የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፬ አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻T፰ ዓም የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ . . . . . . . . . . . . ገጽ ፻፵ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ ፲፱፻፫፫ዓ . ም የኢትዮጵያ የጤናና ሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ . . . . . . . . . . . ገጽ ፻፴፩ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻ዥ፰ የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ - የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት የተቋቋመበትን | አዋጅ ቁጥር ፪፻ሮ፩ ፲፱፻፸፯ መሻር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | 271 / 1985 : መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻ዥ፰ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪• መሻር የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1 2 Repeal ፪፻፸፩ ፲፱፻ሮ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፫• መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ የብሔራዊ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት መብትና ግዴታ በሚኒስ | 3 . Transfer of Rights and Obligations - - - . . . ትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥቿ ለተቋቋመው የኢት | The rights and obligations of the National Research ዮጵያ የጤናና ሥነምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ተላልፋል ። ያንዱ ዋጋ 2 - ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፻፵፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 14 - 15 February 1996 – Page 141 ፬ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅከየካቲት፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ•ም• ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፰ የኢትዮጵያ የጤናና ሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም | | የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትየጵያ የጤናና ሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲ | Republic of Ethiopia Proclamation No . 4 / 1995 . ትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር | 1 . Short Title ፬ ፲፱፻ዥ፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም - ፩• የኢትዮጵያ የጤናና የሥነ ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን | 2 . Establishment የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው መንግሥታዊ ተቋም በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይሆናል ። ዋናው መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት ኣዲስ ኣበባ ሆኖ እንደአስፈ ላጊነቱ በሌሎች ሥፍራዎችም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ለማቋቋም ይችላል ። ፬ . የኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ የበሽታ መንስኤና ስርጭትን ፡ ሥነ ምግብን ፡ የሀገረሰብ | መድኃኒትና የሕክምና ዘዴዎችን እንዲሁም ዘመናዊ መድ ኃኒቶችን በተመለከተ ጥናትና ምርምር በማካሄድ በሀገሪቱ ጤናን ለማሻሻል የሚደረገውን እንቅስቃሴ የማገዝ ፤ ፪ የጤና ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲዳብር አስተዋጽኦ | የማድረግ ። ፭ የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ! ፩ . ለምርምርና ጥናት የሚረዱ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፡ የማጠናቀር ፤ ፪ ለጤና ምርመራ ፡ ለበሽታ መከላከያና ለሕክምና የሚያስ ፈልጉንጥረነገሮችዝግጅትን በተመለከተ ጥናትና ምርምር የማድረግ ፤ ፫• የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማከናወን ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ወይም ተቋሞች ጋር ቅንጅታዊ አሠራር እንዲቀየስ ፡ እንዲጠናከርና እንዲዳብር የጋራ ምርምር እንዲፈጠር የመጣር ፤ ገጽ ፻፵፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 14 - 15 February 1996 – Page 142 ፬• የምግብ እጥረትና ያለመመጣጠን የሚያስከትላቸው በሽታዎች የሚወገዱበትን መንገድና በቤተሰብ ደረጃ የአመጋገብ ሁኔታ እንዲሻሻል ጥናትና ምርምር የማድረግ ፤ ፭ የበሽታዎችን መንስዔ ፡ የሚያስከትሉትን ጠንቅና ሥርጭት በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር ጥናትና ምርምር የማካሄድ ፤ ፮ በሀገረሰብ መድኃኒትና ህክምና እንዲሁም በዘመናዊ መድኃኒቶች ላይ ምርምር የማካሄድ ፡ አጥጋቢ የምርምር ውጤት ያሳዩ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው የሀገረሰብ መድኃኒቶችና የህክምና ዘዴዎች በጤና አገልግሎት ውስጥ የሚገቡበትን ሁኔታ የማጥናት ፤ ፯• ከሌሎች አግባብ ካላቸው አካሎች ጋር በመተባበር | በአገሪቱ ውስጥ የሥነ ምግብ ምርምርና ጥናት የማካሄድ ፤ ፰ በላቦራቶሪና በክሊኒካል ጥናቶች ፈዋሽነታቸው የተረ ጋገጠ የባህል መድኃኒቶች ሊመረቱ የሚችሉበትን ሁኔታ የማጥናት ፤ ፀ ፍቱን የሀገረሰብ መድኃኒቶችን አጠቃቀም ፡ ጥራትና | ብቃትየሚገልጽ መነሻ መጽሐፈ መድኃኒት የማዘጋጀት ፤ ፲ የሀገረሰብ መድኃኒትና ሕክምና ባለሙያዎች ስለሙያው መጐልበትና ስለሚከተሉት የጤና ኣጎልግሎት ጥራትና ብቃት ለመወያየት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን