×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 76/1994 የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፲፫ አዲስ አበባ ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ጅ፮ / ፲፱፻፶፬ ዓም የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፩ሺ፮፻፷፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፻፮ ፲፱፻፲፬ ስለኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ መቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥ ፤ ኣንቀጽ ፭ በተደነገገው መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል ፩ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፻፮ ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ፡ ፩ . “ የጤና ሙያ ” ማለት ማንኛውም የሕክምና ፣ የፋርማሲ ፣ የነርስ ፡ የጤና ረዳት የቴክኒሻኖች እና ማንኛውንም የጤና አጠባበቅ ሙያን ያጠቃልላል ፤ ፪ . “ የጤና ባለሙያ ማህበር ” ማለት እያንዳንዱን የጤና ሙያ ዘርፍ የሚወክል ሕጋዊ ማህበር ነው ! ፫ . “ የጤና ተቋም ” ማለት ሆስፒታል ፣ ጤና ጣቢያ ፣ ክሊኒክ ፡ ፋርማሲ ወይም ጤና ነክ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ በሽታን የመከላከል ተግባር የሚያከናውንና በማስ ከፈል ወይም በነፃ የማከም የማዳን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው ፤ ፬ . “ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ” ማለት የጤና ወይም ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማበ ርከት እንዲቻል የሚሰጥ የሙያ ፈቃድ ነው ፤ ፭ . “ ሚኒስቴር ” ወይም ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ) ገጽ ፩ሺ፮፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም • ክፍል ፪ ስለጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ንዑስ ክፍል ፩ የጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ መቋቋም ፫ . መቋቋም ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ የሆነ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ( ከዚህ በኋላ “ ጉባኤው ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ ደንብ መሠረት ተቋቁሟል ፡ የጉባኤው ሥልጣንና ተግባር ጉባኤው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ በዚህ ደንብ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ሚኒስትሩን ያማክራል ፣ በሀገሪቱ ውስጥ የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ጥራት ባለው ሁኔታ እንዲካሄድ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል ፣ ፫ የሙያ ሥነምግባር በባለሙያዎች መተግበሩን ያረጋ ግጣል ፡ በሀገሪቱ ውስጥ በየጊዜው የሚመዘገቡትና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከመዝገብ የሚሠረዙት ባለሙያዎች ስም ዝርዝር በጽሕፈት ቤቱ በትክክል መያዙን ይከታተላል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ፭ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴን አሠራር ይቆጣጠራል ፣ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፬ ( ፪ ) ፡ ኣንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ፣ ኣንቀጽ ፲፮ ( ፩ ) መሠረት የሚቀርብለትን እንዲሁም የሚኒስቴሩን ውሣኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በመመርመርና የበኩሉን ሃሣብ በማከል ለሚኒስቴሩ ውሳኔ እንዲቀርብ ያደርጋል ፣ በሚኒስትሩ የሚመሩለትን ሌሎች ተግባራት ያከና | . Members of the