የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ታኅሣሥ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፶፬ ዓ.ም በአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ሕግ መሠረት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶችን ወደ አሜሪካ ሀገር ስለመላክ የወጣ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፮ / ፲፪ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፶፬ በአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ሕግ መሠረት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶችን ወደ አሜሪካን ሀገር ስለመላክ የወጣ አዋጅ የአሜሪካ መንግሥት እ.ኤ.አ ሜይ ፲፰ ቀን ፪ሺ ዓም የአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ሕግ ያወጣ በመሆኑ ፣ ይህ የሕግ ሰነድ የተመረጡ ከሠሃራበታች የሚገኙ የአፍሪካ | Act on 18 May , 2000 ; አገሮች ወደ አሜሪካ አገር የሚልኳቸውን ምርቶች ከቀረጥ እና ከኮታ ነፃ ለማስገባት የሚያስችላቸው ስለሆነና ኢትዮጵያም የዚሁ | African countries to export their products to the United States ሕግ ተጠቃሚ እንዲሆኑከተመረጡትከሠሀራ በታችከሆኑ አገሮች | duty and quota - free and Ethiopia is one of the Sub - Saharan ውስጥ አንዷ በመሆኗ በዚሁ ሕግ መሠረት የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶችን ያለ ቀረጥና ኮታ ወደ አሜሪካ ለመላክ የኢትዮጵያ መንግሥት | Government has agreed to export textile and apparel products የተስማማ በመሆኑና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አምራቾችና | duty and quota - free to the United states of America , and it has ላኪዎችም በዚሁ ስምምነት መሠረት እንዲሠሩ ለማድረግ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ በአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ሕግ መሠረት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶችን ወደ አሜሪካ ሀገር ስለመላክ የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፩ / ፲፱፻፶፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፮፻፶፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፤ ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta ፪ ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ በአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ሕግ ” ማለት ( ከዚህ በኋላ “ አዕተሕ ) እ.ኤ.አ ሜይ ፲፰ ቀን ፪ሺ በኣሜሪካ መንግሥት የተደነገገው “ አፍሪካን ግሮውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት ” ነው ፣ ፪ . “ ሥልጣን የተሰጠው ሹም ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፫ እና በአንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ላይ የተደነገጉትን እንዲያስፈጽም በኢትዮጵያ የጉምሩክ ባለሥልጣን የተወከለ ሠራተኛ ነው ፤ ፫ “ በአዕተሕ የሚሸፈኑ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ” ማለት ከዚህ በታች ከምድብ ፩ እስከ ምድብ ፱ የተዘረ ዘሩት ናቸው ፣ ምድብ ፩ : በአሜሪካ ከተመረቱ ድርና ማግ በዚያው አገር ተመርቶና ለስፌት በሚያመች መልክ ተቆራርጦ የተዘጋጀ ጨርቅን በመጠቀም በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ አገሮች የተሰፉ አልባሳት ። ምድብ ፪ ድርና ማጉ በአሜሪካ ሀገር የተሠራ ፣ ጨርቁም በአሜሪካ አገር የተሠራና እዚያው አሜሪካ አገር ተቆራርጦ አንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገሮች የተሰፉ አልባሳት ሆነው፡ አልባሳቱ የአሜ ሪካንን አንድ ወጥ የታሪፍ ሥርዓት ንዑስ ርዕስ ፱ሺ፰፻፪ ዜሮ ዜሮሽ ሊያሟሉ የሚ ችሉ ፣ ነገር ግን የመጥለፍ ፣ የስቶን ወይም የኢንዛይም ወይም የአሲድ እጥበት ፣ የቋሚ ተኩስ ፣ የመቀቀል ፣ የማንጣት ፣ የማቅለም ፣ በስክሪን የማተም እና ሌሎች ይህን የመሳሰሉ ሥራዎች የተከናወኑ ባቸው አልባሳት ። ምድብ ፫ አሜሪካ አገር ከተመረተ ድርና ማግ በአሜሪካ የተሠራ ጨርቅን በመጠቀም በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሀራ በታች በሚገኙ , ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገሮች ተቆራርጦ በተጠቃሚው አገር ውስጥ ፣ በአሜሪካ በተሠራ ክር፡ የተሰፉ አልባሳት ። ምድብ ፬ በአሜሪካ ወይም በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሀራ በታች ከሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገሮች በተመረተ ድርና ማግ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሀራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገሮች ሙሉ በሙሉ የተሠራ ጨርቅን በመጠቀም በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገሮች ሙሉ በሙሉ የተሰፉ ኣልባሳት ። ምድብ ፭ ከየትኛውም አገር በተገኘ ጨርቅ በዕድገ ታቸው ዝቅተኛ በሆኑ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገሮች ሙሉ በሙሉ የተሰፉ አልባሳት ገጽ ፩ሺ፮፻፶፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም Federal Negarit Gazeta No.7 20 December , 2001 – Page 1654 ምድብ ፮ : በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በአብዛኛው ከካሽሚር ሱፍ የተሠሩ እና በአሜሪካ አንድ ወጥ የታሪፍ ሥርዓት በንዑስ ርዕስ ፩ሺ፮፻፲፯ ሥር የሚመደቡ በልብስነት የተመረቱ ሹራቦች ። ምድብ ፯ ፲ በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ሱፍ ከሆነና ፲፰፭ ማይክሮን ውፍረት ወይም ከዚያ በላይ የቀጠነ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በልብስነት የተመረት ሹራብ ። ምድብ ፰ ከሠሃራ በታች በሚገኙ ተጠቃሚ የአፍሪካ አገሮች ሙሉ በሙሉ የተሰፉት አልባሳት ጨርቅ ወይም ጨርቁ የተሠራበት ድርና የተሰፉበት ማግ በአሜሪካን አገር ወይም ከሠሃራ በታች በሚገኝ ተጠቃሚ የአፍሪካ አገር ያልተሠራ ቢሆንም ፣ ከእነዚህ ጨርቆች ወይም ድርና ማግ የተሰፉት አልባሳት በሰሜን አሜሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት አባሪ ፬፻፩ መሠረት የተጠቃ ሚነት መብት ያለው ፣ ወይም አሜሪካ ውስጥ ለንግድ በበቂ መጠን አለመኖሩ የተረጋገጠ ። ምድብ ፱ • ከአሜሪካ መንግሥት ጋር በሚደረጉ ውይይቶች የሚወሰኑ በእጅ የተሠሩ ፣ የተፈተሉ ፣ አልባሳት ። ፬ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥ ልጣን ነው ፣ ፭ “ ተጠቃሚ ” ማለት ማንኛውም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ) መሠረት ልዩ ምዝገባ ያደረገ አምራች ወይም ላኪ ማለት ነው ፣ • “ ሰርቲፊኬት ” ማለት በአዕተሕ መሠረት የሚሰጥ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርት የአምራች ሀገር ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ነው ፣ ፯ . “ መስፈርቶችን ስላለማሟላት ” ማለት የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶችን ወደ አሜሪካ አገር ለመላክ የዚህ አዋጅ እና የአዕተሕን ድንጋጌዎችና መስፈርቶች በተለያዩ ዘዴዎች መጣስ ወይም መተላለፍ ነው ፣ ፰ “ የዋጋ መግለጫ ሰነድ ” ማለት ከሻጩ ለገዥ የሚሰጥ ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ነው ፣ ፱ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፲ . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ወይም ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው ነው ፣ ፲፩ “ አቅጣጫ ማስቀየር ” ማለት የኣዕተሕ ተጠቃሚ ለመሆን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ሀገር የሚላክን የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርት አሜሪካ ከመድረሱ በፊት በሌላ ሦስተኛ ሀገር ክልል ውስጥ የንግድ ተግባር እንዲፈጸምበት ማድረግ ነው ፣ ፲፪ . “ ሐሰተኛ መረጃን መጠቀም ” ማለት የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርትን ወይም ከምርቱ ማናቸውም አካል ( ክፍል ) ጋር በተገናኘ የአምራች ሀገር አመልካችነትን ፤ አፈበራረክን ፤ የአመራረት ሂደትን ወይም መገጣጠምን በተመለከተ ሐሰተኛ መረጃ መጠቀም ነው ፣ ፲፫ . “ የይለፍ ማስረጃ ” ማለት ሥልጣን በተሰጠው ሹም አማካኝነት በዋናው የዋጋ መግለጫ ሰነድ ላይ የሚደረግ ሕጋዊ ማኅተም ነው ። ቀናት ውስጥ ያልተቀበለበትን ምክን፡ ኣ 0 ) ገጽ ፩ሺ፮፻፶፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ታኅሣሥ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta No. 7 20 December , 2001– Page 1655 ፫ • አስፈጻሚ አካል ይህንን አዋጅ የማስፈጸም ኃላፊነት ለባለሥልጣኑ የተሰጠ ሲሆን ፤ በተለይም ባለሥልጣኑ ፤ ፩ . የይለፍ ማስረጃ የመስጠት ፤ ጀ የአምራች ሀገር የምስክር ወረቀት የማረጋገጥ ፤ እና ፫ . በአዕተሕ መሠረት መረጃ የመያዝና ሲጠየቅ የመስጠት ፤ ኃላፊነት አለበት ። ፬ የተጠቃሚ መብት በዚህ አዋጅ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ተጠቃሚ በአዕተሕ መሠረት ጨርቃ ጨርቅንና አልባሳትን ከቀረጥና ኮታ ነጻ ወደ አሜሪካ የመላክ መብት አለው ። ፭ የይለፍማስረጃ ስለማስፈለጉ ማንኛውም ሰው ከባለሥልጣኑ በተገቢ ሁኔታ የተሰጠ የይለፍ | 5. Visa Requirement ማስረጃ ሳይኖረው ማንኛውንም የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶችን በአዕተሕ መሠረት ወደ አሜሪካ ሀገር መላክ አይችልም ። ለይለፍማስረጃ ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ . ማንኛውም በአዕተሕ መሠረት ለጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶች የሚቀርብ የይለፍ ማስረጃ ጥያቄ የሚከተሉትን በማሟላት ለባለሥልጣኑ መቅረብ አለበት ፣ ሀ ) የዋጋ መግለጫውን ዋና ቅጅ እና ሁለት ፎቶ ኮፒዎች ፣ እና ለ ) የሰርቲፊኬቱን ሦስት ቅጂዎች ። ፪ ባለሥልጣኑ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ማመልከቻ ከተቀበለ በኋላ ፤ ሀ ) አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አመልካቹ ሌሎች መረጃዎችን እንዲያቀርብ ይቅ ይችላል ፣ ለ ) በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፰ የተደነገገው እንደተ ጠበቀ ሆኖ ፣ ማመልከቻው ( የአዕተሕን ) እና የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች አሟልቶ ሲገኝ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ የይለፍ ማስረጃ ይሰጣል ። ፫ ባለሥልጣኑ ጥያቄውን ካልተቀበለው በአምስት የሥራ በጽሑፍ ለአመ ልካቹ ያሳውቃል ። ፯ : ስለ ምዝገባና መግለጫ ፩ . ማንኛውም ተጠቃሚ ፣ ሀ ) በሚኒስቴሩ ልዩ ምዝገባ ማድረግ ፤ ለ ) ለእያንዳንዱ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ጭነት የኤክስፖርት መግለጫ ፎርም ሞልቶ ለባለሥ ልጣኑ ማቅረብ ፣ እና ሐ ) የማምረት ተግባሩን ባቋረጠ ወይም ማምረቻውን በዘጋ ጊዜ ልዩ ምዝገባው እንዲሰረዝ ማድረግ ፣ አለበት ። ፪ ከባለሥልጣኑ በስተቀር ማንኛውም ሰው ወደ አሜሪካ አገር ከቀረጥና ኮታ ነፃ ለመላክ የሚያስችል ሠርቲፊ ኬትና ኤክስፖርት መግለጫ ፎርምን ማተም ወይም ማሳተም አይችልም ። ፰ የይለፍማስረጃ ስለመከልከል ባለሥልጣኑ ፣ ፩ . የሚላኩት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶች የዚህን አዋጅ እና ( የአዕተሕን ) ድንጋጌዎች የሚያሟሉ ሆነው ካልተገኙ ፣ ፪ የተጠቃሚው የመዛግብት አያያዝ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ የሰፈረውን የሚያሟላ ሆኖ ካልተገኘ ፣ የይለፍ ማስረጃ አይሰጥም ። ፱ ሰነድና መዛግብት ስለመያዝ ፩ . ማንኛውም ተጠቃሚ የሚከተሉትን የተሟሉ ሰነዶችና መዛግብት በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ መያዝና ቢያንስ ለ፲ ዓመታት መጠበቅ አለበት ፤ ገጽ ፩ሺ፮፻፶ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta ሀ ) የምርት መዛግብት ፣ ለ ) ለማምረት የተጠቀመባቸውን ግብኣቶች ዓይነት ፣ መጠንና ምንጭ ፣ ለማምረት የተጠቀመባቸውን የማምረቻ መሣሪ ያዎች ዓይነት ፣ መለያ እና ብዛት ፣ መ ) በምርት ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች ብዛት ፣ በአዕትሕ መሠረት የተላከውን የምርት መጠን ፣ ረ ) ሌሎች በባለሥልጣኑ የሚጠየቁ አስፈላጊ መረጃ ፪ . በዚህ አዋጅ መሠረት የሚገኘው ማናቸውም ሰነድና መረጃ በሚስጥር መያዝ ኣለበት ። ፲ የተከለከለ ተግባር መስፈርቶችን ያለማሟላት ፣ የምርትን አቅጣጫ ማስቀየር እና ሀሰተኛ መረጃ መጠቀም ለማንኛውም ተጠቃሚ በጥብቅ የተከለከሉ ተግባራት ናቸው ። ፲፩ • ስለመፈተሽ ፩ . ሥልጣን የተሰጠው ሹም ወይም የእርሱ ተወካይ በማን ኛውም ተገቢ በሆነ ሰዓት መታወቂያውን በማሳየት በተጠቃሚው መሥሪያ ቤት በመግባት ፤ ሀ ) ከሀሰተኛ መረጃ መጠቀም ጋር የተያያዙ ጥቆማ ዎችን ለማጣራት ፣ ለ ) የአዕተሕ እና የዚህን አዋጅ ተፈጻሚነት ለማረ ፍተሻ ማድረግ ይችላል ። ፪ ሥልጣን የተሰጠው ሹም ወይም ተወካዩ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተውን ፍተሻ ከአሜሪካ መንግሥት የጉምሩክ ኣገልግሎት ተወካይ ጋር በመሆን ሊያካሂድ ይችላል ። ፫ . ማንኛውም ተጠቃሚ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) የሰፈሩትን ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት መከልከል አይችልም ። ፲፪ ስለፈቃድ መሠረዝ ፩ . ሚኒስቴሩ በዚህ አዋጅ የሠፈሩትን ድንጋጌዎች ያላከበረ ተጠቃሚን የንግድ ፈቃድ ይሰርዛል ። በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የንግድ ፈቃዱ የተሠረዘበት ተጠቃሚ የንግድ ፈቃዱ ከተሰረ ዘበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ተጠቃሚ ኣይሆንም ። ፫ ሚኒስቴሩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የንግዱ ፈቃዱ ለተሠረዘበት ማንኛውም ተጠቃሚ፡ ወይም የንግድ ድርጅቱን ለወረሰ ወራሽ ፣ ወይም በዚሁ ተጠቃሚ ባለቤትነት ለተያዘ ሌላ ድርጅት ፈቃዱከተሰረ ዘበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ማንኛውም የንግድ ፈቃድ አይሰጠውም ። ፲፫ . ቅጣት ማንኛውም፡ ፩ መስፈርቶችን ያላሟላ ፣ ሀሰተኛ ማስረጃ የተጠቀመ ወይም የምርቱን አቅጣጫ ያስቀየረ ፣ ፪ የይለፍ ማስረጃ ለማግኘት ካቀረበው ማመልከቻ ጋር በተያያዘ ተጨባጭ ሁኔታ ሀሰተኛ የሆነ ፣ የተሳሳተ ያልተሟላ ወይም አሳሳችነት ያለው ወይም ከተክክለኛው ምንጭ ያልተገኘ ሰነድ ወይም መረጃ ያቀረበ ፣ ፫ በሀሰተኛ መረጃ የይለፍማስረጃ መገኘቱን ወይም የይለፍ ማስረጃ እንዲሰጥ የቀረበው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን እያወቀ ይህንኑ ለሚመለከተው ባለሥልጣን ያላሳወቀ ፣ ፬ • የይለፍ ማስረጃን ወደ ሀሰተኛነት የቀየረ ፣ የለወጠ ፤ እንዲህ ያለውን ተግባር ተመሳጥሮ የሠራ ፣ ወይም እንዲ ቀየር ፣ እንዲለወጥ ወይም እንዲሠራ ያደረገ ፣ ፭ በአዕተሕ መሠረት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶችን በሚያመርቱ ወይም በሚልኩ ተቋማት ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የሚደረግ ፍተሻን የከለከለ ፣ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት አግባብ ያላቸውን መዛግብትና መረጃ ያልያዘ ወይም ለመያዝ ቸልተኝነት ያሳየ ፣ ገጽ ፭ሺ፮ደ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፮ ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፱ ዓም Federal Negarit Gazeta No. 7 20 ሥ December , 2001 - Page 1657 • የዚህን አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡ ደንቦችን ወይም ሚኒስቴሩ ወይም ባለሥልጣኑ ያወጣ ቸውን የሕዝብ ማስታወቂያዎች ወይም መመሪያዎች የተላለፈ ሰው ወንጀሉ የተፈፀመበትን ንብረት ዋጋ ሶስት እጥፍ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል ። ደንብ ስለማውጣት የሚኒስትሮችምክር ቤት ይህን አዋጅለማስፈፀምደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፭ የሕዝብ ማስታወቂያ ወይም መመሪያዎች ስለማውጣት እንደአስፈላጊነቱ ሚኒስቴሩ ወይም ባለሥልጣኑ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም የሕዝብ ማስታወቂያ ወይም መመሪያ ሊያወጡ ይችላሉ ። ፲፮ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