የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ኣዋጅ ቁጥር ፪፻፶፮ / ፲፱፻፶፬ ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ... ገጽ ፩ሺ፮፻፳፱ አዋጅ ቁጥር ፪፻፶፮ / ፲፱፻፲፬ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የቀድሞው ኣስፈፃሚ አካል አደረጃጀት ለሥራ ጥራትና ቅልጥፍና አመቺ የነበረ ባለመሆኑ ፣ መርሀ ግብሩን በተገቢው የሥራ ቅልጥፍና መፈፀም ያለበት | ecutive body was not conducive for the brilliance and በመሆኑ ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር | 1. Shor Title ፪፻፶፮ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፯ ነው ፣ ፪ ክልል ” ማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፵፯ የተመለ ከተው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አባል የሆነ ክልል ነው ፣ ፫ “ ሚኒስቴር ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ( ፩ ) የተመለከ ተውን ጽሕፈት ቤት ይጨምራል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፮፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ክፍል ሁለት ስለሚኒስትሮች ፫ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባልነት ፩ . የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ሀ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ለ ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ሐ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ የተመለከቱትን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚመሩ ሚኒስትሮች ፣ መ ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአባልነት እንዲሳተፉ የሚመ ርጣቸው ሌሎች ባለሥልጣኖች ፣ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) የተመለከተው ማንኛውም ሚኒስትር በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ሊገኝ በማይችልበት ጊዜ ምክትሉ ወይም ከአንድ በላይ ምክትሎች ካሉ በግልጽ ተለይቶ ውክልና የተሰጠው ምክትል ፣ በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በምትክ አባልነት ይሳተፋል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተመለከተው ምክትል እንደአግባቡ በሚኒስትር ፣ በሚኒስትር ዴኤታ ወይም በምክትል ሚኒስትር ደረጃ ሊሆን ይችላል ። ፬ የሚኒስቴሮች መቋቋም የሚከተሉት ሚኒስትሮች በዚህ አዋጅ ተቋቁመዋል ፣ ፩ . የአቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ፣ ፪ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፣ ፫ የገጠር ልማት ሚኒስቴር ፣ የመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ፣ ፭ የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፣ • የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ፣ ፯ የግብርና ሚኒስቴር ፣ ፰ የትምህርት ሚኒስቴር ፣ ፱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፣ ፲ የፍትሕ ሚኒስቴር ፲፩ የገቢዎች ሚኒስቴር ፣ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ፲፬ . የማስታወቂያ ሚኒስቴር ፣ የውሃ ሀብት ሚኒስቴር ፣ ፲፮ የወጣቶች ፣ የእስፖርትና የባህል ሚኒስቴር ፣ የማዕድን ሚኒስቴር ፲፰ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ። ፭ ተጠሪነት ፩ የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነት ለአቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ይሆናል፡ ሀ ) የትምህርት ሚኒስቴር ፣ ለ ) የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ፣ ሐ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ፣ መ ) የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ፣ ሠ ) የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ረ ) የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ። ረ ) የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎኔ . … . ) ገጽ ፩ሺ፮፻፴፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፪ የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነት ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ይሆናል ፣ ሀ ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ፣ ለ ) የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ፣ ሐ ) የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ፣ መ ) የመንግሥትየልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥ ሠ ) የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱ ስትሪ ኤጀንሲ ፣ ረ ) የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ፣ ሰ ) የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ፣ ሽ ) የእንስሳት ገበያ ባለሥልጣን ። ፫ የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነት ለገጠር ልማት ሚኒስቴር ይሆናል ፣ ሀ ) የግብርና ሚኒስቴር ፣ ለ ) የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ፣ ሐ ) የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተሃድሶና ልማት ፈንድ ፣ መ ) ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ፣ ሠ ) ብሔራዊ የማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ፣ ረ ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት ፣ ሰ ) የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲ ሸ ) የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ። ፬ የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላትና የልማት ድርጅቶች ተጠሪነት ለመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ይሆናል ፣ ሀ ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ፣ ለ ) የአየር ትራንስፖርት ባለሥልጣን ፣ ሐ ) የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ፣ መ ) የመንገድ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ፣ ሠ ) ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ዴፖዎች አስተ ሰ ) የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ ፣ ሸ ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኤጀንሲ ፣ ቀ ) የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ፣ በ ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ፣ ተ ) የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ። ፭ የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነት ለገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይሆናል ፣ ሀ ) የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ፣ ለ ) የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ባለሥልጣን ፣ ሐ ) ብሔራዊ የሥነ ሕዝብ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ፣ መ ) የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ፮ የሚከተሉት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ይሆናል ፣ ሀ ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ለ ) የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ፣ ሐ ) ብሔራዊ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ፣ መ ) የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ፣ ሠ ) የድሬዳዋ ከተማ ኣስተዳደር ። ፯ የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተጠሪነት ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይሆናል ። ፰ የሚከተሉት ኣስፈጻሚ አካላት ተጠሪነት ለገቢዎች ጽ ፩ሺ፮፻፴፪ ፌዴራል ነጋሪተ ጋዜጣ ቁጥር ፪ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ሀ ) የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ፤ ለ ) የጉምሩክ ባለሥልጣን ፤ ሐ ) የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ። ፀ • የሚከተሉት አስፈጻሚ ኣካላት ተጠሪነት ለማስታወቂያ ሚኒስቴር ይሆናል ፤ ሀ ) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ፤ ለ ) የመገናኛ ብዙኃን ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ። ፲ የሚከተሉት አስፈጻሚ ኣካላት ተጠሪነት ለወጣቶች ፤ የእስፖርትና የባህል ሚኒስቴር ይሆናል ፤ ሀ ) የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ፤ ለ ) የብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት ፤ ሐ ) የኢትዮጵያ የስብሰባ ማዕከል ፤ መ ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ። ፲፩ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ተጠሪነት ለማዕድን ሚኒስቴር ይሆናል ። ክፍል ሦስት የሚኒስቴሮች ሥልጣንና ተግባር ፮ . የአቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የአቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የሚከተሉት | 6 Office for the Coordination of Capacity Building ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የሀገሪቱን የአቅም ግንባታ ፖሊሲዎች ያመነጫል ፤ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ፪ • ለሀገሪቱ አቅም ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ የአቅም መገንቢያ አቅሞች እንዲገነቡ ያደርጋል ፤ ፫ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፩ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ ኣካላት በበላይነት ይመራል ፤ ያስተባብራል ፤ ፬ የአቅም ግንባታን በማጎልበት ረገድ ለክልሎች አስፈላ ጊውን ድጋፍ ይሰጣል ፤ ፭ የአቅም ግንባታን ለማጠናከር የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ፯ . የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፩ . የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ T ፯ ኣንቀጽ ፲፬ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፪ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ አካላት በበላይነት ይመራል ፣ ያስተባብራል ። ፰ የገጠር ልማት ሚኒስቴር የገጠር ልማት ሚኒስቴር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ : የገጠር ልማት ፖሊሲ ያመነጫል ፤ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ፪ . ለገጠር ልማት አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች የሚመነጩበ ትንና ተዘጋጅተው ሊቀርቡ የሚችሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል ፤ ፫ የምግብ ዋስትና ፕሮግራምን ይመራል ፤ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭፪ ) የተመለከቱትን ኣስፈፃሚ ኣካላት በበላይነት ይመራል ፤ ያስተባብራል ፤ ፭ የገጠር ልማትን በማስፋፋት ረገድ ለክልሎች አስፈላ ጊውን ድጋፍ ይሰጣል ፤ ፮ የገጠር ልማትን ለማስፋፋትየሚረዱ ሌሎችተግባሮችን ያከናውናል ። - ፬- የመሠረት ልማት ሚኒስቴር ፩ በአዋጅቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯አንቀጽ ፲፰እና በሌሎች ሕጎች ለትራንስፖርትና መገናኛሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩት | 9 ሥልጣንና ተግባሮች ፣ በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፲፭ እና በሌሎች ሕጎች ኢነርጂን በሚመለከት ለማዕ ድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮችእንዲሁም በአዋጅቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ በአንቀጽ ፲፮ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) እና በሌሎች ሕጎች ለሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፴፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ፪ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ የመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፬ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ አካላትና የልማት ድርጅቶች በበላይነት ይመራል፡ ያስተባብራል ፤ ለ ) የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅትን የሥራ እንቅስቃሴዎች በሁለቱ አገሮች መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት ይከታተላል ። ፲ . የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፩ በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፲፫ እና ፲፱ እንዲሁም በሌሎች ሕጎች ለኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴርና ለገንዘብ ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፩ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ ኣካላት በበላ ይነት ይመራል ፣ ያስተባብራል ። ፲፩ . የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ሀ ) ከክልሎችጋር በመተባበር የሕዝቡ ሰላምና ፀጥታ መጠበቁን ያረጋግጣል ፤ ለ ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፰ እና ፳፪ ( ፮ ) ድንጋ ጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ በክልሎች መካከል አለመግባባቶች የሚፈቱባቸውን ሁኔታዎች ያመቻቻል ፤ ሐ ) ለክልሎች በተለይም በልማት ወደኋላ ለቀሩት ክልሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ድጋፍ ያደርጋል ፤ መ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፮ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ አካላት በበላይነት ይመራል ፤ ያስተባ ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፲፮ በንዑስ አንቀጽ ( ፯ ) ( ፲፩ ) ለሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ፲፪ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፲፪ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። • የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፳፯ አንቀጽ ፳፩ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣን ፣ ተግባሮች ይኖሩታል ። ፲፬ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፳፪ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። ፲፭ የፍትህ ሚኒስቴር የፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፳፫ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፴፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም : ፲፮ የገቢዎች ሚኒስቴር ለፌዴራል መንግሥት የገቢዎች ቦርድ በአዋጅ ቁጥር ፭ ፲፱፻ዥ፯ እና በሌሎች ሕጎች ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለገቢዎች ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ፲፯ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ T ፯ አንቀጽ ፳፮ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፳፭ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። ፲፱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ፩ . ለማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፣ ( ፮ ) እና ( ፱ ) እንዲሁም ማስታወቂያን በሚመለከት በሌሎች ሕጎች ተሰጥተውት የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች ፣ በዚህ አዋጅ ለማስታወቂያ ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፱ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ አካላት በበላይነት ይመራል፡ ያስተባብራል ። የውሃ ሀብት ሚኒስቴር የውሃ ሀብት ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፲፯ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች | 20. Ministry of Water Resources ይኖሩታል ። ፳፩ የወጣቶች ፤ የእስፖርትና የባሕል ሚኒስቴር ፩ የወጣቶች ፣ የእስፖርትና የባህል ሚኒስቴር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ሀ ) ወጣቱን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና ሕጎች ያመነጫል፡ ሲፈቀዱም ተግባራዊነታቸውን ይከ ታተላል ፤ ለ ) ጤናማና ኃላፊነት የሚሰማው ወጣት ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ፤ ሐ ) ወጣቱ የሕገ መንግሥቱን መርሆዎች መሠረት በማድረግ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ግንባታ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ኣስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል ። መ ) ወጣቱ የሀገሪቱን ሕዝቦች ባህል እንዲጠብቅና እንዲያዳብር ያበረታታል ፤ ሠ ) ከሚመለከታቸው አካላት በተለይም ከክልሎች ጋር በመተባበር የወጣቱን ሁለንተናዊ ሰብእና ለማዳበር የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከና ረ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፲ ) የተመለከቱትን አስፈጻሚ ኣካላት በበላይነት ይመራል ፥ ያስተባ ፪ • የዚህ ኣንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በአዋጅ ቁጥር ፲፪ / ፲፱፻ዥ፯ እና በሌሎች ሕጎች ለእስ ፖርት ኮሚሽን ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች እና በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ፡ ( ' ( ፬ ) ( ፭ ) ' ( ፯እና ( ፰ ) እንዲሁም ባህልን በሚመለከት በሌሎች ሕጎች ለባህልና ማስታ ወቂያ ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩት ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለወጣቶች ፣ የእስፖርትና የባህል ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ፳፪ • የማዕድን ሚኒስቴር ማዕድንን በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፲፭ እና በሌሎች ሕጎች ለማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለማዕድን ሚኒስቴር ተሰጥተዋል ። ፳፫ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፳ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ። ገጽ ፩ሺ፮፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፬ ስለሌሎች አስፈጻሚ ኣካላት በዚህ አዋጅ ያልተመለከተ የማናቸውም የፌዴራሉ መንግሥት አስፈጻሚ አካል ተጠሪነትም ሆነ ሥልጣንና ተግባር በተቋቋመበት ሕግ በተደነገገው መሠረት ይቀጥላል ። ፳፭ የተሻሩ ሕጎች ፩ የአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፫፯ አንቀጽ ፮ እና ፱ በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ። ፪ ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ፡ መመሪያ ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ አዋጅ በተመለከቱ | 26. Transfer of Rights and Obligations ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳፮ መብትና ግዴታዎች ስለማስተላለፍ ፩ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር እንዲሁም የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ተላልፈዋል ። ፪ . የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተላልፈዋል ። ፫ • የፌዴራል መንግሥት ገቢዎች ቦርድ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለገቢዎች ሚኒስቴር ተላል ፬ . የማስታወቂያና የባህል ሚኒስቴር መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለማስታወቂያ ሚኒስቴር ተላልፈዋል ። ፭ የእስፖርት ኮሚሽን መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለወጣቶች ' የእስፖርትና የባህል ሚኒስቴር ተላልፈዋል ። ፮ : የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለማዕድን ሚኒስቴር ተላልፈዋል ። ፳፯ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓም ጀምሮ የፀና አዲስ አበባ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