የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥራ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፰ አዲስ አበባሇካቲት ፲ ቀን ፲፱፵፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፪ / ፲፱፻፲፰ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፫ሺ፫፻፴፱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፱፻፵፰ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬፻፪፩ / ፲፱፻፵፰ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፩፱፻፶፬ አንቀጽ ፵፯፩ ) ( ሀ ) መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፪ / ፲፱፻፶፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ፪ መቋቋም የተንዳሆ የስኳር ፋብሪካ ( ከዚህ በኋላ ምድር ጅት ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የል ማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ፡፡ ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፩፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ. ፳ሺ ፩ ጽ rfa ዴራል ነጋሪትጋዜጣ ቍጥር ፡ ፲ ቀን ፬ ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት አይላይታ የአፋር ብሐ ራዊ ክልላዊ መስተዳደር ) ይሆናል ። እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጣፍ ሊኖረው ይችላል ፡፡ ፩ ዓላማ ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሉች ተክ ሉች ማልማት ፣ ስኳር ፡ የስኳር ውጤቶችንና የስኳር ተረፈ ምርቶችን በፋብሪካ ማምረት ፣ ምርቶቹን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረ ብና መሸጥ ዓላማዎቹን ስብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሉች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደለት ካፒታል ብር 4 ነጥብ ዜሮ ቴ ቢሊዮን ( ሁለት ቢሊዮን ሰማኒያ ሚሊዮን ብር ) ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፱ ነጥብ 3 ሚሊየን ( ሰጠኝ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር ) በጥሬ ገዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ፡፡ ፰ . ድርጅቱ የሚ ይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፪ . ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ በፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፰ ዓ.ም. መለስ ዘናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