የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ አዲስ አበባ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፩ ፲፱፻፶፭ ዓም ኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ክልከላ ኮንቬንሽን ማስፈፀሚያ ገጽ ፪ሺ፩፻፷፪ አዋጅ ቁጥር ፫፻፴፩ ፲፱፻፲፭ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፣ መመረት ፣ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና እነዚህንም ለማውደም የተደረገውን ኮንቬንሽን ለማስፈጸም የወጣ አዋጅ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፣ መመረት ፣ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና እነዚህንም ለማውደም እ.ኤ.አ ጃንዋሪ ፲፫ ቀን ፲፱፻፫ በፓሪስ የተደረገውን ኮንቬንሽን ከፈረሙት አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ በመሆኗ ፣ ይህንኑ ኮንቬንሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነና ፣ ለዚህም አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፴፰ የወጣ በመሆኑ ፣ በኮንቬንሽኑ መሠረት እያንዳንዱ አባል አገር የገባውን ግዴታ ለመወጣት የሚያስችለውን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የተደነገገ | adopt the necessary measures to implement its obligation በመሆኑና ለዚህም አገር አቀፍ የሆነ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ - መንግ ሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ክልከላ ኮንቬንሽን ማስፈፀሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፴፩ ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ : ዝሸኽ ገጽ ፪ሺ፩፻፷፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፪ : ት ር ጓ ሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ “ ኮንቬንሽን ” ማለት የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፣ መመረት ፣ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልናእነዚህንም ለማውደም እኤአ ጃንዋሪ ፲፫ ቀን ፲፱፻፶፫ በፓሪስ የተደረገው ኮንቬንሽን ነው ። ፪ “ የኬሚካል ጦር መሣሪያ ” ማለት የሚከተሉትን ሁሉንም በአንድነት ወይም በተናጠል ማለት ነው ፣ ሀ ) በኮንቬንሽኑ ላልተከለከሉ ዓላማዎች ከሚውሉት ፣ ዓይነታቸውና መጠናቸው ከዚሁ ዓላማ ጋር የሚስማማ ከሆኑት በስተቀር መርዛማ ኬሚካሎችና ፕሪከርሰሮቻቸው ፣ ለ ) በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፪ ( ሀ ) የተገለጹትን መርዛማ ኬሚካሎች በመጠቀም ሞትና ሌላ ዓይነት ጉዳት ለማስከተል እንዲችሉ ሆነው የተሠሩ ጥይቶችና ለዚሁ ተግባር ብቻ የሚውሉ ሌሎች መጠቀሚያዎች ፣ ሐ ) በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፪ ( ለ ) የተጠቀሱትን ጥይቶችና መጠቀሚያዎች በቀጥታ በጥቅም ላይ ለማዋል እንዲያስችል ሆኖ የተሠራ መሣሪያ ። ፫ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። ፬ . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ወይም የተፈጥሮ ሰው ነው ። ፭ “ መርዛማ ኬሚካል ” ማለት ከማንኛውም ምንጭ የተገኘ ወይም በማንኛውም ዓይነት ዘዴና በማምረቻ ተቋማት ወይም በጥይቶች ውስጥ ወይም በሌላ ቦታ የተመረተ በኬሚካላዊ ውጤቱ በሕይወት ሂደት ላይ ሞትን ፣ ጊዜያዊ የችሎታ ማጣትን ወይም ቋሚ ጉዳትን በሰውና በእንስሳት ላይ ሊያደርስ የሚችል ማንኛውም ኬሚካል ፮ . “ ፕሪከርሰር ” ማለት በማንኛውም ዘዴ የመርዛማ ኬሚካል ማምረት ሂደት ውስጥ በጥቅም ላይ የሚውል ተፀግባሪ ኬሚካል ሲሆን ማንኛውንም ወሳኝ የክልኤ ወይም የብዙ ምንዝር ኬሚካላዊ ዘዴን ያጠቃልላል ፤ ፯ . “ በኮንቬንሽኑ ያልተከለከሉ ዓላማዎች ” ማለት የሚከ ተሉት ዓላማዎች ማለት ነው ፣ ሀ ) ለኢንዱስትሪያዊ ፣ ለእርሻ ፣ ለምርምር ፣ ለሕክምና ፣ ለመድሃኒት ወይም ለሌሎች ሰላማዊ ዓላማዎች መገልገያነት፡ ለ ) ለመከላከል ዓላማዎች ማለትም