የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ፲፩ኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፭ ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ስለውሃ ሀብት አስተዳደር የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገጽ ፫ሺ፲፯ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፭ ፲፱፻፲፯ ስለውሃ ሀብት አስተዳደር የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በኢትዮጵያ የውሃ | pursuant to Article 5 of the Definitions of Powers and Duties ሀብት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፯ ፲፱፻፲፪ አንቀጽ ፬ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፭ ፲፱፻፮፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፯ ፲፱፻፶፪ ለተዘረዘሩት ቃላት የተሰጡት ትርጓሜዎች በተ መሳሳይ ሁኔታ በዚህ ደንብ ላይም ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፪ . “ ፖሊሲ ” ማለት የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲ ነው ። ፫ . “ አዋጅ ” ማለት የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ኣዋጅ ቁጥር ፩፻፲፯ ፲፱፻፶፪ ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፫ሺ፰፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ክፍል ዘጠኝ ስለ ክርክሮች አወሳሰን ፴፭ ስለክርክር አወሳሰን ሥነ ሥርዓት ፩ በአዋጁ አንቀጽ ፬ ፩ መሠረት ከፈቃድ ጋር የተያያዙ መብቶችን ወይም ግዴታዎችን በተመለከተ በባለፈ ቃዶች መካከል ወይም በባለፈቃድና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚነሱ ማናቸውም ክርክሮች የሚታዩበትና የሚወሰኑብት ሥነ - ሥርዓት እንደሚከተለው ይሆናል ፤ ሀ ) አቤት ባዩ የክርክሩን ፍሬ ሃሣብና ማስረጃውን በማመልከቻ ለተቆጣጣሪው አካል ያቀርባል ። ማመ ልከቻው የአቤት ባዩን ቅሬታና እንዲሰጥለት የሚፈ ልገውን ውሣኔ መግለጽ አለበት ። ለ ) ተቆጣጣሪው አካል ማመልከቻውን እንደተቀበለ ተከሣሹ መጥሪያና የማመልከቻ ቅጂ እንዲደርሰው ያደርጋል ። ክርክር የሚሰማበትን ጊዜና ቦታም ለሁለቱም ወገኖች ያሳውቃል ። ሐ ) ባለጉዳዮቹ በቀጠሮ ሰዓትና ቦታ ተገኝተው ጉዳያ ቸውን ለተቆጣጣሪው አካል ያስረዳሉ ፤ ማስረጃዎ ችንም ያቀርባሉ ። ተቆጣጣሪው አካልም የቀረቡ ለትን ማስረጃዎች ይመዘግባል ። ተቆጣጣሪው አካል ጉዳዩ በሌላ ጊዜና ቦታ እንደተይ በቀጠሮ ሊያስተላልፍ እንዲሁም በመጀመሪያውም ሆነ ከዚህ በኋላ በተያዘው ቀጠሮ ከባለጉዮቹ አንዱ በሌለበት ጉዳዩን ማየት ሊቀጥል ይችላል ። መ ) ተቆጣጣሪው አካል በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሣኔ ባለጉዳዮቹ እንዲያውቁት ማድረግና ለእያንዳንዱ ባለጉዳይ የውሣኔውን መዝገብ ግልባጭ መስጠት አለበት ። ሠ ) የዚህ ንዑስ አንቀጽ ሌሎች ድንጋጌዎች እንዲጠበቁ ሆነው በመጀመሪያ ደረጃ የማየት ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት በሚታዩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች በተቆጣጣሪው አካል ዘንድ በሚታዩ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ ። ፪ ተቆጣጣሪው አካል የቀረቡለትን ክሶች የክርክሩን ሂደትና የሰጣቸውን ውሣኔዎች መዝግቦ ይይዛል ። ፴፮ ስለ ሽምግልና ዳኝነት በአዋጁ አንቀጽ ፱፬ ) ላይ በተደነገገው መሠረት በተቆጣ ጣሪው ኣካልና በባለፈቃዱ መካከል የተፈጠረ አለመግ ባባት በቿ ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጋራ ውይይት ሊፈታ ካልቻለ አንደኛው ወገን ልዩነቶቹ ወይም አለመግባባቶቹ በሽምግልና ዳኞች እንዲታዩለቱ መጠየቅ ይችላል ። ይኸውም፡ ሀ ) እያንዳንዱ ወገን ሁለት የግልግል ዳኞች በመምረጥ ለሌላኛው ያሳውቃል ፣ ለ ) በሁለቱ ወገኖች የተመረጡት የግልግል ዳኞች ሰብሳቢ የሚሆን ሦስተኛ የግልግል ዳኛ ይመርጣሉ ። በስምምነት ሰብሳቢውን አፈጻጸሙ በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ በተደነ ገገው መሠረት ይሆናል ፣ ሐ ) የሽምግልና