Council ውናል ። ፭ . ስለጉባኤው አባላት ጉባኤው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፡ ፩ . የክልል መስተዳድር ጤና ቢሮ ወይም ቀጥታ ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግሥት የሆነ የከተማ መስተዳድር ጤና ቢሮ አንዳንድ ተወካዮች ፪ ከሚከተሉት የሚኒስቴሩ መ / ቤት አካላት የተውጣጡ ተወካዮች፡ ሀ ) የጤና አገልግሎትና ስልጠና መምሪያ ለ ) የጤና ባለሙያዎች ትምህርትና ሥልጠና ቡድን አንድ ተወካይ ሐ ) የጤና ባለሙያዎች ደረጃ ምደባና ግምገማ በድን አንድ ተወካይ መ ) የጤና አገልግሎት ቡድን አንድ ሠ ) የሕግና ሜዲኮሌጋል አገልግሎት ኣንድ ተወካይ .... ረ ) አንድ የቀዶ ሕክምና ሙያ እስፔሻሊስት ተወካይ ..... ሰ ) አንድ የውስጥ ደዌ ሕክምና ሙያ እስፔሻሊስት ፫ . ከሚከተሉት የጤና ባለሙያዎች ማኅበራት የተውጣጡ ተወካዮች ፡ ሀ ) የሐኪሞች ማህበር ሁለት ተወካዮች ለ ) የጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ማህበር አንድ የፋርማሲስቶች ማህበር ሁለት ተወካዮች መ ) የነርሶች ማህበር ሁለት ተወካዮች ሠ ) የጤና ረዳቶች ማህበር አንድ ተወካይ ረ ) የላቦራቶሪ ቴክኒሽያኖች ማህበር አንድ ሰ ) የራዲዮግራፊ ቴክኒሽያኖች ማህበር አንድ ገጽ ፩ሺ፮፻ዥ፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 7 ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓም • ፬ . የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ኣንድ ተወካይ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች ፮ ከላይ የተደነገገው ቢኖርም : ኣስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ፈቃደኛ ከሆኑ አግባብነት ያላቸው ሌሎች ኣካላትም በአባልነት ሊወከሉ ይችላሉ ። ፮ • የጉባኤው አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ማንኛውም የጉባኤው ኣባል የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት ኣለበት ፡ የዕዕ ሱስ ያልተጠናወተው፡ የአልኮል ሱሰኝነት ያልተቆራኘው ፡ የጤና ባለሙያ ከሆነ በሙያው የተመዘገበ ፡ በሥነ ምግባሩ የተመሰገነ ፡ በአዕምሮው ጤነኛ የሆነና ፡ ፮ ከሙያው ጋር በተዛመደ ወንጀል ተከሶ ያልተፈረደበት ። ፯ ከጉባኤው አባልነት ስለመነሳትና የጎደሉትን ስለመተካት ፩ አንድ የጉባኤው ኣባል በሚከተሉት ምክንያቶች ከአባ ልነት ሊነሳ ይችላል ፡ ሀ ) በዚህ ደንብ ኣንቀጸ ፮ መሠረት ከተጠቀሱት መመዘኛዎች ውስጥ አንዱን ሳያከብር ሲቀር ወይም : ለ ) ያለምንም ፈቃድ ወይም አስቀደሞ ባለማሳወቅ ከሁለት ተከታታይ መደበኛ ስብሰባዎች ቀሪ ሲሆን እና በጽሑፍም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሳያሻሽል ሲቀር ። ፪ . በአንድ የጉባኤ ኣባል ከኣባልነት መነሳት ምክንያት ክፍተት ሲፈጠር ኣባሉን መርጦ የላከው አካል ምትክ አባል መርጦ መላክ አለበት ። ስለገባዔው የአሠራር ሥነ ሥርዓት ገባኤው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ። ከአባላቱ፡ ከግማሽ በላይ ሲገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይኖራል ። እያንዳንዱ ውሣኔ በድምፅ ብልጫ የሚያልፍ ሲሆን : እኩል በኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ወሣኝ ያምዕ ይኖረዋል ። የገባኤው መደበኛ ስብሰባ በዓመት 6 ጊዜ ይካሄዳል ። ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ፡ ከገባኤው አባላት ከግማሽ በላይ የሆኑት ሲስማሙ የገባኤው ሰብሳቢ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ። የገባኤው አባላት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ። | ስለጉባኤው አካላት ጉባኤው የሚከተሉት ኣካላት ይኖሩታል ፡ ሀ ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፡ ለ ) የትምህርትና ሥልጠና ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ፡ ሐ ) የሙያ ሥነምግባር ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ፡ መ ) የምዝገባና የሙያ ፈቃድ ገዳዮች ንዑስ ኮሚቴ : ሠ ) ጽሕፈት ቤት ናቸው ። ንዑስ ክፍል ፪ ስለ ሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ስለሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው አባላት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፡ ሀ ) የገባኤው ሊቀመንበር ለ ) የገባኤው ም ሊቀመንበር ም ሰብሳቢ ሐ ) የጤና ባለሙያዎች ትምህርትና ሥልጠና በድን አንደ ተወካይ መ ) የጤና ባለሙያዎች ደረጃ ምደባና ግምገማ በድን አንድ ተወካይ ሠ ) የጤና አገልግሎት ቡድን አንድ ተወካይ ረ ) የሦስቱ ንዑሣን ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሰ ) የሕግና ሜዲኮሌጋል አገልግሎት አንድ ሸ ) የመድኃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሥልጣን ኣንድ ተወካይ ቀ ) የነርሶች ማህበር አንደ ተወካይ በ ) የተጓዳኝ መያ ኣንድ ተወካይ ገጽ አሺ ደተህ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር : ጥር ፲ ቀን ፲፻፬ ዓም ዙ የጉባኤው ሰብሳቢና ም ሰብሳቢ ከጉባኤው አባላት መካከል በሚኒስትሩ ተመርጠው ይሾማሉ ። ፫ . የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሚመረጡት ከጉባኤው አባላት መካከል ይሆናል " ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሌሎች አባላትም በኮሚቴው ሊወከሉ ይችላሉ ። ፲፩፡ ስለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሥልጣንና ተግባር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡ ፩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ያቋቁማል ፡ ሥራቸውን ያስተባ ብራል፡ ይቆጣጠራል ፡ በዚህ ደንብ መሠረት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል ፡ - የገባኤውን ውሣኔዎች ያስፈጸማል ፡ 6 • ጉባኤው በማይሰበሰብበት ጊዜ እርሱን ተክቶ ይሠራል ። ሆኖም ጉባኤው የወሰናቸውን ውሳኔዎች ለማገድ ወይም ለመለወጥ አይችልም : ፭ የጉባኤውን የዕለት ተዕለት ተግባራት ያከናውናል ፡ ፮ ከጉባኤው የሚመሩለትን ሌሎች ተግባራት ያከና ስለ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የአሠራር ሥነ ሥርዓት እ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የራሱ የስብሰባ ሥነ ሥርዓት | 12. Meetings of the Executive Committec ይኖረዋል " ዙ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደአስፈላጊነቱ ይሰበ ሰባል * ፫ ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ሲገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይኖራል ። ፬ • እያንዳንዱ ውሣኔ በድምጽ ብልጫ የሚያልፍ ሲሆን፡ ድምፅ እኩል በኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ወሣኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፭ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ” ንዑስ ክፍል ፫ ስለ ንዑሳን ኮሚቴዎች ፲፫ ስለንዑላን ኮሚቴዎች አባላት ጥንቅርና የሥራ ዘመን አ የእያንዳንዱ ንዑሳን ኮሚቴ አባላት ከጉባዔው አባላት | 13. Composition and Terms of the Sub - Committees መካከል ይመረጣሉ * ፪ የንዑስ ኮሚቴ አባላት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ። ፲፬ . የትምህርትና ሥልጠና ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሥልጣንና ንዑስ ኮሜቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ፩ በሕክምና ሙያ ሥርዓተ ትምህርት የአቀራረጽና የማሻሻል ሂደት በመላተፍ የራሱን ሀሳብ ያቀርባል ፤ ጅ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ይሰጣል ፣ ውጤቱንም ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይልካል፡ ? በዚህ ደንብ መሠረት የተላለፉ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ፩ ስለሥራው ክንዋኔ ወርሀዊ ሪፖርት ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል፡ ስለሥራው ዕድገትና መሻሻል ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሀሳብ ያቀርባል፡ ተግባርና ኃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት ይችል ዘንድ ቡድኖችን ለማቋቋም ይችላል፡ ሌሎች በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚሰጡትን ተግባራት ሐናውናል " ገጽ ሺ፮፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ! ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፲፭ • የምዝገባና የሙያ ፈቃድ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሥልጣንና ንዑስ ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . ለምዝገባና ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የማቀርቡ ማመልከቻዎችንና ተያይዘው የሚቀርቡ ማስረጃዎችን መርምሮ የምርመራውን ውጤት ከውሳኔ ሀሳብ ጋር ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል ፤ ፪ . የሙያ ፈቃድ መስፈርቶችን በየደረጃው ኣዘጋጅቶ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል ፡ የ • ስላሥራው ክንዋኔ ወርሀዊ ሪፖርት ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል ፤ ፬ . ስለሥራው ዕድገትና መሻሻል ለሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው ሀሳብ ያቀርባል ። ፭ ተግባርና ኃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት እንዲችል ቡድኖችን ለማቋቋም ይችላል ። የሙያ ሥነ ምግባር ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር ንዑስ ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . የጤና ሙያ የሚጠይቀው ሥነ ምግባር ባለመከበሩ በባለሙያ ላይ የሚቀርብ ክስን ተቀብሎ ምርመራ ያካሂዳል፡ ገዳዩን ያጣራል ፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚቀር በውን ክስ ለማየት በቂ ማስረጃ መኖሩን ካረጋገጠ፡ መልሱን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይዞ እንዲቀርብ በመግለጽ ክሱን ክስ ለቀረበበት ባለሙያ ይልካል፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ ማስረጃ ዎችን ይሰበስባል፡ በባለሙያ ላይ የቀረበውን ክስና ማስረጃ እንዲሁም በባለሙያው የተሰጠውን መልስና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የምርመራውን ውጤት ከቅጣት ሃሳብ ጋር ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል፡ ፭ . ስለሥራው ክንዋኔ ወርሀዊ ሪፖርት ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል፡ ፮ ተግባርና ኃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት እንዲችል ቡድኖችን ለማቋቋም ይችላል፡ ፯ ሌሎች በሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል ። የንዑስ ኮሚቴ የአሠራር ሥነ ሥርዓት ፩ . እያንዳንዱ ንዑስ ኮሚቴ እንደአስፈላጊነቱ ስብሰባ ይኖረዋል ። ፪ . ከእያንዳንዱ ንዑስ ኮሚቴ አባላት ከግማሽ በላይ ሲገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይኖራል ። ፫ . የእያንዳንዱ ንዑስ ኮሚቴ ውሳኔ በድምጽ ብልጫ ያልፋል፡እኩል በእኩል የተከፈለ ደምጽን በተመለከተ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ . በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ እያን ዳንዱ ንዑስ ኮሚቴ የራሱን የአሠራርና የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መመሪያ አውጥቶ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያወድቀው ሊሠራበት