መርዛማ ኬሚካ ሎችና የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች የሚያስከት ሉትን ጎጂነት ከመከላከል ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ዓላማዎች ፣ ሐ ) የኬሚካል የጦር መሣሪያዎችን ከመጠቀም ጋር ያልተያያዙና የኬሚካሎችን ለጦርነት ተግባር በመጠቀም ላይ ያልተመሰረቱ ወታደራዊ ዓላማዎች መ ) የአገር ውስጥ አድማ የመቆጣጠር ተግባርን ጨምሮ ሕግ የማስፈጸም ዓላማዎች ። ፰ “ ሠንጠረዥ ” ማለት ከዚህ አዋጅ ጋር የተያያዘው የመርዛማ ኬሚካሎችንና ፕሪከርሰሮቻቸውን ዝርዝር የያዘው የኮንቬንሽኑ ሠንጠረዥ ፩ ፣ ፪ እና ፫ ነው ፣. ፱ . “ የአድማ መበተኛ ኬሚካል ” ማለት ማንኛውም በሠን ጠረዡ ውስጥ ያልተጠቀሰ ኬሚካል ሆኖ ለኬሚካሉ መጋለጥ እስኪቋረጥ ድረስ በሰዎች ላይ በአጭር ጊዜ የሚቋረጥ የስሜት ህዋሳት መቆጣትን ወይም የአካላዊ ብቃት ማጣትን የሚፈጥር ማንኛውም ኬሚካል ነው ፣ ፬ገጽ ፪ሺ፩፻፷፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ፲ . “ ድርጅት ” ማለት በኮንቬንሽኑ አንቀጽ ፰ መሠረት የተቋቋመው የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች አስወጋጅ ድርጅት ነው ፣ ፲፩ “ ኢንስፔክሽን ” ማለት በኮንቬንሽኑ መሠረት ድርጅቱ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርጉት ከኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ፣ ከመርዛማ ኬሚካሎችና ፕሪከርሰሮቻቸው እና በሠን ጠረዡ ካልተዘረዘሩ እራሳቸውን የቻሉ ኦርጋኒክ ኬሚካሎች ጋር የተያያዘ ምርመራ ነው ፣ ፲፪ • “ የኢንስፔክሽን ቡድን ” ማለት በድርጅቱ ተወክለው በኢትዮጵያ ውስጥ ምርመራ የሚያካሂዱ ኢንስፔክተሮች እና ረዳቶቻቸው ናቸው ፣ ፲፫ . “ እራሱን የቻለ ኦርጋኒክ ኬሚካል ” ማለት በኬሚካላዊ ስም ፣ በመዋቅራዊ ቀመር ( የሚታወቅ ከሆነ ) እና በኬሚካል አብስትራክት አገልግሎት ምዝገባ ቁጥር ( ካለ ) ሊለይ የሚችል ከኦክሳይዶቹ ፣ ከሰልፋይዶቹና ከሜታል ካርቦኔቶቹ በስተቀር ሁሉንም የካርቦን ውህዶች ከያዙት የኬሚካል ውህደት የሚመደብ ማንኛውም ኬሚካል ፲፬ • “ ተቀብሮ የተተወ ኬሚካል ጦር መሣሪያ ” ማለት እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ ፩ ቀን ፲፱፻፳፭ በኋላ በአንድ አገር የግዛት ክልል ውስጥ ኬሚካሉ የተቀበረበት አገር ስምምነት ሳይኖር ተቀብሮ የተተወ የኬሚካል ጦር መሣሪያ እና አሮጌ የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጭምር ማለት ፫የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሥልጣንና ተግባር ሚኒስቴሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፣ ፩ በኮንቬንሽኑ ኢትዮጵያ ያገኘቻቸውን መብቶች እና የገባቻ ቸውን ግዴታዎች ሁሉ መንግሥትን ወክሎ ይፈጽማል ፣ ፪ የኮንቬንሽኑንና የዚህን አዋጅ አፈጻጸም በተመለከተ የተዘጋጁ ፖሊሲዎችን ለመንግሥት ውሳኔ ያቀርባል ፤ ፫ . የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ስምምነት አፈፃፀምና የአማካሪ ቦርድን የሥራ እንቅስቃሴ ይመራል ፣ ፬ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ፣ የመርዛማ ኬሚካሎችንና ፕሪከርሰሮቻቸውን እንዲሁም ተዛማጅ መረጃዎችን ይሰበ ስባል ፣ ያጠናቅራል ፣ በኮንቬንሽኑ ኣንቀጽ ፫ መሠረት መግለጫ አዘጋጅቶ ለድርጅቱ ያቀርባል ፣ ፭ መርዛማ ኬሚካሎችና ፕሪከርሰሮች በኮንቬንሽኑ ላልተከ ለከሉ ዓላማዎች ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ፣ ወደ ውጭ ለመላክ ፣ ለማምረት ፣ ለመጠቀም ፤ ለመያዝና ለማስተላለፍ ፈቃድ ይሰጣል ፣ መጠናቸውንም በኮንቬንሽኑ መሠረት ይወስናል ፣ ዝርዝሩም በመመሪያ ይወሰናል ፣ ፮ : ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ ያስከፍላል ፣ • ለድርጅቱ መግለጫ ለመስጠት የሚሰበሰቡ መረጃዎችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል ፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪዎችን ወይንም ተቋማት አሠራር የኮንቬንሽኑን ድንጋጌዎች የማ ይቃረን መሆኑን ለማረጋገጥ በማንኛውም የኬሚካል ኢን ዱስትሪ ወይንም ተቋም ምርመራ ያደርጋል ፣ ፰ . የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች የሚወገዱብትንና የሚወድ ሙበትን ጉዳት ከደረሰም ስለሚወሰድበት እርምጃዎች መመሪያ ይሰጣል ፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡ ፱ ለዚህ አዋጅና ለኮንቬንሽኑ አፈጻጸም የሚረዳ መዝገብ ያደራጃል ፣ ይይዛል ፣ ፲ የኮንቬንሽኑን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ በሕዝብ ዘንድ ያስተዋውቃል ፣ ፲፩ በማንኛውም ጊዜ በቅድሚያ ማስጠንቀቂያም ሆነ ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ በየትኛውም ቦታ ከኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ፣ መርዛማ ኬሚካሎች ፣ ፕሪከርሰሮች እና የአድማ መበተኛ ኬሚካል ጋር በተያያዘ ምርመራ ያደርጋል ፣ ፲፪- የሚስጥራዊ መረጃዎች አያያዝ በኮንቬንሽኑ ድንጋጌዎች መሠረት መሆኑን ያረጋግጣል ፣ ገጽ ፪ሺ ፩፻፷፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ሚያዝያ ፳ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፲፫ በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ በድርጅቱ የሚደረገው ኢንስፔክሽን በኮንቬንሽኑ መሠረት መሆኑን ያረጋ ግጣል ፣ ለኢንስፔክሽን ሥራው ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ፣ በኮንቬንሽኑ መሠረት ለኢንስፔክሽን ቡድኑም የአገር ውስጥ አጋዥና አስተባባሪ ሆኖ ይሠራል ፣ ፲፬ • ለኢንስፔክሽን ተግባር ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ የኢንስፔ ክሽን ቡድን አባላት በኮንቬንሽኑ ቬሪፊኬሽን አኔክስ ፪ቢ መሠረት ስለሚኖራቸው የመመርመር ሥልጣን ፣ ልዩ መብት ፣ ጥበቃ እና ስለሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች መታወቂያ ይሰጣል ፣ ፲፭ ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ከኬሚካል ጦር መሣሪያዎችና መርዛማ ኬሚካሎች የመከ ላከል ብሔራዊ ፕሮግራም ያወጣል ፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል ፣ ከድርጅቱና ከስምምነቱ ኣባል አገራት ጋር ለሚደረገው የሥራ ግንኙነት ብሔራዊ ተጠሪ አካል ሆኖ ይሠራል ፣ ፲፮ ከዚህ አዋጅ አፈጻጸም ጋር የተያያዙ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል ። ፬ የጉምሩክ ባለሥልጣን ኃላፊነት ፩ . የጉምሩክ ባለሥልጣን ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው | 4. Responsibility of the Customs Authority ሠንጠረዥ የተጠቀሱት መርዛማ ኬሚካሎች እና ፕሪከር ሰሮቻቸው ከኢትዮጵያ ሲወጡና ሲገቡ በሚኒስቴሩ ፈቃድ የተሰጠባቸውና መጠናቸውም በፈቃዱ መሠረት መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት ፣ ፪ • የጉምሩክ ባለሥልጣን ይዞታቸው ከዚህ አዋጅ ጋር በተገናኘ አጠራጣሪነት ያላቸው ገቢና ወጭ ዕቃዎችን ከኣገር እንዲወጡ ወይም ወደ አገር እንዲገቡ ከመፈቀዱ በፊት ሚኒስቴሩን ማማከር አለበት ። ፭ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ስምምነት አፈፃፀም አማካሪ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ የሆነ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ስምምነት አፈፃፀም ኣማካሪ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርድ ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ አዋጅ መሠረት ተቋቁሟል ፣ ቦርዱ በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት የሚመደቡ ሰባት አባላ ይኖሩታል ፣ ሚኒስ ወይም እርሱ የሚወ ክለው የሚኒስቴሩ ባልደረባ የቦርዱ ሰብሳቢ ይሆናል ። ፮ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ የኮንቬንሽኑንና የዚህን አዋጅ አፈጻጸም በተመለከተ ሚኒስ ቴሩን ያማክራል ፣ ፪ • ከኮንቬንሽኑና ከዚህ አዋጅ አፈጻጸም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ፖሊሲዎችን እያመነጨ ለሚኒስቴሩ ውሳኔ ያቀርባል ፣ ፤ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ ቢያንስ በስድስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፣ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ፣ ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይሆናል ፣ ፫ ውሣኔ የሚተላለፈው በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ ይሆናል ፣ ሆኖም ድምፁ እኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምዕ ይኖረዋል ፣ ፬ . የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ - ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፰ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎችን ስለ መከልከል ማንኛውም ሰው በማናቸውም ሁኔታ የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም አይችልም ፣ ፩ . የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ማዘጋጀት፡ ማምረት፡ መያዝ ፣ ማከማቸት ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለማንኛውም ሌላ ሰው ማስተላለፍ እና የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን መጠቀም ፣ ፪ • በኮንቬንሽኑ እና በዚህ አዋጅ መሠረት የተከለከሉ ተግባራት እንዲፈጸሙ በማንኛውም ሁኔታ ማንኛውንም ሌላ ሰው መርዳት ፣ ማበረታታት ወይም መገፋፋት ፣ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ለመጠቀም ወታደራዊ ዝግጅት ማድረግ ፣ ፲፪ ድርጅቱ ስለሚያደርገው ኢንስፔክሽን ገጽ ፱ሺ፩፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : ፫ የአድማ መበተኛ ኬሚካልን እንደጦር መጠቀም ። ፱ ክልከላ ስለማይኖርባቸው ሁኔታዎች ፩ በኮንቬንሽኑ ላልተከለከሉ ዓላማዎች ለመጠቀም ፈቃድ የተሰጠው ማንኛውም ሰው በሠንጠረዡ የተዘረዘሩትን መርዛማ ኬሚካሎችናፕሪከርሰሮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት ፣ ወደ ውጭ መላክ ፣ ማምረት ፣ ማደባለቅ ማዋሃድ መጠቀም ፣ መያዝና ማስተላለፍ ይችላል ፣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ የተጠቀሰው ክልከላ በኮንቬን ሽኑና በዚህ አዋጅ መሠረት የኬሚካል ጦር መሠረያ ዎችን ኣገልግሎት በማይሰጡበት ሁኔታ ከማስወገድ ፣ የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃትን እና በጥቃቱ የሚደር ሰውን አደጋ ከመከላከል ጋር በተያያዘ በሚኒስቴሩ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ተፈጻሚነት የለውም ። ፲ ስለመረጃ እና መዛግብት ስለመያዝ ፩ . ማንኛውም በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ የተሰጠው ወይም በሠንጠረዥ ያልተዘረዘሩ እራሳቸውን የቻሉ ኦርጋኒክ ኬሚካሎችን የሚያመርት ወይም የአድማ መበተኛኬሚካሎች ያሉት ሰው መዝገብ የመያዝ ግዴታ አለበት ፣ ፪ . ማንኛውም ሰው ከኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ፣ ከመርዛማ ኬሚካሎችና ፕሪከርሰሮቻቸው እና በሠንጠረዥ ካልተዘ ረዘሩ እራሳቸውን የቻሉ ኦርጋኒክ ኬሚካሎች ጋር በተያያዘ መረጃ ወይም ሰነድ እንዲያቀርብ በሚኒስቴሩ ሲጠየቅ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡ ፫ . ማንኛውም ሰው ከዚህ አዋጅ ወይም ከኮንቬንሽኑ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ ያገኘውን መረጃ በሚስጢር የመጠበቅ ግዴታ አለበት ፣ ሆኖም መረጃዎቹ ሊሰጡ የሚችሉት ፣ ሀ ) የመረጃው ባለቤት በሆነው ሰው ፈቃድ ፣ ወይም ለ ) ኢትዮጵያ በኮንቬንሽኑ የገባችውን ግዴታ እንድ ትወጣ ለማድረግ ፣ ወይም ሐ ) ይህን አዋጅ ለማስፈፀም ፣ ወይም የሕዝብን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ለሚከናወኑ ተግባራት ብቻ ነው ። ፲፩ . የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ከሚነስቴሩ ጋር የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፩ : የድርጅቱ የኢንስፔክሽን ቡድን በኮንቬንሽኑ መሠረት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ፣ ከመርዛማ ኬሚካሎችና ፕሪከርሰሮቻቸው