| ኣዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፯ አንቀጽ ፭ መሠረት'ቲትዩት ማቋቋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፶፭ አዲስ አበባ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፷፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፱ / ፲፱፻፷፱ ዓም የመገናኛ ብዙኃን ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፮፻፴፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፱ / ፲፱፻፳፬ የመገናኛ ብዙኃን ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የመገናኛ ብዙኃን ማሠልጠኛ ሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፬ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ “ ሚኒስትር ” ማለት የማስታወቂያና ባህል ሚኒስትር ነው ። ፫ መቋቋም ፩ . “ የመገናኛ ብዙኃን ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” ተብሎ የሚጠራ ) እራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው የሥልጠና ተቋም በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ይሆናል ። ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፡ ፩ የኢት : ጵያ ሕዝቦች ማኅበራዊ ፣ ባሕላዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲፋጠን ፡ ነፃ ፡ ዲሞክራሲያዊና በቂ መረጃ የሚያገኝ ኅብረተሰብ እንዲፈጠር ንቁና ገንቢ ሚናን የሚጫ ወት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ማፍራት : ባለሙያው ይኸንን ተግባር በብቃትና በተሟላ መልኩ ገቢራዊ እንዲያደ ርገው የሚያስችል ሙያን ማስጨበጥ ፤ ያንዱ ዋ ? 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፭፻፴፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ከብሔር ፡ ከዘር ፣ ከቋንቋ : ከሃይማኖትና ከሌሎች አድልዎች ነጻ የሆነ ፣ የመከባበርን ፡ የመተማመንን ፡ የመተሳሰብንና የመቻቻልን ባሕል የሚያጎለብት ፣ ሁለንተናዊ ሰብዕናን የሚያበለጽግ የሰውን ልጅ ክቡርነት የሚያጠናክር ትምህርት መስጠትና ባለሙያን መቅረጽ ፤ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ባሕልና ታሪክ የሚያውቅ ከሕዝቦች ጋር ግልጽ ፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት የሚኖረው የመገናኛ ብዙኃን ሰው እንዲፈጠር የሚያዘጋጅና የሚያበቃ ሙያዊ ትምህርት መስጠት ፣ ፬ የጋዜጠኛውና ባጠቃላይም የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ሁለገብ እውቀትእንዲዳብር ፤ የጋዜጠኝነት ሙያ እንዲደረጅ የሙያ ሥነ ምግባር እንዲከበር ፤ የሥራ ክቡርነትእንዲታወቅ ፈር የሚያስይዝ ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ ፤ በልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙኃን መስኮች ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን ማሠራጨት ። ፭ . የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ የሀገሪቱን የትምህርት መሠረታዊ ፖሊሲ በመከተል መንግ ሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ለሚሠሩ ጋዜጠኞ ችና ለሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ፣ እንዲሁም ለአዳዲስ ተማሪዎች የጋዜጠኝነት ሙያ ሥልጠና ይሰጣል ፣ ፪ ዲፕሎማና የምስክር ወረቀት ይሰጣል ፣ ፫ ሴሚናሮች ፡ ወርክሾፖችና ሲምፖዚየሞች ያዘጋጃል ፣ ያካሂ በሀገር ውስጥና በሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ አቻ ተቋማትና ተመሣሣይ ዓላማ ካላቸው አካላት ጋር ግንኙነት ይመሠር ታል ፡ የሥራ ዝምድና ይፈጥራል : ፭ የኢንስቲትዩቱን የማሠልጠን አቅምና የብቃት መመዘኛ ዘዴዎቹን በተመለከተ መመሪያ ያወጣል ፤ ፮ ኢንስቲትዩቱ ስለሚስፋፋበትና በተስማሚ ቴክኖሎጂና በሠ ለጠነ የሰው ኃይል ስለሚደራጅበት ሁኔታ በማጥናት ተግባ ራዊ ያደርጋል ፡ ፯ ለሚሰጠው አገልግሎት በከፊል ወይም በሙሉ ክፍያ ሊያስከ ፍል ይችላል ፣ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፡ ፬ . ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ፮- የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፡ ፩ ቦርድ ፡ ፪ . ዳሬክተር እና ምክትል ዳሬክተር ፡ ፫ • ኣካዳሚክ ካውንስል ፡ እና ፬ • አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፯ : የቦርዱ አባላት ፩ ኢንስቲትዩቱ ፯ ( ሰባት ) ኣባላት ያሉት ቦርድ ይኖረዋል ። የቦርዱ አባላት አግባብ ካላቸው ተቋሞችና ከልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሚኒስትሩ ይሰየማሉ ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ ኢንስቲትዩቱ በዓላማው መሠረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረጉን ያረጋግጣል ፡ ጀ የአስተዳደር ፖሊሲ ያመነጫል ፡ በሚኒስትሩ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል ፡ ቦርዱ ዝርዝር የስብሰባ ሥነ ሥርዓት 0 . ገጽ ፭፻፴፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. ፫ የኢንስቲትዩቱን የአካዳሚክ ፖሊሲ ያፀድቃል ፡ ፬ . ኢንስቲትዩቱ የሚተዳደርበትን መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚኒስ ትሩ አቅርቦ ያስጸድቃል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል ፡ ፭ የኢንስቲቱዩቱን አደረጃጀት ይወስናል ፡ ኢንስቲትዩቱ የሚስፋፋበትን ፡ የሚጠናክርበትንና አሠራሩ የሚሻሻልበ ትን መንገድ ይቀይሳል ፡ ፮ . የኢንስቲትዩቱን ዳሬክተርና ም / ዳሬከተር ይሾማል ፡ ፯ በኢንስቲትዩቱ በማስተማር ወይም በምርምር እንዲሁም በፕሮዳክሽንና በኢንጂነሪንግ ተግባር ላይ የተሰማሩ የአካዳ ሚክ ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚተዳደሩበትን መመ ሪያ ያወጣል ፡ ፰ የኢንስቲትዩቱን ዕቅድና ረቂቅ በጀት ለሚኒስትሩያቀርባል፡ ፱- የኢንስቲትዩቱ መለያ ምልክት የሚሆነውን ዓርማ ይወስ ፲ . ኢንስቲትዩቱ የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች ይወስናል ፡ ፲፩ . የኢንስቲትዩቱ ተማሪዎችና ሠልጣኞች አቀባበልን መመሪያ ያወጣል ፡ ፲፪ • ኢንስቲትዩቱ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር አቻ ተቋማትና ከሌሎች ጋር የሚያደርጋቸውን ስምምነቶች መርምሮ ያፀድ የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ። ፪ አስቸኳይ ሁኔታ ሲያጋጥም በቦርዱ ሰብሳቢ ጥሪ ወይም ከቦርዱ አባላት መካከል ቢያንስ ሁለት አባላት ሲጠይቁ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ፡ በስብሰባው ላይ ከግማሽ በላይ አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ቦርዱ ውሣኔ የሚያስተላልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ። ድምጽ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ሀሳብ የቦርዱ ውሳኔ ይሆናል ። ፭ ከዚህ በላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ : ለማውጣት ይችላል ። ቦርዱ የራሱ ፀሐፊ ይኖረዋል ። ፬ ስለ ኢንስቲትዩቱ ዳሬክተር ሥልጣንና ተግባር ዳሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢንስቲት ዩቱን ሥራ ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አገላለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ ዳሬክተሩ : ሀ ) ለኢንስቲትዩቱ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መርሆዎችን ተከትሎ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በኢንስትቲዩቱ ውስጥ በማስተማር ፡ በማሠልጠን ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሠማሩ የአካዳሚክ ፡ የኢንጂነሪንግና የፕሮዳክሽን ሠራተኞችን ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ደሞዝና አበላቸውን በቦርዱ ውሣኔ መሠረት ያስፈጽ ማል ፡ ሌሎች ሠራተኞችን በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ያስተዳድራል : ሐ ) የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና ረቂቅ በጀት ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ = ጽ ፮፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓም : በቦርዱ ሲፈቀድ በኢንስቲትዩቱ ሥም ማናቸውንም ውሎች ይዋዋላል ፡ ኢንስቲትዩቱን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወክላል ፤ ረ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደው በጀትና ፣ የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ በኢንስቲትዩቱ ስም የባንክ ሂሣብ ይከፍታል ፡ ያንቀሳቅሳል ፤ ሰ ) በየሶስት ወሩ ስለኢንስቲትዩቱ የሥራ እንቅስቃሴ ለቦ ርዱ ሪፖርት ያቀርባል ፡ ሸ ) በቦርዱ ስብሰባዎች ላይ በአስረጅነት ይገኛል ፤ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ዳሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኢንስቲትዩቱ ፡ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፲፩ . ስለኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳሬክተር ፩ . የኢንስቲትዩቱ ዳሬክተር በማይኖርበት ጊዜ ምዳሬክተሩ ፣ ዳይሬክተሩን ተክቶ የኢንስቲትዩቱን ሥራ ይመራል ፣ ያስተባብራል ፡ በዳሬክተሩተለይተው የሚሰጡትን ሥራዎች ያከናውናል ። ፲፪ ስለአካዳሚክ ካውንስል ኢንስቲትዩቱ በቦርዱ የሚሰየሙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘ የአካዳሚክ ካውንስል ይኖረዋል ፣ ፩ . የኢንስቲትዩቱ ዳሬክተር ፪ የኢንስቲትዩቱ ም ዳሬክተር . ፫ ሬጅስትራር . ፬- በኢንስቲትዩቱ ተማሪዎች የሚመረጥ አንድ የተማሪዎች ተወካይ . በኢንስቲትዩቱ ቋሚ መምህራን የሚመረጥ አንድ የመምህራን ተወካይ .. በቦርድ የሚመረጡ ከሦስት የማይበልጡ የፋካሊቲ አባሎች ... የአካዳሚክ ካውንስሉ ሥልጣንና ተግባር የአካዳሚክ ካውንስሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩ ፩ የኢንስቲትዩቱን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ካሌን ደር መርምሮ ለቦርድ ያቀርባል ፡ ፪ : ዲፕሎማ : ሠርተፊኬትና ልዩ ሽልማት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ለቦርዱ የውሣኔ ሀሳብ ያቀርባል ፣ ፫ የተማሪዎችና ሠልጣኞች አቀባበልን ፡ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን ፡ ምዘናን የዲሲፕሊንና የምረቃ ጉዳዮችን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል ፡ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ዘዴና ሁኔታን ይወስናል ፤ ፭ ስለአካዳሚክ ዕድገቶች ጉዳይ አጥንቶ ለቦርዱ በማቅረብ ያስወስናል ፡ ፲ ወደሚቀጥለውየትምህርት እርከን የሚሸጋገሩተማሪዎችን ዝርዝር መርምሮ ይወስናል ፡ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ፤ ፰ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆ ፩ . በፌዴራል መንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፤ ጀ ኢንስቲትዩቱ ከሚያገኛቸው የአገልግሎት ክፍያዎች እና ፫ • ከሌሎች ምንጮች ። ገጽ ፮፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፲፭ የሂሣብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብ ትና ሰነዶችን ይይዛል ። ፪ • የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ሰነዶች በዋናው ኦዲ ተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ሌሎች ኦዲተሮች በየአ መቱ ይመረመራሉ ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