የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፬ አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅቁጥር ፩፻፭ / ፲፱፻፲ ዓም ለመንገዶች ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ከዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ . . . . . ገጽ ፯፻፳ አዋጅቁጥር ፩፻፭ / ፲፱የኝ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ለመንገዶች ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ኤስዲአር ፪፻፳፬ ሚሊዮን ፭፻ሺህ ሁለት መቶ ሃያ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ኤስዲ አር የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ጃንዋሪ ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፰ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው ፣ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፯ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፡ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለመንገዶች ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፭ / ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። [ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ• ሺ፩ ገጽ ፯፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ጃንዋሪ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፰ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመው ቁጥር ፫ሺ፴፪ ኢት• የብድር ስምምነት ነው ። የገንዘብ ሚኒስትሩ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በብድር ስምምነቱ የተገኘውን ኤስዲአር ፪፻፳፬ ሚሊዮን ፭፻ ሺህ ( ሁለት መቶ ሃያ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ኤስዲአር ) በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራላይ እንዲውል ለማድረግበዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ድርጅት