እንዲሁም በሠንጠረዡ ካልተዘረዘሩ እራሳቸውን የቻሉ ኦርጋኒክ ኪሚካሎች ጋር የተያያዘ ኢንስፔክሽን ሊያደርግ ይችላል ፣ ፪ የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባላት በማንኛውም ቦታ ሲጠየቁ መታወቂያቸውን ት ግዴታ አለባቸው ። ፲፫ . ቅ ጣ ት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ፣ ፩ በማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ እና ፲፩ የሠፈሩትን ድንጋጌዎች ተላልፎ ሲገኝ ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከብር ፭ሺህ ( አምስት ሺህ ብር ) እስከ ፲ሺህ ( አሥር ሺህ ብር ) በሚደርስ ገንዘብ ይቀጣል ፣ ፪ • ማንኛውም ሰው ከሚኒስቴሩ ፈቃድ ሳይኖረው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሱትን ተግባራት ሲፈፅም ቢገኝ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከብር ፲ሺህ ( አሥር ሺህ ብር ) እስከ ፴ሺህ ( ሠላሳ ሺህ ብር ) በሚደርስ ገንዘብ ይቀጣል ፣ ፫ . ማንኛውም ሰው ከዚህ አዋጅና ከኮንቬንሽኑ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ መረጃ ያቀረበ ወይም በድርጅቱ ወይም በሚኒስቴሩ የሚደረገውን ምርመራ ያደናቀፈ እንደሆነ ከአምስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከብር ፴ሺህ ( ሠላሳ ሺህ ብር ) እስከ ፱ሺህ ( ሃምሳ ሺህ ብር ) በሚደርስ ገንዘብ ይቀጣል፡ ሚኒስቴሩ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም ስልጉ የሕዝብ / 17. Issuance of Directives ገጸ ፪ሺ፩፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ፬ • ማንኛውም ሰው ፣ ሀ ) የኬሚካል የጦር መሣሪያዎችን የሠራ ፣ ያመረተ ፣ ያከማቸ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ለሌላ ሰው ያስተላለፈ ፣ ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ወደ ውጭ የላከ ፣ የገዛ ፣ ለሽያጭ ያቀረበ ፣ በአደራ ያስቀመጠ ፣ የያዘ ፣ ያመላለሰ ወይም ያደለ እንደሆነ ከአሥር እስከ ኣሥራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ወንጀሉን የፈጸመው በአፍቅሮተ ነዋይ ሲሆን በተጨማሪ እስከ አምስት ሺ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል ፣ ሆኖም ወንጀሉ የተፈጸመው የሕግ ሰውነት አዋጅ ለማስፈጸም በተሰጠው አካል የሆነ እንደሆነ የገንዘቡ ቅጣት እስከ ሦስት እጥፍ ሊደርስ ይችላል ፣ ለ ) የአመጽ መቆጣጠሪያ ኤጀንቶችን እንደጦር መሣሪያ የተጠቀመ ሰው ከአምስት እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ፣ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎችን የተጠቀመ ወይም የኬሚካል የጦር መሣሪያዎችን ለወታደራዊ ዓላማ ለመጠቀም ዝግጅት ያደረገ እንደሆነ ከአሥር እስከ ሃያ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ሆኖም የወንጀሉ አፈጸጸም ከባድ የሆነ እንደሆነ በሞት ይቀጣል ። ፲፱ : ስለመውረስ ሚኒስቴሩ በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ ሳይሰጥባቸው የገቡ ወይም የሚወጡ በሠንጠረዡ የተመለከቱትን መርዛማ ኬሚካሎችና ፕሪከርሰሮች ለመውረስ ይችላል ፣ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፬ ) ላይ የተመለከ ቱትን በመተላለፍ ጥፋተኛ ሆኖ በተፈረደበት ሰው ላይ ፍርድ ቤቱ ከዋናው ቅጣት ጋር በማጣመር በሠንጠረዡ የታቀፉ ኬሚካሎች እና የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች እንዲወረሱ ለማዘዝ ይችላል ። ፲፭ ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ወይም የአሠራር ልማድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም ። ፲፮ ደንብ ስለማውጣት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስ ፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል ። ፲፯ መመሪያ ስለማውጣት ** « ፲፰ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት