×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
ኣዋጅ ቁጥር 176 1991 የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፰ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፸፮ / ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ገጽ ፩ሺ፩፻፭ $ # ጥጥር አዋጅ ቁጥር ፩፻፸፮ / ፲፱፻፲፩ ስለመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር የወጣ አዋጅ ጤና ለሕዝብ የተደላደለ ሕይወትና ምርታማነት መሠረት መሆኑንና መድኃኒትም በጤና አገልግሎት ውስጥ ያለውን ድርሻ | securing proper life and productivity of the people and እንዲሁም ጤና ለእንስሳት ምርትና ምርታማነት ብሎም ለሀገሪቱ | recognizing that drug shares a vital role in the health service , ኢኮኖሚ የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በመገንዘብ ፤ የመድኃኒት ደህንነት፡ ፈዋሽነትና ጥራት ማረጋገጥና ምርቱን፡ ሥርጭቱን አጠቃቀሙን ሥርዓት ማስያዝ በማስፈለጉ ፤ | efficacy and quality of a drug and so to maintain the proper የናርኮቲክና ሣይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን ሕገወጥ ምርት፡ | production , distribution and use ; ሥርጭትና አጠቃቀም መግታት በማስፈለጉ፡ ለዚህም አስተማማኝ የሆነ የመድኃኒት አስተዳደርና ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል ፩ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፻፶፩ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ያንዱዋጋ 440 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፩፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥርቛ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም : ክፍል ፩ የወንጀል ድንጋጌዎች ሕገወጥ የመድኃኒት ንግድ ሥራ ፩ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ፣ ማንኛውም ፈቃድ የተሰጠው ሰው ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ መሠረት የተመደበ ተቆጣጣሪ ተግባሩን እንዳያከናውን እንቅፋት የፈጠረ ከስድስት ወር በማይበልጥ እሥራት ወይም ከብር ፲ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ለ ) ባለሥልጣኑን ሳያስፈቅድ ፈቃዱን በማናቸውም መንገድ ለሌላ ሰው ካስተላለፈ ከአንድ ዓመት በማያንስና ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፭ሺህ በማያንስና ከብር ፳ሺህ በማይ በልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፪ . ማንኛውም ፈቃድ የተሰጠው የመድኃኒት አምራች፡ አስመጪ ፣ ላኪ ወይም ጅምላ አከፋፋይ ፈቃድ ለሌለው ሰው መድኃኒት ካከፋፈለ ከሁለት ዓመት በማያንስ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፭ሺህ በማያንስና ከብር ፳ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፫ . ማንኛውም ሰው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይኖረው በመድኃኒት የንግድ ሥራ ከተሰማራ ከአምስት ዓመት በማያንስና ከሰባት ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፳ሺህ በማያንስና ከብር ፻ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፬ • ማንኛውም የችርቻሮ ድርጅት የሕክምና ሙያ ከሚፈ ቅደው መጠን አስበልጦ ወይም አሳንሶ ከሸጠ ወይም ፈቃድ ከሌለው ሰው መድኃኒት ገዝቶ ካቀረበ ከሁለት ዓመት በማያንስና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፭ሺህ በማያንስና ከብር ፳ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፭ ማንኛውም ሰው መድኃኒት የመከለስ ድርጊት ከፈጸመ ወይም አሳሳች ገላጭ ጽሁፍ በመድኃኒት ማሸጊያ ላይ ለጥፎ ወይም በአባሪነት ከትቶ ከተገኘ ወይም ጊዜው ያለፈበት መድኃኒት ከሽጠ ወይም ለአገልግሎት ካዋለ ከአሥር ዓመት በማያንስና ከሃያ ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፳ሺህ በማያንስና ከብር ፻ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፮ የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም ይህን አዋጅ ለማስ ፈጸም የወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን በመተላለፍ የመድኃኒት ንግድ ሥራን የሚመለከቱ ሌሎች ጥፋቶችን የፈጸመ ማንኛውም ሰው ከሁለት ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፲ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም መድኃኒት ማለት የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን አይጨምርም ። የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን አጠቃቀም የሚገፋፉ ድርጊቶች ማንኛውም ሰው ፤ ፩ የናርኮቲክ ወይም የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን ሕገወጥ አጠቃቀም ለመገፋፋት በማናቸውም መንገድ ካስተዋወቀ ወይም ሌሎች እንዲያስተዋውቁ ካደረገ ወይም ከፈቀደ ፤ ገጽ ፩ሺ፩፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፪ : በባለቤትነት ወይም በባለይዞታነት በያዘው ቤት ፣ ግቢ ወይም በማናቸውም ሌላ ቦታ ናርኮቲክ ወይም ሳይኮት ሮፒክ መድኃኒቶች ሕገ ወጥ ተጠቃሚዎች እንዲገለገ ሉበት ካደረገ ወይም ከፈቀደ ፤ ፫ የናርኮቲክ ወይም የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች ለማዘዝ የሚያስችል ፈቃድ ሳይኖረው እንዲወሰዱ ካደረገ ወይም ከፈቀደ ፣ ፬ / የናርኮቲክ ወይም የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች ለማዘዝ ፈቃድ ቢኖረውም ያለበቂ ምክንያት ወይም ከተገቢው መጠን በላይ ካዘዘ ፤ ፭ የሐኪሙ ትእዛዝ የተጭበረበረ ፣ በሕገወጥ መንገድ የተቀየረ ፣ የተደለዘ ወይም ጊዜው ያለፈበት መሆኑን እያወቀ የናርኮቲክ ወይም የሳይኮትሮፒክ መድኃኒ ቶችን ከሸጠ ወይም ካቀረበ ፤ ከሰባት ዓመት በማያንስና ከአሥራ አምስት ዓመት በማይበልጥ እሥራትና ከብር ፴ሺህ በማያንስና ከብር ፻ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፵፭ ስለውርስ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፴፫እና ፴፬ የተመለከቱት ወንጀሎች የተፈጸመበት ወይም ከወንጀሉ የተገኘ ንብረት ይወረሳል ። መድኃኒቶችን በተመለከተ ስለሚፈጸሙ ሌሎች ወንጀሎች ፩ ከመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥራ ጋር በተያያዙ የሥራ መስኮች ተመድቦ የሚሠራ የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ኃላፊ መደለያ በመቀበል ወይም በዝምድና ወይም አግባብ ባልሆነ ሌላ ግንኙነት በዚህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም በሚወጡትደንቦች ከተደ ነገገው ውጭ ፥ ሀ ) የመድኃኒት ንግድ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠ ወይም እንዲሰጥ ያደረገ ወይም ያደሰ ወይም እንዲታደስ ያደረገ ። ለ ) የመድኃኒት ወይም የመድኃኒት ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች ደህንነት ፣ ፈዋሽነትና የጥራት ደረጃ ተገቢውን ግምገማ ወይም ቁጥጥር ሳያደርግ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የፈቀደ ወይም እንዲፈቀድ ያደረገ እንደሆነ ከ፰ ዓመት በማያንስና ከ፲፭ ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከብር ፴ሺህ የማያንስና ከብር ፻ሺህ የማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ቅጣት መደለያ በሰጠው ባለጉዳይ ላይም ተፈጻሚ ይሆናል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተመለከቱት ጥፋቶች በመፈጸም ተግባር ውስጥ የተሳተፈና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ስለተፈጸመው ጥፋትና ስለተባባ ሪዎቹ ሚና ጠቋሚ መረጃ ለሰጠ ሰው የፍትህ ሚኒስቴር በዚህ ሕግ መሠረት ክስ እንዳይመሠረትበት ሊያደርግ ይችላል ። ክፍል ፯ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴፯ መረጃ ስለማስተላለፍ የመድኃኒት ንግድ ሥራ ፈቃድ የሚሰጡ አግባብ ያላቸው አካላት ስለሰጡትና ስላደሱት የመድኃኒት ንግድ ሥራ ለባለሥልጣኑ መረጃ የማስተላለፍ አለባቸው ። ጽ ፩ሺ፩፻፲፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥርቛ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፴፰ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በዚህ አዋጅ መሠረት እንደተሰጠ ተቆጥሮበዚህ አዋጅናይህን አዋጅለማስፈጸም በሚወጡት ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ይተዳደራል ። ፴፱ ክልከላ ማንኛውንም የመድኃኒት ንግድ ሥራ ያለመድኃኒት ባለ ሙያ ማካሄድ አይቻልም ። Ø የተሻሩ ሕጎች ፩ የሚከተሉት በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፤ ሀ ) የመድኃኒት አቀማመምና አሰጣጥ የፋርማኮፒያ ድንጋጌ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፵ ፣ ለ ) የፋርማሲ ደንብ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፶፮ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖ ፪ : ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ ፥ ደንብ ወይም መመሪያ በዚህ አዋጅ ውስጥ የተመለከቱ ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈጸሚነት አይኖረውም ። ፴፩ ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል ። ፪ ባለሥልጣኑ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፵፪ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅከሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ ' ' ' ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ገጽ ፩ሺ፩፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፩ « መድኃኒት » ማለት የሰውን ወይም የእንስሳትን በሽታ ለመመርመር፡ ለማከም፡ለማስታገስ ወይም ለመከላከል የሚያገለግል ማንኛውም ንጥረ ነገር ወይም የንጥረ ነገሮች ውህድ ሲሆን የናርኮቲክናግይኮትሮፒክ መድኃ ኒቶችን፡ የእንስሳት መኖ ጥንቅሮችን፡ መርዞችን፡ ደምና የደም ተዋጽኦዎችን፡ ቫክሲኖችን፡ ሴሪዎችን፡ ጨረር አፍላቂ መድኃኒቶችን፡ ኮስሞቲኮችን፡ የሳኒተሪ ዝግጅ ቶችን፡ የሕክምና መሥሪያዎችን እና የሕክምና መገልገ ያዎችን እንዲሁም ለማንኛውም ዘርፍ አገልግሎት የሚውሉ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችን ይጨምራል ፣ ፪ « የናርኮቲክ መድኃኒት » ማለት ኢትዮጵያ በተቀበ ለችው የተባበሩት መንግሥታት የናርኮቲክ መድኃ ኒቶች ቁጥጥር ስምምነት መሠረት ዓለምአቀፍ ቁጥጥር የሚካሄድበት መድኃኒት ሲሆን ባለሥልጣኑ የናርኮቲክ መድኃኒት ብሎ የሚሰይመውንም ይጨምራል ፤ ፫ « የሳይኮትሮፒክ መድኃኒት » ማለት ኢትዮጵያ በተቀበ ለችው የተባበሩት መንግሥታት የሳይትሮፒክ መድኃ ኒቶች ቁጥጥር ስምምነት መሠረት ዓለምአቀፍ ቁጥጥር የሚደረግበት መድኃኒት ሲሆን ባለሥልጣኑ የሳይኮት ሮፒክ መድኃኒት ብሎ የሚሰይመውንም ይጨምራል ፤ « መርዝ » ማለት በአነስተኛ መጠን ሲወሰድ በሰው፡ በእንስሳት በዕፅዋትና በአካባቢ ደህንነት ላይ አደጋ የሚያስከትል ማንኛውንም ንጥረ ነገር ነው፡ « ፀረ ተባይ መድኃኒት » ማለት ማንኛውንም ተባይ ለመከላከል፡ ለመቆጣጠር፡ ወይም ለማጥፋት የሚያገ ለግል ተጨማሪ ንጥረነገር ውህድ ወይም ሕይወት ያለው ነገር ነው፡ ፮ « ኮስሜቲክ » ማለት ሰውነትን ለማጽዳት ፣ ለማቆንጀት ፣ ደምግባት ለመጨመር በሚል ወይም የአካልን ቅርጽና አሠራሩን ሳይቀይር ገጽታን ለመቀየር በገላ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ዝግጅት ሲሆን የቆዳ ቅባቶችን ፣ ሎሽኖችን : ሽቶዎችን፡ የከንፈር ቀለሞችን፡ የዓይንና የፊት ማቆንጃ ዝግጅቶችን ፡ ሻምፑዎችን ፣ የጸጉር ማቅለሚያዎችን፡ የጠረን መቀየሪያ ዝግጅቶችን ፣ ሳሙ ናዎችን እና ለእነዚህ ዝግጅቶች መሥሪያ የሚውሉ ንጥረ ነገሮችን ይጨምራል፡ ፯ « የሳኒተሪ ዝግጅት » ማለት የሰውና የእንስሳትን ንጽሕና እንዲሁም የቤትና የውስጥ ንጽህናን ለመጠ በቂያ የሚያገለግል ማንኛውም ዝግጅት ሲሆን ፓዶችን፡ታምፖችን፡ የጥርስ ንጽሕና መጠበቂያ ዝግጅ መምጠጫዎችን፡ ዲተርጀንቶችን ይጨምራል ። ፰ « የሕክምና መሣሪያ » ማለት የሰው ወይም የእንስሳትን በሽታ ለመመርመር ወይም ለማከም በውስጥ ወይም በውጭ አካል ላይ ጥቅም ላይ የሚውል ማንኛውም መሣሪያ ሲሆን የተለያዩ የመመርመሪያ ፡ የላቦራቶሪ ፣ መሣሪያዎችን ይጨምራል ። ፬ « የሕክምና መገልገያ » ማለት የሰው ወይም የእንስሳትን በሽታ ለመመርመር ወይም ለማከም በውስጥ ወይም በውጭ አካል ላይ ጥቅም ላይ የሚውል ማንኛውም መገልገያ ፡ የቁስል መሥፊያ ክሮችን ፡ ሲሪንጆችን ፣ መርፌዎችን፡ ፋሻ፡ ጐዝ ፡ ጥጥና መሰል ዝግጅቶችን ፥ አርቲፊሻል ጥርሶችን፡ ኬሚካሎችንና ፊልሞችን ይጨምራል፡ ፲ • « የመድኃኒት