደረጃዎች አቅጣጫዎችን ይወስናል ፣ 1 የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ሠራተኞችሎጥር መርምሮ ያጸድቃል፡ ፯ : የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ያቀርባል ፣ ፰ ዩኒቨርሲቲው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎችእንዲወስን ለቦርዱሃሳብ ያቀርባል ፣ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ይወስናል ፣ ፲ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመትና ተጠሪነት ፩ . የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በመንግሥት ይሾማል፡ ተጠ ሪነቱም ለቦርዱ ይሆናል ። ጅ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፯ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረትይሾማሉ፡ ተጠሪነ ታቸውም ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል ። ፲፩ : የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት የዩኒቨርሲቲው ዋና መሪና አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ • የዩኒቨርሲቲውን ሥራ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተዳ ድራል ፣ ይቀጣጠራል ፤ ጅ በቦርድና በጉባዔው የተላለፉ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል ፤ ገጽ ፩ሺ፩፻፲፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ፫ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ሠራተኞች ቦርዱ በሚያ ወጣው መተዳደሪያ ደንብና መንግሥት ባጸደቀው የደሞዝ ስኬል መሠረት ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን የአስተዳደር ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ ፬ . የዩኒቨርሲቲውን ዓመታዊ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል፡ በቦርዱ ሲፈቀድ በዩኒቨርሲቲው ስም የሚደረጉ ማናቸ ውንም ስምምነቶችና የውል ሰነዶች ይፈርማል፡ ፮ ዩኒቨርሲቲው ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ዩኒቨርሲቲውን ይወክላል፡ ፯ . በዩኒቨርሲቲው ስም የባንክ ሂሣብ እንዲከፈትና እንዲን ቀሳቀስ ያደርጋል፡ ፰ ስለዩኒቨርሲቲው የሥራ እንቅስቃሴ ለቦርዱ በየሦስት ወሩ ሪፖርት ያቀርባል፡ እንደ አስፈላጊነቱ ሥልጣኑን በውክልና ይሰጣል፡ በቦርዱና በጉባዔው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲፪ ስለዩኒቨርሲቲው ም ፕሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር ፩ . የዩኒቨርሲቲው ም ፕሬዚዳንቶች በዩኒቨርሲቲው ፕሬ ዚዳንት በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩዋቸዋል፡ ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥራ በሚመለከት የዩኒቨርሲ ቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራሉ፡ ይረዳሉ፡ ለ ) ለእነርሱ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎችን ሥራ ይቆጣጠራሉ፡ በቦርዱና በጉባዔው የተላለፉ ውሣኔ ዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከ ሐ ) በቦርዱ፡ በጉባዔውና በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናሉ ። ፪ • የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በማይኖርበት ጊዜ የዩኒቨር ሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም ኘሬዚዳንት ፕሬዚዳ ንቱን ተክቶ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ ይመራል፡ ያስተባ ፲ የዩኒቨርሲቲው ሌሎች አካላት የዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ፋኩልቲዎች የምርምር ክፍሎች አመሠራረትና አሠራር እንዲሁም የአመራር አካላት አሰያየም በቦርዱ ይወሰናል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ 10 በጀት የዩኒቨርሲቲው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል፡ ሀ ) ከመንግሥት ከሚመደብለት በጀት፡ ለ ) ዩኒቨርሲቲው ከሚሰበስባቸው የአገልግሎት ክፍያዎች፡ ሐ ) ከሌሎች ምንጮች ። የሂሣብ መዛግብት ፩ ዩኒቨርሲቲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የዩኒቨርሲቲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ገጽ ፩ሺ፩፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፲፮ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ይህን ደንብ የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፪ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?