×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 117/1990 ዓም የእንስሳት' የእንስሳት ምርትናተዋጽኦገበያ ልማት ባለሥልጣን ማብኣዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፴፭ አዲስ ኣበባ - ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፯ / ፲፱፻፲ ዓም የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ ልማት ባለሥልጣን | Animal , Animal Products and By - products Marketing ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . ገጽ ፯፻፳፩ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፯ / ፲፱፻፲ የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ ልማት ባለሥልጣንን “ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ . እንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያለው የግብርና ሀብት በመሆኑ ፡ የዚህንም ሀብት አቅርቦትና ግብይት ሥርዓት በተገቢው | are agricultural resources having an important role in the መንገድ በመምራት ፡ በመቆጣጠርና በማስተባበር ሀገሪቱ ልታገኝ | economy of the country , የምትችለውን ጥቅም ማሳደግ በማስፈለጉ ፡ : በእንስሳት ፡ እንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች መረጃና ድጋፍ መስጠት እንዲሁም የገበያ ሁኔታን ማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ፡ . እስከአሁን ድረስ ባለቤት አጥቶ በተበታተነ ሁኔታ ሲከናወን የነበረውን የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ የውጭ አገር ገበያ አቅርቦት ሁኔታዎችን በተመለከተ በሥራዎቹ ልዩ ባህርይ | thereof : . ምክንያት በሌላ መሥሪያ ቤት እንዲካሄዱ የግድ አስፈላጊ ከሆኑት አገልግሎቶች በስተቀር ለአፈጸጸም በሚያመችና በተጠቃለለ መልክ መከናወን እንዳለበት ስለታመነበት ፣ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ራሱን የቻለና ሥራዎቹን በባለቤትነት የሚመራ አስፈላጊው ሥልጣንና ተግባር ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ ያንዱ ዋጋ 340 . ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሸ፩ ገጽ ፯፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፶ ዓም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትናተዋጽኦ ገበያ ልማት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፯ ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ ፩ “ እንስሳት ” ማለት የዳልጋ ከብት ፥ በግ ፥ ፍየል ፥ ግመል ፡ ዶሮ ፡ አሳማ ፡ ንብና ባለሥልጣኑ ወደፊት ለዚህ አዋጅ ዓላማ እንስሳት ብሎ የሚሰይማቸውን ሁሉ ያጠቃልላል ፤ “ የእንስሳት ምርት ” ማለት ሥጋ ፡ ወተት ፡ ቅቤ ፡ አይብ ፥ እንቁላል ፡ ማር ፡ ሰም ፡ የበግ ፀጉርና ሱፍ ፡ ባለሥልጣኑ ወደፊት የእንስሳት ምርት ብሎ የሚሰይማቸውን ያጠቃ ፫ . “ የእንስሳት ተዋጽኦ ” ማለት ከእንስሳት እርድ የሚገኙ ተረፈውጤቶች ፡ እንደ ቆዳ ፡ ሌጦ ፥ ቀንድ ፡ ሸኮና ፡ ከሥጋ ደምና አጥንት የተሠራ መኖ እንዲሁም ባለሥልጣኑ ወደፊት የእንስሳት ተዋጽኦ ብሎ የሚሰይማቸውን ያጠቃ ፬ . “ ኳራንቲን ” ማለት የተለያዩ ተላላፊና በካይ የእንስሳት በሽታዎች በሀገር ውስጥ ከቦታ ወደቦታ ፡ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ ፡ ከውጭም ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይዛመቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሠራር ነው ፡ ፭ “ የኳራንቲን ጣቢያ ” ማለት በአንድበተወሰነና በተከለለ ቦታ እንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት ቦታ ነው ፡ ፮ . “ የማረፊያ ቦታ ” ማለት የእንስሳት ንግድ የጉዞ አቅጣጫን ተከትሎ ለእንስሳቱ የውኃ ፡ የመኖ ፡ የጤናና የማረፊያ አገልግሎት ለመስጠት በተወሰነ ርቀት የሚቋቋም የተከለለ ቦታ ነው ። ፯ . “ የአገልግሎት ክፍያ ” ማለት ባለሥልጣኑ ለሚሰጠው ማናቸውም አገልግሎት ወደፊት በሚወጣ ደንብ መሠረት ተወስኖ የሚከፈል ገንዘብ ነው ፣ ፰ “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) ላይ የተመለከ | ቱትን ማለት ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የአዲስ | 3 . Establishment ! " አበባና የድሬዳዋ አስተዳደርንም ይጨምራል ። ፫ መቋቋም የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ “ ባለሥልጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ | ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። • የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። | a ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖእንደአስፈላ | ጊነቱ በክልሎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሊኖሩት ይችላል ። | ባለሥልጣኑ የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር እንዲስፋፋ ኣቅርቦቱ በመጠንና በጥራት እንዲያድግ የማድረግ ዓላማ ይኖረዋል ። ገጽ ፯፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም . . . ፮ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፡ ፩ የሀገሪቱን የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ ለማስፋፋት የሚረዱ ፖሊሲዎችን ፡ ሕጎችንና ደንቦችን ያዘጋጃል ። ሲፈቀዱም ተግባራዊ የሚሆኑበትን ስልት ይቀይሳል ፡ በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፡ ይቆጣ ጠራል ፡ የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ወደ ሀገር ሲገባና ወደ ውጭ አገር ሲላክ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የጥራት ደረጃ አጠባበቅ መመሪያ እንዲወጣ ያደርጋል ፡ የንግዱንም እንቅስቃሴ ይከታተላል ፡ ' ' ፫ " ለውጭና ለአገር ውስጥ ገበያ ለሚቀርቡ እንስሳት የማረፊያ ቦታዎችን ከነሙሉ ድርጅታቸው ጋር ያቋቁማል ፡ እንዲቋቋሙ ያበረታታል ፡ የመጓጓዣ ዘዴዎችም እንዲመቻቹ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመሆን ይከታተላል ፡ - ፬ . ወደውጭ አገር ለሚላኩና ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ እንስሳት ፣ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ የመቆጣጠሪያ ኳራንቲን ጣቢያዎች ያቋቁሟል ፡ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የኳራንቲን አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል ፡ ፭ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የእንስሳት ገበያዎችን ፡ ቄራዎችንና የቆዳና ሌጦ ማደራጃ መጋዘኖችን እንዲ ደራጁ አገልግሎታቸውም እንዲስፋፋ ያደርጋል ፡ ፮ . ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ለውጭ ገበያ ማዘጋጃና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲቋቋሙ ዓለም አቀፍ መስፈርት እንዲጠበቅ እንዲሟላ ያደርጋል ፡ የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል ፡ ፡ ፯ . በእንስሳት ፡ በእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ንግድ ( ለሚሰማሩ የአገር ውስጥ ላኪና አስመጪ ነጋዴዎች . ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ ሁኔታዎች መስፈርት ያወጣል ፡ ለሚመለከታቸው ክፍሎችም መረጃ ይሰጣል ፡ ፰ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር የንግድ ግንኙነት በመፍጠር በውጭ አገር የእንስሳት ፥ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ የሚስፋፋበትን መንገድ ይቀይሳል ፡ ፱ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመሆን ለእንስሳት የጉዞ አቅጣጫን ይወስናል ፡ የጉዞ ሥርዓትን መመሪያ ያወጣል ፡ የዝውውርሥርዓቱን ይከታ ፲ . የዓለም አቀፍና አገር ውስጥ የእንስሳት ምርት ተዋጽኦ ገበያ ሁኔታን እየተከታተለ ወቅታዊ የገበያ መረጃ በማሰ ባሰብ ተንትኖ ለአርቢዎች ፡ ለአገር ውስጥና ውጪ ተጠቃ ሚዎችና ነጋዴዎች ያሰራጫል ፡ " ፲፩ . የእንስሳት ፡ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ ምርምርና ጥናት እንዲካሄድ ያበረታታል ፡ የምርምርና ጥናት ውጤቶችን ለተጠቃሚዎቹ ያሰራጫል ፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግብይቱን ለማፋጠን የሚረዳ ተግባራዊ ጥናት ያካሂዳል ፡ ፲፪ ፡ ባለሥልጣኑ ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ለመሰብሰብ መመሪያ በማውጣት ያስወስናል ፡ ሲፈቀድም በተግባር ያውላል ፡ ፲፫ : ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር የእንስሳት የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ልማት የሚዳብርበት ሁኔታ እንዲ መቻች ያበረታታል ፡ ደጋ ገጽ Lደ፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም . ፲፬• የቆዳና ሌጦ ምርት ከእርድ ጀምሮ ገበያ እስኪደርስ ድረስ - ጥራቱ የሚጠበቅበትን መንገድ ይከታተላል ፡ ፡ ፲፭ - ከክልሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የቴክኒክ እገዛና | ምክር ይሰጣል ፡ ! , : : . . . . : : : . . . . ! ! - ፲፮ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ - - 1 ንብረቶች ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ; በስሙ ይከሳል ፡ ይከሰሳል ። ፮ . የባለሥልጣኑ አቋም { ን : : : ) : 1 : 1 | ባለሥልጣኑ : : ን ! ! ! : . . ፩ - የሥራ አመራር ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ 6 የሚጠራ ) ፡ ፪ . በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ሥራ - አስኪያጅ : እና : : : : . . : ሌሎች ሠራተኞች . . . . . . . . . ፰ የቦርዱ አባላት ' ቦርዱ በመንግሥት የሚሰየሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል ። ፱ . የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በየ፫ ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፡ | ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ • ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሆኑት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ ፣ የቦርዱ ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፡ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። 17 1 : : : : : 6 የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፡ ቦርዱ . . የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። | 10 . Powers and Duties of the Board - ፲ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር • ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ . ባለሥልጣኑ ' በዓላማው መሠረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ | ማድረጉን ያረጋግጣል ፡ የባለሥልጣኑን ሥራዎች በበላ - 1 . 2 ይነት ይመራል ፡ ይቆጣጠራል ፡ የአጭርና የረጅም ጊዜ - ዕቅድና ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ለመንግሥት እያቀረበ ያስወስናል ፡ ፪ በባለሥልጣኑሥራ አስኪያጅ በሚቀርቡ ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ፡ ይወስናል ፣ . . . ፫ ለባለሥልጣኑ ሥራ አስኪያጅ አጠቃላይ የሥራ መመሪያ ' ' ይሰጣል ፡ : 1 : ! ' . . . ፩ በሥራ አስኪያጁ የሚቀርብለትን የሥራ ፕሮግራምና ' ' የበጀት ጥያቄ ይመረምራል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ፲፩ የሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር _ ፩ : ሥራ አስኪያጁ ተጠሪነቱ ለቦርዱ ሆኖ የባለሥልጣኑ ዋና . ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ። . . . . . . . . . . . ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር | እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ሥራ አስኪያጁ ፡ : : ያ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ የተመለከተውን የባለሥል | : : : : 1 ጣኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የባለሥል | ጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ገጽ ፯፻፷፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓ•ም• ሐ ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ። መ ) ለበለሥልጣኑ በተደፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ሠ ) ባለሥልጣኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ፣ ረ ) ስለ ባለሥልጣኑ የሥራ እንቅስቃሴና ሂሳብ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ ሥራ አስኪያጁ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስ ፈልግ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለባለሥልጣኑ የሥራ ክፍልኃላፊዎች በውክልና ሊያስተላልፍይችላል ። ፲፪ . በጀት ባለሥልጣኑ ከሚሰበስበው የአገልግሎት ክፍያ ፡ ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ከሚያገኘው ገቢ እና ከመንግሥት በሚመደብለት የበጀት ድጎማ ይተዳደራል ። ፲፫ የሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች | 14 . Power to Issue Regulations በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፭ የተሻሩና ተፈጻሚነት የሌላቸው ሕጐች ፩ . የሚከተሉት ሕጎች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፡ ሀ የከብት እርባታና የሥጋ ቦርድ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፪ ለ የከብት እርባታና የሥጋ ቦርድን ለማቋቋም የወጣ ትዕዛዝ ቁጥር ፴፬ / ፲፱፻፶፮ ። ፪ . ማንኛውም ሌላ ሕግ ወይም የተለመደ አሠራር ከዚህ | 16 . Effective Date አዋጅ ጋር ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት ከሚወጡደንቦች ጋር የሚቃረን ሆኖ ከተገኘ ይህን አዋጅ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፲፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?