ንግድ ሥራ » ማለት መድኃኒቶች ማምረት፡ ማስመጣት መላክ፡ በጅምላና በችርቻሮ ማከፋፈል ሲሆን ጥራት መመርመር ፣ ሳይንሳዊ ቢሮ ማቋቋምና ማካሄድ እና በንግድ ወኪልነት መሥራትን ይጨምራል፡ ገጽ ፩ሺ፩፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም ፲፩ « የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት » ማለት በመድ ኃኒት ንግድ ሥራ ለሚሠማራ ሰው ሥራውን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅትና ድርጅታዊ ብቃት ያለው መሆኑ የተረጋገጠበት የምስክር ወረቀት ነው፡ ፲፪ • ማሸጊያ » ማለት መድኃኒት በውስጡ ለመሙላት ወይም ለመክተት ወይም ለመጠቅለል የሚያገለግል ማንኛውም መያዣ ሲሆን ከመድኃኒቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነትያላቸውን መያዣዎችን ለመጠቅለያ የሚያገለግሉ ሌሎች ዕቃዎችን ይጨምራል፡ ፲፫ « ገላጭ ጽሁፍ » ማለት ስለአንድመድኃኒት አስፈላጊውን መረጃ የሚገልጽ በማሸጊያው ላይ የሚታተም ወይም የሚለጠፍ ጽሁፍ ሲሆን በማሸጊያው ውስጥ በአባሪነት የሚከተተውን መግለጫ ጽሁፍ ይጨምራል ፤ ፲፬ « አስመስሎ ማቅረብ » ማለት የአንድን አምራች የመድ ኃኒት ማሸጊያ ወይም መለያ ፣ የንግድ ምልክት የንግድ ስም ወይም ማንኛውንም ዓይነት ልዩ ምልክት ያለአ ምራቹ ፈቃድ በመጠቀም መድኃኒቱ በእውነተኛው አምራች እንደተመረተ አስመስሎ ማቅረብ ነው፡ ፲፭ « መከለስ » ማለት በአንድ መድኃኒት ይዘት ላይ ሌላ ነገር በመጨመር ወይም ይዘቱን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በሌላ ነገር በመተካት ወይም በተገቢው መንገድ በንጽሕና ባለመመረቱና ባለመያዙ ከባዕድ ነገር ጋር እንዲነካካ ማድረግ ነው፡ ፲፮ « የሕክምና ሙከራ » ማለት የአንድን መድኃኒት ፈዋሽ ነትና ደህንነት ለማረጋገጥ በእንስሳት ወይም በሰዎች ላይ የሚደረግ የመድኃኒት ሙከራ ነው፡ ፲፯ « የመድኃኒት ባለሙያ » ማለት ፋርማሲስት ፣ ድራጊስት ፣ የፋርማሲቴክኒሽያን ሲሆን የእንስሳት ጤና ሙያተኛንም ይጨምራል፡ ፲፰ « የእንስሳት ጤና ሙያተኛ » ማለት በየደረጃው የሚሰ የእንስሳት ሕክምና ትምህርት ተከታትሎ ሙያውን ለመተግበር የሚያስችለው ዲግሪ ፣ ዲፕሎማ ወይም ሰርቲፊኬት ያለው ሰው ነው፡ ፲፬ « የሕክምና ባለሙያ » ማለት ሕመምተኛውን በመመ ርመር የበሽታውን ዓይነት የሚለይና በመድኃኒት ወይም አካልን በመቅደድ የሚያክም የሰው ወይም የእንስሳ ሐኪም ወይም እነዚሁኑ ተግባራት እንዲያከናውን የተፈ ቀደለት ሰው ነው፡ ፳ « የመድኃኒት ማዘዣ » ማለት ፈቃድ ባለው የሕክምና ባለሙያ ተጽፎ ለሕሙማን የሚሰጥ የመድኃኒት ዕደላ ትዕዛዝ ነው፡ ፳፩ « እንስሳት » ማለት የቤትና የዱር እንስሳት ሲሆኑ የባሕር እንስሳትንና ንብንም ይጨምራል ፤ ፳፪ « ሰው » ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ፪ የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣንን ስለማቋቋም ፩ የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ « ባለሥልጣኑ » በመባል የሚታወቅ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ . ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖእንደአስፈላ | 4. Head Office ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። ገጽ ፩ሺ፩፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ፭ ዓላማ የባለሥልጣኑ ዓላማ መድሐኒቶች ደህንነታቸው፡ መድኅንነታ ቸውና ጥራታቸው የተጠበቁ መሆናቸውንና በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ ይሆናል ። ፮ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ የመድኃኒት ደኅንነት፡ መድኅንነትና ጥራት ማረጋገጫ መመዘኛዎች ስታንዳርድ ያዘጋጃል፡ በመመዘኛው መሠረት መሠራታቸውን ይቆጣጠራል፡ ፪ በመድኃኒት ንግድ ሥራ ለሚሠማሩ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ መመዘኛዎች ያዘጋጃል፡ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡ ይቆጣጠራል፡ ምስክር ወረቀቱን ያግዳል፡ ይሠርዛል፡ መታገዱን ወይም መሠረዙን ለሚመለከተው ክፍል በወቅቱ ያስታውቃል፡ ፫ የሀገሪቱን የመድሀኒት መዘርዝር ያዘጋጃል፡ በመዘርዝሩ የተካተቱትን መደኃኒቶች በደረጃ ይመድባል፡ መዘር ዝሩን እንደአስፈላጊነቱ ይከልሳል፡ የሀገሪቱ የመድኃኒት ዘርፍ የሚመራበትን ፖሊሲ ያመነጫል፡ ረቂቅ ሕጐች ያዘጋጃል ፣ ለመንግሥት ለውሳኔ ያቀርባል፡ ፭ የመድኃኒት ንግድ ሥራ የሚስፋፋበትንና