የማመ ቻቸት ፡ ሥልጠናና ትምህርትም እንዲያገኙ ከሚመለከ ታቸው ጋር በመተባበር የመሥራት ፤ ፲፩• በሀገረሰብ መድኃኒትነት የሚያገለግሉ ዕፅዋቶችና የሕክምና ቅርሶች እንዳይጠፉ የኣካባቢ ጥበቃ እንዲደረ ግላቸው ከሚመለከታቸው ድርጅቶች ጋር በመተባበር ኣስፈላጊውን ጥረት የማድረግ ፤ ፲፪ : እንደ አስፈላጊነቱ የሙያ ምክር የመስጠት ፡ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ተቋሞች ለከፍተኛ ምርመራ ጥያቄዎች ሲቀር ቡለት የሚላኩለትን ናሙናዎች በመቀበል የላቦራቶሪ ምርመራዎችን የማከናወን ፤ ፲፫• ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ የማስከፈል ፤ ፲፬• የንብረት ባለቤት የመሆን ፡ ውል የመዋዋል ፤ ፲፭ በራሱ ስም የመክሰስ ፡ የመከሰስ ፤ ፲፮• ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉትን ሌሎች ተግባ ሮችን የማከናወን ። ፮ የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፤ ፩ . የዲሬክተሮች ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፤ ፪ . በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም ኣንድ ዲሬክተር ፤ ፫• አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፯• የቦርዱ አባላት ፩• የጤና ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ሰብሳቢ | 3 ) Representatives of higher ፪• የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ተወካይ . ኣባል ፫ የሕክምና ትምህርት ከሚካሄድባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች የሚወከሉ ባለሙያዎች . . . . . . . . . . . . ፬• በመንግሥት የሚሰየም አንድ ኣባል ፭ የኢትዮጵያ የጤናና ሥነምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ዲሬክተር አባልና ፀሐፊ ገጽ ፻፵፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም : _ Federal Negarit Gazeta - - No . 14 - 15ቃ February 1996 – Page 143 የማጽደቅ ፤ ፰ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬እና፭ የተመለከቱት የኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች እንዲሁም ስልጣንና ተግባሮች በሚገባ ሥራ ላይ መዋላቸውን የመከታተል ፤ ፪ በኢንስቲትዩቱ ተቀርጸው የሚቀርቡትን ፖሊሲና መመሪ ያዎች የመገምገምና የማፅደቅ ፤ ፫ የኢንስቲትዩቱን የምርምር ፕሮግራሞችገምግሞ የማጽደቅ ፡ በሥራ መተርጐማቸውን የመከታተልና የመቆጣጠር ፤ ፬ ለኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር ተጠሪ የሆኑኃላፊዎችን ሹመት ፭ በቴክኒክና በሳይንቲፊክ ሥራዎች ላይ የተሠማሩ ሠራት ኞችን መተዳደሪያ ደንብ የማጽደቅ ፡ ደሞዝና አበላቸውን የመወሰን ፤ ፮ የኢንስቲትዩቱን ረቂቅ በጀት የማጽደቅ ፡ አመዳደቡን የመመጠንና አወጣጡን የመወሰን ። . ፀ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል ። | 9 . Meetings of the Board ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ ከቦርዱ አባላት አብዛኞቹ በስብሰባው ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሣኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ። ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፩ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዲሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት ኢንስቲ ትዩቱን በሚገባ የማስተዳደርና ሥራውንም የመምራት ኃላፊነት አለበት ። ፪ . ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዲሬክተሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ለኢንስቲትዩቱ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ የማዋል ፤ ለ ) በኢንስቲትዩቱ በቴክኒክ እና በሳይንቲፊክ ሥራ ላይ የተሠማሩ ሠራተኞችን ቦርዱ ባፀደቀው መመሪያ መሠረት የመቅጠር • የማስተዳደር እንዲሁም የኢንስ ቲትዩቱን ሌሎች ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት የማስተዳደር ፤ ሐ ) የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ' ፕሮግራም ኣዘጋጅቶ ለቦርዱ የማቅረብ ፤ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ የማድረግ ፤ ሠ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ ክንውን የሚያሳይ ዓመታዊ ሪፖርት ለቦርዱ የማቅረብ ። ፫ የኢንስቲትዩቱን ተግባሮች በሚገባ ለማከናወን ባስፈለገ መጠን ሥልጣኑን በከፊል ለኢንስቲትዩቱ ምክትል | ዲሬክተር ወይም ለሌሎች የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በውክልና ሊሠጥ ይችላል ። ገጽ ፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት 3 ቀን ፲፱፻፷፰ ዓም ፲፩ : በጀት ፩ የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል ፤ | - ሀ ) ከፌዴራል መንግሥቱ የሚመደብ በጀት ፡ ለ ) በዚህ ደንብ መሠረት የሚሰበሰብ የአገልግሎት ሐ ) ከሌሎች ምንጮች ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከተው ገንዘብ በኢንስቲትዩቱ ስም ባንክ ተቀማጭ ሆኖ የኢንስቲት ዩቱን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ የመንግሥትን የበጀት አሠራር መመሪያ በማድረግ ወጪ ያደርጋል ። ፲፪ : የሂሣብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት | 12 . Books of Accounts . ይይዛል ። ፪ የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፫፫ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን | 13 . Effective Date ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር | ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ብርትንና ሰላም ማተሚ ድርጅት ታተመ |