ሠላሳ አንደኛ ዓመት ቍጥር ፲፮
ነ ጋ ሪ ት ' ጋ ዜ ጣ ።
የጋዜጣው ዋጋ
ባገር ውስጥ ባመት
ለውጭ አገር እጥፍ ይሆናል "
ማ ው ጫ ።
፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
አዋጅ ቍጥር F ፻፩ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በጽሕፈት ሚኒስቴር ተጠባባቂነት የቆመ ።
የንግድ ሥራንና ዋጋን ለመቈጣጠር የወጣ
ገጽ ፩፻፬
አዋጅ ቍጥር ፫፻፩ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. የንግድ ሥራንና ዋጋን ለመቈጣጠር የወጣ አዋጅ
ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ለነፃ ውድድር እንቅፋት የሆኑትን የንግድ ሥራዎች መከ ልከልና አሁንም ሆነ ወደፊት ተገቢ ካልሆነ የንግድ ሥራ ሕዝቡን ለመጠበቅ ሌሎችን የንግድ ሥራዎችና ዋጋን ለመ ቈጣጠር አስፈላጊ ስለሆነ ፤
በንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚደረገውን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለመከልከልና ዕቃዎች እንደልብ በማይ ገኙበት ጊዜ የተባሉት ዕቃዎች በሚገባ መከፋፈላቸውን ለማ ረጋገጥ ሥልጣን እንዲኖር ስለሚያስፈልግ ፤
የአገር ውስጥ ንግድን ለመቈጣጠር አንድ ጠቅላላ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ስለሆነ ፤
፩ ፤ አጭር አርእስት
ይህ አዋጅ « የ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. የንግድ ሥራንና ዋጋን ለመቈ ጣጠር የወጣ አዋጅ » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ።
፪ ፤ የተሠረዙ ሕጎች
፩ በ፲፱፻፴፮ ዓ. ም. በቍጥር ፵፮ በወጣው አዋጅ የተሻሻ ለው ከውጪ አገር የሚመጡትን ዕቃዎች ዋጋ ለመ ቈጣጠር በ፲፱፻፴፭ ዓ. ም. በቍጥር ፴፰ የወጣው አዋ ጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡት የሕግ ክፍል ማስታወቂያዎች ፤ ትእዛዞችና ደንቦች ፤
፪ በሀገር ውስጥ የሚሠሩትን ዕቃዎች ዋጋ ለመቈጣጠር በ፲፱፻ ü ፮ ዓ. ም. በቍጥር ፶፫ የወጣው አዋጅና በዚህ አዋጅ ሠረት የወጡት የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ዎች ትእዛዞችና ደን q ች ፤
አዲስ አበባ ሰኔ ፲ ቀን ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
ቢ 7 ስ በወር አን: ጊዜ ይ
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ፫፻፷፬ (1364)
በሕገ መንግሥታችን በአንቀጽ ፴፬ እና ፹፰ የተጻፈውን ተመልክተንና የሕግ መምሪያና መወሰኛ ምክር ቤቶቻችን መክ ረውበት ያቀረቡልንን ተቀብለንና ፈቅደን ቀጥሎ ያለውን 88 of Our Constitution, We approve the resolution of Our አውጀናል ።