×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 277/1994 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንና የኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፳፬ ኣዲስ ኣበባ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፲፬ ጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፯ / ፲፱፻፲፬ ዓም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንና የኢን ዱስትሪ ልማት ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፯፻፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፯ / ፲፱፻፲፬ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንንና የኢንዱስትሪ ልማት ፈንድን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የልማት ድርጅቶች በመንግሥት ይዞታ ሥር እስካሉ ድረስ ተወዳ ዳሪና አትራፊ ሆነው በመቀጠል የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ በማስፈጸምና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማምጣት ረገድ | under state ownership , it is necessary to provide them with ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ የሚያስችል አመራርና | such guidance and support so as to enable them to be ድጋፍ መስጠት በማስፈለጉ ፣ ይህንን ዓላማ ለማስፈጸም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች | in the implementation of the country's industrialdevelopment ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንን በማጠናከር ራሱን የቻለ የመንግሥት | strategy and the enhancement of economic growth ; መሥሪያ ቤት አድርጎ ማደራጀትና በሥራ ላይ ያለውን የኢንዱ [ supervising Authority needs to be strengthened and or ስትሪ ልማት ፈንድ በሕግ ማቋቋም በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት | Industrial Development Fund has to be established by law , አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ | 1. Short Title ባለሥልጣንና የኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፯ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር | 2 . Definitions በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ያ ዎች ይኖሩታል ገጽ ፩ሺ፯፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta No. 24 27 June , 2002 – Page 1761 ፩ . “ የመንግሥት የልማት ድርጅት ” ማለት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፫፬ አንቀጽ ፪ ፲፩ የተመለከተውን ትርጓሜ የሚያሟላ ድርጅት ፣ ወይም አክሲዮኖቹ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤ ትነት የተያዙ አክሲዮን ማኅበር ሲሆን በሌሎች ሕጎች ወይም በመንግሥት ውሳኔ የተለየ ተቆጣጣሪ ባለሥ ልጣን የተሰየመላቸውን ድርጅቶች አይጨምርም ፤ ፪ “ አክሲዮን ማኅበር ” ማለት በከፊል በመንግሥት ባለቤ ትነት የተያዘ አክሲዮን ማኅበር ሲሆን መንግሥት በልማት ድርጅቶች አማካይነት ባለአክሲዮን የሆነባ ቸውን አክሲዮን ማኅበራት አይጨምርም፡ ፫ . “ የሥራ አመራር ቦርድ ” ማለት የመንግሥት የልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘ አክሲዮን ማኅበር የዲሬ ክተሮች ቦርድን ይጨምራል ፬ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክፍል ሁለት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ፫ . መቋቋም ፩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥ ልጣን ከዚህ በኋላ “ ባለሥልጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ . ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንዳስፈላ ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ፩ : የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አቅማቸውን በተሻለ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲያውሉ በማስቻልና የተሻሻለ የማኔጅመንት ሥርዓቶችንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሥራ አፈጻጸማቸው እንዲሻሻልና የላቀ ውጤት እንዲ ያመጡ ማገዝ ' ፪ • በተለያዩ ምክንያቶች የግል ባለሀብቶች ሊሳተፉባቸው ባልቻሉ ለኢኮኖሚው አጠቃላይ ልማት ማነቆ ሊሆኑ በሚችሉ ዘርፎች አዳዲስ የልማት ድርጅቶች እንዲ ቋቋሙ ማድረግ፡ ፫ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አመራር መቆጣጠር፡ ፬ . በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማኅበራት የመንግሥትን የባለቤትነት መብት ማስከበር ። ፮ ሥልጣንና ተግባር አግባብነት ያላቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኣዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፬ እና የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች እንደተ ጠበቁ ሆኖ ፤ ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የልማት ድርጅቶችን ለማቋቋም የሚያስችሉ የፕሮጄክት ጥናቶችን ማካሄድና የዚህ ኣዋጅ ኣንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) / ሀ / እና / ፪ / ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፣ ለመነሻ ካፒታል የሚያ ስፈልገውን ገንዘብ ከመንግሥት ማስመደብ፡ ፪ ከመንግሥት ጋር በቅንጅት ኢንቨስት ለማድረግ የሚፈልጉ ባለሀብቶች የሚያቀርቧቸውን የፕሮጄክት ሃሳቦች መገምገምና ለሚኒስቴሩ አቅርቦ ማስፀደቅ ' ተግባ ራዊነታቸውንም መከታተል ገጽ ፩ሺ፯፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም • ፫ • የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አቅም ለመገንባት የሚረዱ ጥናቶችን በማካሄድ አጠቃላይ መመሪያዎችን መስጠት፡ ፬ . የመንግሥት የልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና አባላትን መመደብና ማንሳት ' አበላቸውንም መወሰን ሆኖም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፷፬ የአንቀፅ ፲፪ / ፪ / ድንጋጌ አክሲዮኖቹ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የአክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምደባ በሚመለከትምተፈፃሚነትይኖረዋል ። ፭ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የውጭ ኦዲተሮች ምደባ ማጽደቅ ፮ : የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አጠቃላይ ግቦችና የኢንቨስትመንት እቅዶች ማጽደቅ፡ ፯ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አፈጻጸም መከታ ተልና መገምገም ፰ በውጭ ኦዲተሮች የተመረመሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የሂሳብ ሪፖርቶች ማጽደቅ፡ ፱ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች አጠቃላይ የተጣራ ትርፍ ላይ በየዓመቱ ለመንግሥት ፈሰስ ሊደረግ የሚገ ባውን መጠን በመንግሥት ለማስወሰን የሚያስችል መረጃ ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ለሚኒስቴሩ ማቅረብ፡ ፲ . የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሂሳብ ከመዝገብ ስለ ሚሰረዝበት ሁኔታ መመሪያ ማውጣትና አፈጻጸሙን መከታተል ፲፩ : የመንግሥት የልማት ድርጅት ካፒታል እንዲጨምር ወይም እንዲቀንስ መወሰን፡ ፲፪ የመንግሥት የልማት ድርጅት የተፈቀደ ካፒታል በመ ንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፳ / ፪ / በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ እንዲያልቅ የመጠባበቂያ ሂሳቦች እንዲያዙ ፣ ወይም ከመንግሥት ገንዘብ እንዲመደብ ማድረግ ፲፫ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ማዋሃድ ወይም መከፋፈል ሲያስፈልግ ተገቢውን ጥናት አካሂዶ ለሚኒ ስቴሩ የውሣኔ ሃሳብ ማቅረብ፡ ፲፬ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሥራ አመራር ቦርድና የማኔጅመንት አባላት ተፈጻሚ የሚሆን በውጤት ላይ የተመሠረተ የማበረታቻ ሥርዓት መዘር ጋትና ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ ፲፭ በአክሲዮን ማኅበራት የባለአክሲዮኖች ጉባኤ መንግ ሥትን መወከል ' በመንግሥት በኩል የሚቀርቡ የዲሬ ክተሮች ቦርድ እጩ አባላትን መሰየም፡ ፲፮ : የመንግሥት የልማት ድርጅት በማኔጅመንት ወይም በሊዝ ኮንትራት የሚተዳደርበትን ሁኔታ ማጥናትና በሚኒስቴሩ ሲፈቀድ አፈጻጸሙን መከታተል ፲፯ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በቅንጅት በመሥራት የጋራ ዓላማዎቻቸውን ለማራመድ እንዲችሉ ማበረታ ታትና ማገዝ ' ፲፰ በሕግ መሠረት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሠራተ ኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ስለማቆየት በሚቀርብ ጥያቄ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት፡ ፲፱ የንብረት ባለቤት መሆን ' ውል መዋዋል በስሙ መክሰስና መከሰስ ፳ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ። ገጽ ፬ሺ፯፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም . Federal Negarit Gazeta No. 24 ፯ . የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፩ በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ዳይሬክተር፡ እና ፪ አስፈላጊው ሠራተኞች፡ ይኖሩታል ። ፰፡ የዋናው ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ዳይሬክተር የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖሚኒስትሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዋናው ዳይሬ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የባለሥ ጣኑን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የባለሥል ጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ መ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፣ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ፣ ረ ) የባለሥልጣኑን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ። ፫ ዋናው ዳይሬክተር ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለሥ ልጣኑኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተ ላልፍይችላል ። ሆኖም እርሱ በማይኖርበትጊዜ ተክቶት የሚሠራው ኃላፊ ከ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ ለሚኒስቴሩ ቀርቦ መፈቀድ አለባት ። ፱ . በጀት የባለሥልጣኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ፲ የሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የባለሥልጣኑ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በየዓመቱ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር ይመረመራሉ ። ክፍል ሦስት የኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ ፲፩ መቋቋም የኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፲፪ የፈንዱ ምንጭ የፈንዱ የገንዘብ ምንጭ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ( ፪ ) መሠረት ተወስኖ ለመንግሥት ፈሰስ የሚያደርጉት የትርፍድርሻ ከተቀነሰ በኋላ ከሚቀረው ትርፋቸው ላይ ባለሥልጣኑ በሚያቀርበው የውሳኔ ሃሣብ መሠረት ሚኒስቴሩ በሚወስነው መቶኛ የሚቀነስ ሂሳብ ይሆናል ። ገጽ ፩ሺ፯፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • Federal Negarit Gazeta No. 24 ፲፫ • የፈንዱ አጠቃቀም ፩ ፈንዱ ለሚከተሉት ዓላማዎች ይውላል ፣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፪ ) መሠረት ለሚቋቋሙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ፕሮጄክቶች ማስፈጸሚያና ለማቋቋሚያ ካፒታል ፣ ለ ) በአገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ነባር የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለማሻሻልና ለማስፋፋት የሚያስፈልገውን የካፒታል ወጭ ለመሸፈን ፣ ሐ ) ኪሣራ የደረሰበት የመንግሥት የልማት ድርጅት ከመፍረስእንዲድን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኪሣራ የጐደለውን ካፒታል ለመተኪያ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ከፈንዱ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ክፍያ በሚኒስቴሩ መፈቀድ አለበት ። የፈንዱ ሂሳብ ፩ . ባለሥልጣኑ የፈንዱን ሂሳብ በሚመለከት የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት በተለይ ይይዛል ። ፪ የፈንዱ ሂሳብ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰ ይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፭ ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ፩ . የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፷፬ አንቀጽ ፲፩ ድንጋጌዎች ባለሥልጣኑን በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆኑም ። ፪ ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ ፣ ደንብ ፣ መመሪያ ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፲፮ መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ጽ / ቤት በመባል ይታወቅ የነበረው አካል መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለባለሥልጣኑ ተላልፈዋል ። ፲፯ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?