የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፵፪ አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፻፶፩ ዓ.ም የኢትዮ ማሌዥያ የንግድ ስምምነት ማጽደቂያ ገፅ ፩ሺህ፮ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፻፲፩ የኢትዮ ማሌዥያ የንግድ ስምምነትን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በማሌዥያ መንግሥት መካከል የተደረገው የንግድ ስምምነት ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ ም • ኩዋላ ላምፑር ላይ የተፈረመ ስለሆነ ፤ ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ ሀገሮች ከተፈ ረመና በየሕጐቻቸው መሠረትም መሟላት ያለባቸው ሕጋዊ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ከተገላለጹ በኋላ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ ስለተመለከተ ፣ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮ ማሌዥያየንግድ ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ ስምምነቱ ስለመጽደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በማሌዥያ መንግሥት መካከል ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ኩዋላ ላምፑር ላይ የተፈረመው የንግድ ስምምነት ጸድቋል ። ያንዱ ዋጋ ብር 230 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺህ፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፪ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ፫ • የአስፈጻሚው አካል ሥልጣን ይህ ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