ዳኞች አግባብነት ባላቸው የፌዴራልና የክልል ሕጎች ይመራሉ ፣ መ ) ተከራካሪዎቹ በሽምግልና ዳኞች የሚጠየቁትን መረጃዎች የማቅረብና የመተባበር አለባቸው ፣ ገጽ ፫ሺ፯ ፤ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ሠ ) በሽምግልና ዳኞች የተወሰነበት አካል ውሣኔውን የመቀበል ግዴታ አለበት ሆኖም መብቱ ለሚፈቅ ድለት ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል ። ፪ • የሽምግልና ዳኝነቱ የሚካሄድበትና ውሳኔ የሚሰጥበት ቦታ የተቆጣጣሪው አካል ዋና መ / ቤት በሚገኝበትከተማ ይሆናል ። ፫ ለሽምግልና ዳኞች አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን ግራ ቀኞቹ በጋራ የመሸፈን ግዴታ አለባቸው ፣ በዚህ አንቀጽ ያልተሸፈኑ ጉዳዮችን አስመልክቶ የኢት ዮጵያ ፍትሐብሔር ሕግ እና የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል ። ክፍል አሥር ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴፯ መረጃዎችን የመጠየቅ ሥልጣን ተቆጣጣሪው አካል ከዚህ በታች የተመለከቱት ሰዎች | 37 . በያዙት ፈቃድ መሠረት ወይም ሕጉ በሚያዘው መሠረት ስለሚያካሄዱት ተግባር መረጃ እንዲሰጡት በዝርዝር ሊጠይቅ ይችላል ። እነዚህም ፦ ሀ ) በዚህ ደንብ ክፍል ፪ ፣ ፫ ፣ ፬ ፣ ፭ ፣ ፮ እና ፯ ድንጋጌዎች መሠረት ፈቃድ የያዘ ሰው ወይም ለ ) በአዋጁ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የውሃ ጉድጓድ የሚቆፍር ወይም ከዚሁ ጉድጓድ ውሃ የሚወስድ | 38 ማንኛውም ሰው ። ፴፰፡ የመግባት ፣ የመመርመርና ናሙናዎችን የመውሰድ ሥልጣን ተቆጣጣሪው አካል የፈቀደለት ወይም ሥልጣን የሰጠው ማንኛውም ሰው ሥልጣኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመያዝ በማንኛውም መሬት ወይም ቦታ ተገኝቶ ፣ ሀ ) የአዋጁና ድንጋጌዎች እንደዚሁም በተሰጠው ፈቃድ ውስጥ የተዘረዘሩት ገደቦችና ሁኔታዎች የተጠበቁ መሆኑን ለመከታተል ፣ ለ ) የውሃ ጥራት ሁኔታዎችን ለመመርመርና ለማጥናት ፣ ሐ ) ለአዋጁና ለዚህ ደንብ ዓላማዎች ኣስፈላጊ የሆኑ ማንኛቸውንም መሣሪያዎች ለመትከል ለመጠገን ለማንበብ ወይም ለመፈተሽ ፣ መ ) በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ተቆፍረው የወጡትን ነገሮች ለመመርመር ፣ ሠ ) በማንኛውም ዓይነት ዘዴ የተወሰደውን ወይም ሊወሰድ የሚችለውን የውሃ መጠን ለማረጋገጥ ፣ ረ ) በዚህ ደንብ መሠረት የተያዙ መዝገቦችን ለመመ ሰ ) የማንኛውንም ውሃ ናሙና ወይም ፍሳሽ ወይም የውሃ ጥራትን ሊነካ ይችላል ብሎ የሚገመተውን ማንኛውንም ነገር ለመውሰድ ፣ ሥልጣን ይኖረዋል ። ፴፱ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከመጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ ፫ሺ፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓም : ሠንጠረዥ ፩ የፈቃድ አገልግሎት ክፍያ ተመን የፈቃድ አገልግሎት የውሃ ባለሙያ የምሥክር ወረቀት ለማውጣት የውሃ ኮንስትራክሽን ባለሙያ የምሥክር ወረቀት ለማውጣት የዲዛይን የረጅም ጊዜ ባለልምድ ባለሙያ የምሥክር ወረቀት ለማውጣት የአማካሪነት አገልግሎት የብቃት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ለማውጣት የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ወይም ጠረጋ ሥራ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ 72:00 የምሥክር ወረቀት የውሃ ሥራዎች ተቋራጭነት የብቃት ምሥክር ወረቀት ለማውጣት የታከመ ቆሻሻ ወደ ውሃ አካል ለመልቀቅ ፈቃድ ለማውጣት የውሃ ለመጠቀም ፈቃድ ለማውጣት የውሃ ሥራዎችን ለመሥራት ወይም ለመለወጥ ጣልቃ ገብ ሥራዎችን መሥራት ወይም ለመለወጥ በውሃ ለመጠቀም የተሰጠ ፈቃድን ለማሠረዝ ፣ ለማስተላለፍ ወይም ለመለወጥ የውሃ ሥራዎችን ለመሥራት ወይም ለመለወጥ የተሰጠ ፈቃድን ለማራዘም ፣ ለማሠረዝ ፣ ለማስተላለፍ ወይም ለመለወጥ ቆሻሻን ወደ ውሃ አካል ለመልቀቅ የተሰጠ ፈቃድን ለመለወጥ ወይም 41:00 ለማሠረዝ የውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ዕውቅና ለማግኘት የውሃ ባለሙያ የምስክር ወረቀት ለማደስ የውሃ ኮንስትራክሽን ባለሙያ የምሥክር ወረቀት ለማደስ የዲዛይን የረጅም ጊዜ ለልምድ ባለሙያ የምሥክር ወረቀት ለማደስ የአማካሪነት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ለማደስ 91-00 የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ወይም ጠረጋ ሥራ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ 63:00 የምሥክር ወረቀት ለማደስ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭነት የብቃት የምሥክር ወረቀት ለማደስ የታከመ ቆሻሻ ወደ ውሃ አካል ለመልቀቅ የተሰጠ ፈቃድን ለማደስ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ገጽ ፪ሺ፲፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፩ . “ የውሃ ጉድጓድ ” ማለት በእጅ ከሚቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶች በስተቀር ለተለያዩ አገልግሎቶች የተለያዩ መሣሪያዎችን ( ሪግ ) በመጠቀም የከርሰ ምድር ውሃ አመንጪ ወይም አስተላላፊ አካሎችን በመዝለቅ የሚቆፈር ጉድጓድ ነው ። ፭ . “ የውሃ አቅርቦት ጉድጓድ ” ማለት ለመጠጥ ፤ ለእርሻም ለኢንዱስትሪ ወይም ለሌሎች ግልጋሎቶች የሚቆፈር ጉድጓድ ነው ። ፮ . “ የውሃ አጠቃቀም ” ማለት ውሃን ለመጠጥ ፤ ለመስኖ ለእርሻ ፤ ለኢንዱስትሪ ፤ ለኃይል ምንጭነት፡ ለትራንስ ፖርት ፤ ለቱሪዝም ፤ ለእንስሳት እርባታ ፤ ለዓሣ ማስገር ወይም ለሌሎች ግልጋሎቶች መጠቀም ማለት ነው ። ፯ . “ ተቆጣጣሪ አካል ” ማለት የውሃ ሀብትሚኒስቴር ወይም በአዋጁ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ / ፪ መሠረት ከሚኒ ስቴሩ ውክልና የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ሁለት የውሃ ሀብት አጠቃቀም የፈቃድ ማመልከቻ በአዋጁ አንቀጽ ፲፫ ድንጋጌ መሠረት በውሃ ሀብት ለመጠቀም ፈቃድ እንዲሰጥ ለተቆጣጣሪ አካል የሚቀርብ ማመልከቻ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ አለበት ፣ ህ ) የአመልካቹን ስምና ቋሚ አድራሻ ፤ ለ ) የውሃ ሀብቱ የሚገኝበትንና ጥቅም ላይ የሚውልበትን ክልል ልዩ ቦታ ፤ ሐ ) የውሃ ሀብቱ ጥቅም ላይ እንዲውል የታቀደበት የግል ጋሎት ዓይነት ፤ መ ) በየወሩና በየዓመቱ ሊወሰድ የታቀደው የውሃ መጠን ፤ ሠ ) በምን ዓይነት ዘዴ ወይም ሁኔታ ውሃን ወስዶ ለመጠቀም እንደታቀደ ፤ ረ ) እንደኣግባቡ የኢንቨስትመንት ሠርቲፊኬት ፤ ሰ ) ተቆጣጣሪው አካል ያስፈልጋሉ ብሎ የሚጠይቃቸው ዝርዝር ጥናቶችና ካርታዎች ፣ የተቆጣጣሪው አካል ተግባራት የመጠቀም ማመልከቻ ተቆጣጣሪው አካል ሲደርሰው ማመልከቻው የደረሰው መሆኑን ወዲያውኑ ለአመልካቹ በጽሑፍ ያረጋ ፪ ተቆጣጣሪው አካል በውሃ ሀብት ለመጠቀም ፈቃድ ለማግኘት የቀረበ ማመልከቻን በሚያይበት ጊዜ ፤ በአመ ልካቹ የቀረበው በውሃ ሀብት የመጠቀም ጥያቄ ፖሊሲውን ፤ የተፋሰስ ማስተር ፕላኖችን ፣ አዋጁን ፣ ይህ ደንብ እና መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ መሆኑን ያረጋግጣል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ተቆጣጣሪው አካል የቀረበውን ማመልከቻ አስመ ልክቶ የሚሰጠውን ውሣኔ ለአመልካቹ ማስታወቅ አለበት ። ተቆጣጣሪው አካል በውሃ ሀብት የመጠቀምማመልከቻን አስመልክቶ የሰጠውን ውሣኔ ፤ በአዋጁ አንቀጽ ፲፪ መሠረት መዝግቦ መያዝ አለበት ። ፭ ጥቅም ላይ የዋለ ውሃን ስለመልቀቅ የአዋጁ አንቀጽ ፲፫ / ፪ / እና የዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፩ እንደተ ጠበቁ ሆነው በውሃ የመጠቀም ፈቃድ ጥቅም ላይ የዋለ ውሃን በአግባቡ ኣክሞ ወደ ውሃ ሀብት የመልቀቅ መብትን ጨምሮ ሊሰጥ ይችላል ። ጽ ፪ሺ፲፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም • በውሃ የመጠቀም ፈቃድን ስለመሰረዝ ፤ ማገድ ፤ ማስተላለፍና በአዋጁ አንቀጽ ፲፯ መሠረት በውሃ የመጠቀም ፈቃድ በተቆጣጣሪው አካል በሙሉ ወይም በከፊል ሊታገድ ወይም ሊሰረዝ ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ፈቃዱን በሙሉ ወይም በከፊል ሊያሳግዱ የሚችሉ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው ። ሀ ) በፈቃዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ገደቦችና ግዴታዎች አለመጠበቅ ወይም አለማክበር ፤ ለ ) ከተፈቀደ አገልግሎት ውጪ በውሃ መጠቀም ፤ ሐ ) የውሃ ግልጋሎት ዋጋ ማስታወቂያ በደረሰ በስድሳ ( ፳ ) ቀናት ውስጥ የውሃ ግልጋሎት ዋጋ ያለመ መ ) የውሃ ሀብቱ ጊዜያዊ በሆነ መልክ እየመነመነ መሆኑን ተቆጣጣሪው አካል ሲደርስበት ፤ ሠ ) የውሃ ጥራት ደረጃዎችን አለመጠበቅ ፤ ፫ . ተቆጣጣሪው አካል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክን ያቶች የሰጠውን ፈቃድ ሊሰርዝ ይችላል ፤ ሀ ) በፈቃድ ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ በተፈቀደው ፈቃድ ሳይጠቀሙ መቅረት ፤ ለ ) ተቆጣጣሪው አካል ሳይፈቀድ በውሃ የመጠቀም ፈቃድን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ። ሐ ) ባለፈቃዱ ፈቃዱን ሊያገኝ የቻለው የሀሰት ማስረጃ በመስጠት መሆኑ በተቆጣጣሪው አካል ሲረጋገጥ ፤ መ ) የውሃ ሀብቱ ዘለቄታዊ በሆነ መልክ እየመነመነ መሆኑን ሲያረጋግጥ ፤ ሠ ) የባለፈቃዱ የውሃ አጠቃቀም በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፱ / ፲፱፻፶፭ በተደነገጉት ድንጋጌዎች መሠረት በአካባቢው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ሲረጋገጥ ፤ ፬ • ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ከተዘረ ዘሩት ምክንያቶች ማናቸውም መፈጸማቸውን ሲያረጋግጥ ለፈቃድ ያዡ በሚሰጠው የአሥራ አምስት ቀናት የጽሑፍ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ባለፈቃዱ ሁኔታውን በማስረጃ ካላስተባበለ በስተቀር ፈቃዱን በከፊል ወይም በሙሉ ሊያግድ ይችላል ። ፭ ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫ ሐ ከተመለከተው ምክንያት በስተቀር በንዑስ አንቀጽ ፫ / ሀ [ ለ / መ / ወይም / ሠ / የተዘረዘሩት ምክንያቶች መፈጸማ ቸውን ሲያረጋግጥ ለፈቃድ ያዡ በሚሰጠው የአሥራ አምስት ቀናት የጽሑፍ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ባለፈቃዱ ሁኔታውን በማስረጃ ካላስተባበለ በስተቀር ፈቃዱን ሊሰርዝ ይችላል ። በውሃ የመጠቀም ፈቃድ እንዲለወጥለት ወይም በሙሉ ወይም በከፊል እንዲተላለፍለት ፈቃድ ያዡ ለተቆጣ ጣሪው አካል ሊያመለክት ይችላል ። ማመልከቻውም በውሃ የመጠቀም ፈቃዱ እንዲለወጥ ወይም እንዲተላለፍ የተፈለገበትን ምክንያትና መለወጡን ወይም መተላለፉን ለመፈጸም እንዲሟሉ የሚያስፈልጉትን ሁኔታዎችና ገደቦች መግለጽ አለበት ። ገጽ ፫ሺ፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም ፯ . ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ መሠረት የተወሰደ ማንኛውንም እርምጃ በውሃ የመጠቀም ፈቃድ መዝገብ ውስጥ እንዲመዘገብ ያደርጋል ። ክፍል ሦስት የውሃ ሥራ ፈቃድ ፯ . ማመልከቻዎችና አፈጻጸማቸው የውሃ ሥራዎች የመሥራት ፤ የማደስ ወይም የመለወጥ ፈቃድን የሚመለከት ማመልከቻ ለተቆጣጣሪው አካል መቅረብ አለበት ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የሚቀርበው ማመልከቻ የውሃ ሥራውን ዲዛይን ፤ ደህንነትና አደጋ አልባነትን ያካተተ ሙሉ ዝርዝር ጥናት የያዘ መሆን ኣለበት ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የውሃ ሥራዎችን ለመሥራት ለማደስ ወይም ለመለወጥ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ንዑስ ኣንቀጽ ፩ ፣ ፪ ፣ ፫ ፣ እና ፬ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ቿ ፈቃዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜና የሚራዘምበት ሁኔታ የውሃ ሥራዎች ፈቃድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የውሃ ሥራውን የአገልግሎት ዘመን ታሳቢ በማድረግ በተቆጣ ጣሪው አካል ይወሰናል ። የውሃ ሥራውን ለመሥራት በፈቃዱ ውስጥ ተወስኖ የተጠቀሰው የፈቃድ ጊዜ የውሃ ሥራውን ፕሮጀክት ባህሪ መሠረት በማድረግ በተቆጣጣሪው አካል ሊራዘም ይችላል ። ፱ : በፈቃድ ያዡ እና በተቆጣጣሪው አካል መፈጸም ስላለባቸው ተግባራት የውሃ ሥራውን ለመሥራት በተወሰነው ወይም በተራ ዘመው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲሠራ የተፈቀደው ሥራ እንደተጠናቀቀ ወይም ከመጠናቀቁ በፊት ወዲያውኑ እንደነገሩ ሁኔታ ፈቃድ ያዡ ለተቆጣጣሪው አካል ሥራው መጠናቀቁን ወይም ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበ ቀውን ጊዜ በጽሑፍ ማስታወቅ ኣለበት ። ፪ . ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ስለሥራው መጠናቀቅ ማስታወቂያ ሲደርሰው ሥራው የተሠራው በፈቃዱ ውስጥ በተመለከቱትገደቦች እና ሁኔታዎች መሠረት መሆኑን ያረጋግጣል ። በውሃ መውረጃዎች ወይም በውሃ ሥራዎች ጣልቃ ስለሚገቡ ፩ ከተቆጣጣሪው አካል ፈቃድ ሳይሰጠው ማንኛውም ሰው በውሃ ጉዞ ላይ ችግር የሚያስከትል ፤ የውሃ መውረጃን አቅጣጫ የሚቀይር ፤ በውሃ መውረጃው የሚፈሰውን የውሃ አፈሳሰስ ፤ ፍጥነትንና ኃይል የሚለውጥ ወይም የማንኛውንም የውሃ ነክ ሥራ ትክክለኛ እንቅስቃሴ የሚገታ መሰናክል ሊሰራ ወይም ሊያስቆም አይችልም ። • ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የቀረበን ማመልከቻእንደተቀበለ በእቅዱና በሃሳቡ የታቀ ፈውን ሥራ ዓላማ ፤ እቅዱና ሀሳቡ የሚመለከተው የውሃ መውረጃ በመስጠት ላይ ያለውን ግልጋሎት ሁኔታ የመጠበቅና የመንከባከብ ኣስፈላጊነትን ግምት ውስጥ በማስገባት ሥራው እንዲሠራ ሊፈቅድ ወይም ለውሃ መውረጃ ደህንነት በቂ ዋስትና ካልተሰጠ በስተቀር ላይፈቅድ ይችላል ። ገጸ ፫ሺ፰፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ክፍል አራት የውሃ ጥራት ቁጥጥር ፲፩ የታከመ ቆሻሻ ውሃ የመልቀቅ ፈቃድ ፩ በአዋጁ አንቀጽ ፲፫ ፪ እና በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ድንጋጌዎች መሠረት ማንኛውም ሙያ ነክ ወይም ኢንዱስትሪ ነክ ፍሣሽን ወይም የተበከለ ፍሳሽን ወይም ማንኛውንም መርዛማ ፣ ጐጂ ወይም በካይ ነገርን አክሞ በየብስ ውሃ ወይም በከርሰምድር ውሃ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለመልቀቅ የሚያስችል ፈቃድን ለማግኘት ማመልከቻ ለተቆጣጣሪው አካል መቅረብ አለበት ። ፪ ተቆጣጣሪው አካል ውሃ ሀብት ውስጥ የታከመ ቆሻሻ የመልቀቅ ፈቃድ ለመስጠት ወይም ለመከልከል ከሌሎች ሁኔታዎች በተጨማሪ የፍሣሽ እና የጅረት ውሃ ጥራት ደረጃን ግምት ውስጥ ያስገባል ። ፫ ከዚህ በላይ የተመለከቱት የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጾች እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ደንብ ኣንቀጽ ፬ ውስጥ የተደነገጉት ሁኔታዎች የታከመቆሻሻ ለመልቀቅ ፈቃድ ለመጠየቅ በሚቀርቡማመልከቻዎችም ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል ። ፲፪ : የታከመ ቆሻሻ ውሃ የሚለቁ ሰዎች ግዴታ ፩ . ማንኛውም ውሃን ለኢንዱስትሪ ወይም ብክለትን ሊያስ ከትል ለሚችል ማንኛውም ሥራ ወይም አገልግሎት የሚጠቀም ሰው ፤ የቆሻሻ ማጣሪያ ዘዴዎችን ወይም መሣሪያዎችን የመትከልና የመጠቀም ግዴታ አለበት ፣ ለ ) እንዲለቅ የተፈቀድለትን የታከመ ቆሻሻ ዓይነትና መጠን ብቻ መልቀቅ አለበት ፣ ሐ ) ተቆጣጣሪው አካል በማናቸውም ጊዜ የሚለቀውን የታከመ ቆሻሻ ናሙና እንዲወስድ የመፍቀድ ግዴታ አለበት ፣ የዚህን አንቀጽ ድንጋጌዎች ለማስፈፀም ሚኒስቴሩ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ፣ ፲፫ የታከመ ቆሻሻ የመልቀቅ ፈቃድ እድሳት ፩ የታከመ ቆሻሻ ወደ ውሃ ሀብት የመልቀቅ በተቆጣጣሪው አካል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በየሁለት ዓመቱ መታደስ አለበት ። ፪ የታከመ ቆሻሻ የመልቀቅ ፈቃድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከማለቁ ከአንድ ወር በፊት እንዲታደስ ፈቃድ ያዡ ለተቆጣጣሪው አካል ማመልከት ይኖርበታል ። ፫ . ተቆጣጣሪው አካል የታከመ ቆሻሻ የመልቀቅ የፈቃድ ማሳደሻ ማመልከቻውን በተቀበለ በአምስት ቀናት ውስጥ በማመልከቻው መሠረት ፈቃዱ ባለበት ሁኔታ መታደሱን ወይም በፈቃዱ ላይ ማሻሻያ ተደርጐ መታደሱን ወይም ማመልከቻው ውድቅ መደረጉን ለአመልካቹ በጽሑፍ ያሳውቃል ። ፬ . ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ንዑስ አንቀጽ መሠረት ተቆጣ ጣሪው አካል ማመልከቻውን ውድቅ ካደረገ ወይም በፈቃዱ ላይማሻሻያዎች ካደረገ ውሳኔው የተመሠረተባ ቸውን ምክንያቶች ጨምሮ በጽሑጽ ለአመልካቹ ማሳወቅ አለበት ። ፭ ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫ መሠረት የወሰዳቸውን ማናቸውንም ዓይነት እርም ጃዎች በውሃ የመጠቀም ፈቃድ መዝገብ ውስጥ ይመዘ ገጽ ፫ሺ፰፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓም ፲፬ የታከመቆሻሻ ውሃ የመልቀቅ ፈቃድ መሰረዝ ወይምመታገድ | 14. Tremination or Suspension of Treated Waste Water በአዋጁ አንቀጽ ፲፯ ለተቆጣጣሪው አካል በተሰጠው ስልጣን የታከመ ቆሻሻ ውሃ የመልቀቅ ፈቃድን በሙሉ ወይም በከፊል ሊያሳግዱ የሚችሉ ምክንያቶች የሚከ ተሉት ናቸው ። ሀ ) በፈቃዱ ውስጥ የተጠቀሱ ገደቦችና ሁኔታዎችን አለመጠበቅ ወይም አለማክበር ፣ ለ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፪ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች መተላለፍ ፣ ባለፈቃዱ ፈቃዱን ሊያገኝ የቻለው የሀሰት ማስረጃ በመስጠት መሆኑ በተቆጣጣሪው አካል ሲረጋገጥ ፈቃዱ ሊሰርዝ ይችላል ። ተቆጣጣሪው አካል በዚህ አንቀጽ መሠረት የተወሰደ ማንኛውምንም እርምጃ የታከመ ቆሻሻ የመልቀቅ ፈቃድ መዝገብ ውስጥ እንዲመዘገብ ማድረግ አለበት ፣ ፲፭ የውሃ አቅርቦት ጉድጓዶች የሚቆፈሩበት ቦታ የውሃ አቅርቦት ጉድጓድ የሚቆፈርበት ቦታና ሁኔታ በሚኒ ስቴሩ በሚወጣ መመሪያ መሠረት ይወሰናል ። ፲፮ የከርሰ ምድር ውሃ ጥራት ምርመራ ፩ . የውሃ አቅርቦት ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የጉድጓድ ውሃ ናሙና ሕጋዊ ፈቃድ ላለው ላቦራቶሪ ቀርቦ ለመጠጥነት የሚውል መሆኑ መረጋገጥ አለበት ። ፪ . የማንኛውም የውሃ አቅርቦት ጉድጓድ ጠረጋ ሥራ ከተካሄደ በኋላ ከጉድጓዱ እድሜ አንጻር ወይም በጠረጋው ሥራ ምክንያት በውሃው ጥራት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የባክቴሪዎሎጂካልና የኬሚካል ለውጦች መኖ ራቸውን ወይም አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ ሕጋዊ ፈቃድ ባለው ላቦራቶሪ የውሃው ናሙና ቀርቦ ምርመራ መደረግ አለበት ። ፲፯ ስለ ውሃ አቅርቦት ጉድጓዶች አያያዝ ፩- የውሃ አቅርቦት ጉድጓድ ውስጥ ማንኛውም በካይ ፍሳሽ ሰርጐእንዳይገባ በጉድጓዱ ቀፎና በጉድጓዱ መካከል ያለ ክፍት ቦታ መታሸግ አለበት ። ፪ . ማንኛውም የውሃ ጉድጓድ በቁፋሮና በግንባታ ወቅት በሚያጋጥሙ ችግሮች ሥራው ሳይጠናቀቅ ቢቀር በሰውና በእንስሳት ላይ አደጋ እንዳይደርስና የከርሰ ምድር ውሃ አዘል አካል እንዳይበክል ቆፋሪውጉድጓዱን በጥንቃቄ መድፈን አለበት ። ፲፰ ዘገባ የማቅረብ ግዴታ በዚህ ደንብ በተገኘ ፈቃድ መሠረት ሥራቸው ስለተጠናቀቀ ወይም ስላልተጠናቀቀ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራዎች አፈፃፀም ቆፋሪው ሥራው ከተጠናቀቀ ወይም ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ በ፴ ቀናት ውስጥ ለተቆጣጣሪው አካል ዘገባ የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ክፍል አምስት ስለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ስለ ደረጃ አመዳደብ ፲፱ : ስለውሃ ሥራዎች ግንባታ ፩ በማንኛውም የውሃ ሥራዎች መስክ መሰማራት የሚፈልግ ባለሙያ ከተቆጣጣሪው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እስከሌለው ድረስ በአዋጁ አንቀጽ ፲፩ መሠረት የውሃ ሥራዎች ግንባታ ሥራ ማከናወን አይችልም ። ፪ . ማንኛውም ሕጋዊ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ የውሃ ሥራዎች ግንባታን በተመለከተ ከማንኛውም ሰው ጋር ውል ከመፈጸሙ በፊት የውሃ ሥራው እንዲሠራ በተቆጣ ጣሪው አካል የተፈቀደ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ገጽ ፫ሺ፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም የውሃ ሥራዎች ግንባታ እንዲሠራለት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ጋር ውል ከመፈጸሙ በፊት የሥራ ተቋራጩ ድርጅት ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያለው መሆኑን እና ባለሙያዎቹም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ፳ አስፈላጊዎች ፩ . ማንኛውም የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ሚኒስቴሩ በሚያ ወጣው መመሪያ ውስጥ የሚዘረዘሩ መሣሪያዎችና ባለሙያ ያሉት ወይም የእነዚህኑ መሣሪያዎችና ባለሙ ያዎች አገልግሎት ሊያገኝ የሚችል መሆን አለበት ። የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ለመሆን ያመለከቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት በመመሪያው ተዘርዝሮ የተቀመጠውን መመዘኛ አሟልተው ሲገኙ በሚመጥኑት ደረጃ በተቆጣጣሪው አካል ይመደባሉ ። ፳፩ ስለደረጃ አመዳደብ ፩ . ተቆጣጣሪው አካል የውሃ ሥራዎች ባለሙያ ለመሆን የቀረበ ማመልከቻን በመገምገም ፣ ሀ ) አመልካቹ አዋጁ ፣ ደንቡ እና መመሪያው የሚጠይ ቃቸውን ሁኔታዎች የሚያሟላ ሆኖ ሲያገኘው ደረጃውን በመመደብ አመልካቹ በአለው ደረጃ ለመሥራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ለ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ / ሀ / መሠረት የቀረበ ማመልከቻን ተቆጣጣሪው አካል ሲመረምር አዋጁ ፣ ደንቡና መመሪያው የሚጠይቃቸውን ሁኔታዎች የማያሟላ ሆኖ ሲያገኘው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን ይከለክላል ፤ የከለከ ለበትንም ምክንያት ለአመልካቹ ያሳውቃል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን በየዓመቱ ለተቆጣ ጣሪው አካለ ቀርቦ መታደስ አለበት ። ፫ ተቆጣጣሪው አካል የሰጠውን የውሃ ሥራዎች ተቋራ ጭነት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን ተቋ ራጩ በምስክር ወረቀቱ የተዘረዘሩ ግዴታዎችን ባለመ ፈፀሙ ምክንያት በማንኛውም ጊዜ ለመሰረዝ ይችላል ። ክፍል ስድስት ስለአማካሪነት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ፳፪ • የአማካሪነት አገልግሎት ብቃትማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ኣስፈላጊነት በአዋጁ አንቀጽ ፲፱ እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ከተቆጣ ጣሪው አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳያኖረው ለንግድም ሆነ ለሌላ ዓላማ ከውሃ ሀብት ጥናት ፣ ዲዛይን ፣ ቁጥጥር እና ግንባታ ጋር የተያያዘ የአማካሪነት አገልግሎት ለመስጠት አይችልም ። ፳፫ • የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማውጣት ስለሚቀርብ ማመልከቻ የአማካሪነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ መሠረት የሚጠየቁ አግባብ ያላቸው መረጃዎችን የያዘ ማመልከቻ ለተቆጣጣሪው አካል ማቅረብ አለበት ። ገጽ ፫ሺ፰፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም : ፳፬ • የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ስለመስጠት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፳፫ መሠረት ለተቆጣጣሪው አካል ማመልከቻ በደረሰው አስር ቀናት ውስጥ አመልካቹ በመመሪያ የወጣውን ደረጃ ያሟላ መሆኑን በመገምገምና ብቁነቱን በማረጋገጥ የተጠየቀውን የብቃት በማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ወይም ማመልከቻውን ያልተቀ በለው ከሆነ ያልተቀበለበትን ምክንያት በጽሑፍ ለአመልካቹ ያሳውቃል ። ፳፭ ስለ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እድሳት ፩ . የአማካሪነት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተቆጣጣሪው አካል በተሰጠ በየአመቱ መታደስ አለበት ። ፪ . ተቆጣጣሪው አካል የእድሳት ጥያቄ ሲቀርብለት የአማካሪ ኣገልግሎቱ የሚጠበቅበትን ግዴታ አክብሮና ደረጃውን ጠብቆ የሠራ መሆኑን አረጋግጦ የምስክር ወረቀቱን ያድሳል ። ፫ . ተቆጣጣሪው አካል የምስክር ወረቀት እድሳት ጥያቄውን ያልተቀበለው ከሆነ ያልተቀበለበትን ምክንያት በአስር ቀን ውስጥ በጽሑፍ ለአመልካቹ ያሳውቃል ። ፳፮ ስለ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ክፍያ የአማካሪነት አገልግሎት የምስክር ወረቀት ለማውጣትና ለማሳደስ የሚደረገው ክፍያ በሕግ በሚወሰነው መሠረት ይሆናል ። ፳፯ : ስለ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መሰረዝ ፩ ተቆጣጣሪው አካል የአማካሪነት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከሚከተሉት ምክንያቶች ባንዱ ሊሰርዝ ይችላል ። ሀ ) የምስክር ወረቀቱ የተሰጠው ሀሰተኛ መረ በማቅረብ መሆኑ ሲረጋገጥ ፣ ለ ) የአማካሪነት አገልግሎቱ የዚህን ደንብ ድንጋ ጌዎችእና ይህን ደንብ ለማስፈጸም የወጡ መመሪያ ዎችን ባለማክበሩ በተቆጣጣሪው አካል የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በተሰጠው የአንድ ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ጉድለቶቹን ያላስተካከለ ከሆነ ፣ ፪ • የምስክር ወረቀት የተሰረዘበት ወይም ሥራውን ያቋረጠ ማንኛውም የአማካሪነት አገልግሎት ሰጪ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን ለተቆጣጣሪው አካል መመለስ አለበት ። ክፍል ሰባት የውሃ ተገልጋዮች ማህበራት ፳፰ ስለ ማህበሮች መቋቋም ፩ በአዋጁ አንቀጽ ፳፯ / ፪ / መሠረት በውሃ የመጠቀም ፈቃድ ያላቸው ወይም ከፍቃድ አስፈላኒት ነጻ የሆኑ ሰዎች የውሃ ተገልጋዮች ማህበር ማቋቋም ይችላሉ ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት በሚቋቋሙ የውሃ ተገልጋዮች ማኅበራት ላይ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ ፲፱፻፲፩ ተፈጻሚ ይሆናል ። ፳፱ ስለማኅበራት ምዝገባ ፩ የሚቋቋመው የውሃ ተገልጋዮች ማኅበር የመለስተኛ ወይም ከፍተኛ መስኖ ልማትን የሚመለከት ከሆነ በተቆጣጣሪው አካል መመዝገብ አለበት ። ገጽ ፫ሺ፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ መጋቢት ፳ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ፪፡ የሚቋቋመው የውሃ ተገልጋዮች ማኅበር የአነስተኛ መስኖ ልማትን የሚመለከት ከሆነ በክልሉ ወይም በከተማ መስተዳድሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማደ ራጀት በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል መመዝገብ አለበት ። ፫ : በየክልሉ ወይም በከተማ መስተዳድር ደረጃ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማደራጀት በሕግ ሥልጣን የተሰ ጣቸው አካላት የውሃ ተገልጋዮች ማኅበራትን የሚመ ለከቱ መረጃዎችን ለተቆጣጣሪው አካል የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው ። ክፍል ስምንት ስለፈቃድ ክፍያ እና የውሃ ግልጋሎት ዋጋ ስለፈቃድ አገልግሎት ክፍያ በአዋጁ እና በዚህ ደንብ መሠረት የሚሰጡ ፈቃዶችን ለማግኘትና እነዚሁ ፈቃዶች እንዲታደሱ ፣ እንዲሠረዙ ፣ እንዲለወጡ ወይም እንዲተላለፉ ማመልከቻዎች ሲቀርቡ በዚህ ደንብ በሠንጠረዥ ፩ ላይ የተወሰኑ የአገልግሎት ክፍያዎች ለተቆጣጣሪው አካል መከፈል አለባቸው ። ፴፩ ስለ ውሃ አገልግሎት ዋጋ ፩ . በአዋጁ እና በዚህ ደንብ መሠረት የውሃ ሀብትን ለማንኛውም ለተፈቀደ ግልጋሎት ለማዋል የውሃ ግልጋሎት ዋጋ ለተቆጣጣሪው አካል መከፈል አለበት ። በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚከፈሉ የውሃ አገልግሎት ዋጋዎች በተቆጣጣሪው አካል ተተምነው በክፍያ መጠየቂያ በዓመት አንድ ጊዜ ወይም እንደ ሁኔታው ከዚህ ባጠረ ጊዜ ውስጥ መከፈል አለባቸው ። የውሃ አገልግሎት ዋጋ በዋጋ መጠየቂያ ማስታወቂያ ውስጥ ከሚጠቀሰው ቀን ጀምሮ በ፳ ቀናት ውስጥ መከፈል አለበት ። የውሃ አገልግሎት ዋጋ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወሰናል ። ፴፪ በውሃ ሀብት ውስጥ የታከመ ቆሻሻን ለመልቀቅ ወይም ለመድፋት ስለሚደረግ ክፍያ በአዋጁ እና በዚህ ደንብ መሠረት በውሃ ሃብት ውስጥ የታከመ ቆሻሻን ለመልቀቅ ወይም ለመድፋት ፈቃድ የተሰጣቸው ሰዎች በሕግ የተወሰነ ክፍያ ለተቆጣጣሪው አካል መክፈል አለባቸው ። በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚከፈሉ ክፍያዎች በየዓመቱ በክፍያ መጠየቂያ ማስታወቂያ ውስጥ ከሚጠቀሰው ቀን ጀምሮ በ፰ ቀናት ውስጥ መከፈል አለባቸው ። ፴፫ ከመንግሥት ፕሮጀክት ለተወሰደ ውሃ ስለሚፈጸሙ ክፍያዎች በዚህ ደንብ በተሰጠ ፈቃድ መሠረት ከመንግሥት ፕሮጀክት ለተወሰደ ውሃ የሚከፈለው ክፍያ መዋዕለ ወጪውን ተመላሽ በማስደረግ መሠረተ ሃሣብ ላይ ተመሥርቶ በተቆጣጣሪው አካል በሚሰላ ተመን መሠረት ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚከፈሉ ክፍያዎች በየዓመቱ በክፍያ መጠየቂያ ማስታወቂያ ውስጥ ከሚጠቀሰው ቀን ጀምሮ በ፰ ቀናት ውስጥ መከፈል አለባቸው ። ፴፬ • የውሃ ግልጋሎት ዋጋን ሳይፈጽሙ መቅረት ስለሚያስከ ትለው ውጤት ተቆጣጣሪው አካል የውሃ ግልጋሎት ዋጋ መከፈል ከነበረበት የመጨረሻ ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ሥልሣ ( ፰ ) ተጨማሪ የችሮታ ቀናት ውስጥ ካልተከፈለ የውሃውን አገልግሎት ማቋረጥ ይችላል ።