ይችላል ። ንዑስ ክፍል ፬ ስለ ገባዔው ጽሕፈት ቤት ፲፰ . ስለጉባዔው ጽሕፈት ቤት መቋቋም ጉባዔው ከሚኒስቴሩ መሥሪያ ቤት በሚኒስትሩ ተመርጠው | 18. Establishment of the Secretariat of the Council በሚመደቡ ሬጅስትራር፡ ምክትል ሬጅስትራር የሚመራና የዕለት ተዕለት የጽ / ቤት ተግባራት የሚያከናውን ጽ ቤት ይኖረዋል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም በ፱ : ስለጉባዔው ጽ ቤት ተግባራት የጉባዔው ጽ ቤት የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡ ፩ የሙያ ችሎታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጣ ቸውን ባለሙያዎች ሥምና የሙያ ደረጃ እንዲሁም ሌሎች አግባብ ያላቸው መረጃዎች መዝግቦ ይይዛል፡ መዝገቡም ለሕዝብ ክፍት ይሆናል፡ እንዲሁም ዝርዝሩ በየዓመቱ በመንግሥት ጋዜጣ እንዲወጣ ያደርጋል ። ፪ በሞት፡ ሞያውን በመተው፡ በወንጀል ቅጣት፡ በሥነ ምግባር ጉድለት ውሣኔዎች ወይም በመሳሰሉት ምክን ያቶች ባለሙያዎች የሚሰጡት አገልግሎት ሲቋረጥ መግቦ ይይዛል፡ ለምዝገባና ለሙያ ችሎታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችንና የባለሙያዎችን ሰነዶች ከሚኒስቴሩ ሲመራለት ለምዝገባና ለሙያ ፈቃድ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ያቀርባል ። ሌሎች ከምዝገባ ጋር የተዛመዱ ተግባራትን ያከና ፭ . የትምህርትና የሥነ ምግባር ጉዳዮችን ይቀበላል፡ ለተፈ ጻሚነታቸውም ጉዳዩ ለሚመለከተው ኮሚቴ ይመራል ፣ ፮ እንደአግባቡ ከሚኒስቴሩና ከጉባዔው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል ። ክፍል ፫ ስለመያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ምዝገባ ፳ ስለሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አስፈላጊነት ማንኛውም የጤና ባለሙያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር | 20 . ወረቀት ሊኖረው ይገባል ። ፳፩ . የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማግኘት | 21. Application for Professional Competence Confirmation የሚቀርብ ጥያቄ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በሚዘጋጅ ፎርም ተሞልቶ መቅረብ አለበት ። ፪ . አመልካቹ ከማመልከቻው ጋር የሚከተሉትን ኦሪጅናል ሰነዶች አያይዞ ማቅረብ አለበት፡ ሀ ) ሥልጠና ከወሰደበት የትምህርት ተቋም የሚቀርብ የትምህርት ማስረጃ፡ ለ ) እንደአስፈላጊነቱ በልምምድ ( ኢንተርንሺፕ ) ፕሮግራም ውስጥ ካለፈበት ተቋም የሚቀርብ ማስረጃ፡ ሐ ) ሚኒስትሩ በሚወስነው መሠረት የሙያ ብቃት ፈተና መውሰድ ያለባቸውን በተመለከተ ይህንኑ ፈተና ማለፋቸውን የሚያሳይ ማስረጃ፡ መ ) እንደአስፈላጊነቱ በሚኒስትሩ የሚጠየቁ ሌሎች ሰነዶች፡ • ኣመልካቹ ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አግባብ ባለው ደንብ የተወሰነውን ክፍያ ይከፍላል ። ፳፪ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ስለማሳደስ ፩ . የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በየአምስት ዓመቱ መታደስ አለበት፡ ፪ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማሳደስ የሚፈልግ ማንኛውም ባለሙያ የሚከተሉትን ማሟላት ኣለበት፡ ሀ ) የምስክር ወረቀቱ ጊዜ ከማለቁ ከአንድ ወር በፊት ማመልከቻ የማቅረብ፡ ለ ) የሙያ ሥነ ምግባር መለኪያዎችን የማሟላት፡ ሐ ) እንደአስፈላጊነቱ በጉባዔው የሚሰጠውን ፈተና የማለፍ፡ መ ) የማሳደሻ ክፍያ የመክፈል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፳፫ የሙያ ፈቃድ ስለማገድ ወይም ስለመሠረዝ ይህን ደንብ ወይም በዚህ ደንብ መሠረት የሚወጡ የጤና ባለሙያ ስነምግባር መመሪያዎችን የጣሰ ጤና ባለሙያ እንደሁኔታው ፈቃዱ ይታገዳል ወይም ይሰረዛል ። ክፍል ፬ ስለሚኒስትሩ ሥልጣንና ተግባር ፳፬ • ስለሚኒስትሩ ሥልጣን ፩ ሚኒስትሩ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) መሠረት የሚቀር ቡለትን ጉዳዮች ከመረመረ በኋላ ፣ ሀ ) የውሳኔ ሃሳቡን