×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
“የሚኒስትሮችምክር ቤት ደንብቻርተር) ቁጥር ፩Trg Zeri፯ ዓም የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋሚያ የወጣ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነጋሪት ጋዜጣ አሥራ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ - መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ “ የሚኒስትሮች ምክር ቤትደንብ ( ቻርተር ) ቁጥር ፩፻፲፪ / ፲፱፻፶፯ዓም የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋሚያ የወጣ ደንብ ....... ገጽ ፪ሺ፱፻፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ( ቻርተር ) ቁጥር ፩፻፲፪ / ፲፱፻፲፯ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት | REGULATIONS NO.112 / 2004 COUNCIL OF MINISTER ደንብ ቻርተር ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እንዲሁም የከፍተኛ | Pursuant to Artice 5 of Definitions of Powers and Duties of ትምህርት አዋጅ ቁጥር ፪፻፶፩ / ፲፱፻፵፭ አንቀጽ ፰ መሠረት ይህን ደንብ ( ቻርተር አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ቻርተር “ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚኒስ | 1. Short Title ትሮች ምክር ቤት ደንብ ( ቻርተር ) ቁጥር ፩፻፲፪ / ፲፱፻፮፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ቻርተር ውስጥ ፡ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያ ሰጠው ካልሆነ በስተቀር ፣ ፩ “ አዋጅ ” ማለት የከፍተኛ ትምህርተአዋጅቁጥር፫፻፲፩ / ፲፱፻፶፭ ነው ። ፪ “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፯ ፩ ) የተጠቀሰው ክልል ፫ “ መንግሥት ” ፣ “ ሚኒስቴር ” ፡ “ ሚኒስትር ” ፣ ቦርድ ” ፣ “ ሴኔት ” ፡ “ የአካዳሚክ ሠራተኛ ” ፣ “ ፈንድ ” “ ድርጅት ” ፡ “ የከፍተኛትምህርትተቋም ” የሚሉ ቃላት በአዋጅ የተሰጣቸው ትርጉም ይኖራቸዋል ። ያንዱ ዋጋ 4.40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ግለጫና የሥራ እንቅስቃሴ የድርጅቱ ገጽ ፪ሺ፱፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ - መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም ፳፩ የገቢ ምንጭ በአዋጁ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ፩ : ይህ ቻርተር ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ከዩኒቨርሲቲው የገቢ ምንጭ አካላት የተገኙ ገቢዎች የድርጅቱ የገቢ ምንጭ ይሆናሉ ። ፪ : ቻርተሩ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የነበሩ የዩኒቨርሲቲው የገቢ ማመንጫ አካላት በድርጅቱ ሥር ይሆናሉ ። ፳፪ የድርጅቱ ሥልጣንና ተግባራት ፈቃድ ማግኘትን የመሣሠሉ በሕግ የተደነገጉ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ድርጅቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፩ . የማማከር አገልግሎት መስጠት ፣ ፪ . ላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ፫ የእርሻ ውጤቶችን ማምረትና ማሠራጨት ፬ . የሆስፒታል አገልግሎት ፭፡ ጥናቶችና ንድፍ ሥራዎችን እና የፕሮጀክት ሰነዶችን ማዘጋጀትና አስተያየት መስጠት ፣ ፮ : ልዩ ፋርማሲዎች ፯ ኢንተርኔት ካፌና ኮምፒዩተር ማዕከል ፣ ፰ ያሉትን መሣሪያዎችና መገልገያዎች ማከራየት ፱ መጸሕፍትንና የህትመት ውጤቶችን መሸጥ ፣ ፲ የንብረቶች ባለቤት መሆን ፣ ፳፫ • የድርጅቱ አስተዳደር የድርጅቱ ኣጠቃላይ አስተዳደር ድርጅቱን ፣ አካላቱን የሚመሩሰዎችየሚመረጡበትእና የሚተዳደሩበት የድርጅቱ መዋቅር ፣ የካፒታሉና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ጉዳዮች በቦርዱ ይወሰናሉ ። ፳፬ • የድርጅቱ የፋይናንስ መግለጫና የሥራ እንቅስቃሴን ስለማ የድርጅቱ የፋይናንስ የበጀት ዓመት ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት የ፫ ወራት ጊዜ ውስጥ በሚመለከተው የድርጅቱ አካል ለቦርዱ መቅረብ አለበት ። ፳፭ ስለ ፈንድ መቋቋም ዓላማና የገቢ ምንጩ በአዋጁ የተገለጸው የዩኒቨርሲቲው ፈንድ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፳፮ የፈንዱ ኣካላት ፩ . ፈንዱ ፣ ሀ ) የፈንዱ አስተዳደር ቦርድና ( ከዚህ በኋላ ቦርድ ተብሎ የሚጠራ ) ለ ) ሴክሬታሪያት ይኖረዋል ። ፪ • ቦርዱ ተጠሪነቱ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ይሆናል ። ፳፯ የፈንዱ ቦርድ አባላት ፩ : ቦርዱ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ፪ • የቦርዱ የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል ። ፫ የቦርዱ አባላት በማናቸውም ሁኔታ ሥራቸውን መሥራት ካልቻሉ በምትካቸው አዲስ አባል ይሰየማል ። ፳፰ የፈንዱ ቦርድ ስልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፤ ፩ የፈንዱ ዓላማዎችን ሥራላይመዋሉን ይቆጣጠራል ለአፈጸ ጸማቸው ኣስፈላጊውን መመሪያ ያወጣል ፣ ይህን ቻርተር የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ገጽ ፪ሺ፱፻፲፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም : ፪ ከልዩ ልዩ የፈንዱምንጮች የተገኙገቢዎች በተገቢ ሁኔታ ሥራ ላይ መዋላቸውን በተመለከተ በሴክሬታሪያቱ የሚቀ ርብለትን ሪፖርት መርምሮ ያጸድቃል ። ፫ • የፈንዱ ገቢዎች በየጊዜው መሰብሰባቸውን ያረጋግጣል ። ፬ • ለፈንዱ ዓላማ መሳካት የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ። ፳፱ • የፈንዱ ቦርድ ስብሰባዎች የቦርዱ ስብሰባዎች የሚካሄዱበት ሁኔታና የድምጽ አሰጣጡ ሥነ - ሥርዓት ቦርዱ በሚያወጣውየውስጥ ደንብ ይወሰናል ። ፴ • የአስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ ሥልጣንና ተግባር አስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ። ፩ ዓመታዊ በጀት ፣ የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ መግለጫ ሪፖርቶችን ለፈንዱ ቦርዱ አቅርቦ ያጸድቃል ። ፪ . በፈንዱ ድጋፍ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን ይመረምራል ፣ በቦርዱ መመሪያ መሠረት የፕሮጀክቶቹን የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ይፈቅዳል ፣ ፫ • ለፈንዱ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታ ዎችን ያጠናል ፣ ፬ • የቦርዱን የሥራ መዛግብት ፣ ዘገባዎችና የስብሰባ ቃለ ጉባዔዎችን ይይዛል ፣ የቦርዱ ውሣኔዎች በትክክል መፈጸማ ቸውን ያረጋግጣል ፣ ፭ በፈንድ ቦርዱ የሚሰጡ ሌሎች ሥራዎችን ያከናውናል ። ፴፩ : የፈንዱ ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር የፈንዱ ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ፈንዱን በሚመለከት ጉዳዮች ተጠሪነቱ ለቦርዱ ሆኖ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፴ | 31. Powers and Duties of Director of the Secretariat of the የተመለከቱትን የሴክሬታሪያቱን ሥልጣንና ተግባር ሥራላይ ያውላል ። ክፍል ስድስት ስለ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ፴፪ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች አይኖራቸውም ። ፴፫ የመብትና ግዴታ መተላለፍ ጎንደር በመባል የሚታወቀው ዩኒቨርሲቲ በዚህ ቻርተር | 33. Transfer of Rights and Duties ከመቋቋሙ በፊት ያለው መብትና የነበረበት ግዴታ በዚህ ቻርተር ለዩኒቨርስቲው ተላልፋል ። ፴፬ • ቻርተሩ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ቻርተር በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ ፪ሺ፱፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ክፍል ሁለት የዩኒቨርሲቲው መቋቋመና ዓላማ መቋቋምና ተጠሪነት ፩ . ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ( ከዚህ በኋላ “ ዩኒቨርሲቲ ” ተብሎ | 3 . Establishment and Accountability የሚጠራ ) ራሱን የቻለና የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሆኖ በዚህ ቻርተር ተቋቁሟል ። ፪ ዩኒቨርሲቲ በሥሩ የሚከተሉት ተቋማትንና ፋካልቲ ዎችን እና ትምህርት ቤቶችን ያካትታል ፦ ሀ ) የህክምናነ ጤና ሣይንን ኮሌጅ ለ ) የሳይንስ ፋኩልቲ ሐ ) የኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ መ ) የማህበራዊ ሣይንስ ፣ ሁማኒቲስና ቢዝነስ ፋኩልቲ ሠ ) የእንስሳት ህክምና ፋኩልቲ ረ ) የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ሰ ) ወደፊት በቦርዱና በሚኒስቴሩ የሚቋቋሙ ሌሎች ፋኩልቲዎች ፣ ኮሌጆችና ተቋማት ፫ ዩኒቨርሲቲው ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ይሆናል ። ፬ ዓላማ ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ። ሀገሪቱን በተለያዩ ሙያዎች ሊያገለግል የሚችል | 4. Objective የሰለጠነ የሰው ኃይል በብዛትና በጥራት ማፍራት ፣ የዘር ፣ የሃይማኖት ፣ የፆታ ፣ የፖለቲካና የመሳሰሉት ልዩነቶች የማይደረግበት የከፍተኛ ትምህርት አገል ግሎት መስጠት ፣ ሚዛናዊ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሥርጭት እንዲኖር ማድረግ ፣ ፬ • ችግር ፈቺ የሆነና የሀገሪቱን እምቅ ሃብት ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ትምህርታዊና ተቋማዊ ሥርዓት መዘርጋት እና ጥናትና ምርምር ማድረግ ፣ ፭ ከሀገሪቱእናከክልሉ ፍላጎት እና ዕድገት ጋር የተጣጣመ የከፍተኛ ትምህርት እና የህብረተሰብ አገልግሎት መስጠት ፣ ፮ የዩኒቨርሲቲውን ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት መዘርጋት ፣ ፯ በአስተዳደር ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚመለከተውን ተሳትፎን ማረጋገጥ ፣ የአሳታፊነት ባህልን መፍጠርና ማሣደግ ፣ ፰ በሰዎች መካከል መከባበር ፣ መቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል እንዲጎለብትና እንዲሰርፅ ማድረግ ፣ ፭ ሥልጣንና ተግባር ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፩ ፋኩልቲዎች ፣ ኮሌጆችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ተቋሞች አቋቁሞ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መቀየስና ሥራ ማካሄድ ፣ ፪ : የምስክር ወረቀት ፣ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የአካዳሚክ ሽልማቶችን መስጠት እንዲሁም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የአካዳሚክ ሜዳይ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት ፣ ፫ • ለሃገር ዕድገት ቅድሚያ በሚሰጥባቸው መስኮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ ፣ ፩ . ሴሚናሮች ፣ ዓውደ ጥናቶችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋ ጀትና ማካሄድ ፣ ፭ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ከሚገኙ አቻ ዩኒቨርስ ቲዎች የምርምር ተቋሞችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አካላት ጋር ግንኙነት መመሥረት ፣ ፮ የማማከር ፣ የሥልጠናና ሌሎች አገልግሎቶች ለህብረ ተሰቡ ፣ ለክልል መስተዳድሮችና ለፌዴራል መንግስት በአግባቡ መስጠት ፣ እንዲሁም ውጤቱን ለማሠራጨት የመዓዛ ሳራሞች | ገጽ ፪ሺ፬፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ፯ የትምህርት መጽሔቶችና ማቋቋምና ማሠራጨት ፣ ፰ የማንኛውንም ንብረት ባለቤት የመሆን ፣ ፬ / ከሶስተኛ ወገን ጋር ውል የመፈራረም ፣ በሥሙ የመክሰስና የመከሰስ ፣ ፲፩ ለሚሰጠው አገልግሎት ተገቢ ክፍያ የማስከፈል ፣ የገቢ ፈንድ እና የገቢ ማመንጫ ድርጅት ማቋቋም ማስተዳደር ፣ ፲፫ . የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን ። ፮ ነጻነትና ተጠያቂነት በቦርዱ የውስጥ ደንቦችና በሌሎች ህጎች የተደነገገው እነደተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ነፃነትና ተጠያቂነት በሚከተሉት ላይ ይኖረዋል ። የሲቪል ሰርቪስ መርሆዎችን መሠረት በማድረግ የተቋሙ ሠራተኞች አስተዳደር ፣ ቅጥር ፣ ዕድገት ፣ እገዳና ሌሎች ጉዳዮችን መፈጸም ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ አስተዳደር ህግ በመንተራስ አስተዳደር ፣ በውስጡ ላሉ አካላት በጀት የማከፋፈልና በአግባቡ የመጠቀም ፣ ሐ ) የሃገሪቱን እና የዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ ሥርዓት ትምህርት የመገምገምና የማሻሻል ፣ መ ) የግልፅነትና ተጠያቂነት መርህር የተከተለ የምርምር ስትራቴጂ መንደፍና ማስፈጸም ፣ ሠ ) የሲቪል ሰርቪስ መርሆዎችን በመመርኮዝ የውስጥ አደረጃጀትን የመወሰን ፣ ረ ) የትምህርት ፣ የምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሀገር ውስጥና ከዉጪ ሀገር ዩኒቨርስቲዎች ጋር የትብብር ግንኙነት መፍጠር ሰ ) የገቢ ማመንጫ ድርጅትን ማቋቋምና ገቢዎቹን የመጠቀም ፣ በህግ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨር ሲቲው ዕውነትን ለመሻት ፣ ዕውቀትን ለማበልጸግ ማስተማር እና ምርምር