የሚጠናከር በትን መንገድ ያመቻቻል፡ በዘርፉ የተሠማሩትን ይረዳል፡ ያበረታታል፡ ፮ ለመድኃኒት ምርት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችንና የማሸጊያ ዕቃዎችን ጥራት ይቆጣጠራል፡ ፯ የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን አመራረት፡ ማስመጣት፡ መላክ፡ ሥርጭትና አጠቃቀምን ይከታ ተላል፡ ይቆጣጠራል፡ ቿ የሀገረሰብ መድኃኒቶችን ደህንነት፡ መድኅንነትና ጥራት መመዘኛዎችን ያዘጋጃል፡ የላቦራቶሪና የክሊ ኒካዊ ጥናቶችን ይገመግማል፡ በጤና አገልግሎት ውስጥ ገብተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይፈቅዳል ፣ ፬ . መድኃኒቶችን በሚመለከት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ይሠራል፡ እንደአስፈላጊነቱ መረጃዎችን ለባለሙያ ዎችና ለኅብረተሰቡ ያስተላልፋል፡ ሌሎች መረጃ የሚያ ስተላልፉ ሰዎች የሚያስተላልፉትን መረጃ ወቅታዊ ነትና ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡ ፲ የመድኃኒት ዘርፍን ለማጠናከርና ለማስፋፋት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚደረጉ አዳዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶችን በመከታተል ለሀገሪቱ በሚጠቅም ሁኔታ በተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፡ የመድኃኒት ሙከራ ጥያቄዎችን እየመረመረ ይፈቅዳል ፣ ይከታተላል፡ ውጤቱንም ይገመግማል ፣ ለሀገሪቱ በሚጠቅም ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይፈቅዳል፡ ፲፪ በመድኃኒት መመረዝ ለሚደርስ የሞት ወይም የጤንነት መታወክ መንስኤ የሆነውን ንጥረ ነገር ልዩ ልዩ ናሙናዎችን በመቀበል መርምሮ ምንነታቸውን ያረጋ ግጣል፡ መፍትሔውንም ይጠቁማል፡ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን የምርመራ ላቦራቶሪዎች ያደራጃል፡ ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፡ ፲፭ የንብረት ባለቤት ይሆናል፡ ውል ይዋዋላል፡ በራሱ ስም ይከስሳል፡ ይከሰሳል፡ ፲፮ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ገጽ ፩ሺ፩፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ፯ . የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ፡ ፩ . - አንድ ቦርድ፡ ፪ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና አንድ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፡ እንዲሁም አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። የቦርድ አባላት ቦርዱ በመንግሥት የሚሾሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል ። ፬ . የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፣ ፩ . ባለሥልጣኑን በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ፪ • የመድኃኒት ደኅንነት፡ መድኅንነትና ጥራት ማረጋገጫ መመዘኛዎችን መርምሮ ያጸድቃል፡ የሀገሪቱን የመድኃኒት መዘርዝር ያጸድቃል፡ ፬ . የአዋጁን ኣፈጻጸም በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፡ ፭ የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና ረቂቅ በጀት ያጸድቃል፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ መዋሉን ያረጋ ፲ የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ። ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ይሰበሰባል ። በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹአባላት ከተገኙምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባሎች በአብዛኛው ድምዕ ይሆናል ። ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምዕ ይኖረዋል ። የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፣ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፩ ስለባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት ይሾማል ። ዋና ሥራ አስኪያጁ የባለሥልጣኑ ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ የተመለከተውን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ። ለ ) የፌዴራል የሲቪል ሰርቪስ ኰሚሽንን መሠረታዊ መርህ በመከተል የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ ሐ ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና ረቂቅ በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፡ መ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሠ ) ባለሥልጣኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደር ጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለባለሥልጣኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅና ለሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ገጽ ፩ሺ፩፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥርኟ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ፲፪ . የባለሥልጣኑ በጀት የባለሥልጣኑ በጀት ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል ፤ ፩ በመንግሥት ከሚመደብ በጀት፡ ፪ • ከሚሰበሰበው የፈቃድ / የአገልግሎት ክፍያ ፣ እና ፫ ከሌላ ምንጭ ከሚገኝ ገቢ ። ፲፫ . ስለሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟላና ትክክለኛ የሆነ መዛግብት ይይዛል ። የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ስለተቆጣጣሪዎች ይህን አዋጅና ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን ለመከታተልና ለማረጋገጥ ባለሥልጣኑ የመድኃኒት ባለሙያዎችን በተቆጣጣሪነት ይመድባል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የተመደበ ተቆጣጣሪ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፤ ሀ ) በመድኃኒት ንግድ ሥራ የተሠማሩ ድርጅቶችን ፣ የጤና ድርጅቶችንና የመግቢያ ኬላዎችን ክፍት በሚሆኑበት በማናቸውም ሰዓት በመግባት ለመቆ ለ ) መድኃኒት ነክ የሆነ ማንኛውንም ሪኮርድ ፣ ማዘዣ ወይም ሠነድ ለመመልከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገ ኘውም ፎቶ ኮፒ ተደርጐ እንዲሰጠው ለማድረግ ፤ ሐ ) ባለሥልጣኑ በሚያወጣው የናሙና አወሳሰድ መመሪያ መሠረት ከተመረቱ ወይም ከውጭ ከመጡ መድኃኒቶች ላይ ለማስረጃነት የሚያገ ለግሉ ናሙናዎችን ለመውሰድ ፣ መ ) የተከለከሉ፡ የተበላሹ ፣ የተጭበረበሩ ፣ የተበከሉ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት በተጠ ቃሚው ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ተብለው በተጠ ረጠሩ መድኃኒቶች ላይ የላቦራቶሪ ምርመራ እንዲካሄድ ለማድረግና ውጤቱ እስከሚታወቅ ድረስም በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ታሽገው እንዲቆዩ ለማዘዝ ፤ ሠ ) መድኃኒቶች የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያበቃ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት ጥቅም ላይ እንዳ ይውሉ ሲወሰን በተገቢው መንገድ እንዲወገዱ ለማድረግና በዚህ አንቀጽ በንዑስ ቁጥር ( ፪ ) ( መ ) መሠረት የታሸጉትን በሠላሳ ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኙ ማድረግ ። ፲፭ ውክልና ስለመስጠት ባለሥልጣኑ ለሥራው ቅልጥፍና አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለክልል አካላት በውክልና መስጠት ይችላል ። ክፍል ፫ ስለመድኃኒቶች ምዝገባና ቁጥጥር ፲፮ ምዝገባ ፩ . ማንኛውም በአገር ውስጥ የሚመረት ወይም ከውጭ የሚመጣ መድኃኒት ደህንነቱ ፤ መድኅንነቱና ጥራቱ ተገምግሞ በባለሥልጣኑ ሳይመዘገብ በአገልግሎት ላይ ሊውል አይችልም ። የምዝገባ ተግባር የሚከናወነው ይህን አዋጅ ለማስ ፈጸም በሚወጣ ደንብ መሠረት ይሆናል ። ፲፯ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፩ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፮ መሠረት ለተመዘገበ መድኃኒት ለአምስት ዓመት የሚያገለግል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ገጽ ፩ሺ፩፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም : ፪ • የምስክር ወረቀቱ መድኃኒቱ በመድኃኒትማዘዣ ወይም ያለመድኃኒት ማዘዣ እንዲሁም በየትኛው የጤና ድርጅትና የመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅት ደረጃ አገል ግሎት ላይ ሊውል እንደሚችል ማመልከት አለበት ። ፲፰ ስለዳግም ምዝገባ ፩ . ማንኛውም የተመዘገበ መድሐኒት የተሰጠው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ወይም የአገልግሎት ዘመን ከማለቁ በፊት ቢያንስ ከመቶ ሃያ ቀን በፊት ለዳግም ምዝገባ መቅረብ አለበት ። ባለሥልጣኑ ከዳግም ምዝገባ ማመልከቻ ጋር መቅረብ ስለሚገባቸው መረጃዎች ዝርዝር መመሪያ ያወጣል ። ፲፱ • የጥራት ደረጃ ባለሥልጣኑ በሚያወጣው ፋርማኮፒያ ወይም በተቀ በለው የሌሎች ሀገሮች ፋርማኮፒያ መሠረት የጥራት ደረጃ ያረጋግጣል ። ፪ • የወጣለትን የጥራት ደረጃ የማያሟላ መድኃኒት ፣ ጥሬና የማሽጊያ ዕቃ ለአገልግሎት ሊውል አይችልም ። ፳ በአገልግሎት ላይ በዋሉ መድኃኒቶች ላይ ስለሚደረግ ፩ . በአገልግሎት ላይ የዋሉ መድኃኒቶችን ደኅንነት ፣ መድኅንነትና ጥራት ለማረጋገጥ ባለሥልጣኑ ክትትል ያደርጋል ። ፪ . ማንኛውም መድኃኒት በአገልግሎት ላይ ከዋለ በኋላ ይኖረዋል ተብሎ የተገመተው የመድኅን ሰጪነት ባህሪ አለመኖሩ ሲረጋገጥ ወይም የሚያስከትለው ጉዳት ከሚሰጠው ጥቅም አመዝኖ ሲገኝ ባለሥልጣኑ መድኃኒቱ በጥቅም ላይ እንዳ ውል የማገድና ምዝገ ባውን የመሠረዝ ሥል ይኖረዋል ። ፳፩ ስለሕክምና ሙከራ የሕክምና ሙከራ በሰው ወይም በእንስሳት ላይ ለማድረግ የሚቻለው ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብ መሠረት በባለሥልጣኑ ሲፈቀድና ሰውየው በራሱ ላይ የሕክምና ሙከራ እንዲካሄድበት በጽሁፍ ከተስማማ ወይም እንስሳ የሆነ እንደሆነ የእንስሳው ባለቤት ፈቃድ ከተገኘ እና የዱርና የባሕር እንስሳት ከሆኑ ከመንግሥት ፈቃድ ሲገኝ ብቻ ይሆናል ። ፪ • የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ ቢኖርም ፤ በአጥቢና ነፍሰጡር እናቶች ፣ ለአቅመአዳም ባልደረሱ ሕጻናት ፣ በእስረኞች ፡ በአእምሮ ሕመምተኞች እና የሙከራ አድራጊው ባለሙያ ወይም ድርጅት ሰዎች ላይ የሕክምና ሙከራ ማድረግ አይቻልም ። ፫ በባለሥልጣኑ ተገምግሞ ያልጸደቀ የሕክምና ሙከራ ውጤትን በማንኛውም ሕትመት ላይ ማውጣት ወይም በማንኛውም መንገድ ማሠራጨት አይቻልም ። ፬ . የሕክምና ሙከራ ስለሚደረግባቸው ሰዎች የሚገልጽ መረጃ በምሥጢር መጠበቅ አለበት ። መረጃ ስለማስተላለፍና ስለንግድ ማስታወቂያዎች ፩ . ማንኛውም ሰው መድኃኒት ነክ መረጃዎች ለባለሙያ ዎችም ሆነ ለኅብረተሰቡ ሊያስተላልፍ የሚችለው የመረጃዎቹ ትክክለኛነትና ጠቃሚነት በባለሥልጣኑ እየተረጋገጠ ሲፈቀድለት ነው ። ገጽ ፩ሺ፩፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም : ፪ . ማንኛውም ሰው ስለ ንግድማስታወቂያ የወጣውን ሕግ ወይም በባለሥልጣኑ የወጣውን መመሪያ ያልተከተለ ወይም በማናቸውም አኳኋን ኅብረተሰቡን ሊያሳስት የሚችል መድኃኒትን የሚመለከት የንግድ ማስታወቂያ በጽሑፍ ወይም በማናቸውም መንገድ ሊያወጣ አይችልም ። ፳፫ ስለመድኃኒት ማሸጊያዎችና ገላጭ ጽሑፍ ፩ . ማንኛውም መድኃኒት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብና መመሪያ መሠረት በአግባቡ ካልታ ሸገና ገላጭ ጽሑፍ ካልተደረገበት በስተቀር ለገበያ ሊቀርብ ወይም በማናቸውም አኳኋን ሊሠራጭ አይችልም ። ፪ • ማንኛውም የመድኃኒት አምራች ፣ አስመጪ ፣ አከፋፋይ ወይም ቸርቻሪ ድርጅት ወይም የጤና ድርጅት ለአገል ግሎት የሚያቀርባቸው መድኃኒቶች በአግባቡየታሸጉና ጽሑፍ የተደረገባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ክፍል ፬ ስለ ናርኮቲክና ሣይኮትሮፒክ መድኃኒቶች ልዩ ፈቃድ ስለማስፈለጉ ፩ ናርኮቲክ መድኃኒቶችን ለማስመጣት ፣ ለመላክ ፣ ለማምረት ወይም ለማከፋፈል ከባለሥልጣኑ ልዩ ፈቃድ ማውጣት ያስፈልጋል ። ፪ • የናርኮቲክና የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን የማስ መጣት፡ የመላክ ፡ የማምረት ፡ የመያዝ ፣ ወይም የማከማቸት ልዩ ቋሚ ፈቃድ የሚሰጠው የመድኃኒት ንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ብቻ ይሆናል ። ፳፭ ስለማስመጣትና መላክ ፩ የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን የማስመ ጣትና የመላክ ልዩ ቋሚ ፈቃድ የተሰጠው ሰው በየጊዜው የማስመጣት ወይም የመላክ ልዩ ፈቃድ መጠየቅ ይኖርበታል ፡ በአንድ ጊዜ የሚሰጠው ልዩ ፈቃድም ከዘጠና ( ፮ ) ቀን በላይ አያገለግልም ። ፪ ናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን በፖስታ ቤት