ለማጽደቅ ወይም የራሱን የተለየ ውሳኔ ለመስጠት ፣ ለ ) በአግባቡ ያልተጣራ ወይም ያልተጤነ ጉዳይ ካለ ሁኔታው እንደገና ተጣርቶ ከውሳኔ ሃሳብ ጋር እንዲቀርብ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲ መለስ ለማድረግ ይችላል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ለ ) መሠረት ለሁለተኛ ጊዜ በሚመለከተው ንዑስ ኮሚቴ የታየን ጉዳይ በተመ ለከተ ሚኒስትሩ የሚያሳልፈው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል ። ፫ ጉባዔው በሚያቀርብለት የውሳኔ ሃሳብ መሠረት ሚኒስትሩከሚከተሉት በአንዱ እንደሁኔታው ለተወሰነ ጊዜ ፈቃዱን ሊያግድ ይችላል ፣ ፩ ሳይመዘገብ ወይም የሙያ ፈቃዱን ሳያሳድስ የጤና ባለሙ ያነት ተግባር ሲሰራ ቢገኝ፡ ፪ በተሰጠው የሙያ ፈቃድ መነሻ በኃላፊነቱ በከፈተው የጤና ተቋም ውስጥ በዚህ ደንብ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሙያ ፈቃዱ የታገደበት ወይም የተሰረዘበትን ወይም የሙያ ፈቃደ ጨርሶ የሌለውን የጤና ባለሙያ ሲያሠራ የተገኘ እንደሆነ፡ ፫ በአንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ( መ ) የተጠቀሰው ህገወጥ ተግባር ለፍ ቤት ወይም ለጉባዔው ቀርቦ ውሳኔ እስኪወሰን ድረስ፡ ይሁንና በአንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተጠቀሰው ተግባር የሚታየው በሚኒስትሩ ወይም በጉባዔው ወይም በንዑስ ኮሚቴው ከሆነ እገዳው በ፮ ወር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ማግኘት አለበት ። ፬ . በአንቀጽ ፳፫ የተጠቀሰው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ጉባዔው በሚያቀርብለት የውሳኔ ሃሳብ መሠረት ሚኒስትሩ ከዚህ በሚከተሉት ሁኔታዎች በአንዱ ፈቃዱን ሊሰርዝ ይችላል፡ ሀ ) ፈቃዱ የተገኘው በሐሰት ማስረጃ አማካይነት ለመሆኑ በሚመለከተው አካል በማስረጃ ሲረጋገጥ ፣ ለ ) ለጤና ባለሙያነት ብቃት የሌለው መሆኑን በሚያሣይ ከባድ የወንጀል ድርጊት ተከሶ ጥፋተኛነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ሐ ) ሆነብሎ የጤና ባለሙያነት ስነምግባርን በሚቃረን ሁኔታ ከተሰጠው ደረጃ በላይ ሲሠራ የተገኘ እንደሆነ ፣ መ ) ከጤና ባለሙያነቱ በታገደበት ወቅት ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት ሲል የጤና ባለሙያነት አገልግሎት መስጠቱ ተረጋግጦ በተደጋጋሚ በጽሑፍ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያና የእገዳ ውሳኔ ጥሶ ሲሠራ የተገኘ እንደሆነ ፣ ፭ . የአንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተ ጠበቀ ሆኖ ፡ በወንጀል ቅጣትና በሥነምግባር ጉድለት ውሳኔዎች በእገዳም ሆነ በመሠረዝ ምክንያት አገልግሎት ሲቋረጥ የተያዘ መዝገብ ለሕዝብ ክፍት ይሆናል ። በመን ግሥት ጋዜጣም በ፰ ሰዓት ውስጥ እንዲወጣ ይደረጋል ። ፮ ሚኒስትሩ ለዚህ ደንብ አፈጻጸም የሚረዱ የጤና ባለሙያ ሥነ ምግባር መመሪያዎችን ለማውጣት ይችላል ። ገጽ ቪደቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ፲፫ ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ክፍል ፭ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፭ የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ባለሙያ ወይም መሥሪያ ቤት ወይም የጤና ተቋም ወይም ምርመራ የያዘ አካል በዚህ ደንብ የተመለከተውን ተግባር ለማከናወን ከጤና ባለሙያ ጋር በተያያዘ መረጃ ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት ። ተፈጻሚነት ስለሌላቸው ህጎች ይህን ደንብ የሚቃረን ማንኛውም ደንብ ፣ መመሪያ ወይም | 26. Inapplicable Laws አሠራር በዚህ ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳፯ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን | 27. Effective Date ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፲ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?