ነፃነት ይኖረዋል ። ፫ . የዩኒቨርሲቲው ተጠያቂነት በተለይ ፤ ሀ ) የሚያካሂዳቸው የትምህርትና ምርምር ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መሆናቸው ፣ ለ ) ለመንግስት ፕሮግራሞች ቅድሚያ መስጠቱንና ከሃገራዊ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘቡ መሆናቸውን ፣ ( ሐ ) አጠቃላይ አሠራሩ በግልጽነትና በአሳታፊነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ፣ መ ) የበጀትና ሃብት ኣደላደሉና አጠቃቀሙ ወጪ ቆጣቢና ለህዝብ ኃላፊነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ፣ ሠ ) የመማር ማስተማርና የምርምር ሥራዎች ተቋማዊ ሆነው በግልጽ የሚከናወኑ መሆኑን ፣ ረ ) ዩኒቨርሲቲውና የተቋሙ ማኅበረሰብ በሚያስመዘ ግቡት የጥራትና ተገቢነት ውጤት የሚለኩ መሆኑን ፣ ሰ ) ማንኛውም በማስተማር ፣ በመመራመር በማስተዳ ደርና በመምራትኃላፊነት ላይ ያለ የተቋሙ ባልደረባ በተናጠልም ሆነ በጋራ ለተጠሪው አካልና ለህብረ ተሰብ ተጠያቂነት ያለው መሆኑ ፣ በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ ይሆናል ። ፯ የመረጃ ልውውጥ ቦርዱ በሚያወጣው የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት መመሪያ መሠረት ከግል ተቋማት ፣ ከመንግስታዊ ተቋማት እና ከሌሎች አካላት ጋር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል ። ገጽ ፪ሺ፱፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ፲፱፻፷፯ ዓም : ፪ ዩኒቨርሲቲው ማንኛውም ከትምህርት ጋር የተያያዘ ምርምር የሚሠራ ሠራተኛ ወይም ተማሪ ጥያቄ ሲያቀር ብለት መረጃ ይሰጣል ወይም መረጃ እንዲያገኝ ያደርጋል ። ፫ የምርምርና ጥናት ጽሑፎች ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ፣ ተማራማሪዎችና ሌሎች ተጠቃሚዎች በሙሉ እንዲ ደርሱ የሚደረጉ መሆን አለባቸው ። ፰ ጥናትና ምርምር ፩ የጥናትና ምርምር ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው አደረጃጀት በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ደንብና የአስተዳደር መዋቅር የሚወሰን ሆኖ የሚከተሉት መስፈ ርቶች ይኖሩታል ። ሀ ) የዩኒቨርሲቲው የምርምር ተግባራት በአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዚዳንት ይመራል ። ለ ) ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የምርምር ተቋማት ሊከፍት ይችላል ። ሐ ) ዩኒቨርሲቲው ለሚያከናውነውምርምርና ጥናት በቂ ገንዘብ ማፈላለግ ፣ መመደብና በሥራ ላይ ማዋል ይኖርበታል ። መ ) ዩኒቨርሲቲው የምርምር ሥራን የሚሠሩ ተመራማ ሪዎችና የምርምር ረዳቶች በግል ወይም በጋራ ቅጥር ሊቀጥር ይችላል ። ሠ ) ዩኒቨርሲቲው የሚያካሂዳቸው ምርምሮች አግባ ብነት ካላቸው ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር ሊሆን ይችላል ። ፪ • የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ርዕስ አመራረጥ ፣ የበጀት አጠቃቀምና የሃብት አያያዝ ፣ እንዲሁም የምርምር አፈጻጸም ግልጽና ተጠያቂነት መርሆዎችን የተከተለ ይሆናል ። ክፍል ሦስት ስለ ዩኒቨርሲቲው ፖሊሲና የሥራ አስፈጻሚ አካላት ፱ : ስለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ፩ . የዩኒቨርሲቲው ቦርድ በሚኒስቴሩ የሚሰየም ሰብሳቢ ይኖረዋል ። ፪ • ቦርዱ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታለ ። ሀ ) የትምህርት ሚኒስቴር ለ ) የፌዴራል መንግስት ተወካይ ( አንድ ) ሐ ) የክልል መንግስት ተወካዮች ( አራት ) መ ) ታዋቂ ግለሰብ ሠ ) ሌሎች በቦርዱ የሚሰየሙ አባላት ረ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አባል እና ጸሓፊ ፫ . በቦርዱ የሚሰየሙ ኣባላት ለልማት አስተዋጽኦ ያደረጉ የዩኒቨርሲቲው አገልግሎት ተጠቃሚዎች መሆን አለባቸው ። ቦርዱ በአዋጅ የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፲ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሴኔቱ ተጠሪነቱ ለፕሬዚዳንቱ ሆኖ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ። ፩ . የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፪ . የዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች ፫ . አካዳሚክ ፕሮግራም ኃላፊ ፬ የፋኩልቲ ፣ የኢንስቲትዩት ፣ የት / ቤቶችና ኮሌጆች ፭ የህዝብና ውጭ ግንኙነት ኃላፊ ፮ . የሆስፒታል ዳይሬክተር ፯ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ፰ የዩኒቨርሲቲው የቤተመጻሕፍትኃላፊ ፲፩ . በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች . ” \ ገጽ ፪ሺ፬፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም የተማሪዎች ዲን የአካዳሚክ ሠራተኞች ሁለት ተወካዮች ሁለት የተማሪዎች ተወካዮች ፲፪ . የዩኒቨርሲቲው የሴቶች ጉዳይ የምርምርና ህትመት ኃላፊ ቦርዱ የሚሰይማቸው አግባብነት ያላቸው ሌሎች ኃላፊዎች የሴኔቱ ሥልጣንና ተግባር በአዋጁ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ሴኔቱ የሚከ ተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ በቦርዱ የሚወጡ አጠቃላይ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ፣ የተማሪዎች አቀባበልን ፣ የትምህርት ደረጃ አወሳሰን የዲሲፕሊን ጉዳዮችንና ምረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ማውጣት ፣ በዚህ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታ ዎችን መመርመር ፣ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥና ደረጃዎች አቅጣጫዎችን መወሰን ፣ የሚወጡ ፖሊሲዎችን መሠረት በማድረግ በተለይ በተማሪዎች አስተዳደር ፣ የዩኒቨር ሲቲው የትምህርት ነክ ጉዳዮች ፣ የትምህርት ኃላፊዎች የምርጫ ሥነ ሥርዓት ፣ የአካዳሚክ ሠራተኞች ቅጥር ፣ ዕድገት ፣ ጥቅማ ጥቅም ፣ ዲሲፒሊን ፣ ደመወዝ በሚመ ለከት መመሪያ ማውጣት ፣ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እነዲሰጥ ለቦርዱ ሃሣብ ማቅረብ ፣ የረዳትና የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን መስጠት ፣ የአካዳሚክ ሠራተኞችን ቅጥር መመርመርና ማስጽደቅ ፣ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መወሰን ፣ ፕሬዚዳንቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የሚጠራው ስብሰባ እንደተጠበቀ ሆኖ በየሩብ ዓመቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ መሰብሰብ ፣ ተግባሩን ለሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላትና ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ማስተላለፍ ፣ ፲፪ ስለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች ፩ የዩኒቨርሲቲው እጩ ፕሬዚዳንት ሆነው የሚቀርቡ ሰዎች የተመሰከረለት የአካዳሚክና አስተዳደር ብቃት እንዲሁም መልካም ሥነ ምግባር ሊኖራቸው ይገባል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው ለፕሬዚዳንቱ ተጠሪ የሆኑ ሦስትም / ፕሬዚዳ ንቶች ይኖሩታል ። ፫ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ። ፬ • የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በአዋጁ የተመለከቱት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፲፫ . የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር ፩ የአካዳሚክና ምርምር ም / ፕሬዚዳንት ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ የዩ ቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራል ፣ ይረዳል ፣ ለ ) በቦርዱና በሴኔቱ የተላለፉ ውሣኔዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ በማዋል ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ ክፍሎችን ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ሐ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በማይኖርበት ጊዜ ተተከቶ ዩኒቨርሲቲውን ይመራል ፣ ያስተባብራል ፣ ገጽ ፪ሺ፬፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓም መ ) የትምህርት ማዕከላትን እንደፋኩልቲ ፣ ኮሌጅ ፣ ተቋም ፣ ትምህርት ቤት እና ተከታታይ ትምህርት ክፍሎችን ሥራ ያቅዳል ፤ ይመራል ፣ በበላይነት ይቆጣ ሠ ) የምርምር እና ጥናት እንቅስቃሴዎችን ያቅዳል ፣ ይመራል ፣ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ ረ ) የዩኒቨርሲቲውን መጻሕፍት ቤት ፣ ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች በሥሩ ያሉትን ክፍሎች ይመራል ፣ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ ሰ ) ብሔራዊና ዓለምአቀፍ ግንኙነቶችንና ትብብሮችን ያፈላልጋል ፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ፣ ሸ ) በሥራ ያሉ ክፍሎችን የሥራ አፈጻጸም ፣ በጀት ክፍፍልና አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች እንቅስቃሴ ዎችን በተመለከተ ሪፖርት ለፕሬዚዳንት ያቀርባል ፣ ቀ ) በቦርዱ ፣ በሴኔቱና በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሣሣይ ተግባራት ያከናውናል ። ፪ . የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ም / ፕሬዚዳንት ፣ ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመ ቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራል ፣ ይረዳል ፣ ለ ) ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ የዩኒቨርሲቲው ክፍሎችን ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ሐ ) የተማሪዎች አገልግሎትን ፣ የአስተዳደርና የፋይናንስ ሥራ ያቅዳል ፣ ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ መ ) በቦርድና በሴኔቱ የተሰጡ ውሣኔዎችንና መመሪያ ዎችን ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ሠ ) የተቋሙን አስተዳደርና ማኔጅመንት አቅም ለማሻሻል ከብሔራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር ግንኙነት ይፈጥራል ፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል ፣ ረ ) የሥራ አፈጻጸም ፣ የበጀት አመዳደብና አጠቃቀም እንዲሁም የሌሎች እንቅስቃሴችን ሪፖርት ለፕሬዚ ዳንቱ ያቀርባል ፣ ሰ ) በቦርዱ ፣ በሴኔቱና በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሣሣይ ተግባራት ያከናውናል ። ፫ . የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም / ፕሬዚዳንት ፣ ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ የዩኒ ቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራል ፣ ይረዳል ፣ ለ ) ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ የዩኒቨርሲቲውን ክፍሎች ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ሐ ) በቦርድና በሴኔቱ የተላለፉ ውሣኔዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፣ መ ) የገቢ ማመንጫ ድርጅቶችንና የዩኒቨርሲቲውን የቢዝነስ ክፍሎች በተመለከተ ያቅዳል ፤ ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ የሥራ ባህልን ያጎለብታል ፣ ሠ ) በዩኒቨርሲቲው ኣዳዲስ የቢዝነስ ሃሣቦችንና ልማትን ያቅዳል ፤ ይመራል ፤ ይቆጣጠራል ፣ ረ ) የዩኒቨርሲቲውን አዳዲስ የልማትና የማስፋፋት የካፒታል ኢንቨስትመንቶችን ያቅዳል ፣ ያስተዳ ሰ ) ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የተገናኙና እርሱን የሚመ ስምምነቶችና ፕሮጀክቶችን አፈጸጸም ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ሸ ) ብሔራዊና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችንና ትብብሮችን ያፈላልጋል ፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ፣ ቀ በሥሩ የሚገኙትን አካላት የሥራ አፈጻጸሙን ፣ የበጀት ድልድልና አጠቃቀምን በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል ፣ ገጽ ፪ሺ፬፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. በ ) የቢዝነስና የስትራቲጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት ያቀርባል ፣ ረ ) ሌሎች ከቦርድ ፣ ከሴኔቱና ከፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል ። ፬ • የህክምናና ጤና ኮሌጅ ለአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዚዳንት ተጠሪ በሆነና የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት በሚኖሩት ተባባሪ ምክትል ፕሬዚዳንት ሊመራ ይችላል ። ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ የዩኒ ቨርሲቲውን ምክትል ፕሬዚዳንት ያማክራል ፣ ይረዳል ፣ ለ ) የህክምናና ጤና ኮሌጅን ትምህርት ፣ ምርምርና አገል ግሎት ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ሐ ) የሆስፒታሉን ታካሚዎችና ጤና አጠባበቅ አገል ግሎት እንዲሁም የአስተዳደርና ፋይናንስ እንቅስቃሴ ዎችን ያቅዳል ፣ ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ መ ) ለህብረተሰብ ተኮር የተግባር ትምህርት የሚያገለግሉ ከተቋሙ ውጭ ያሉ የማሠልጠኛ ጣቢያዎችን እንቅ ስቃሴ ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ሠ ) ከብሔራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ግንኙነትና ትብብር ያፈላልጋል ፣ ረ ) ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ ክፍሎችን የሥራ አፈጸጸም ፣ የበጀት አመዳደብና አጠቃቀም እንዲሁም የሌሎች እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ሰ ) የቢዝነስና የስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ሸ ) በቦርዱ ፣ በሴኔቱና በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሣሣይ ተግባራት ያከናውናል ። ፲፬ . የአካዳሚክ ኮሚሽን ፩ እያንዳንዱ ፋኩልቲ ኮሌጅ ኢንስቲትዩት እና ትምህርት ቤት ለዲኑ ተጠሪ የሆነ የራሱ አካዳሚክ ኮሚሽን ይኖረዋል ። ፪ • የአካዳሚክ ኮሚሽኑ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፣ ሀ ) የፋኩልቲ ፣ ኮሌጅ ፣ ኢንስቲትዩት ወይም ትምህርት ቤት ዲን ለ ) የፋኩልቲ ፣ ኮሌጅ ፣ ት / ቤት ወይም ኢንስቲትዩት ምክትል ዲኖች ካሉ ሐ ) የትምህርት ክፍሎች ኃላፊዎች . መ ) ኣንድ የተማሪዎች ተወካይ ሠ ) በአካዳሚክ ሠራተኞች ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጠ አንድ የመምህራን ተወካይ ረ ) የፋኩልቲው የተከታታይ ትምህርት አስተባባሪ ሰ ) በኮሚሽኑ የሚመደቡ አግባብነት ያላቸው ኃላፊዎች ፫ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የሚያወጣው መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ሀ ) የፋካልቲውን ፣ የኮሌጁን ፣ የተቋሙን ወይም የትም ህርት ቤቱን ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ በጀት በማዘጋጀት ይደለድላል ፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል ፣ ለ ) የሥልጠናና የትምህርት መርሀ ግብሮችን ሥርዓተ ትምህርቶች አዘጋጅቶ በሚመለከተው ያጸድቃል ፣ ሐ ) በሴኔቱ መመሪያ መሠረት የተማሪዎችን ትምህርትና ሥነ ምግባር የተመለከቱ ዝርዝር መስፈርቶችን ይወስናል ፣ መ ) ከትምህርት ጋር የተያያዙ ሽልማቶችንና የክብር ዲግሪእንዲሰጥ ለሴኔቱ ሃሣብ ያቀርባል ሠ ) የሌክቸር ፣ ረዳት ሌክቸረር ፣ ረዳት ምሩቅና ቴክኒክ ረዳቶችን ዕድገት በሴኔቱ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት አጣርቶ ይወስናል ፣ ገጽ ፪ሺ፱፻፲፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም • ረ ) የተባባሪና ረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ለሴኔቱ አቅርቦ ያጸድቃል ፣ ሰ ) የአካዳሚክ ሠራተኞች ቅጥርን ይመረምራል ፣ የነፃ ትምህርት ዕድልና የምርምርና ሰባቲካል እረፍቶችን ያጸድቃል ፣ ሸ ) የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓትና የውስጥ ደንብ ይወስናል ፣ ቀ ) ከሴኔቱ እና ከፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል ። ፲፭ የትምህርት ክፍል ጉባዔ ፩ እያንዳንዱ የትምህርት ክፍል የራሱ ጉባዔ ይኖረዋል ። ፪ የትምህርት ክፍልጉባዔ በትምህርት ክፍሉኃላፊየሚመራ ሆነ ሁሉንም የሙሉ ጊዜ መምህራንን ያካትታል ። ፫ የትምህርት ክፍል ጉባዔ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ሀ ) ተፈላጊ በሆኑና ሰርቲፊኬት ወይም ዲፕሎማ ዲግሪ የሚያሰጡ መርሃ ግብሮችን ለአካዳሚክ ኮሚሽኑ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድ ያስፈጽማል ፣ ለ ) የትምህርት ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ በጀትና ሪፖርት ያዘጋጃል ፣ ይመዘግባል ፣ ሐ ) የትምህርት ክፍሉን የሰው ኃይልና ፋይናንስ ይከታ መ ) የመምህራንና የተማሪዎችን ግምገማና ክትትል ያከና ውናል ፣ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መርምሮ ይወስናል ፣ ሠ ) ፈተናዎችንና የአካዳሚክ ግምገማ ሥርዓትን ደረጃ ያወጣል ፣ ይከታተላል ፣ ረ ) የማስተማሪያ ጽሑፎችን አመራረጥና ዝግጅት ይወስናል ፣ የመምህራንን የሥራ ጫና ይወስናል ፣ ሰ ) በሥርዓተ ትምህርትና በመማር ማስተማር ሥርዓት ማሻሻያዎችና ፈጠራዎች እንዲጎለብቱ ሁኔታዎች ያመቻቻል ፣ ሸ ) የተማሪዎችን ውጤት ያጸድቃል ፣ ቀ ) ሌሎች በፋካልቲውና በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል ። ፲፮ ስለዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ክፍሎች የውስጥ ሥልጣን ፩ . በዚህ ቻርተር አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ፪ ሥር የተዘረሩት እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላት አደረጃጀት ቦርዱ ባጸደቀው መዋቅር መሠረት ይወሰናል ። ፪ . እያንዳንዱ ፋኩልቲ ፣ ተቋም ፣ ትምህርት ቤት ወይም እና ኮሌጅ የበጀት ማዕከል ደረጃ ሊኖረው ይችላል ፣ ፫ • እያንዳንዱ የበጀት ማዕከል የራሱን ዕቅድና በጀት ማዘጋጀት ፣ የበጀት እና ሃብት አጠቃቀምን መወሰንና ሪፖርት ማዘጋጀት ይኖርበታል ። ፲፯ የማኔጅመንት አመራር አሰያየም በዩኒቨርሲቲው አካላት ውስጥ ያሉ አካላትን ለመምራት የሚታጭ ሰው በተለይ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት ። ሀ ) የማኔጅመንት የአስተዳደርና የአመራር ብቃት ያለው ፣ ለ ) በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፣ የምርምርና የኅብረተሰብ ኣገልግሎት ውስጥ ብቁ ተሳትፎ ያለው ፣ ሐ ) ሥራዎቹ ውጤት ያሣዩና መልካም ሥነ ምግባር ያለው ፣ መ ) ዲሞክራሲያዊ እሴቶችን የመተግበርና የማስረጽ ዝግጁ ነትና ቁርጠኝነት ያለው ፣ ገጽ ፪ሺ፱፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ክፍል አራት ስለ ዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችና ተማሪዎች ፲፰፡ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ፩ ዩኒቨርሲቲው የተመለከቱት ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፪ • ዩኒቨርሲቲው ከሌላ መንግሥታዊ ወይም የግል ተቋም ሠራተኛን በጋራ ቅጥር መቅጠር ይችላል ። ፫ • የጋራቅጥሩ በሁለቱ ተቋማት መካከል በሚደረግ ውለታና በግለሰቡ ስምምነት መሠረት ተግባራዊ ይሆናል ። ፩ በጋራ የተቀጠረው ባለሙያ እንደቋሚ መምህር የሚታይ ሆኖ በሕጉ የተመለከቱት ግዴታና መብቶች ይኖሩታል ። ፭ የዩኒቨርስቲው ሠራተኞች መብትና ግዴታ በአዋጁ የተመ ለከተው ይሆናል ። ፲፱ • ስለተማሪዎች መቀበያ መመዘኛ ተማሪዎች ፩ . በሌሎች ህጎች ስለመቀበያ መመዘኛ የተደነገገው እንደተ | 19. Admission of Students ጠበቀ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው ፣ ሀ ) ተገቢውን መመዘኛ ላሟሉ ኢትዮጵያውን ያለምንም ልዩነት ክፍት ይሆናል ለ ) የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ የመዘጋጃ ትምህርት ወይም ሚኒስቴሩ በሰጠው ግምት ደረጃ ያለው የውጭ ሀገር ሁለተኛ ደረጃን ያጠናቀቀ እና በዩኒቨርሲቲ አቸውየተሰጠውን የመግቢያ መመዘኛያሟላ ተማሪን ለቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ትምህርት ይቀበላል ፣ ሐ ) የዲፕሎማ ( 12 + 2 እና 10 + 3 ) ደረጃ ያላቸው ተማሪ ዎችን በአድቫንስድ ተማሪነት በቅድመ ምረቃ ይቀበላል ፣ መ ) የከፍተኛ ትምህርትየቅድመ ምረቃ ትምህርት ያጠና ቀቀና በዩኒቨርሲቲው የተወሰኑ መመዘኛዎችን ያሟላ ተማሪን ለድህረምረቃ መርሃ ግብር ትምህርት ይቀበላል ሠ ) ለሴቶች ፣ ለታዳጊ ክልል ብሔረሰብ እንዲሁም ለጎልማሣ ወይም ልምድ ላላቸው ተማሪዎች የተለየ አቀባበል ሥርዓት ሊወሰን ይችላል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው የሚቀበለው ተማሪ በወጪ መጋራት መርህ መሠረት ያለበትን ግዴታ የሚያሟላ መሆን አለበት ። ፫ ዩኒቨርሲቲው የተማሪውን ችሎታ እና የዕውቀት ደረጃ እንዲሁም ክህሎት ለመገምገም የሚያስችል መመዘኛ ያዘጋጃል ። ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫ መሠረት የሚሰጥ መመዘኛ ለተማሪው በተሰጠው ትምሀርት ወይም ሥልጠና ይዘት ላይ የተመሠረተ ተከታታይ ምዘና መሆን አለበት ፣ ፭ መመዘኛው የሚሰጥበት መንገድ በቃል ፣ በጽሑፍ ፣ በተግ ባርና ሌሎች ሴኔቱ በሚወስንባቸው መንገዶች ሊሆን ይችላል ፣ ፮ • የምዘና ውጤቶች እና የፈተና ወረቀቶችን ለተማሪው መመለስ ወይም በግልጽ ማሳወቅ አለበት ። ክፍል አምስት ስለድርጅትና ፈንድ ፈንድ ፳ ስለ ድርጅቱ መቋቋምና አካላቱ ተጠሪነቱ ለዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚ የሆነ የሚከተሉት አካላት ያሉት የዩኒቨርሲቲው | 20. Establishment ofEnterprise and Its Units ድርጅት ተቋቁሟል ። ሀ ) የምክር አገልግሎት ለ ) የምርት አገልግሎት ሐ ) የፕሮጀክት አገልግሎት መ ) የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኣገልግሎት ሠ ) ወደፊት የሚቋቋሙ ሌሎች አገልግሎቶች

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?