ወይም በመርከብ ማስመጣት ወይም መላክ አይፈ ቀድም ። ፫ ማንኛውም ሰው ናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድኃኒ ቶችን ከሌሎች መድኃኒቶች ወይም ዕቃዎች ጋር አሽጐ ማስመጣት ወይም መላክ አይፈቀድለትም ። ማንኛውም ሰውናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድኃኒ ቶችን ሲያስመጣ ወይም ሲልክ ባለሥልጣኑ ስለአስተ ሻሸግ ያወጣውን መመሪያ መከተል ይኖርበታል ። ፳፮ ስለመድኃኒት ማዘዣ ወረቀቶች አስተዛዘዝ ሥርዓት ፩ : ናርኮቲክ መድኃኒቶችን ማዘዝ የሚችለው በሙያው እንዲሠራየተመዘገበናልዩ ፈቃድ የተሰጠውየሕክምና ባለሙያ ብቻ ይሆናል ። ፪ የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች የሚታዘዙት በሙያው እንዲሠራ በተመዘገበና ልዩ ፈቃድ በተሰጠው የሕክምና ባለሙያ ይሆናል ። ፫ • ማንኛውም የሕክምና ባለሙያ ናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን ለራሱ ማዘዝ አይችልም ናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች የሚታዘዙት በልዩ የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀት ብቻ ይሆናል ። ፭ ማንኛውም የናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድኃኒት ማዘዣ ወረቀት ማሟላት ያለበት መስፈርትና አሠራር ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ገጽ ፩ሺ፩፻፲፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ • ም • ፳፯ . ስለአያያዝ የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችና ስለነዚህ የሚገልፁ ኢንቮይሶች : ሪኮርድ መያዣ ደብተሮችና የማዘዣ ወረቀቶች ቁልፍባለው የብረት ሳጥን ውስጥ ወይም በተለየ ክፍል ውስጥ መቀመጥና ቁልፉም በተፈቀደለት ባለሙያ እጅ መያዝ አለበት ፡፡ ስለአወጋገድ ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው የተበላሹ ፣ የአገል ግሎት ጊዜያቸውም ያለፈባቸው : ወይም በሕገወጥነት የተያዙ ናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን በተለየ ቦታ ይይዛል ፡ ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረትም እንዲወገዱ ያደርጋል ። ሥራ ስለማቋረጥ ማንኛውም ፈቃድ የተሰጠው ሰው ሥራውን ሲያቋርጥ በእጁ ስለሚገኙ ናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች ፣ ኢንቮይሶች፡ ሌሎች ዶክመንቶችናማዘዣ ወረቀቶች ባለሥ ልጣኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት አስፈላጊውን መፈጸም ይኖርበታል ። ፴ ሪኮርድ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ማንኛውም ፈቃድ የተሰጠው ሰው ስለናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች አገልግሎት ባለሥልጣኑ በሚያ ወጣው መመሪያ መሠረት ሪኮርድ መያዝና ሪፖርት ማቅረብ ይኖርበታል ። ክፍል ፭ ስለመርዞችና ጨረር አፍላቂ መድኃኒቶች ፴፩ : ስለ መርዞች ፩ ) ባለሥልጣኑ ዓለምአቀፍ መለኪያዎችን መሠረት በማድረግ የመርዞችን ዝርዝር አውጥቶ ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቃል ፡ ስለመርዞች አያያዝ ፡ አሻሻጥና አወጋ ገድም መመሪያ ያወጣል ። ፪ . ማንኛውም ሰው ከባለሥልጣኑ ልዩ ፈቃድ ሳያገኝ መርዞችን ማምረት ፡ ከውጭ ማስመጣት ማከፋፈል አይችልም ። ፫ . ማንኛውም መርዞችን የሚያመርት ፡ የሚያስመጣ ወይም የሚያከፋፍል ሰው ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ስለመርች ዝርዝር መረጃ የመያዝና ለባለሥ ልጣኑ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ፴፪ • ስለጨረር አፍላቂ መድኃኒቶች ባለሥልጣኑ በዓለምአቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መመሪያ መሠረት ስለጨረር አፍላቂ መድኃኒቶች አያያዝ፡ ሥርጭት፡ አጠቃቀምና አወጋገድ መመሪያ ያወጣል ። ፪ . ማንኛውም ሰው ልዩ ፈቃድ ሳይኖረው ጨረር አፍላቂ መድኃኒቶችን ሊያመርት፡ ሊያስመጣ ፡ ሊያከፋፍል ወይም ሊሸጥ አይችልም ። ፫ • ማንኛውም ልዩ ፈቃድ የተሰጠው ሰው ስለአመራረ ታቸው ፡ ስለአስመጣቸው ወይም ስለአከፋፈላቸው ጨረር አፍላቂ መድኃኒቶች ባለሥልጣኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት መረጃ የመያዝናሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?